Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚፈጸሙ ጥቃቶች በክልሉ የመንግስት መዋቅር ክፍተት መሆኑ ተገለጸ
************************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ:- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚፈጸሙ ጥቃቶች በክልሉ የመንግስት መዋቅር ክፍተት እና በአንዳንድ አመራሮች ችግር ምክንያት መሆኑን የአማራ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት በበኩሉ ችግሮችን ለይቶ እርምጃ መውሰዱን ገልጿል።
የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ትናንት ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመንግስት መዋቅር ክፍተት አለ ፤ ይህንን ክፍተት የክልሉ መንግስት በአቋም ደረጃ ወስዶ አልሰራበትም። በዚህም ምክንያት በአማራና በአገው ብሄረሰቦች ላይ ጥቃት ሊደርስ ችሏል።
ለችግሩ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ዘላቂ መፍትሄ እየተሰጠ አይደለም፤ እሳት የማጥፋት ስራ ነው እየተሰራ ያሉት አቶ ግዛቸው፤ ከዘላቂ መፍትሄ አንጻር ከክልሉ አመራሮች ጋር በመድረክ ስምምነት የተደረሰበት አማራው፣ አገው እና ሁሉም ዜጋ በአፈጻጸሙና በብቃቱ ተመርጦ በየአካባቢው መደራጀትና የአካባቢውን ጸጥታ መጠበቅ እንዳለበት አመልክተዋል።
“የክልሉ መንግስት አመራሮች በመድረክ ደረጃ የሌላውን ብሄር አደረጃጀት በመዋቅር ውስጥ ለማስገባት ፈቃደኛ ናቸው፤ ምክንያቱም ችግሩ የጋራ ነውና፤ ግድያው አማራን እና አገውን አነጣጥሮ ቢፈጸምም አልተባበር ያለውን ጉሙዝን እና ሺናሻንም ያካተተ ነው ጥቃት አድራሹ ጽንፈኛ ቡድን የክልሉን መንግስትም አዳክሞ ወደ ስልጣን የመምጣት ፍላጎት ያለው እንደሆነም አመልክተዋል።
“የቤኒሻንጉል ጉሙዝ መንግስት ይሄንን ያውቃል። ስለዚህ ይሄን አልቀበልም አይልም፤ ችግሩ ያለው ቁርጠኛ ሆኖ መፈጸም ላይ ነው፤ ይሄ ደግሞ የሆነው መሃላቸው ላይ የዚህ ጽንፈኛ አመለካከት ተጋሪዎች ስላሉ ነው። ይሄንን ማረም አለባቸው” ብለዋል።
አማራ እና አገውን ከሚሊሻ፣ ከቀበሌና ከወረዳ አደረጃጀት ውስጥ ያገለለ ነው ያሉት አቶ ግዛቸው፤ በዚህም ምክንያት የጥቃቱ ሰለባ የሚሆኑ ወገኖች ራሳቸውን የመከላከል አቅም እንዳጡ አመልክተዋል።
በአማራና በአገው ብሄር ተወላጆች ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት መድረሱን ያስታወሱት አቶ ግዛቸው በሰሞኑ ጥቃት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የአማራ ክልላዊ መንግስት የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
ከአጭር ጊዜ መፍትሄ አንጻር በጥቃቱ ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ የማድረግና የማረጋጋት ስራ እየተሰራ መሆኑን ያነሱት ዳይሬክተሩ፤ በዚህም አስፈላጊው የእለት ደራሽ ሰብአዊ ድጋፍ እየቀረበላቸው መሆኑን አስታውቀዋል።
በጉዳይ ዙሪያ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ መለሰ በየነ በበኩላቸው፤ “የተፈጠረው ችግር ሁላችንንም አሳስቦናል፤ በእኛ መዋቅር ድክመት የተፈጠረ ችግር ነው፤ ያንን ችግር እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በአብሮነት በጋራ መፍታት እና በጀመርነው ልክ መሄድ አንድ መፍትሄ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
ቀደም ብሎ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የክልሉን መዋቅር መልሶ የማየትና የማስተካከል ስራ መከናወኑን የገለጹት አቶ መለሰ፤ በሁሉም ወረዳዎችና ዞኖች ላይ የአመራር ሁኔታ ተፈትሾ ፤ በሂስና በግለ ሂስ ውጤት መሰረት ከሃላፊነት የሚነሱት በሙሉ ተነስተዋል፤ በህግ የሚጠየቁም አመራሮች ተለይተዋል ብለዋል።
“ጥቃቱን እያደረሱት ያሉት የትኛውንም ማህበረሰብ የማይወክሉ ሽፍታዎች ናቸው፤ እነዚህን ሽፍታዎች ደግሞ በጋራ በመሆን የመደምሰስ ስራ ይሰራል፤ አሁንም በተጨባጭ እየተካሄደ ያለው ይሄው ነው” ያሉት አቶ መለሰ፤ የችግሩ ዘላቂ መፍትሄ የጋራ ልማት ማከናወን መሆኑን በማንሳት፤ ከዚህ አንጻር ሁለቱ ክልሎች የጋራ የልማት ትብብር እንዳላቸው አመልክተዋል።
