Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
አዲሱ የብር ለውጥ ከተጀመረ በሁዋላ በ14 ቀናት ብቻ 580 ሺህ ዜጎች አዲስ የሂሳብ አካውንት ከፍተዋል፤ ከባንክ ውጭ የነበረ 14 ቢሊዮን ብር ወደ ባንክ ገቢ ሆኗል
***********************
(ኢ ፕ ድ)
አዲሱ የብር ለውጥ ከተጀመረ በሁዋላ ባሉት 14 ቀናት ውስጥ ብቻ 580 ሺህ ዜጎች አዲስ የሂሳብ አካውንት ከፍተዋል፤ በእነዚህ አካውንቶች ውስጥም ከባንክ ውጭ የነበረ 14 ቢሊዮን ብር ወደ ባንክ መግባቱን ብሄራዊ ባንክ አስታወቀ።
የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ ዛሬ እንዳስታወቁት፤ አዲሱ ብር በመላ አገሪቱ ባሉ የባንክ ቅርንጫፎች 99 ነጥብ 9 በመቶ ተዳርሷል። በዚህም ምክንያት በሁሉም ባንኮች 580 ሺህ ዜጎች የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል።
በእነዚህ 580 ሺህ አዲስ የሂሳብ አካውንቶች ውስጥም በ14 ቀናት ውስጥ ብቻ 14 ቢሊዮን ብር ወደ ባንክ ገቢ መደረጉን ዶ/ር ይናገር ገልጸዋል። በነባር አካውንት ውስጥ የገባው ገንዘብ መጠንን በተመለከተ ደግሞ ተጠቃሎ ይፋ እንደሚሆን አስታውቀዋል።
የብር ለውጡ ያስፈለገበት አንዱ ዓላማ ከባንክ ውጭ ያለን ገንዘብ ወደባንክ የማስመለስ ጉዳይ እንደነበር ያስታወሱት የባንኩ ገዥ፤ ከዚህ አንጻር በ14 ቀናት ውስጥ ብቻ በአዲስ አካውንት ይሄንን ያህል ገንዘብ ወደ ባንክ ስርዓቱ መመለሱ የዓላማውን መሳካት ያሳያል ብለዋል። በቀሪ ቀናትም ተጨማሪ ገንዘብ እንደሚገባ ይጠበቃል ብለዋል።
በሁለተኛ ደረጃ የብር ለውጡ አለማ የነበረው የባንክ አገልግሎት ተደራሽነትን ማሳደግ እንደሆነ የገለጹት ዶ/ር ይናገር፤ ከዚህ አንጻር በ14 ቀናት ውስጥ ብቻ 580 ሺህ ዜጎች የባንክ አካውንት ከፍተዋል፤ በቀሪዎቹ ቀናት ውስጥ በሚሊን የሚቆጠሩ ዜጎች አካውንት ይከፍታሉ ተብሎ ይጠበቃል ነው ያሉት።
አዲሱን ብር በመላ አገሪቱ ባሉ የባንኮች ቅርንጫፎች ደርሷል ያሉት ዶ/ር ይናገር፤ በዚህ ሂደትም 67 ቢሊዮን ብር ለባንኮቹ ቅርንጫፎች ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲዳደረስ ተደርጓል ነው ያሉት።
አዲሱ የገንዘቡ ኖት በሁሉም ባንኮች መዳረሱን የጠቀሱት የባንኩ ገዥ፤ ህብረተሰቡ በተያዘው የጊዜ ውስጥ በእጁ ያለውን ብር መቀየር አለበት ብለዋል።
በተለይ ከ100 ሺህ እስከ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር ድረስ በእጃቸው ያላቸው ሰዎች የማጠናቀቂያ ጊዜው የተወሰኑ ቀናት ስለቀሩት በኋላ ላይ ከሚፈጠር መጨናነቅ ተጠብቀው ገንዘባቸውን በፍጥነት መቀየር እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በትግራይ ክልል የሚገኙ ዐቃቢ ህጎች በክልሉ መንግስት የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት እና ውሳኔ ምክንያት የሥራ ማቆም አድማ ሊያደርጉ ነው
**************************
(ኢ.ፕ.ድ)
በትግራይ ክልል የሚገኙ ዐቃቢ ህጎች በክልሉ መንግስት የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት እና በአመራሮቹ ፓለቲካዊ ጫና ምክንያት የሥራ ማቆም አድማ ሊያደርጉ ነው።
ባለብን ከፍተኛ የደህንነት ስጋት ምክንያት ሥማችን አይጠቀስብን ያሉ አቀቤ ህጎች ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዛሬ እንደተናገሩት፤ የክልሉ መንግሥት የፓለቲካ ጣልቃ ገብነት ስራቸውንም ኑሯቸውንም እየጎዳው ነው።
የፖለቲካ አመራሮች በደል መገለጫው ብዙ ቢሆንም ዋናው ከሙያ ነጻነት ማጣት እና ከደመወዝ ክፍያ ፍትሃዊነት መጓደል ጋር በተያያዘ ያቀረቡትን ተደጋጋሚ ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ አቃቤ ህጎችን ከሥራ ለመቀነስ እየሠሩ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህ እና ተደጋጋሚ በሆነው የክልሉ መንግስት የፓለቲካ ጣልቃ ገብነት ምክንያት ከነገ ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ ሊያደርጉ መሆኑን አብራርተዋል።
በትግራይ ክልል ያሉ አቃቤ ህጎች ደመወዝ በሌሎች ክልሎች ካሉ ተመሣሣይ አቃቤ ህጎች በጣም ያነሰ ነው። ይህ እንዲስተካከል ቢጠይቁም የክልሉ መንግስት ቃል ከመግባት ባለፈ ሊያስተካክል እንዳልቻለም ተናግረዋል።
የክልሉ መንግስት ኢፍትሃዊነት ከሌሎች ክልሎች አቃቤ ህጎች አንጻር ብቻ ሳይሆን በትግራይ ክልል ካሉ ዳኞች ደመወዝም በእጅጉ ያነሰ ነው ብለዋል።
ጥያቄያችን ብዙ ነው ያሉት አቃቤ ህጎቹ፤ "ቅድሚያ በክልሉ በተባባሰው የኑሮ ውድነት ምክንያት እየደረሠብን ያለውን ጫና ለመቋቋም ጥያቄያችን ይመለስልን ብለን እንጂ በተቋሙ ላይ ያለው የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ሥራዥንን በነጻነት እንዳንሰራ እያደረገን ነው" ሲሉም ተናግረዋል።
የክልሉ መንግስት ጥያቄያቸውን እንደሚመልስላቸው በመግለጽ አድማውን እንዳይመቱ በመወትወት ላይ እንደሚገኝ የጠቀሡት አቃቤ ህጎቹ፤ በደረሳቸው መረጃ መሠረት ደመወዙን ከማስተካከል ይልቅ የአቃቤ ህጎችን ቁጥር ለመቀነስ እየሠራ ነው ብለዋል።
በሥራቸው ላይ በክልሉ መንግሥት እየተደረገባቸው ያለው የፖለቲካ ጣልቃ ገብነትም ለትግራይ ህዝብ ትክክለኛ ፍትህ ለመስጠት እንዳዳገታቸው ነው የተናገሩት።
ሥለሆነም ቀጣዩ ጥያቄያቸው በተቋማቸው ውስጥ ሙያዊ ነጻነት እንዲከበር ማድረግ መሆኑንም አስታውቀዋል።
ለ34 ሺ ትምህርት ቤቶች በዘላቂነት ውሃ ለማቅረብ የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ
***************
(ኢ.ፕ.ድ)

