Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
344 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የእስያ መሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ ፕሬዚዳንት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኘ
****
(ኢ ፕ ድ)
በእስያ መሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ ፕሬዚዳንት ጂን ሊኩን የተመራ ልዑክ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኘ።

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ጋርም ውይይት አድርገዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድን አጠቃላይ የስራ እስቅስቃሴና በአፍሪካ አህጉር በመሪነት የሚጠቀስባቸውንና በዓለም ደረጃ ተወዳዳሪነቱን ያስጠበቀባቸውን የስራ ክፍሎችና የአቪዬሽን ቴክኖሎጂዎችን መመልክታቸውን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ህዳር 21 ቀን 2017 ዓም
👍4
በገቢዎች ቢሮ ሰራተኛ ስም ደረሰኝ በመጠየቅ ሲያጭበረብር የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ
**
(
ኢ ፕ ድ)
መርካቶ በተለምዶ ድር ተራ እየተባለ በሚጠራ አካባቢ በገቢዎች ቢሮ ሰራተኛ ስም ደረሰኝ በመጠየቅ ሲያጭበረብር የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አሰታወቀ።

በህግ ቁጥጥር ስር የዋለው ተጠርጣሪ ግለሰብ በመርካቶ የቢሮው ሰራተኛ ነኝ በማለት ደረሰኝ በመጠየቅ ንግድ ቤቶች በመግባት የዕቃዎች ደረሰኝ ሲጠይቅና ሲያጭበረብር የነበረ መሆኑ ለማወቅ ተችሏል።

ተጠርጣሪው ግለሰብ በቁጥጥር ስር የዋለው በመርካቶ በተመደቡ የቢሮው የቁጥጥር ባለሙያዎች መሆኑን የመርካቶ ቁጥር 1 ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የህግ ተገዥነት ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ፓርቲ  ንጉሴ ገልጸዋል።

የንግዱ ማህበረሰብ በቢሮው የተመደቡ የቁጥጥር ባለሙያዎች በቡድን የሚንቀሳቀሱ፣ መለያ ባጅና መታወቂያ ያላቸው መሆኑን መለየት እንዳለበት ቢሮው አሳስበዋል።

መሰል ድርጊት ሲያግጥም በነፃ የስልክ መስመር 7075 እና በአቅራቢያው ለሚገኙ የህግ አስከባሪዎች መጠቆም እንዳለበት ተመላክቷል።

ህዳር 21 ቀን 2017 ዓም
👍3😁1
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዳዲስ ሹመቶችን ሰጠ፤

✍️ አቶ ግርማ ሰይፉ - የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ

✍️ ወ/ሮ ቆንጂት ደበለ- የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር

✍️ ወ/ሮ ኒዕመተላህ ከበደ⁠ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ

✍️ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ - የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ስራ አስኪያጅ

✍️ አቶ ሙባረክ ከማል- የባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ

✍️ አቶ ሁንዴ ከበደ - የባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የባህል ዘርፍ ምክትል ኃላፊ

✍️ አቶ ታረቀኝ ገመቹ - የንግድ ቢሮ ፅሕፈት ቤት ኃላፊ⁠ ሆነው መሾማቸውን የከንቲባ ጽሕፈት መረጃ ያመለክታል።

ህዳር 21 ቀን 2017 ዓም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክhttps://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍8👎4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከእስያ መሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ ፕሬዝዳንት ጂን ሊኩን ጋር ያደረጉት ውይይት‼️
👍6👎6
የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና እና የአዘርባጃኑ አላት ነፃ የንግድ ቀጣና በትብብር ለመስራት ተስማሙ
*****
(ኢ ፕ ድ)
የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና እና የአዘርባጃኑ አላት ነፃ የንግድ ቀጣና በትብብር ለመስራት ተስማሙ።

በኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች የተመራ ልዑክ በአዘርባጃን የአላት ነፃ የኢኮኖሚ ዞንን ጎብኝቷል።

ጉብኝቱ በቅርቡ ወደ ሙሉ ትግበራ ለገባው የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና የአንድ መስኮት አገልግሎት አሰጣጥን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ አሰራሮች ፤ ልምድና ተሞክሮዎች የተቀሰሙበት እንደነበረም ተገልጿል።

የመስክ ምልከታው በአላት እና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና መካከል ተቋማዊ ግንኙነት በመፍጠር በቀጣይ በትብብር ለመስራት የሚያስችል መደላድል የፈጠረ መሆኑ ተገልጿል።

ከተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት የተውጣጣው ልዑካን ቡድኑ ከአላት ነፃ ኢኮኖሚ ዞን በተጨማሪ ከኢንዱስትሪ ፓርክ ተቋማት ከጥቃቅንና አነስተኛ ኤጀንሲ የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይትና የመስክ ምልከታ አድርገዋል።

የአላት ነፃ ኢኮኖሚ ዞን በአዘርባጃን ርዕሰ መዲና ባኩ በ719 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ መሆኑን ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ህዳር 22 ቀን 2017 ዓም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍41
የፎረንሲክ ምርመራ ማዕከልየተደራጁ ወንጀሎችን በመመርመር ለፍትህ ሥርዓቱ አጋዥ መረጃዎችን ይሰጣል
********
(ኢ ፕ ድ)

የፎረንሲክ ምርመራ ማዕከል እንደሀገር ሊፈጸሙ የሚችሉ የተለያዩ የተደራጁ ወንጀሎችን መመርመርና ለፍትህ ሥርዓቱ አጋዥ የሆኑ መረጃዎችን የመስጠት አቅም እንዳለው የፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ። ማዕከሉ ለጎረቤት ሀገራት አገልግሎት የመስጠት አቅም እንዳለውም ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የፎረንሲክ ምርመራ ማዕከሉ በቀጣዩ ዘመን እንደሀገር ሊፈጸሙ የሚችሉ የተለያዩ የተደራጁ ወንጀሎችን መመርመርና ለፍትህ ሥርዓቱ አጋዥ የሆኑ መረጃዎችን የመስጠት አቅም ያለው ነው፡፡

የፎረንሲክ ምርመራና የምርምር ልህቀት ማዕከሉ የፎረንሲክ አቅምን ሊያሳድጉ የሚችሉ ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም በሚያስችል መልኩ ተደራጅቷል ያሉት ጀነራል መስፍን፤ በዘመኑ በሚስተዋሉ የወንጀል አይነቶች ላይ ምርመራዎችን ማካሄድ የሚያስችል የቴክኖሎጂ ግብዓቶች ተሟልተውለታል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ሕገ-ወጥ የአደንዛዥ እጽ ዝውውር ወንጀልን መከላከል የሚያስችል ጠንካራ የምርመራ ማዕከል መሆኑን ጠቅሰው፤ በማዕከሉ ወደ ውጭ ተልኮ ሲከናወን የነበረውን........https://press.et/?p=141955
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍3
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️

ኢንስታግራም/Instagram👇
https://www.instagram.com/agencyethiopianpress/
👍1🔥1
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት ‼️

ከሳርቤት አደባባይ_መካኒሳ_ፉሪ ሀና በመገንባት ላይ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት የስራ ሂደት ገምግመናል።

18 ኪሜ የሚሸፍነው የኮሪደር ልማት ስራ በአካባቢው ያለውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ለማቃለል የመንገድ ደረጃውን ማሻሻል፣ የአረንጓዴ ልማት፣ የህዝብ መዝናኛ ፕላዛዎች፣ የህጻናት መጫዎቻዎች፣የእግረኛ መንገድ፣ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች፣ የታክሲና አውቶቡስ መጫኛና ማውረጃ ተርሚናሎች እንዲሁም ለረዥም ጊዜ ግንባታቸዉ ሳይጠናቀቅ የቆዩ ህንጻዎችን በፍጥነት በማጠናቀቅ ወደ አገልግሎት የማስገባትና ነባር ህንፃዎችን የማደስ ስራዎችን ያካተተ ነዉ።

በከተማ ደረጃ ከጀመርነው የኮሪደር ልማት ስራ በተጨማሪ የንፋስስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ማህበረሰቡን በማስተባበር የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን በመገንባት ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህም በአቃቂ ቃሊቲ ከተጀመረው ጋር የሚገጥም ይሆናል።

በዛሬው ጉብኝታችን አንዳንድ ቅሬታ የቀረበባቸዉ ጉዳዮችን በቦታዉ በመገኘት ከባለ ጉዳዩቹ ጋር ተመካክረን የፈታን ሲሆን፣ ስራው በፍጥነትና በጥራት እንዲከናወን ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመቆም እየደገፋችሁ ያላችሁ የአካባቢው ነዋሪዎች በራሴ እና በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ህዳር 22 ቀን 2017 ዓም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍61👎1😱1