Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአፍሪካ ከሚገኙ ምርጥ አስር ዩኒቨርሲቲዎች ተርታ መመደቡ ተገለጸ
*****************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ ፡- የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአፍሪካ ከሚገኙ ምርጥ አስር ዩኒቨርሲቲዎች ተርታ መመደቡን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ገለጹ፡፡ በህትመት ስኬታማነት በአፍሪካ ካሉ ሶስት ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ መሆኑም ተጠቆመ፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት ፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባደረጋቸው ችግር ፈቺ የምርምር ተግባራት በዓለም አቀፍ የዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ መዳቢ አካላት በአፍሪካ ከሚገኙ ምርጥ አስር ዩኒቨርሲቲዎች ተርታ መመደቡን ገልጸዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ለዚህ የበቃው በምርምር ውጤቶችና በዩኒቨርሲቲው የሚታተሙ ህትመቶች ለሌሎች ተመራማሪዎች እና ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ባላቸው የችግር ፈቺነት አቅም መሆኑን አመልክተዋል።
የካይሮ ዩኒቨርሲቲ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሚያሳትመው ህትመት ብዛት እንደሚበልጥ ያመለከቱት ፕሬዝደንቱ ፤ በህትመቶች ተጠቃሽነት ግን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንደሚበልጥ አስታውቀዋል።
ይህ የሆነው በዩኒቨርሲቲው የሚደረጉ ጥናቶች እና ምርምሮች ከካይሮ ዩኒቨርሲቲ በበለጠ ለህብረተሰባችን ፣ ለአፍሪካ ብሎም ለዓለም ሊጠቅሙ የሚችሉ ጥናቶች እንደሆኑ በደረጃ መዳቢ አካላት እውቅና በማግኘቱ እንደሆነ ጠቁመዋል።
ሌሎች የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች እዚህ ውድድር ውስጥ ገብተው እንደነበር የጠቆሙት ፕሬዚዳንቱ ፤ ነገር ግን በሀገራችን ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች የአዲስ አበባ እና የጎንደር የኒቨርሲቲ ብቻ ከ1 ሺ 500 ምርጥ የዓለማችን ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መካተታቸውን ገልጸዋል።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከአፍሪካ 49ኛ ደረጃ ላይ መሆኑንም አመልክተዋል።
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው በ26 ወሳኝ የምርምር ጉዳዮች ላይ ቅድሚያ በመስጠት በሀገሪቱ ፣ በአህጉሪቱ እና በዓለም ችግር ላይ ሁነኛ መፍትሔ ለመፈለግ እየተጋ ያለ ዩኒቨርሲቲ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ ፤ በአሁኑ ሰዓት በአፍሪካ ካሉ አስር ምርጥ የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ከመሆን ባለፈም በህትመት ስኬታማነት ደግሞ በአፍሪካ ካሉ ሶስት ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ነው ብለዋል።
እንደ ፕሬዚደንቱ ገለጻ፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመማር ማስተማር ፣ በምርምር እና በማህበረሰብ አገልግሎት ላይ በመሳተፍ ለአለፉት ሰባ ዓመታት በርካታ ስራዎችን ሲከናውን ቆይቷል።
ዩኒቨርሲቲው በ1950 ዓ.ም 33 ተማሪዎች እና 7 አስተማሪዎች ትምህርት እና ምርምር በማካሄድ የጀመረው መሆኑን ጠቁመው፤ በአሁኑ ሰዓት ከ3 ሺ በላይ መምህራን ፣ 5 ሺ የሚሆኑ የአስተዳደር ሰራተኞች ፣ 1 ሺ 200 የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች ፣ ከ46 ሺ በላይ ተማሪዎች ፣ 12 ኮሌጆች እና 10 የምርምር ተቋማትን ይዞ የሀገሪቱን የልማት አቅጣጫ ተከትሎ እየሰራ ያለ ትልቅ ተቋም መሆኑን አመልክተዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ካሉት ዩኒቨርሲቲዎች ልዩ የሚያደርገው በእድሜ ትንሹ እና ብቸኛው በቅኝ ገዥዎች ያልተቋቋመ ዩኒቨርሲቲ ነው ያሉት ፕሬዚደንቱ ፤ ይሁን እንጂ እድሜ ሳይገድበው እድሜ ጠገብ ከሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ቀድሞ መቆም የቻለ መሆኑን አስታውቀዋል።
ዩኒቨርሲቲው አጠቃላይ በሁለንተናዊ መልኩ ከአምስት ዓመት ወዲህ እያሳየ ያለው መሻሻል ወደ ፊት በአፍሪካ ብሎም በዓለም ከሚገኙ ዩኒቨርሰቲዎች ተርታ ቀዳሚ ሊያደርገው እንደሚችልም እምነታቸው እንደሆነ ጠቁመዋል።
አዲስ ዘመን መስከረም 18/2013
በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ዘርፍ በሁለት ወራት ብቻ ከወጪ ንግድ 31 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር መገኘቱ ተገለጸ
********************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ፡- በ2013 በጀት ዓመት በሐምሌና በነሐሴ ወር ብቻ ከጨርቃጨርቅና አልባሳት ዘርፍ ከወጪ ንግድ 31 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ማግኘት መቻሉን ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት አስታውቋል።
የኢንስቲትዩቱ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ባንቲሁን ገሰስ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ በ2013 በጀት ዓመት ከውጭ ንግድ ለማግኘት ከታቀደው 210 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በሁለቱ ወራት ብቻ 31 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ማግኘት ተችሏል፡፡ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተገኘ ገቢ ጋር ሲነጻጻር የተሻለ ገቢ መገኘቱን እንደሚያመላክት አስታውቀዋል።
ኮቪድ 19 ቫይረስ በጨርቃጨርቅና አልባሳት ዘርፍ የውጭ ሀገራት የንግድ ግንኙነት ላይ ተጽዕኖ ያሳደረ መሆኑን የተናገሩት አቶ ባንቲሁን፤ እንደዛም ሆኖ ግን ከዘርፉ ከውጭ ገበያ ለማግኘት ከታቀደው ገቢያ አኳያ ሲታይ ከተላኩ ምርቶች የተሻለ ገቢ ተገኝቷል፡፡
ምንም እንኳን ቫይረሱ ከፍተኛ ተጽዕኖ የፈጠረ ቢሆንም ፤ መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው ትኩረትና በፋብሪካዎች ጥረት ቫይረሱን በመቋቋም የተሻለ ውጤት መመዝገቡን ጠቁመው፤ ካምፓኒዎችም ገበያውን ሳያቋርጡ ምርቶቹን ለውጭ ገበያ በማቅረብ የተሻለ የውጭ ገቢያ እንዲገኝ ማድረግ የቻሉ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
የገበያ መዳረሻዎቹ ጀርመን፣ ጣሊያን ፣ አሜሪካ ፣ ቻይና እና የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ሲሆኑ፤ የገበያ መዳረሻዎቹን ለማስፋት ከተለያዩ የውጭ አገራት ገበያ ጋር ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ገቢ ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ኃላፊው አስረድተው፤ ለውጭ ንግድ ገበያ የተላኩት ምርቶች ክር፣ ጨርቅ ፤ አልባሳትና ባህላዊ አልባሳት መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡
ከሀገሪቱ ከ200 በላይ የሚሆኑ መካከለኛና ከፍተኛ የጨርቃጨርቅና የአልባሳትና ኢንዱስትሪዎች ያሉ ሲሆን፤ 60 ያህል ፋብሪካዎች በውጭ ንግድ ገበያው ተሳታፊ መሆናቸውን ጠቅሰው ፤ አብዛኛዎቹ የሀገር ውስጥ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ፋብሪካዎች የሀገር ውስጥ ገበያ ላይ በመሰማራታቸው ወደ ዓለም ገበያ ከመግባት አኳያ ክፍተቶች ያሉ መሆኑን አመልክተዋል አክለውም በቅርቡ ወደ ገበያ እየገቡ ያሉ እንደ ደስታ ጋርመንት አይነት አዳዲስ ፋብሪካዎች መኖራቸውን አስረድተዋል፡፡
ፋብሪካዎች የኤክስፖርት ገበያ ላይ የተሻለ ውጤት እንዲያገኙ የመወዳደር አቅማቸውን በማሳደግ ፣ ዓለም አቀፍ ጥራት የጠበቀ ምርት በማምረት በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚሠሩ ሥራዎች አሉ ያሉት ኃላፊው፤ የቀጣይ 5 ና 10 ዓመታት የስትራቴጂ በማዘጋጀት ፋብሪካዎችን በማሳተፍ ባለድርሻ አካላትም የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ለማድረግ እየተሠራ መሆን አስረድተዋል፡፡
እንደ ኃላፊው ገለጻ፤ በግብዓት አቅርቦት ረገድ ችግር እንዳይገጥም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው፡፡ ለጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ዘርፉ የጥጥ ግብዓት አቅርቦት ትልቁን ድርሻ እንዳለው የሚጠቅሱት ኃላፊው፤ በአፋር አካባቢ የአዋሽ ወንዝ ባስከተለው ጎርፉ በ 7 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የነበረ የ26 ባለሀብቶች የጥጥ እርሻ ወድሟል። በውድመቱም 500 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ ያጋጠመ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በቅርቡ በአዋሽ ወንዝ ሙላት ምክንያት የጥጥ እርሻቸው ለወደመባቸው ባለሀብቶች መንግሥት ተከታታይነት ያለው ድጋፍ ይሰጣል ያሉት ኃላፊው፤ በቅርቡም የደረሰውን ጉዳት አጥንቶ ለመንግሥት ