Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
344 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የፎረንሲክ ምርመራ ማዕከልየተደራጁ ወንጀሎችን በመመርመር ለፍትህ ሥርዓቱ አጋዥ መረጃዎችን ይሰጣል
********
(ኢ ፕ ድ)

የፎረንሲክ ምርመራ ማዕከል እንደሀገር ሊፈጸሙ የሚችሉ የተለያዩ የተደራጁ ወንጀሎችን መመርመርና ለፍትህ ሥርዓቱ አጋዥ የሆኑ መረጃዎችን የመስጠት አቅም እንዳለው የፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ። ማዕከሉ ለጎረቤት ሀገራት አገልግሎት የመስጠት አቅም እንዳለውም ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የፎረንሲክ ምርመራ ማዕከሉ በቀጣዩ ዘመን እንደሀገር ሊፈጸሙ የሚችሉ የተለያዩ የተደራጁ ወንጀሎችን መመርመርና ለፍትህ ሥርዓቱ አጋዥ የሆኑ መረጃዎችን የመስጠት አቅም ያለው ነው፡፡

የፎረንሲክ ምርመራና የምርምር ልህቀት ማዕከሉ የፎረንሲክ አቅምን ሊያሳድጉ የሚችሉ ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም በሚያስችል መልኩ ተደራጅቷል ያሉት ጀነራል መስፍን፤ በዘመኑ በሚስተዋሉ የወንጀል አይነቶች ላይ ምርመራዎችን ማካሄድ የሚያስችል የቴክኖሎጂ ግብዓቶች ተሟልተውለታል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ሕገ-ወጥ የአደንዛዥ እጽ ዝውውር ወንጀልን መከላከል የሚያስችል ጠንካራ የምርመራ ማዕከል መሆኑን ጠቅሰው፤ በማዕከሉ ወደ ውጭ ተልኮ ሲከናወን የነበረውን........https://press.et/?p=141955
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍3
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️

ኢንስታግራም/Instagram👇
https://www.instagram.com/agencyethiopianpress/
👍1🔥1
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት ‼️

ከሳርቤት አደባባይ_መካኒሳ_ፉሪ ሀና በመገንባት ላይ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት የስራ ሂደት ገምግመናል።

18 ኪሜ የሚሸፍነው የኮሪደር ልማት ስራ በአካባቢው ያለውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ለማቃለል የመንገድ ደረጃውን ማሻሻል፣ የአረንጓዴ ልማት፣ የህዝብ መዝናኛ ፕላዛዎች፣ የህጻናት መጫዎቻዎች፣የእግረኛ መንገድ፣ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች፣ የታክሲና አውቶቡስ መጫኛና ማውረጃ ተርሚናሎች እንዲሁም ለረዥም ጊዜ ግንባታቸዉ ሳይጠናቀቅ የቆዩ ህንጻዎችን በፍጥነት በማጠናቀቅ ወደ አገልግሎት የማስገባትና ነባር ህንፃዎችን የማደስ ስራዎችን ያካተተ ነዉ።

በከተማ ደረጃ ከጀመርነው የኮሪደር ልማት ስራ በተጨማሪ የንፋስስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ማህበረሰቡን በማስተባበር የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን በመገንባት ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህም በአቃቂ ቃሊቲ ከተጀመረው ጋር የሚገጥም ይሆናል።

በዛሬው ጉብኝታችን አንዳንድ ቅሬታ የቀረበባቸዉ ጉዳዮችን በቦታዉ በመገኘት ከባለ ጉዳዩቹ ጋር ተመካክረን የፈታን ሲሆን፣ ስራው በፍጥነትና በጥራት እንዲከናወን ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመቆም እየደገፋችሁ ያላችሁ የአካባቢው ነዋሪዎች በራሴ እና በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ህዳር 22 ቀን 2017 ዓም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍61👎1😱1