የሁለቱ ክልሎች የ3 ዓመት የጋራ የልማት ፕሮጀክት ይፋ ሆኗል፤ ይሄንን በይበልጥ ለማጠናከር የጋራ ጽ/ቤትና መዋቅር ለማቋቋም ስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል።
ከአደረጃጀት አንጻር የእኛ ክልል ምሳሌ መሆን የሚችል ነው፤ የአማራ ብሄረሰብ በሚበዛባቸው አካባቢዎች ከቀበሌ ጀምሮ የመዋቅሩ አካል የሚሆኑበት አሰራር አለ ያሉት አቶ መለሰ፣ በክልል ደረጃም ከህዝቡ ቁጥር አንጻር እየታየ በመዋቅር ውስጥ የሚሳተፉበት አሰራር ተግባራዊ እንደሆነ አመልክተዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት በትናንትናው እለት በ45 የክልሉ አመራሮች ላይ እርምጃ መውሰዱ ታውቋል። ከነዚህም ውስጥ አስሩ አመራሮች በህግ እንዲጠየቁ ተወስኗል።
አዲስ ዘመን መስከረም 19/2013
የፌዴራል ፖሊስ ነገ መስከረም 20 ቀን በመስቀል አደባባይ በሚያካሂደው ትርኢት ሳቢያ ለትራፊ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች
ነገ መስከረም 20 ቀን 2013 ዓ/ም ከጠዋቱ 1፡30 እስከ 6፡30 ሰዓት በመስቀል አደባባይ የመንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የፌዴራል ፖሊስ የሰልፍ ትርኢት ይካሄዳል፡፡
በዚህመሰረት
• ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ኦሎምፒያ አደባባይ
• ከመገናኛ፣በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኒያለም፣በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያ አካባቢ
• ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባሻ ወልዴ ችሎት ወይም ፓርላማ መብራት
• ከቸርችል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ አገር አስተዳደር መብራት ወይም ኢሚግሬሽን መ/ቤት አካባቢ
• ከተክለሀይማኖት በሜትሮሎጂ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ
• ከተክለሀይማኖት፣በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣ኢሚግሬሽን ጥቁር አንበሳ የኋላ በር
• ከጌጃ ሰፈር፣ጤና ጥበቃ፣ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ
• ከሳሪስ በጎተራ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር አካባቢ
• ከጦር ኃይሎች፣ልደታ፣ፖሊስ ሆስፒታል ሜክሲኮ አደባባይ
• ከጦር ኃይሎች፣ልደታ፣ፖሊስ ሆስፒታል፣ሜክሲኮ፣ለገሀር መብራት የሚወስደው ለገሃር መብራት
የይለ ፍፈቃድ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ዝግ መሆኑን አሽከርካሪዎች ተገንዝበው የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን አስተላልፏል፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር ሁለት የግል ትምህርት ቤቶችን አገደ
*************************
(ኢ ፕ ድ)
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን የክፍያ መመሪያ ተላልፈው የተገኙ ሁለት የግል ትምህርት ቤቶች ለግዜው መታገዳቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
እገዳው የተላለፈባቸው ትምህርት ቤቶች አንድነት ኢንተርናሽናል እና ሄሌኒክ-ግሪክ ማህበረሰብ ት/ቤት ናቸው፡፡
በትምህርት ቤቶቹ ላይ ውሳኔ የተላለፈው ትምህርት ቤቶቹ የተቀመጠውን መመሪያ ተግባራዊ ባለማድረጋቸው የወላጅ ኮሚቴዎች ተደጋጋሚ አቤቱታ በማቅረባቸው መሆኑም ተገልጿል፡፡
ትምህርት ቤቱ ከዛሬ ጀምሮ መንግስት( ትምህርት ሚኒስቴር) ያወጣውን መመሪያ ከወላጅ ኮሚቴ ጋር በመነጋገር ፈጥኖ ሪፖርት እስኪያደርጉ ድረስ ትምህርት ቤቶቹ ምንም አይነት የትምህርት ስራ እንዳይሰሩ መታገዳቸውን ተገልጿል፡፡
የኢሬቻ በዓልን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር የተለያዩ ዝግጅቶችን እያደረገ መሆኑን በአዲስ አበባ ከተማ የኦሮሚያ ወጣቶች ማህበር አስታወቀ
