Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የተቀላጠፈ የመንጃ ፈቃድ እድሳት አገልግሎት እያገኙ ባለመሆናቸው ደንበኞች ቅሬታ አቀረቡ
********************
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ ከተማ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን የአራዳ ክፍለ ከተማ ቅርጫፍ አንዳንድ ደንበኞች የተቀላጠፈ የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት አገልግሎት እያገኙ አለመሆናቸውን ቅሬታ አቀረቡ። ቅርጫፍ ጽህፈት ቤቱ ቅሬታውን በመቀበል ደንበኞች ከዚህ በኋላ በየትኛውም የአገልግሎት መስጫዎች የሚስተናገዱበት የአሰራር ሥርዓት እንደሚዘረጋ ገለጸ።
ቅሬታቸውን ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ የገለጹ አንዳንድ የቅርጫፉ ደንበኞች በቅርጫፉ የሚሰጠው አገልግሎት ጊዜና ገንዘብ ቆጣቢ አለመሆኑ፤ ተቋሙ ማሟላት ያለበትን ባለማሟላቱ በአጭር የቀጠሮ ጊዜ ለአገልግሎት መመላለሳቸው፣ ለኮቪድ 19 ቫይረስ ወረርሽኝ በሚያጋልጥ የአገልግሎት አሰጣጥ መስተናገዳቸው ቅሬታ እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል።
ከደንበኞቹ መካከልም ወይዘሮ ሰናይት አበበ የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት አገልግሎት ለማግኘት ጠዋት አንድ ሰአት ላይ ቀድመው በቅርጫፉ መገኘታቸውን ገልጸው፣ ከሰአታት ቆይታ በኋላ ተራ ደርሷቸው የሚያስተናግዳቸው ጋር ሲደርሱ ፎቶግራፍ በሲዲ እንዲያመጡ በመጠየቃቸው ከቅርጫፉ ውጭ ወጥተው የተጠየቁትን ካሟሉ በኋላም እስከ ቀኑ ዘጠኝ ሰአት ድረስ አገልግሎት እንዳላገኙ ተናግረዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=39493
ገቢያቸውን እያሳወቁ ታክስ የሚከፍሉ ነጋዴዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ተጠቆመ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ ከተማ ገቢያቸውን እያሳወቁ ታክስ የሚከፍሉ ዜጎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የኮሙኒኬሽን ቡድን አስተባባሪ አቶ በላይነህ ወልደሰንበት ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፣ በደረጃ ‹‹ሀ›› ፣ ‹‹ለ›› እና ‹‹ሐ›› የተመዘገቡ ግብር ከፋይ ደንበኞች ገቢያቸውን እያሳወቁ ታክስ የመክፈል ልምዳቸው እያደገ መጥቷል።
በበጀት ዓመቱ ሩብ ዓመት 390 ሺ 649 ግብር ከፋዮች ገቢያቸውን አሳውቀው የሚጠበቅባቸውን ይከፍላሉ ተብሎ ዕቅድ ተይዞ እንደነበር አመልክተው፣ እስከ አሁን ድረስ 307 ሺ 298 ገቢያቸውን አሳውቀው የሚጠበቅባቸውን ግብር መክፈላቸውን አስታውቀዋል። ይህም ከእቅዱ 78 ነጥብ ስምንት በመቶ መሆኑን ጠቁመዋል።
ይህም ከአምናው ተመሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ17 በመቶ በላይ ብልጫ እንዳለው ጠቁመው ፣ ይህም ዜጎች ሃላፊነታቸውን ተረድተው የሚጠበቅባቸውን ታክስ የመክፈል ግንዛቤያቸው እያደገ መምጣቱን የሚያሳይ ነው ብለዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=39501
ጤና ቢሮው ህፃናት የአፍና የአፍንጫ መከላከያ ሳያደርጉ ትምህርት ቤት እንዳይሄዱ ማድረግ እንደሚገባ መክሯል
**********************
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ በአፀደ ህፃናት (ኬጂ) የሚማሩ ህፃናት ተማሪዎች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ መከላከያ በማድረግ ኮቪድ 19 ቫይረስ ወረርሽኝን እንዲከላከሉ ወላጆችና ትምህርትቤቶች አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው አስታወቀ።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሳሙኤል ዘመንፈስ ቅዱስ በአፀደ ህፃናት (ኬጂ) የሚማሩ ህፃናት ተማሪዎች ኮቪድን ለመከላከል የሚረዳውን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ባያደርጉም ጉዳት የለውም የሚል አመለካከት በአንዳንዶች እየተነገረ ስላለው ሐሳብ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች እና ከዚያ በላይ ባሉት መካከል የአተነፋፈስ ልዩነት መኖሩ፣ ህፃናቱ የሚያወጡት ትንፋሽም ብዙ ርቀት የማይሄድ በመሆኑ ወረርሽኙን ወደ ሌላ የማስተላለፍ ዕድሉ ጠባብ ነው የሚሉ የዓለም አቀፍ ጥናቶች እንዳሉ አመልክተዋል።
ይህ ሲባል ግን ልጆቹ በቫይረሱ አይያዙም ማለት እንዳልሆነ የጠቆሙት ሃላፊው ፣ በጉዳዩ ዙሪያ በኢትዮጵያ በጥናት የተደገፈ መረጃ ባለመኖሩ ጤና ቢሮ የመከላከያ መሸፈኛውን እንዲጠቀሙ፣ ወላጆችም ትምህርትቤቶችም እንዳይዘናጉ መክረዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=39502
የተማሪዎችን የመጽሐፍት ሥርጭት አንድ ለአንድ ለማዳረስ በትኩረት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
*************************
(ኢ ፕ ድ)
በ2013 የትምህርት ዘመን ተማሪዎች ለኮቪድ 19 እንዳይጋለጡ የመጽሐፍት ሥርጭት አንድ ለአንድ ለማዳረስ በትኩረት እየሠራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።
በትምህርት ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሓረግ ማሞ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ ትርፍ የመጽሐፍት ክምችት ያለባቸው አካባቢዎች እጥረት ወደ አለባቸው አካባቢዎች በማሰራጨት ለተማሪዎች አስፈላጊ የሆኑት መጽሐፎች አንድ ለአንድ እንዲደርስ ዕቅድ ተይዞ እየተሠራ ነው።
በአንዳንድ ቦታዎች የመጻሕፍት ክምችት መኖሩን የገለፁት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተርዋ፤ በክልሎች፣ ዞኖች፣ ወረዳዎች እንዲሁም ከዚህ በፊት ታትመው በክምችት የሚገኙ መፃህፍት እንዲለዩ ተደርጎ እጥረት ወደ አለባቸው አካባቢዎች እንዲሰራጩ አቅጣጫ ተቀምጦ ከባለድርሻ አካላት ጋር በምክክር እየተሠራ መሆኑንም ተናግረዋል።
ተጨማሪ ህትመት የሚያስፈልጋቸው የትምህርት አይነቶች ካሉ ክልሎች ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመመካከር ታትሞ የሚሠራጭበት ሁኔታ ሊኖር እንደሚችልም ጠቁመዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=39503
የትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ቤቶች ዝግጁነት ላይ የመስክ ምልከታ እያደረገ ነው
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በተለያዩ ክልሎች ያሉ ትምህርት ቤቶች ያሉበትን ደረጃ ተዘዋውረው እየተመለከቱ ነው።
በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሳቢያ ተቋርጦ የነበረውን የመማር ማስተማር ሂደት ለማስጀመር ትምህርት ቤቶች የተለያዩ ዝግጅቶችን እያደረጉ ነው።
የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ርጌታሁን መኩሪያ የራቡ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት፣ በሰበታ ከተማ ሙልጌታ ገሌ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ አለም ገና 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ያሉበትን ደረጃ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ትምህርት ቤቶች የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል የተቀመውጡ መመሪያዎችን ለመተግበር ዝግጁ ካልሆኑ ትምህርት እንደማይጀምሩ መገለፁ የሚታወስ ነው።
የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ተጀመረ

ዘመቻው - ከመስከረም 27 እስከ መስከረም 30 ድረስ ይቆያል፡፡
በዘመቻው - አራት ክልሎች (በደቡብ/ብ/ብ/ህ/፣ በኦሮሚያ፣ በሶማሌ፣ በሐረሪ) እና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች(አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ) ይደረሳል፡፡
በዘመቻው- እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች ለሆኑ ሰባት ሚሊዮን ህፃናት ይሰጣል፡፡

ማህበረሰቡ ይህን አውቆ ልጆችን ቤት ለቤት በሚመጡ የጤና ባለሙያዎች እንዲያስከትብ ጤና ሚኒስቴር ያሳስባል፡፡
ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ማንኛቸውም ተጓዥ መንገደኞች የኮቪድ 19 ምርመራ የ RT- PCR ነጌቲቭ ውጤት ይዞ መምጣት ግዴታ እንደሆነ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)

ወደ ሀገር ቤት የሚገቡ ማንኛቸውም ተጓዥ መንገደኞች የኮቪድ 19 ምርመራ የ RT- PCR ነጌቲቭ ውጤት ይዞ መምጣት ግዴታ እንደሆነ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በመመሪያው መሰረት የኮቪድ 19 የ RT-PCR ነጌቲቭ ውጤት ያልያዙ እንዲሁም ቀኑ ያለፈበት የRT-PCR ነጌቲቭ ውጤት የያዙ መንገደኞች ወደ ሀገር ውስጥ መግባት አይችሉም።