ለ34 ሺ ትምህርት ቤቶች በዘላቂነት ውሃ ለማቅረብ የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌታሁን መኩሪያ የተቋማቸውን የ 3 ወር የስራ አፈፃፀም በተመለከተ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፉ ካሉ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 34 ሺ ትምህርት ቤቶች የውሃ አቅርቦት የላቸውም ያሉት ሚኒስትሩ ይህንን ችግር ለመቅረፍ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በ3ሺ ትምህርት ቤቶች ላይ ውሃ በምን ያክል የመሬት ጥልቀት ውስጥ እንዳለ ጥናት እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመዋል።

እንደየ ትምህርት ቤቶቹ ሁኔታ የሁሉንም ትምህርት ቤቶች የውሃ አቅርቦት ችግር ለመፍታት በቀጣይ እንደሚሰራ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
የፌደራል መንግስት ከትግራይ ክልል መንግስት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳያደርግ ውሳኔ ተላለፈ
************************************
(ኢፕድ)
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ጉባዔ የፌደራል መንግስት ከትግራይ ክልል መንግስት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳያደርግ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

ይህ ውሳኔ ሊተላለፍ የቻለው ባለፈው ነሃሴ 30 2012 ዓ.ም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አድርጎት በነበረው አስቸኳይ ጉባዔ በትግራይ ክልል የሚካሄደው ምርጫ እንዳልተደረገ፣ እንዳልተፈጸመ እና እንደማይጸና ውሳኔ ማስተላለፉን ተከትሎ ነው፡፡