**************************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ የኢሬቻ በዓልን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር የተለያዩ ዝግጅቶችን እያደረገ መሆኑን በአዲስ አበባ ከተማ የኦሮሚያ ወጣቶች ማህበር አስታወቀ።
ማህበሩ በበአሉ ዋዜማና በእለቱ በአዲስ አበባ ከተማ የፀጥታ ማስከበር ስራዎችን እንደሚያከናውንም ዛሬ በአዲስ አበባ በተደረገ የውይይት መድረክ ላይ አስታውቋል።
የማህበሩ ሰብሳቢ ወጣት ባጫ ጂሬኛ በዚሁ መድረክ ላይ ባደረገው ንግግር፤ ማህበሩ ከ68 ሺህ በላይ አባላት ያሉትና ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ አደረጃጀቱን በማጠናከር በልማት ስራዎች ላይ አበክሮ ሲሳተፍ መቆየቱን ገልጿል።
"ወጣቶች የሀገሪቱ የማህበረ-ኢኮኖሚው ዋልታ በመሆናቸው መደራጀታቸው የራሳቸውን ችግር ከመፍታት አልፈው ለሀገር ችግር ቁልፍ መፍቻ ናቸው" ሲል ተናግሯል።
በአሁኑ ሰዓትም ማህበሩ በአዲስ አበባ ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር በመሆን እየሰራ እንደሆነ የገለጸው ሰብሳቢው፤ የዘንድሮውን የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓልን በሰላማዊ መንገድ ለማክበር በእነሱ በኩል አሰፈላጊው የቅድመ ጥንቃቄ ዝግጅት ስራዎች መሰራቱን አስታውቋል።
ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ በማያደርግ መልኩ የገዳ አባቶች በሚያስቀምጡት አቅጣጫ መስረት በአሉ እንደሚከበርም ነው የእለቱ መድረክ ተሳታፊዎችም ያስታወቁት፡፡
በውይይት መድረኩም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ አባ ገዳዎችና ወጣቶች መገኘታቸውን ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በወንድማሸኝ አሸብር
ምርጫ ቦርድ ለ6ተኛው አገራዊ ምርጫ እያደረገ ያለውን ዝግጅት ለሚዲያ አካላት ሊያስጎበኝ ነው
*******************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ6ተኛው አገራዊ ምርጫ ኦፕሬሽን እያደረገ ያለውን ዝግጅት ለሚዲያ አካላት ሊያስጎበኝ ነው።
ቦርዱ ለሚዲያዎች ባወጣው ጥሪ፤ በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የተመዘገቡ ሚዲያዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ6ተኛው አገራዊ ምርጫ ኦፕሬሽን እያደረገ ያለውን ዝግጅት እንዲጎበኙ ጋብዟል።
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ማናቸው?
በ1922 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ነው የተወለዱት።
ዕድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እትጌ መነን ተምረዋል።
ከ1955 ዓ.ም ጀምሮ በለንደንና በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከፍተኛ ትምህርት ተከታትለዋል። እንዲሁም በመምህርነት አገልግለዋል።
ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ መንግሥታትን በመተቸትና ሂስ በመስጠት የሚታወቁ የፖለቲካ ሰው ናቸው።
ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲን ከመሰረቱት ሰዎች አንዱ ናቸው።
በተለይም ኢህአዴግን ፊት ለፊት በመቃወም ይታወቃሉ።
አንጋፋው ምሁርና የሰብዓዊ መብት ተሟጓቹ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም መጋቢት 7ቀን 2011 ዓም ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ሰፋ ያለ ቆይታ አድርገው ሃሳባቸውን አጋርተዋል።
በፕሮፌሰሩ ህልፈተ ህይወት የተሰማንን ሃዘን እየገለጽን በወቅቱ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ በድጋሜ እንድታነቡት አቅርበናል።
ሊንኩን ተጭነው መረጃዉን ማግኘት ይችላሉ!
https://www.press.et/Ama/?p=6932...