አንዳንድ መንገደኞች ይህንን ወደ ጎን በመተው የRT-PCR ነጌቲቭ ውጤት ሳይዙ፣ ቀኑ ያለፈበት የRT-PCR ነጌቲቭ ውጤት እንዲሁም የRT-PCR ምርመራ ያልሆነውን እንደ RDT Anti Body test በመያዝ ወደሀገር ውስጥ ለመግባት ሙከራ እንደሚደረግ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በመሆኑም ማንኛቸውም ተጓዦች ወደ ኢትዮጵያ ከመሳፈራቸው በፊት ናሙና ከሰጡበት ሰዓት ጀምሮ 120 ሰዓታት ወይም አምስት ቀን ያላለፈው የRT- PCR ነጌቲቭ ውጤት ይዘው መምጣት ግዴታ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

በተጨማሪም ከዚህ ቀደም ሲሰራበት የነበረው መንገደኞች ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡ የRT-PCR ነጌቲቭ ውጤት ይዘው ሲመጡ ናሙና ተወስዶ ለ14 ቀናት ራሳቸውን በቤታቸው ለይተው እንዲቆዩ ይደረግ የነበረው አሰራር ቀርቶ መንገደኞች ናሙና ከሰጡበት ሰዓት ጀምሮ 120 ሰዓታት ያላለፈው የRT-PCR ነጌቲቭ ውጤት ይዘው ሲመጡ ለ7 ቀናት ራሳቸውን ለይተው መቆየት እንደሚገባቸው በመመሪያው መቀመጡን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በአዋጅ የተሰጣቸውን ሥልጣን በመጠቀም በጋራ ያዘጋጁት መመሪያ ሰሞኑን ሥራ ላይ መዋሉ ይታወሳል፡፡
በህወሓት አምባገነን አመራሮች የትግራይ ሕዝብ መጎዳት የለበትም - የድሬዳዋ ከተማ የትግራይ ተወላጆች
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)

የፌዴራል መንግስትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔዎች የትግራይን ህዝብ ለመጉዳት ነው እያሉ ህዝቡን ለማደናገር ጥቂት የህወሓት አመራሮችና ሚዲያዎች የከፈቱትን ዘመቻ የውይይትና ምክክር መድረኮችን በማዘጋጀት ግልጽነት ሊፈጠር ይገባል ሲሉ በድሬዳዋ ከተማ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ገለጹ፡፡

የፌዴራሉ መንግስትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የወሰኑት በህወሓት የተካሄደው ምርጫ እንዳልተካሄደ መቆጠሩ፣ የበጀት ድጎማ ማገዱና የፌዴራል መንግስት ከክልሉ መንግስት ጋር ግንኙነት እንዳያደርግ መወሰኑ ትክከለኛ ውሳኔ ነው ብለዋል፡፡

የህወሓት አመራሮች የትግራይን ህዝብ አይወክሉም ያሉት ተሳታፊዎቹ የትግራይን ሕዝብ ባልተገባ መንገድ ቀስቅሰው ወደ ጦርነት ለማስገባት የሚያደርጉትን ውዥንብር የፌዴራል መንግስት እርምጃ በመውሰድ ህገ ወጦችን ከህዝቡ መነጠል አለበት ብለዋል ሢል የዘገበው ዋልታ ነው።
የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌታሁን መኩሪያ በአዳማ ከተማ በ ህብረተሰብ ተሳትፎ በ 1.2 ሚሊየን ብር የተገነባውን ደምበላ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጎበኙ።

በትምህርት ቤቱ በ ህብረተሰቡ ተሳትፎ 4 አዳዲስ ክፍሉች የተሰሩ ሲሆን 3 ክፍሉች ደግሞ ታድሰው ለ አገልግሎት ዝግጁ ሆነዋል።

በትምህርት ቤቱም የውሃ ቧንቧዎች እና የማንበቢያ ፖርኮች ተገንብተው ተጠናቀዋል

ትምህርት ቤቶቹም በህብረተሰቡ ተሳትፎ መገንባታቸውን የአዳማ ከተማ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ታምሬ ቡሹ ተናግረዋል።
በሰሜን ሸዋ ዞን አራት ወረዳዎች የበረሃ አንበጣ መንጋ መከሰቱ ተገለጸ
**************

በሰሜን ሸዋ ዞን አራት ወረዳዎች በቀወት ወረዳ እምባይ ጎድ ሙቅ ውኃ በሚባል አካባቢ 16 ሄክታር መሬት ላይ የበረሃ አንበጣ መንጋ መከሰቱ ተገልጿል።