ውሳኔውን የሚከታተል የህገ መንግስት ጉዳዮች እና የማንነት ጉዳዮች አጣሪ ቋሚ ኮሚቴ ጉዳዩን ሲከታተል ቆይቶ ውሳኔው ባለመፈጸሙ ባዛሬው ዕለት ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ነው ይህንን ወሳኔ ሊያሳልፍ ያቻለው፡፡

ምክር ቤቱ በትግራይ ክልል መንግስት ላይ ሶስት ውሳኔዎችን ማሳለፉን ገልጿል፡፡

የመጀመሪያው የትግራይ ክልል ያካሄደውን ኢ-ህገ መንስታዊ ምርጫ ተከትሎ ከተመሰረቱ የትግራይ ክልል ምክር ቤትና ከፍተኛ የህግ አስፈጻሚ አካል ጋር የፌዴራል መንግስት ምንም አይነት ግንኙነት እንደማያደርግ ወስኗል፡፡

ሁለተኛው የፌደራል መንግስት የትግራይ ህዝብን የልማትና መሰረታዊ አገልግሎቶች ፍላጎት ማዕከል በማድረግ የከተማ እና የቀበሌ አስተዳደርን ጨምሮ በክልሉ ከሚገኙ ህጋዊ ተቋማት ብቻ የስራ ግንኙነት ያደርጋል፡፡