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ለቤተሰቦቻቸው ፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን ተመኝተዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሙሉ መልዕክት ....
"የሐሳብ ልዕልና ምልክት፤ የሰላማዊ ትግል አርአያ፣ ላመኑበት ነገር እስከ መጨረሻቸው ሞጋች፣ ላመኑበት እውነት ብቻ የሚቆሙት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም በማረፋቸው ጥልቅ ኀዘን ተሰምቶኛል። ለቤተሰቦቻቸው ፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን እመኛለሁ"
“የእነ ዶክተር ዐብይ አህመድ ለውጥ የተለየ የሆነው ከነበረው አስተሳሰብ አፈንግጠው መውጣታቸው ነው። ራሳቸውን ነፃ አድርገው በነፃነት ለመምራት መነሳታቸው ከሌሎቹ የተለየ ያደርጋቸዋል”። በየመድረኩ የሚናገሩትም በጣም የሚያስደንቅ ንግግር ሆኖ ነው ያገኘነው። ስለዚህ እነዚህ ሰዎች ችሎታ ያላቸው ከመሆናቸው በላይ ዋናው ነገር ወኔያቸው፤ ራሳቸውን ነፃ አድርገው ሌላውን ነፃ ማድረጋቸው፤ እስረኞችን መፍታታቸውና ሌሎችም ተግባራት አስደሰተኝ”
የኢሬቻ በዓልን ለመረበሽ የተዘጋጁ 503 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
**********
(ኢ.ፕ.ድ)

መስከረም 23 እና 24 የሚከበረውን የኢሬቻ በአል ለመረበሽ የተዘጋጁ 503 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ኮማንደር አራርሳ መርዳሳ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለፁት፤ የኢሬቻ በዓል ላይ የሚሳተፉ የበዓሉ ታዳሚዎች በሰላም ወጥተው እንዲገቡ ኮሚሽኑ በጥብቅ እየሰራ ነው።

የግል ፍላጎታቸውን ለማሳካት በተለያየ አቅጣጫ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ሀይሎች እንዳሉና ኮሚሽኑም እንደደረሰባቸው የገለፁት ኮማንደሩ፤ እስካሁን ድረስ 503 ሰዎች፣14 ክላሽ ፣ 26 ቦምብ እና 103 ሽጉጦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል፡፡

ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የኢሬቻ በዓል በኮረና ምክንያት እንደ ከዚህ ቀደሙ በርከት ባለ ሰው የማይከበር ሲሆን በገዳ አባቶች የተላለፈውን ውሳኔን ህብረተሰቡ ስራ ላይ ማዋል እንዳለበትም ጄኔራል ኮማንደር አራርሳ ተናግረዋል፡፡

ህብረተሰቡ ከፀጥታ ሀይሉ ጋር በመሆን ከህወሓት እና ከሸኔ የተሰጣቸውን ግዳጅ በመውሰድና ኦሮሚያን የጦርነት አውድማ ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ሀይሎችን በማጋለጥ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የስልጣን ጥም ያላቸው አካላት "ከመስከረም 25 በኋላ መንግስት የለም" እያሉ ህብረተሰቡን ለማወክ የሚፈልጉ አካላት በምንም ሁኔታ እንደማይሳካላቸው ጄኔራል ኮማንደር አራርሳ ተናግረዋል፡፡

የኦሮሚያ ፖሊስ የህዝቡን ሰላም የሚያውኩትን በመከታተል ህግ ለማስከበር በቁርጠኝነት መዘጋጀቱንም ኮማንደሩ አስታውቀዋል፡፡

በሐይማኖት ከበደ
በእንጦጦ ጫካ ለአመታት እንጨት በመልቀም ኑሯቸውን ሲገፉ የኖሩ ሴቶች በእንጦጦ ፓርክ ውስጥ አዲስ ስራ እንደተፈጠረላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አስታወቁ
**************************
(ኢ ፕ ድ)
