Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
344 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
አትሌት ታምራት ቶላ እና አትሌት ሲምቦ አለማየሁ የአመቱ ምርጥ አትሌቶች ተባሉ

አትሌት ታምራት ቶላ ከስታዲየም ውጭ በተደረጉ ውድድሮች የ2024 የዓመቱ ምርጥ አትሌት ሽልማትን አሸንፏል፡፡

አትሌት ሲምቦ አለማየሁ የዓመቱ ተተኪ ወጣት (Rising Star) አትሌት ሽልማትን ማሸነፏን የዓለም አትሌቲክስ መረጃ አመልክቷል።
👍238
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
1👍1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ መዳረሻዎች ቁጥር 140 መድረሱ ተገለጸ
**************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን 80ኛ የምስረታ በዓልን አስመልከቶ የትራንሰፖርትና ሎጂስቲክስና የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው መንግስቴ እንደገለፁት፤ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከ114 አገራት ጋር የሁለትዮሽ የአየር ትራንስፖርት ስምምነት ተፈራርሟል።

በዚህም የአየር መንገዱ የበረራ መዳረሻዎች ቁጥር 140 ደርሷል ብለዋል::

ኢትጵያን ከተቀረው ዓለም ጋር በማገናኘት፣ ንግድና ቱሪዝምን በማቀላጠፍ ረገድ ለሚደረገው ሥራ የአቪዬሽን ባለስልጣን ድርሻ ትልቅ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የኢትዮጵያ የአየር ትራንስፖርት ጥራትና ደህንነቱ የጠበቀ እንዲሆን የባለስልጣኑ ሚና ትልቅ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት መሰረት በዓለም ላይ ጥራቱ የተጠበቀ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ከሚሰጡ ጥቂት ሀገራት መካከል የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አንዱ ነው ሲሉ ገልፀዋል::

የትራንሰፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ደኤታ አቶ ደንጌ ቦሩ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን የምስረታ በአል ከህዳር 30 እስከ ታህሳስ 3 ቀን 2017 ዓ.ም በተለያዩ ፕሮግራሞች ያከብራል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ምስረታን የተቀላቀለችው የአየር ትራንስፖርት በተጀመረበት ጊዜ ነው ያሉት ሚኒስትር ድኤታው፤ ላለፉት 80 ዓመት በስኬት ቆይቷል ብለዋል።

ትልቅ አየር መንገድ በማቋቋም ዓለምን የማገናኘት ሥራ አየተሠራ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከዚህ ስኬት ጀርባ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬን ባለስልጣን ትልቅ ሚና አለው ብለዋል።

ጥራቱና ደህነቱ የተረጋገጠ የአየር ትራንስፖርት እንዲኖር በማድረግ ረገድ የተጫወተው ሚና ጉልህ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ ተወዳዳሪና ተመራጭ አዬር መንገድ አንድኖራት ማስቻሉንም ገልፀዋል::

ከአቪዬሽን ኢንዱስትሪውን ፊት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይታያል ያሉት ሚኒስትር ድኤታው፤ ከጀርባ ደግሞ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ያለው ድርሻ ትልቅ ነው።

ባለፉት 80 ዓመታት ውስጥም ስኬታማ አየር መንገድ አብዲኖር የባለስልጣኑ ድርሻ ጉልህ መሆኑን ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ የኤርፖርቶች ቁጥር 23 ሲሆን ከዚህ ውስጥ 4ቱ ዓለም አቀፍ ደረጃ የያዙ መሆናቸውም ተጠቅሷል።

በሞገስ ፀጋዬ
ህዳር 23 ቀን 2017 ዓም
👍101