ሶስተኛ የውሳኔውን አፈጻጸም በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ እና ጉዳዩ በሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴ ክትትል መደረግ እንዳለበት ውሳኔ ተላልፏል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የክብር ካባቸውን ለገሱ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶክተር) የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ባሳዩት የአመራር ቁርጠኝነት የሸለማቸውን ካባ ለአማራ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሺህ ሰይድ አህመድ በክልሉ ሰላም እንዲመጣ ላደረጉት አስተዋጽኦ ሸልመዋል። ይህ ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ከአደራ ጋር አሳስበዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው እና የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ብናልፍ አንዷለም በፓርኩ ስለነበራቸው ሚና ከባሕር ዳር ከተማ አስተዳድር የክብር ካባ ተሸልመዋል።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ክልል መንግስት ላይ ያሳለፈው ውሳኔ ተገቢና ትክክለኛ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ሃይሎች ጥምረት አስታወቀ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
👉 ጥምረቱ አገር ወዳዱ የትግራይ ህዝብ የፌዴሬሽን ምክርቤት ውሳኔን
ተቀብሎ ጎጠኛውን ቡድን ማስወገድ እንዳለበት ጥሪ አቅርቧል
የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ክልል መንግስት ላይ ያሳለፈው ውሳኔ ተገቢና ትክክለኛ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ሃይሎች ጥምረት አስታወቀ።
ጥምረቱ አገር ወዳዱ የትግራይ ህዝብ የፌዴሬሽን ምክርቤት ውሳኔን ተቀብሎ ጎጠኛውን ቡድን ማስወገድ እንዳለበት ጥሪ አቅርቧል።
የፌዴራሊስት ሀይሎች ጥምረት ሰብሳቢ አቶ ደረጀ በቀለ ዛሬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት ማብራሪያ እንደተናገሩት፤ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ያሳለፈው ውሳኔ የትግራይ ክልል ህዝብን ያከበረ ነው።
ጥምረቱ የተወሰኑ ጎጠኛ ቡድኖች የክልሉን ህዝብ ስለማይወክሉ የፌዴራሊስተ ሃይሎች ጥምረት የተለላፈው ውሳኔ ተገቢና ትክክል ነው ብሎ ያምናል።
ጥቂት ጎጠኞች በክልላቸን ማንም አያገባውም እያሉ ያዙኝ ልቀቁኝ ሲሉ ቆይተዋል ያሉት አቶ ደረጀ፤ እነዚህ ጥቂት ቡድኖች መላውን የትግራይ ህዝብ ስለማይወክሉ የፌዴረሽን ምክር ቤት በዚህ አግባብ ውሳኔ ማሳለፉ ተቀባይነት ያለው ነው ብለዋል።
“የተላለፈው ውሳኔ በቂ አይደለም” ያሉት አቶ ደረጀ፤ ማንም እየተነሳ እኔ ነኝ ትክክል ህዝቡን እኔ ነኝ መምራት ያለብኝ እያለ መፎከሩ ትክክል ስላልሆነና ህዝቡን የማይወክልም እስከሆነ ድረስ የፌዴራል መንግስት ያለውን ሃይል አማራጭ ሁሉ ተጠቅሞ እነዚህን ጥቂት ጎጠኞች ማስወገድ አለበት ነው ያሉት።
መንግስት ሃይሉን የሚያሰባስበው ወይንም የሚጠቀመው ለውጭ ጠላት ብቻ አይደለም ያሉት አቶ ደረጀ፤ በአገር ውስጥም እንደዚህ አይነት ጎጠኞችንና በህዝብ ላይ ጫና የሚፈጥሩ ቡድኖችን ማስወገድና ስርአት ማስያዝ አለበት፤ ይህ የማይሆን ከሆነ ሁሉም እየተነሳ የሰፈር ጀብደኛ መሆኑ አይቀርም ሲሉ አሳስበዋል።
በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደረው አገር ወዳዱ የትግራይ ህዝብ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔን ተቀብሎ በአንድነት ተነስቶ እነዚህን ጎጠኞች አስወግዶ ከተቀረው ወንድምና እህቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር አብሮ እንዲጓዝ ጥሪ አቅርበዋል።
በጥቂት ጎጠኞች የተነሳ የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ ልማትና አስተዳደር መነጠል የለበትም ያሉት አቶ ደረጀ፤ የእነዚህን ማንአለብኝ የሚሉ ጎጠኞች አካሄድ ተረድቶ ከላዩ ላይ ማስወገድና አደብ ማስገዛት አለበ፤ ይሄንን ማድረግ ካልቻሉ የማታ ማታ ዋናው ተጎጂ የሚሆነው ህዝቡ ነው ብለዋል።
የፌዴራሊስት ሀይሎች ጥምረት ከዚህ በፊት ህወሓትን ከጥምረቱ ማባረሩ ይታወሳል።
በአዲስ አበባ በአንድ ንግድ ቤት ውስጥ የተከማቸ ከ ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ በላይ ብር በቁጥጥር ስር ዋለ
******************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በአንድ ንግድ ቤት ውስጥ የተከማቸ ከሁለት ሚሊዮን 600 ሺህ በላይ የኢትዮጵያ ብር በህዝብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ደንበል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአንድ የንግድ ቤት ውስጥ የተከማቸ ገንዘብ ስለመኖሩ ከህዝብ ጥቆማ መምጣቱን የደንበል አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ሀላፊ ኢንስፔክተር ሰለሞን ደጀኔ የጠቀሱ ሲሆን፤ ፖሊስም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማውጣት በንግድ ቤቱ ላይ ባደረገው ብርበራ ብሄራዊ ባንክ ካስቀመጠው መመሪያ ውጪ ተከማችቶ የተገኘ ሁለት ሚሊዮን 631 ሺህ 735 አዲሱን እና ነባሩን የኢትዮጵያ ብር በቁጥጥር ሰር መዋሉን ገልፀዋል፡፡
መንግስት እና የፀጥታ አካላት የሀገርን ኢኮኖሚ ለማረጋጋት የሚያከናውኑትን በህገ- ወጦች ላይ እርምጃ የመውሰድ ተግባር በመደገፍ ህብረተሰቡ የጀመረውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ኢንስፔክተር ሰለሞን ደጀኔ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በህዳሴ ግድብ በግዳጅ ላይ ያለው ወታደር በእንቁጣጣሽ ሎተሪ የ600 ሽህ ብር እድለኛ ሆነ

በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግዳጅ ላይ ያለው ሃምሳ አለቃ ዘርኡ ኃ/ማርያም በእንቁጣጣሽ ሎተሪ 4ኛ ዕጣ በ1 ነጠላ ትኬት የ600 ሽህ ብር እድለኛ ሆኗል፡፡

እድለኛው ህዳሴ ግድቡ በሚገነባበት ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ ወረዳ በግዳጅ አገሩን እያገለገለ ባለበት ጊዜ አሶሳ ከተማ ለስራ በመጣበት አጋጣሚ በ20 ብር የቆረጣት 1 ነጠላ ትኬት እድለኛ እንዳደረገችው ብሄራዊ ሎተሪ አስታውቋል፡፡
የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ለሁሉም ትምህርት ቤቶች በነፃ ይሰጣል- ትምህርት ሚኒስቴር
*************************
(ኢ ፕ ድ)
የትምህርት ሚኒስቴር መደበኛ ትምህርት ለመጀመር አስፈላጊ ዝግጅቶችን እያጠናቀቀ እና በትምህርት ቤቶች አስፈላጊ ግብዕቶች ለማሟላት ስራዎችን እየሰራ መሆኑን አስታወቋል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ሃረጓ ማሞ ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ለሁሉም የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በነፃ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡
የአፍና አፍንጫ መሸፈኛውም አዲስ አበባ እና ሀዋሳን ማዕከል በማድረግ ለክልል እና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እንደሚከፋፈሉ ዳይሬክተሯ አስታወቀዋል፡፡
የአለም የጤና ድርጅት መስፈርቶችን የሚያሟሉ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዎችም ሀገር ውስጥ ካሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግዢ የመፈፀም ስራ እየተከናወነ እና በቅርቡ ወደ ትምህርት ቤቶች እንደሚደርሱ ተገልጿል፡፡
ለተማሪዎች የሚከፋፈለው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በተደጋጋሚ ታጥቦ ዳግም አግልግሎት መስጠት የሚችል እንደሆነም ተነግሯል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በገበታ ለአገር ፕሮጀክት ከሚገነቡት አንዱ የሆነውን የጎርጎራ አካባቢን ጎበኙ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በገበታ ለአገር ፕሮጀክት ከሚገነቡት አንዱ የሆነውን የጎርጎራ ፕሮጀክት መተግበሪያ አካባቢን ጎብኝተዋል፡፡
ዛሬ ረፋድ ላይ የባህርዳር ኢንዱስትር ፓርክን የመረቁት ጠቅላይ ሚንስትሩ፣ በጣና ዳርቻ ላይ መሰረቱን ያደረገውን እና በገበታ ለአገር መርሃ ግብር ለመገንባት በሂደት ላይ ያለው የጎርጎራ ፕሮጀክት የጎበኙት ከቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገዱ አንዳርጋቸው እና ከፌደራልና የአማራ ክልል ባለስልጣናት ጋር በመሆን ነው፡፡
በገበታ ለአገር መርሃ ግብር ስር እንዲገነቡ ይፋ የተደረጉት በኦሮሚያ ክልል ወንጪ፣ በደቡብ ክልል ኮይሻ እና በአማራ ክልል ደግሞ የጎርጎራ ፕሮጀክቶችን እውን ለማድረግ በፌደራልና በክልሎች ደረጃ ሀብት የማሰባሰብ እና የዲዛይን ስራዎች በመሰራት ላይ እንዳሉ ይታወቃል፡፡
ደንበኞች እየተጠቀሙበት የሚገኘውን የሞባይል አገልግሎት ቁጥር በስማቸው ማስመዝገብ እንዳለባቸው ኢትዮ-ቴሌኮም አሳሰበ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)

ኢትዮ-ቴሌኮም ደንበኞች እየተጠቀሙበት የሚገኘውን የሞባይል አገልግሎት ቁጥር በስማቸው ማስመዝገብ እንዳለባቸው ኢትዮ-ቴሌኮም አሳሰበ።

ኢትዮ-ቴሌኮም ለድርጅታችን በላከው መረጃ በስማቸው ያልተመዘገበ የሞባይል አገልግሎት እየተጠቀሙ የሚገኙ ደንበኞች የስም ዝውውር ለውጥ ማድረግ የሚችሉበትን አሰራር ተግባራዊ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ደንበኞች እየተጠቀሙበት የሚገኘውን የሞባይል አገልግሎት ቁጥር በስማቸው የተመዘገበ መሆን እንደለበትም አሳስቧል፡፡

ቀደም ሲል የሞባይል አገልግሎት ደንበኞች እየተጠቀሙበት የሚገኘውን የሞባይል አገልግሎት ቁጥር በስማቸው ያልተመዘገበ በመሆኑ ሞባይላቸው በሚጠፋበት ጊዜ ምትክ ሲም ካር ለማግኘት፤ አገልግሎታቸው በተለያያ ምክንያት ሲቋረጥ መልሶ ለማስቀጠል ደንበኞች ወደ ተቋሙ የሽያጭ ማዕከላት ሲቀርቡ ጥያቄያቸውን ለማስተናገድ እንደተቸገረ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አሰፈጻሚ ፍሬሕይውት ታምሩ ገልጸዋል።

በመሆኑም በስማቸው ያልተመዘገበ የሞባይል አገልግሎት እየተጠቀሙ የሚገኙ ደንበኞች የስም ዝውውር ለውጥ አገልግሎቶች ማግኘት የሚችሉበትን አሰራር ተግባራዊ ማደረጉን ገልጸዋል፡፡