በእንጦጦ ጫካ ለአመታት እንጨት በመልቀም ኑሯቸውን ሲገፉ የኖሩ ሴቶች በእንጦጦ ፓርክ ውስጥ አዲስ ስራ ተፈጥሮላቸው እየሰሩ መሆናቸውን የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ገጻቸው ላይ፤ "ጠንካራዎቹ የእንጦጦ ሴቶች ከአዳዲሶቹ ሥራዎቻቸው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ" በሚል ከምስል ጋር ባሰፈሩት መልዕክት እንዳሉት፤ የእንጦጦ ሴቶች ለዓመታት ወገብ ከሚያጎብጥ የማገዶ እንጨት ለቀማና ሸክም ተሠማርተው ኖረዋል፡፡
እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፤ አሁን ግን በእንጦጦ ፕሮጀክት አማካይነት በመቶዎች የሚቆጠሩት ሠልጥነው በአዲሱ መናፈሻ ውስጥ ለተከፈቱ ንግድ ሥራዎች በግብዓት አቅራቢነት ተደራጅተዋል፡፡
ዶ/ር አብይ በመልዕክታቸውም፤ "ትራንስፎርሜሽን በሂደቱ ውስጥ ሌሎችን ማንሣትን ይጠይቃል" ሲሉ ተናግረዋል።
ሁለተኛው የኢሬቻ ፎረም በሸራተን አዲስ በመካሄድ ላይ ነው
***********************
(ኢ ፕ ድ)
ሁለተኛው የኢሬቻ ፎረም በሸራተን አዲስ ሆቴል በመካሄድ ላይ ነው።
በፎረሙ ላይም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፣የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ዲፕሎማቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡
በፎረሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እንደተናገሩት፤ የኦሮሞ ህዝብ በብዙ ችግሮች ውስጥ አልፎ ዛሬ ላለበት ድል ደርሷ ብለዋል፡፡
የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ በሆራ ፊንፊኔ እንዲከበር የጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አመራር ከፍተኛ አስተዋፆኦ እንደነበረው ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በኋላ ቀጣዩ ትውልድ የገዳ ስርአቱን እየኖረበት ሊያስተዋውቀውም ይገባል ብለዋል፡፡
በአሉ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ እየተጉ ላሉ አካላት ምስጋናቸውን በማቅረብ ሰላምን ለማደፍረስ የሚጥሩ ቡድኖች መቼም እንደማይሳካላቸውም አስታውቀዋል፡፡
ኢሬቻ ስጋት እንዲሆን የሚፈልጉ አካላት ቢኖሩም የሰላምና የይቅርታ በአል የሆነው ኢሬቻ ግን ስጋት ሊሆን አይችልም ነው ያሉት አቶ ሽመልስ።
ያለፈው አመት የኢሬቻ በአል በሰላም ተከብሮ ማለፉን ያስታወሱት ፕሬዝዳንቱ፤ ዘንድሮ በኮቪድ ምክንያት በውስን ሰው ለማክበር መገደዳቸውን አስታውቀዋል።
በሀይማኖት ከበደ
መጪው መስከረም 30 ቀን 2013 ዓ.ም ብቻ አይደለም የወደፊቶቹም
መስከረሞች በሰላም ይቀጥላሉ፤ የሚያስቆምም የሚገታም ኃይል
የለም፤
👉 ኢትዮጵያ ሰላሟ ተጠብቆ ብዙ መስከረሞችን ታልፋለች፤ መከላከያ
ሠራዊቱ፣ ሕዝቡ፣ ሀገሪቱም ትቀጥላለች፤
👉 አንዳንድ ሰዎች ያልሆነ መልዕክት አስተላልፈዋል በሚል
ኅብረተሰቡ መረበሽ የለበትም፤
👉 ምንም የሚፈጠር ረብሻና ሁከት አይኖርም፤ ሕግና ሥርዓት ተከብሮ
ይቀጥላልም ብለዋል፤
ጀነራል ብርሃኑ ጁላ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም በሰኔ ወር 2012 ዓ.ም ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቆይታ ያስተላለፉት መልዕክት ሲሆን፤ ሙሉ ቃለ መጠይቁን ከታች ካለው ሊንክ ማግኘት ይችላሉ።
https://www.press.et/Ama/?p=34383
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እና ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ በኮሮና ተያዙ
***********
(ኢ.ፕ.ድ)
