Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
344 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️

ኢንስታግራም/Instagram👇
https://www.instagram.com/agencyethiopianpress/
🔥2
"ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት አምስት ዓመታት በሁሉም ዘርፎች በርካታ ስኬቶችን ያስመዘገበ ፓርቲ ነው"

- የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንትና የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
******
(ኢ ፕ ድ)
ብልፅግና ፓርቲ በአምስት ዓመታት ጉዞው በሁሉም ዘርፎች በርካታ ስኬቶችን ያስመዘገበ የአፍሪካ ግዙፉ ፓርቲ ነው ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንትና የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት ምስረታ በዓል ሀገራዊ ማጠቃለያ መርሐግብር ዓድዋ መታሳቢያ ሙዚየም ተካሄዷል፡፡

በወቅቱ የብልፅግና ፕሬዚዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ብልፅግና ኢትዮጵያ ከድህነትና ከችግር እንድትወጣ ሌት ተቀን የሚሰራ ፓርቲ ነው። ፓርቲው አባላቱና መላውን ህዝብ በማስተባበርና በማሳተፍ ሁለተናዊ ስኬቶችን አስመዝግቧል።

ብልጽግና ራዕያችን እንድናሳካ፤ ህልማችንንና ችግሮቻችን ፈትተን እንድንስራ የሚያደርገን ጉልበታችን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ መላ ኢትዮጵያዊያን የወል እውነታችን ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ብልጽግና መለያው እውነት፣ እውቀትና ጥበብ መሆኑን ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያን የላቀ ከፍታ ላይ ለማድረስ ሙሉ ዕይታ ያለውና በሁሉም ዘርፎች በርካታ ስኬቶችን ያስመዘገበ ፓርቲ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዲፕሎማሲ፣ በኢኮኖሚ፣ በኮሪደር ልማት፣ በግብርና፣ በቱሪዝም፣በቴክኖሎጂና በሌሎች ዘርፎች የሚጨበጡና የሚታዩ ስኬቶችን ባለፉት አምስት ዓመታት ማስመዝገቡን ጠቅሰዋል፡፡

በጌትነት ምህረቴ

ህዳር 21 ቀን 2017 ዓም
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍10🖕3👎2😁1
የእስያ መሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ ፕሬዚዳንት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኘ
****
(ኢ ፕ ድ)
በእስያ መሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ ፕሬዚዳንት ጂን ሊኩን የተመራ ልዑክ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኘ።

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ጋርም ውይይት አድርገዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድን አጠቃላይ የስራ እስቅስቃሴና በአፍሪካ አህጉር በመሪነት የሚጠቀስባቸውንና በዓለም ደረጃ ተወዳዳሪነቱን ያስጠበቀባቸውን የስራ ክፍሎችና የአቪዬሽን ቴክኖሎጂዎችን መመልክታቸውን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ህዳር 21 ቀን 2017 ዓም
👍4
በገቢዎች ቢሮ ሰራተኛ ስም ደረሰኝ በመጠየቅ ሲያጭበረብር የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ
**
(
ኢ ፕ ድ)
መርካቶ በተለምዶ ድር ተራ እየተባለ በሚጠራ አካባቢ በገቢዎች ቢሮ ሰራተኛ ስም ደረሰኝ በመጠየቅ ሲያጭበረብር የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አሰታወቀ።

በህግ ቁጥጥር ስር የዋለው ተጠርጣሪ ግለሰብ በመርካቶ የቢሮው ሰራተኛ ነኝ በማለት ደረሰኝ በመጠየቅ ንግድ ቤቶች በመግባት የዕቃዎች ደረሰኝ ሲጠይቅና ሲያጭበረብር የነበረ መሆኑ ለማወቅ ተችሏል።

ተጠርጣሪው ግለሰብ በቁጥጥር ስር የዋለው በመርካቶ በተመደቡ የቢሮው የቁጥጥር ባለሙያዎች መሆኑን የመርካቶ ቁጥር 1 ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የህግ ተገዥነት ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ፓርቲ  ንጉሴ ገልጸዋል።

የንግዱ ማህበረሰብ በቢሮው የተመደቡ የቁጥጥር ባለሙያዎች በቡድን የሚንቀሳቀሱ፣ መለያ ባጅና መታወቂያ ያላቸው መሆኑን መለየት እንዳለበት ቢሮው አሳስበዋል።

መሰል ድርጊት ሲያግጥም በነፃ የስልክ መስመር 7075 እና በአቅራቢያው ለሚገኙ የህግ አስከባሪዎች መጠቆም እንዳለበት ተመላክቷል።

ህዳር 21 ቀን 2017 ዓም
👍3😁1
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዳዲስ ሹመቶችን ሰጠ፤

✍️ አቶ ግርማ ሰይፉ - የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ

✍️ ወ/ሮ ቆንጂት ደበለ- የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር

✍️ ወ/ሮ ኒዕመተላህ ከበደ⁠ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ

✍️ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ - የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ስራ አስኪያጅ

✍️ አቶ ሙባረክ ከማል- የባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ

✍️ አቶ ሁንዴ ከበደ - የባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የባህል ዘርፍ ምክትል ኃላፊ

✍️ አቶ ታረቀኝ ገመቹ - የንግድ ቢሮ ፅሕፈት ቤት ኃላፊ⁠ ሆነው መሾማቸውን የከንቲባ ጽሕፈት መረጃ ያመለክታል።

ህዳር 21 ቀን 2017 ዓም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክhttps://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍8👎4