እንደ ዋና ስራ አሰፈጻሚዋ ገለጻ፤ ደንበኞች ቀደም ሲል አገልግሎቱን በስማቸው ካሰመዘገቡት ደንበኛ ጋር በአካል በመቅረብ፤ በቋሚነት ከሀገር ውጪ የሚኖሩ ከሆነ አልያም በተለያየ ምክንያት በአካል መገኘት ከልቻሉ ለዚህ አሰራር በተዘጋጀ ቅፅ በመሙላት የስም ዝውውሩን በቀላሉ መንገድ ማከናወን ይችላሉ።

በሌላ በኩል የተቋሙ ደንበኞች በስማቸው የተመዘገበውን የአገልግሎት ቁጥር ለሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ በሚፈልጉበት ጊዜ በኩባንያው የሽያጭ ማዕከላት በመቅረብና ህጋዊ በሆነ መንገድ ዝውውሩን ማከናወን ይችላሉ ተብሏል፡፡

ኩባንያው ደንበኞች ራሳቸውን ከቴሌኮም ማጭበርበርና ከሌሎች የወንጀል ድርጊቶች እንዲጠበቁ ስራ አሰፈጻሚዋ አሳስቧል፡፡

በወንድማገኝ አሸብር
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአማራ ክልል መንግሥት አመራሮች ጋር ተወያዩ
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አመራሮች ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል

ውይይቱ ኩታ ገጠም እርሻ የክልሉን ልማት እና አምራችነት ለማሳደግ ያለውን ሚና በተመለከተ እንደነበር ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
አትሌት ለተሰንበት ግደይ የሴቶች 5ሺ ሜትር የዓለም ክብረወሰንን ሰበረች
********************
(ኢ.ፕ.ድ)

ኢትዮጵያዊቷ የ22 ዓመቷ ለተሰንበት ግደይ ዛሬ በስፔን ቫሌንሺያ በነበረው ውድድር ላይ 14 ደቂቃ ከ06 ሰከንድ ከ62 ማይክሮሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት ሪከርድ በመስበር ጭምር አሸንፋለች።