የተከተሰውን የበረሃ አንበጣ መንጋ ለመከላከልም ከሌሊት 10 ሰዓት ጀምሮ የአካባቢው አርሶ አደሮች፣ የመንግሥት ሠራተኞችና የአማራ ክልል የልዩ ኃይል ፖሊስ አባላት ጥረት እያደረጉ መሆኑ ተገልጿል።

የበረሃ አንበጣ መንጋው በባሕሪው ተንቀሳቃሽ በመሆኑ የመከላከል ሥራውን ፈታኝ እንዳደረገባቸው የቀወት ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታደሰ ማሙሸት አስታውቀዋል።

የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል ግብረ ኃይል መቋቋሙንና በአውሮፕላን ርጭት ለማካሄድ ሸዋ ሮቢት የሚገኘውን የአውሮፕላን ማረፊያ የማፅዳት ሥራ ተሰርቶ ወደ ርጭት እንደሚገባ አብመድ ዘግቧል።
በመምህርነት ሲያገለግሉ የነበሩ ባለሙያዎች ሀገራዊ ሃላፊነታቸውን ለመወጣት ዝግጅት እንዲያደርጉ ተጠየቀ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለ7 ወራት የተቋረጠውን የመማር ማስተማር ሂደት ለማገዝ ከዚህ ቀደም በመምህርነት ሙያ ሲያገለግሉ የነበሩ መምህራን በአቅራቢያቸው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለማገልገል ዝግጅት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር መደበኛ ትምህርትን በሚያስቀጥልበት ወቅት በትምህርት ቤቶች አካላዊ እርቀትን ለማስጠበቅ የተማሪዎች ቁጥር ከ20-25 እንዲሆን መወሰኑን ተከትሎ ትምህርት ቤቶች እንደየ አካባቢያቸው ሁኔታ በፈረቃ ትምህርት የሚሰጡ ይሆናል፡፡
በዚህም ወቅት በትምህርት ቤቶች የመምህራን እጥረት እንዳይኖር ለማድረግ ከዚህ ቀደም በመምህርነት ሲያገለግሉ የነበሩና የ መምህርነት ስልጠናን ወሰደው ሌላ ዘርፍ የተቀላቀሉ ባለሙያዎች በየአካባቢያቸው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተመልሰው ሃገራዊ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌታሁን መኩሪያ "እኔም አስተምራለው" በሚል መሪ ቃል ከ ሰኞ ጀምሮ በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች ከዚህ ቀደም በምህርነት ሲያገለግሉ የነበሩና በ መምህርነት ሙያ የሰለጠኑ ባለሙያዎችን የመመዝገብ ስራ ይሰራል ብለዋል።
በዚህም መሰረት ባለሙያዎች በአቅራቢያቸው ባሉ ትምህርት ቤቶች በመሄድ እና በመመዝገብ የትምህርቱን ዘርፍ በሙያቸው እንዲያግዙ ሚኒስትሩ ጥሪ ማቅረባቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
️እንጦጦ ድሮ እና ዘንድሮ!

👉 እንጦጦ መስከረም 2012 ዓ.ም
እና
👉 እንጦጦ መስከረም 2013 ዓም
በቦሌ ኤርፖርት 3.4 ሚሊዮን ብር የሚገመት ወርቅ በቁጥጥር ስር ዋለ
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)

አንድ ነጥብ አራት ኪሎ ግራም መጠን ያለው ወርቅ አዲስ አበባ ከሚገኘው የካሜሮን ኤምባሲ ወደ ካሜሮን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተላከ መልዕክት በማስመሰል ከሀገር ለማስወጣት ሲሞከር በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

በአዲስ አበባ ኤርፖርት ወደ ካሜሮን ለመጓዝ ዝግጅት ሲያደርግ የነበረ መንገደኛ የዲፕሎማቲክ መልዕክት በማስመሰል ለማሳለፍ ሲሞክር በማሽን በታገዘ ፍተሻ ሊያዝ ችሏል፡፡

የተያዘው ወርቅ በወቅታዊ የብሔራዊ ባንክ የመግዣ ዋጋ ሶስት ሚሊዮን አራት መቶ ሺህ (3,400,000) ብር ግምታዊ ዋጋ ወጥቶለታል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር የሀገርን ሀብት ከምዝበራ የታደጉ የጉምሩክ ሰራተኞች እና የፀጥታ አካላት ምስጋናውን አቅርቧል።
"በአለም አቀፍ ደረጃ በየ10-15 ሰከንዶች ውስጥ በኮቪድ ሳቢያ አዲስ ሞት ይመዘገባል፡፡ እያንዳንዱ ሕይወት ውድ ነው:: እባካችሁ: እባካችሁ እንጠንቀቅ!"
ዶ/ር ሊያ ታደሰ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጥቅምት 04 ቀን 2013 ዶ/ር አረጋዊ በርሔን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አድርገው ሾመዋል።