የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት ‼️
ከሳርቤት አደባባይ_መካኒሳ_ፉሪ ሀና በመገንባት ላይ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት የስራ ሂደት ገምግመናል።
18 ኪሜ የሚሸፍነው የኮሪደር ልማት ስራ በአካባቢው ያለውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ለማቃለል የመንገድ ደረጃውን ማሻሻል፣ የአረንጓዴ ልማት፣ የህዝብ መዝናኛ ፕላዛዎች፣ የህጻናት መጫዎቻዎች፣የእግረኛ መንገድ፣ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች፣ የታክሲና አውቶቡስ መጫኛና ማውረጃ ተርሚናሎች እንዲሁም ለረዥም ጊዜ ግንባታቸዉ ሳይጠናቀቅ የቆዩ ህንጻዎችን በፍጥነት በማጠናቀቅ ወደ አገልግሎት የማስገባትና ነባር ህንፃዎችን የማደስ ስራዎችን ያካተተ ነዉ።
በከተማ ደረጃ ከጀመርነው የኮሪደር ልማት ስራ በተጨማሪ የንፋስስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ማህበረሰቡን በማስተባበር የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን በመገንባት ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህም በአቃቂ ቃሊቲ ከተጀመረው ጋር የሚገጥም ይሆናል።
በዛሬው ጉብኝታችን አንዳንድ ቅሬታ የቀረበባቸዉ ጉዳዮችን በቦታዉ በመገኘት ከባለ ጉዳዩቹ ጋር ተመካክረን የፈታን ሲሆን፣ ስራው በፍጥነትና በጥራት እንዲከናወን ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመቆም እየደገፋችሁ ያላችሁ የአካባቢው ነዋሪዎች በራሴ እና በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ህዳር 22 ቀን 2017 ዓም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et

👍6❤1👎1😱1
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ
******
(ኢ ፕ ድ)
የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አመራር የነበሩት ጃል ሰኚ ነጋሳ መንግስት ያቀረበላቸውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት በአዲስ አበባ ላይ በዛሬው ዕለት የሰላም ስምምነቱን ተፈራርመዋል።
በስምምነቱ ላይ የተገኙት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ለመጡት ምስጋና አቅርበዋል።
ከጦረኞች በላይ ጦርነትን የሚያባብሱት ስለጦርነት የማያውቁ ናቸው። እኔ ካለኝ ልምድ አንፃር ጦርነት ጎጂ በመሆኑ የሰላምን መንገድ መርጣችሁ በመምጣታችሁ ልትመሰገኑ ይገባል ብለዋል።
ይህ አይነቱ ተግባር በሌሎች አካባቢዎችም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
የኦሮሚያ ክልል ርዕስ መስተደድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በበኩላቸው የኦሮሞ ህዝብ በባህልና በወጉ መሰረት በሮቹን ጠምዶና ፈረሶችን ጭኖ በመውጣት ሰላም ይውረድ ባለው መሰረት ጥሪውን ተቀብላችሁ በመምጣታችሁ በራሴና በክልሉ መንግስት ስም አመሠግናለሁ ብለዋል።
የመከላከያ ሠራዊት ለሰላም ስምምነቱ ላበረከተው አስተዋፅኦም ምስጋና አቅርበዋል።
በዚህ ዓለም የሰው ልጅ የፖለቲካ ልዩነት ያለው መሆኑን ያወሱት የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አመራር ጃል ሰኚ ነጋሳ እኛ ያለንን የፖለቲካ ልዩነት በጠመንጃ ከመፍታት በሰለጠነ መንገድ በጠረጴዛ ዙሪያ ለመፍታት ወስነን ስምምነቱን መርጠናል ብለዋል።
ይህ ስምምነት ለኦሮሞ ህዝብ ትልቅ እፎይታን እንደሚሰጥም ተናግረዋል።
በመረሐግብሩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ጋዛሊ አባሲመል፣ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮምሽነር ሌተናል ጄነራል ዲሪባ መኮንን የኢትዮጵያ መከላከያ መረጃ አመራሮች አባገዳዎች ሀደ ሲንቄዎችና የሃይማኖት አባቶችና ታዋቂ አትሌቶች የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመለክታል።
ህዳር 22 ቀን 2017 ዓ.ም

❤17👍12👏4😁3
አትሌት ታምራት ቶላ እና አትሌት ሲምቦ አለማየሁ የአመቱ ምርጥ አትሌቶች ተባሉ
አትሌት ታምራት ቶላ ከስታዲየም ውጭ በተደረጉ ውድድሮች የ2024 የዓመቱ ምርጥ አትሌት ሽልማትን አሸንፏል፡፡
አትሌት ሲምቦ አለማየሁ የዓመቱ ተተኪ ወጣት (Rising Star) አትሌት ሽልማትን ማሸነፏን የዓለም አትሌቲክስ መረጃ አመልክቷል።

👍23❤8
ሥራ ፈላጊ ነዎት❓
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️

❤1👍1