ላለፉት 12 ዓመታት የዚህ ክብረወሰን ባለቤት የነበረችው ጥሩነሽ ዲባባ ነበረች።
የዱቄት እጥረት የዳቦ ቤቶችን ስራ እያስተጓጎለ መሆኑ ተጠቆመ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ ከተማ በተከሰተው የስንዴ ዱቄት እጥረት ዳቦ ቤቶች ስራቸው እየተስተጓጎለ መሆኑን አመለከቱ። ከዳቦ ስንዴ ጋር በተያያዘ የሚነሳው ቅሬታ ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ምላሽ እንደሚያገኝ የከተማዋ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታውቋል።
በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ በዳቦ ንግድ ስራ ላይ የተሰማሩና ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ ግለሰብ በሰጡት አስተያየት መንግስት የሚያደርገው የዳቦ ዱቄት ድጎማ ከተቋረጠ ከሶስት ወር ወዲህ በርካታ ዳቦ ቤቶች ስራቸው ተስተጓጉሏል።
ዳቦ ቤቶች ከዚህ በፊት በሚደረግላቸው የመንግስት ድጎማ መቶ ኪሎ ግራም የስንዴ ዱቄትን በ796 ብር ሂሳብ እየገዙ፣ መቶ ግራም ዳቦን በ1 ብር ከ30 ሳንቲም ለህብረተሰቡ ተደራሽ ያደርጉ እንደነበር አመልክተው ፣አሁን ባጋጠመው እጥረት እንድ ኩንታል የስንዴ ዱቄትን ከግል ተቋማት ላይ ከ2ሺ ሶስት መቶ እስከ 2ሺ አራት መቶ ብር በመግዛት ስራውን ለማስቀጠል ቢሞክሩም ለኪሳራ እንደተዳረጉ ተናግረዋል።
የሰራተኞች ደመወዝና የተለያዩ ወጪዎችን ጨምሮ በወር ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ እየከሰሩ መሆኑን የገለጹት ግለሰብ፣ ህረተሰቡም ያለውን ወቅታዊ ችግር ያልተገነዘበ በመሆኑ ዋጋን ጨምሮ ለመሸጥ አስቸጋሪ ሆኖብናል ብለዋል። መንግስት ለችግሩ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ በመጠየቅም እስከዚያው ድረስ በመቶ ግራም ዳቦ ላይ የደነገገውን የዋጋ ተመን በይፋ ማሻሻል እንደሚገባው አመልክተዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=39492
የዱቄት እጥረት የዳቦ ቤቶችን ስራ እያስተጓጎለ መሆኑ ተጠቆመ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ ከተማ በተከሰተው የስንዴ ዱቄት እጥረት ዳቦ ቤቶች ስራቸው እየተስተጓጎለ መሆኑን አመለከቱ። ከዳቦ ስንዴ ጋር በተያያዘ የሚነሳው ቅሬታ ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ምላሽ እንደሚያገኝ የከተማዋ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታውቋል።
በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ በዳቦ ንግድ ስራ ላይ የተሰማሩና ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ ግለሰብ በሰጡት አስተያየት መንግስት የሚያደርገው የዳቦ ዱቄት ድጎማ ከተቋረጠ ከሶስት ወር ወዲህ በርካታ ዳቦ ቤቶች ስራቸው ተስተጓጉሏል።
ዳቦ ቤቶች ከዚህ በፊት በሚደረግላቸው የመንግስት ድጎማ መቶ ኪሎ ግራም የስንዴ ዱቄትን በ796 ብር ሂሳብ እየገዙ፣ መቶ ግራም ዳቦን በ1 ብር ከ30 ሳንቲም ለህብረተሰቡ ተደራሽ ያደርጉ እንደነበር አመልክተው ፣አሁን ባጋጠመው እጥረት እንድ ኩንታል የስንዴ ዱቄትን ከግል ተቋማት ላይ ከ2ሺ ሶስት መቶ እስከ 2ሺ አራት መቶ ብር በመግዛት ስራውን ለማስቀጠል ቢሞክሩም ለኪሳራ እንደተዳረጉ ተናግረዋል።
የሰራተኞች ደመወዝና የተለያዩ ወጪዎችን ጨምሮ በወር ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ እየከሰሩ መሆኑን የገለጹት ግለሰብ፣ ህረተሰቡም ያለውን ወቅታዊ ችግር ያልተገነዘበ በመሆኑ ዋጋን ጨምሮ ለመሸጥ አስቸጋሪ ሆኖብናል ብለዋል። መንግስት ለችግሩ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ በመጠየቅም እስከዚያው ድረስ በመቶ ግራም ዳቦ ላይ የደነገገውን የዋጋ ተመን በይፋ ማሻሻል እንደሚገባው አመልክተዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=39492
“ህውሃት ለትግራይ ህዝብ ፍላጎት ደንታ እንደሌለው በተጨባጭ እያሳየ ነው’’ – አቶ ደረጀ በቀለ የኢትዮጵያ የፌዴራሊስት ሃይሎች ጥምረት ሰብሳቢ
************************
(ኢ ፕ ድ)
ጎጠኛ የህወሃት አመራሮች እየሄዱበት ያለው መንገድ በተጨባጭ ለትግራይ ህዝብ ፍጎላጎት ደንታ እንደሌላቸው አመላካች መሆኑን የኢትዮጵያ የፌዴራሊስት ሃይሎች ጥምረት ሰብሳቢ አቶ ደረጀ በቀለ አስታወቁ ። የፌደሬሽን ምክር ቤት የደረሰበት ውሳኔ ትክክለኛ መሆኑን አስታወቁ ።
