Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌታሁን መኩሪያ በአዳማ ከተማ በ ህብረተሰብ ተሳትፎ በ 1.2 ሚሊየን ብር የተገነባውን ደምበላ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጎበኙ።

በትምህርት ቤቱ በ ህብረተሰቡ ተሳትፎ 4 አዳዲስ ክፍሉች የተሰሩ ሲሆን 3 ክፍሉች ደግሞ ታድሰው ለ አገልግሎት ዝግጁ ሆነዋል።

በትምህርት ቤቱም የውሃ ቧንቧዎች እና የማንበቢያ ፖርኮች ተገንብተው ተጠናቀዋል

ትምህርት ቤቶቹም በህብረተሰቡ ተሳትፎ መገንባታቸውን የአዳማ ከተማ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ታምሬ ቡሹ ተናግረዋል።
በሰሜን ሸዋ ዞን አራት ወረዳዎች የበረሃ አንበጣ መንጋ መከሰቱ ተገለጸ
**************

በሰሜን ሸዋ ዞን አራት ወረዳዎች በቀወት ወረዳ እምባይ ጎድ ሙቅ ውኃ በሚባል አካባቢ 16 ሄክታር መሬት ላይ የበረሃ አንበጣ መንጋ መከሰቱ ተገልጿል።

የተከተሰውን የበረሃ አንበጣ መንጋ ለመከላከልም ከሌሊት 10 ሰዓት ጀምሮ የአካባቢው አርሶ አደሮች፣ የመንግሥት ሠራተኞችና የአማራ ክልል የልዩ ኃይል ፖሊስ አባላት ጥረት እያደረጉ መሆኑ ተገልጿል።

የበረሃ አንበጣ መንጋው በባሕሪው ተንቀሳቃሽ በመሆኑ የመከላከል ሥራውን ፈታኝ እንዳደረገባቸው የቀወት ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታደሰ ማሙሸት አስታውቀዋል።

የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል ግብረ ኃይል መቋቋሙንና በአውሮፕላን ርጭት ለማካሄድ ሸዋ ሮቢት የሚገኘውን የአውሮፕላን ማረፊያ የማፅዳት ሥራ ተሰርቶ ወደ ርጭት እንደሚገባ አብመድ ዘግቧል።
በመምህርነት ሲያገለግሉ የነበሩ ባለሙያዎች ሀገራዊ ሃላፊነታቸውን ለመወጣት ዝግጅት እንዲያደርጉ ተጠየቀ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለ7 ወራት የተቋረጠውን የመማር ማስተማር ሂደት ለማገዝ ከዚህ ቀደም በመምህርነት ሙያ ሲያገለግሉ የነበሩ መምህራን በአቅራቢያቸው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለማገልገል ዝግጅት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር መደበኛ ትምህርትን በሚያስቀጥልበት ወቅት በትምህርት ቤቶች አካላዊ እርቀትን ለማስጠበቅ የተማሪዎች ቁጥር ከ20-25 እንዲሆን መወሰኑን ተከትሎ ትምህርት ቤቶች እንደየ አካባቢያቸው ሁኔታ በፈረቃ ትምህርት የሚሰጡ ይሆናል፡፡
በዚህም ወቅት በትምህርት ቤቶች የመምህራን እጥረት እንዳይኖር ለማድረግ ከዚህ ቀደም በመምህርነት ሲያገለግሉ የነበሩና የ መምህርነት ስልጠናን ወሰደው ሌላ ዘርፍ የተቀላቀሉ ባለሙያዎች በየአካባቢያቸው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተመልሰው ሃገራዊ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌታሁን መኩሪያ "እኔም አስተምራለው" በሚል መሪ ቃል ከ ሰኞ ጀምሮ በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች ከዚህ ቀደም በምህርነት ሲያገለግሉ የነበሩና በ መምህርነት ሙያ የሰለጠኑ ባለሙያዎችን የመመዝገብ ስራ ይሰራል ብለዋል።
በዚህም መሰረት ባለሙያዎች በአቅራቢያቸው ባሉ ትምህርት ቤቶች በመሄድ እና በመመዝገብ የትምህርቱን ዘርፍ በሙያቸው እንዲያግዙ ሚኒስትሩ ጥሪ ማቅረባቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
️እንጦጦ ድሮ እና ዘንድሮ!