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እና ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ።
ዶናልድ ትራምፕ የቅርብ አማካሪያቸው በኮሮናቫይረስ መያዟን ተከትሎ እርሳቸው እና ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ የኮሮናቫይረስ ምርመራ አድርገው ውጤቱን በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን ብለው ነበር።
የምርመራውን ውጤቱን ተከትሎ እርሳቸው እና ባለቤታቸው በቫይረሱ መያዛቸውን ዶናልድ ትራምፕ በትዊተር ገጻቸው ላይ ይፋ አድርገዋል።
ኢሬቻ የፍቅር፣ የይቅርታ፣ የምስጋና፣ የሰላም እና የአንድነት በዓል ነው። በሆራ ፊንፊኔ እየተከበረ ባለው የኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ አባገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ የኃይማኖት አባቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
አዲሱ የብር ለውጥ ከተጀመረ በሁዋላ በ14 ቀናት ብቻ 580 ሺህ ዜጎች አዲስ የሂሳብ አካውንት ከፍተዋል፤ ከባንክ ውጭ የነበረ 14 ቢሊዮን ብር ወደ ባንክ ገቢ ሆኗል
***********************
(ኢ ፕ ድ)
አዲሱ የብር ለውጥ ከተጀመረ በሁዋላ ባሉት 14 ቀናት ውስጥ ብቻ 580 ሺህ ዜጎች አዲስ የሂሳብ አካውንት ከፍተዋል፤ በእነዚህ አካውንቶች ውስጥም ከባንክ ውጭ የነበረ 14 ቢሊዮን ብር ወደ ባንክ መግባቱን ብሄራዊ ባንክ አስታወቀ።
የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ ዛሬ እንዳስታወቁት፤ አዲሱ ብር በመላ አገሪቱ ባሉ የባንክ ቅርንጫፎች 99 ነጥብ 9 በመቶ ተዳርሷል። በዚህም ምክንያት በሁሉም ባንኮች 580 ሺህ ዜጎች የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል።
በእነዚህ 580 ሺህ አዲስ የሂሳብ አካውንቶች ውስጥም በ14 ቀናት ውስጥ ብቻ 14 ቢሊዮን ብር ወደ ባንክ ገቢ መደረጉን ዶ/ር ይናገር ገልጸዋል። በነባር አካውንት ውስጥ የገባው ገንዘብ መጠንን በተመለከተ ደግሞ ተጠቃሎ ይፋ እንደሚሆን አስታውቀዋል።
የብር ለውጡ ያስፈለገበት አንዱ ዓላማ ከባንክ ውጭ ያለን ገንዘብ ወደባንክ የማስመለስ ጉዳይ እንደነበር ያስታወሱት የባንኩ ገዥ፤ ከዚህ አንጻር በ14 ቀናት ውስጥ ብቻ በአዲስ አካውንት ይሄንን ያህል ገንዘብ ወደ ባንክ ስርዓቱ መመለሱ የዓላማውን መሳካት ያሳያል ብለዋል። በቀሪ ቀናትም ተጨማሪ ገንዘብ እንደሚገባ ይጠበቃል ብለዋል።
በሁለተኛ ደረጃ የብር ለውጡ አለማ የነበረው የባንክ አገልግሎት ተደራሽነትን ማሳደግ እንደሆነ የገለጹት ዶ/ር ይናገር፤ ከዚህ አንጻር በ14 ቀናት ውስጥ ብቻ 580 ሺህ ዜጎች የባንክ አካውንት ከፍተዋል፤ በቀሪዎቹ ቀናት ውስጥ በሚሊን የሚቆጠሩ ዜጎች አካውንት ይከፍታሉ ተብሎ ይጠበቃል ነው ያሉት።
አዲሱን ብር በመላ አገሪቱ ባሉ የባንኮች ቅርንጫፎች ደርሷል ያሉት ዶ/ር ይናገር፤ በዚህ ሂደትም 67 ቢሊዮን ብር ለባንኮቹ ቅርንጫፎች ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲዳደረስ ተደርጓል ነው ያሉት።
አዲሱ የገንዘቡ ኖት በሁሉም ባንኮች መዳረሱን የጠቀሱት የባንኩ ገዥ፤ ህብረተሰቡ በተያዘው የጊዜ ውስጥ በእጁ ያለውን ብር መቀየር አለበት ብለዋል።
በተለይ ከ100 ሺህ እስከ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር ድረስ በእጃቸው ያላቸው ሰዎች የማጠናቀቂያ ጊዜው የተወሰኑ ቀናት ስለቀሩት በኋላ ላይ ከሚፈጠር መጨናነቅ ተጠብቀው ገንዘባቸውን በፍጥነት መቀየር እንዳለባቸው አሳስበዋል።