የፌዴራሊስት ሃይሎች ጥምረት ሰብሳቢ አቶ ደረጀ በቀለ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት ፣የህወሃት አመራሮች እየሄዱበት ያለው መንገድ በተጨባጭ ለትግራይ ህዝብ ፍጎላጎት ደንታ እንደሌላቸው አመላካች ነው ። የፌዴሬሽን ምክር ቤት በህገ ወጥ መልኩ ለተቋቋመው የትግራይ ክልል ስራ አስፈጻሚ የበጀት ድጎማንና ማንኛውም ከፌዴራል መንግስት ጋር የሚደረግን ግኙነት ማቋረጡ ትክክል ነው ብለዋል ፡፡
የህወሃት አካሄድ የትግራይን ህዝብ ለመጥቀም ሳይሆን ከተጠያቂነት ለማምለጥ ያለመ መሆኑን ገልጸው፤ እነዚህ ጥቂት ቡድኖች ለትግራይ ህዝብ ልማት ከማምጣትና ህይወቱን ከመለወጥ ይልቅ ጦርነትን እንደሚመኙለት ተግባራቸው ያረጋግጣል ብለዋል፡፡
እነዚህ ሃይሎች ራሳቸውን አንደ አንድ አገር የመቁጠር አዝማሚያ እንደሚያሳዩና ፍላጎታቸው እንደሆነ ጠቁመው ፤ በአንጻሩ የትግራይ ህዝብ ከሌሎች የኢትዮጵያ ብሄሮችና ብሄረሰቦችና ህዝቦች ጋር ተደጋግፎ ማደግና በአንድነት መኖር የሁልጊዜ ፍላጎቱ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ እነዚህ ሃይሎች የሚያራምዱት አቋም ለትግራይ ህዝብ ፍላጎት ደንታ እንደሌለው በተጨባጭ እንደሚያሳይ አስታውቀዋል፡፡
ጥቂት የህወሃት ቡድን ከህግ ውጭ በክልሉ ያካሄደው ምርጫና ያንን ተከትሎ ያሳየው ህገ ወጥነት ከፌዴራል መንግስት ጋር በበጀት፣ በአስተዳደር እና በሌሎችም ግንኙነቶች ላይ ችግር መፍጠሩ እንደማይቀር አስታውቀዋል፡፡
https://www.press.et/Ama/?p=39483
የተቀላጠፈ የመንጃ ፈቃድ እድሳት አገልግሎት እያገኙ ባለመሆናቸው ደንበኞች ቅሬታ አቀረቡ
********************
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ ከተማ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን የአራዳ ክፍለ ከተማ ቅርጫፍ አንዳንድ ደንበኞች የተቀላጠፈ የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት አገልግሎት እያገኙ አለመሆናቸውን ቅሬታ አቀረቡ። ቅርጫፍ ጽህፈት ቤቱ ቅሬታውን በመቀበል ደንበኞች ከዚህ በኋላ በየትኛውም የአገልግሎት መስጫዎች የሚስተናገዱበት የአሰራር ሥርዓት እንደሚዘረጋ ገለጸ።
ቅሬታቸውን ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ የገለጹ አንዳንድ የቅርጫፉ ደንበኞች በቅርጫፉ የሚሰጠው አገልግሎት ጊዜና ገንዘብ ቆጣቢ አለመሆኑ፤ ተቋሙ ማሟላት ያለበትን ባለማሟላቱ በአጭር የቀጠሮ ጊዜ ለአገልግሎት መመላለሳቸው፣ ለኮቪድ 19 ቫይረስ ወረርሽኝ በሚያጋልጥ የአገልግሎት አሰጣጥ መስተናገዳቸው ቅሬታ እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል።
ከደንበኞቹ መካከልም ወይዘሮ ሰናይት አበበ የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት አገልግሎት ለማግኘት ጠዋት አንድ ሰአት ላይ ቀድመው በቅርጫፉ መገኘታቸውን ገልጸው፣ ከሰአታት ቆይታ በኋላ ተራ ደርሷቸው የሚያስተናግዳቸው ጋር ሲደርሱ ፎቶግራፍ በሲዲ እንዲያመጡ በመጠየቃቸው ከቅርጫፉ ውጭ ወጥተው የተጠየቁትን ካሟሉ በኋላም እስከ ቀኑ ዘጠኝ ሰአት ድረስ አገልግሎት እንዳላገኙ ተናግረዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=39493
ገቢያቸውን እያሳወቁ ታክስ የሚከፍሉ ነጋዴዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ተጠቆመ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ ከተማ ገቢያቸውን እያሳወቁ ታክስ የሚከፍሉ ዜጎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የኮሙኒኬሽን ቡድን አስተባባሪ አቶ በላይነህ ወልደሰንበት ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፣ በደረጃ ‹‹ሀ›› ፣ ‹‹ለ›› እና ‹‹ሐ›› የተመዘገቡ ግብር ከፋይ ደንበኞች ገቢያቸውን እያሳወቁ ታክስ የመክፈል ልምዳቸው እያደገ መጥቷል።
በበጀት ዓመቱ ሩብ ዓመት 390 ሺ 649 ግብር ከፋዮች ገቢያቸውን አሳውቀው የሚጠበቅባቸውን ይከፍላሉ ተብሎ ዕቅድ ተይዞ እንደነበር አመልክተው፣ እስከ አሁን ድረስ 307 ሺ 298 ገቢያቸውን አሳውቀው የሚጠበቅባቸውን ግብር መክፈላቸውን አስታውቀዋል። ይህም ከእቅዱ 78 ነጥብ ስምንት በመቶ መሆኑን ጠቁመዋል።
ይህም ከአምናው ተመሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ17 በመቶ በላይ ብልጫ እንዳለው ጠቁመው ፣ ይህም ዜጎች ሃላፊነታቸውን ተረድተው የሚጠበቅባቸውን ታክስ የመክፈል ግንዛቤያቸው እያደገ መምጣቱን የሚያሳይ ነው ብለዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=39501