👉 እንጦጦ መስከረም 2012 ዓ.ም
እና
👉 እንጦጦ መስከረም 2013 ዓም
በቦሌ ኤርፖርት 3.4 ሚሊዮን ብር የሚገመት ወርቅ በቁጥጥር ስር ዋለ
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)

አንድ ነጥብ አራት ኪሎ ግራም መጠን ያለው ወርቅ አዲስ አበባ ከሚገኘው የካሜሮን ኤምባሲ ወደ ካሜሮን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተላከ መልዕክት በማስመሰል ከሀገር ለማስወጣት ሲሞከር በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

በአዲስ አበባ ኤርፖርት ወደ ካሜሮን ለመጓዝ ዝግጅት ሲያደርግ የነበረ መንገደኛ የዲፕሎማቲክ መልዕክት በማስመሰል ለማሳለፍ ሲሞክር በማሽን በታገዘ ፍተሻ ሊያዝ ችሏል፡፡

የተያዘው ወርቅ በወቅታዊ የብሔራዊ ባንክ የመግዣ ዋጋ ሶስት ሚሊዮን አራት መቶ ሺህ (3,400,000) ብር ግምታዊ ዋጋ ወጥቶለታል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር የሀገርን ሀብት ከምዝበራ የታደጉ የጉምሩክ ሰራተኞች እና የፀጥታ አካላት ምስጋናውን አቅርቧል።
"በአለም አቀፍ ደረጃ በየ10-15 ሰከንዶች ውስጥ በኮቪድ ሳቢያ አዲስ ሞት ይመዘገባል፡፡ እያንዳንዱ ሕይወት ውድ ነው:: እባካችሁ: እባካችሁ እንጠንቀቅ!"
ዶ/ር ሊያ ታደሰ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጥቅምት 04 ቀን 2013 ዶ/ር አረጋዊ በርሔን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አድርገው ሾመዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአማራ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ መስተዳድሮችና ከጸጥታ አካላት ጋር በመተከል ዞን በተከሰቱ ግጭቶች ዙሪያ ተወያዩ
**************************
(ኢፕድ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከአማራ፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የክልል መስተዳድሮች እንዲሁም ከጸጥታ አካላት ጋር በመሆን በመተከል ዞን የተከሰቱ ግጭቶችን አስመልክቶ ውይይት አካሄዱ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ያሉትን ችግሮች በመፈተሸ፣ የአካባቢውን ዘላቂ ሰላም ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ቀጣይ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።
በደላሎች ተታለው ወደ ሱዳን ገብተው ታስረው የነበሩ 38 ኢትዮጵያውያን ክስ ሳይመሰረትባቸው ከእስር ተፈቱ
**********************************
(ኢ.ፕ.ድ)

በደላሎች አማካኝነት ተታለው ወደ ሱዳን ገብተው ታስረው የነበሩ 38 ኢትዮጵያውያንን ክስ ሳይመሰረትባቸው ከእስር መፈታታቸው ተገለጸ።

እነዚሁን ዜጎች ከእሥር በማስፈታት በኮሚዩኒቲ እና በኤምባሲው አስፍላጊውን ድጋፍ በማድረግ ወደ አገራቸው የሚመለሱበትና ከቤተስባቻቸው ጋር የሚቀላቀሉበትን መንገድ እያመቻቸ መሆኑም በሱዳን የኢትዮጵያ ኤንባሲ አስታውቋል።

ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ሱዳንን እንደ መሸጋገሪያ በመጠቀም ወደ ተለያዩ የመካከለኛው ምስራቅ አገራት ዜጎችን በማይጨበጥ ተስፋ በመደለልና በማታለል በየጊዜው ብዛት ያላቸውን ኢትዮጵያውያንን ወደ ሱዳን በሕገወጥ መንገድ በማስገባት መንገላታት የሚደርስባቸውን ዜጎች ፣ ኤምባሲው ከሚመለከታቸው የሱዳን የጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር ተጠቂዎችን ከደላሎች መጋዝን እና ከእስር ነጻ በማውጣት ለአገራቸው እንዲበቁ ሲያደርግ መቆየቱ አስታውሷል፡፡

ዜጎች መንግስት የስራ ስምምነት ከተፈራረመባቸው አገራት ብቻ በአገር ቤት በመመዝገብ፣ አስፈላጊው የስልጠና ቅድመ ሁኔታ በማሟላት ወደ ውጭ ጉዞ እንዲያደርጉ ኤንባሲው መክሯል።
በአዲስ አበባ ከነገ ጀምሮ 560 አውቶብሶች ወደ ስምሪት ይገባሉ
*******************************
(ኢፕድ)
የአዲስ አበባ ከተማን የትራንስፖርት ችግር ለመቅርፍ ከነገ ጀምሮ 560 የግል ማህበራት አውቶብሶች በኪራይ ወደ ስምሪት አንደሚገቡ ተገልጿል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ከግል የትራንስፖርት ማህበራት ጋር ስምምነት በማድረግ ነው አውቶብሶቹ በኪራይ ወደ ስምሪት አንደሚገቡ የተጠቆመው፡፡

በዛሬው እለትም የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ዣንጥራር አባይን ጨምሮ ሌሎች የከተማዋ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት በመስቀል አደባባይ የስምሪት ፕሮግራሙ ይፋ በመደረግ ላይ ነው።

ፕሮግራሙ በይፋ መጀመሩን አስመልክቶ ለከተማዋ ማህበረሰብ ከነገ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚሰጥም ተነግሯል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
"የመደመር መንገዳችን ያለ ልዩነት ለሁሉም ዜጎቻችን የተዘረጋ አዲስ የብርሃን መንገድ ነው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ

የመደመር መንገዳችን ያለ ልዩነት ለሁሉም ዜጎቻችን የተዘረጋ አዲስ የብርሃን መንገድ ነው ፡፡መዳረሻ ግባችን ብልጽግና ነው። ብልጽግና ንጋት እንጂ ሌት ሆኖ ማንንም አይጋርድም፣ አይሸፍንምም፡፡

በትኅትና የማይበርድ ቁጣ፣ በልግስና የማይጠወልግ ስስት፣ በደግነት የማይሰበር ክፉት፣ በመደመር የማይጠገን ልዩነት፣ በብልጽግና የማይኮሰምን እርዛት፣ በሐቅ የማይረታ ሐሰት አለመኖሩን ዐውቀን በጽናት ጉዟችንን እንቀጥላለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
"በራሳችን ዘመን ደረጃ የምንመዘን ትውልዶች ነን፡፡  ለሀገራችን ባስቀመጥነው ጡብ፣ ለኢትዮጵያ በከፈልነው መስሥዋትነት፣ ለሕዝባችን በዋልነው ውለታ ልክ እንዳኛለን። አዲስ ታሪክ ሠሪዎች ጭምር እንጂ፤ ነባር ታሪክ ተራኪዎች ብቻ አይደለንም፡፡ በራሳችን ሐሳብ ተነጋግረን የምንግባባ እንጂ፤ እየተወዛገብን ዕንቁ ዘመናችንን በከንቱ አናባክንም። የእኛ ትውልድ በሀገራችን ታሪክ ወርቃማው ትውልድ ሆኖ ያልፋል"

- የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው በሰጡት ማብራሪያ ስለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች ( 3 )
👉 ህዳሴ ግድብ ባለፈው አመት ጥሩ ስራ ተሰርቶ ጥሩ ውጤትም
መጥቷል ከዚህ በኋላ የባለፈውን አመት ድል መተረት መቆም
አለበት፤
👉 ህዳሴ ሀ ብሎ የሚጀምረው ዘንድሮ ነው ዘንድሮ የምንሰራው ስራ
ከአምናው በብዙ እጥፍ ይፈትነናል በገንዘብ እንፈተናለን ፣በቴክኒክ
እንፈተናለን፤
👉 የህዳሴ ግድብ ግንባታ ትልቅ ክትትልና ድጋፍ የሚፈልግ ፕሮጀክት
ነው፤
👉 የህዳሴ ግድብ ግንባታ እንዲደናቀፍ ከውስጥም ከውጪም
የሚፈልገው ሀይል በጣም ብዙ ነው፤
👉 ዘንድሮን ጠንክረን ከሰራን በሚቀጥለው ዓመት ግን እንደዘንድሮ
ከባድ አይሆንም፤
👉ስራው በሁሉም መስክ በጥሩ መንገድና በቅርብ ክትትልና ድጋፍ
እየተደረገ እየሄደነው፤
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው በሰጡት ማብራሪያ ላይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች.. ( 2 )
👉 ባለፈው አመት ኮሮና በዓለም ላይ ከፍተኛ ጫና ባሳደረበት ወቅት
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ 6.1 በመቶ እድገት አስመዝገቧል፤
👉 ዘንድሮ ለጤናው ዘርፍ 16 ቢሊዮን ብር ነው የተመደበለት፤ ካምናው
አንጻር ትልቅ እድገት ካሳዩ ዘርፎች መካከል አንዱ ያደርገዋል፤
👉20 የሚጠጉ የአዳዲስ የባንክ ምስረታ ጥያቄ ቀርቧል፤ አብዛኛዎቹ
ሂደቱን ጨርሰው ወደ ኢኮኖሚው ከተቀላቀሉ ትልቅ ሚና
ይጫወታሉ፤
👉 ነባር ባንኮች በዘንድሮው አመት በጥናት ላይ በመመስረት
ካፒታላቸውን ከፍ እንዲያደርጉ ይደረጋል፤ በቀጠና ደረጃ ለመወዳደር
የሚያስችል ምዕራፍ ላይ መድረስ አለባቸው፤
👉 አነስተኛና ጥቃቅን የነበሩ የፋይናንስ ተቋማት ወደ ባንክ
እንዲያድረጉ የተለያዩ ስራዎች ይሰራሉ፤
👉 በሀምሌ ነሀሴና መስከረም የተሰሩ ዋና ዋና ስራዎች መካከል አንዱ
የገንዘብ ለውጥ ነው፤ ይህ ለውጥ ያስፈለገበት ብዙ ስብራት ያለበትን
ኢኮኖሚ ለማረቅም ታስቦ ነው፤ ብዙ ሀብት ወደኢኮኖሚው የተረጨ
በመሆኑና ለመቆጣጠር አስቸጋሪ አድረጎት ቆይቷል፤
👉 ከብር ለውጡ በኋላ 1.3 ሚሊዮን ሰዎች አዳዲስ አካውንት ከፍተዋል፤
በዚህም 37 ቢሊዮን ብር ተቆጥቧል፤
👉 ህገ ወጥ ገንዘቦች ተይዘዋል፤ ገና ብዙ ገንዘብ እንደሚመክን
ይጠበቃል፤
👉 እስካሁን በነበረው ሁኔታ በአጠቃላይ የገንዘብ ለውጡ እንቅስቃሴ ላይ
በመቶ በመቶ በሚባል ደረጃ ስራው በስኬት ተከናውኗል፤ ሁሉም
ባለድርሻዎች ምስጋና ይገባቸዋል፤
👉 ከሸቀጦች የወጪ ንግድ ገቢ በሀምሌ ነሀሴና መስከረም ላይ 832.3
ሚለዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፤ ያለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት
የተገኘው 723 ሚሊዮን ዶላር ነበር፤ ይህ ማለት የ15 በመቶ እድገት
አሳይቷል፤
👉 ባለፉት ሶስት ወራት የነበረው ገቢ 63.1 ቢሊዮን ብር ነው፤ ከእቅድ
አንጻር 106 በመቶ ከአምናው አንጻር 10 በመቶ እድገት አሳይቷል፤
ይሄንን ጠብቀን ከሄድን ባሰብነው ልክ እናስገባለን፤
👉 የወጪ ምንዛሬ ክምችት ባለፉት ሶስት ወራት የነበረው ክምችት
ከአምናው አንጻር የ20 በመቶ እድገት አሳይቷል፤
👉 ከካፒታል ወጪ አንጻር ባለፉት ሶስት ወራት 96 ቢሊዮን ብር ወጪ
አድርገናል፤ ከእቅዳችን የበለጠ አይደለም፤
👉 የዋጋ ግሽበት ባለፉት ሶስት ወራት መቀነስ አሳይቷል፤ ነገር ግን በቂ
አይደለም፤
👉 በምግብ ነክ ላይ ያለው ግሽበት በመስከረም ወር ላይ 21 በመቶ
መሆኑን ያሳያል፤
👉 የዋጋ ንረት ገፊ ምክንያቶች ምንድን ናቸው የሚሉተን በጥናት
በደንብ መለየት ያስፈልጋል፤
👉 የግብርና ምርት ስራዎችን በቴክኖሎጂ፣ በመስኖና በኩታ ገጠም
በመጠቀም ምርትን ማሳደግ ያስፈልጋል፤
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው በሰጡት ማብራሪያ ላይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች ( 1 )
👉ባለፈው አመት የባንኮች ቅርንጫፍ ተበራክቷል፤ የቅርንጫፎች ቁጥር
በ18 በመቶ አድጓል፤
👉 የጣና በለስ ፕሮጀክትን ሜቴክ 8 አመት ሰርቶ 62 በመቶ ነው
ያደረሰው፤ ኮንትራቱን ከሜቴክ አቋርጠን ለቻይና ኩባንያ ሰጥተን
ስራውን በስምንት ወር 85 በመቶ አድርሶታል፤ የፕሮጀክቱ ዋና
ችግር ፋይናንስ አይደለም፤ እስካሁን 23 ሚሊዮን ዶላር መድበናል፤
👉 የቅርንጫፎች መስፋፋት ትልቅ ለውጥ አምጥቷል፤ ባለፈው አመት
የተቀማጭ ሂሳብ የነበራቸው ዜጎች ቁጥር 38.7 ሚሊዮን ነበር፤ አሁን
ላይ 50.7 ሚሊዮን ዜጎች የተቀማጭ ሂሳብ ከፍተዋል፤ ይህ ብቻ 31
በመቶ እድገት መመዝገቡን ያሳያል፤
👉 ባንኮች በቁጠባ አንድ ትሪሊየን ብር ሰብስበዋል፤
ከተሰበሰበው ሀብት 60 በመቶ የሚሆነው በአዲስ አበባ
የሚገኝ ነው፤ በኦሮሚያ 13.7 በመቶ ተሰብስቧል፤ በአማራ 7.3፣
በደቡብ 5.2 ሲሆን የተቀረው በሌሎች ክልሎች የተሰበሰበው ነው፤
👉 ዘንድሮ ከተሰበሰበው ገንዘብ ውስጥ 271 ቢሊዮን ብር ባንኮች
አበድረዋል፤ ከዚህ ውስጥ 70 ከመቶው ለግል ሴክተር የተሰጠ ነው፤
👉 የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተጽዕኖ ያሳረፈባቸው ዘርፎች አሉ፤
ከእነዚህም መካከል--
👉 ትራንስፖርት ከሚጠበቀው እድገት በ21 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል፤
👉 ትምህርት 1.8 በመቶ ብቻ ነው ያደገው፤
👉 የህዝብ አገልግልት በ2.3 በመቶ ብቻ ነው ያደገው፤
👉 ቱሪዝም በ9 በመቶ ወድቋል፤
👉 መንግስት ለቱሪዝምና ለሆቴል አገልግሎት በኮሮና ምክንያት
ለደረሰባቸው ጉዳት የ3.3 ቢሊዮን ብር ብድር አመቻችቷል፤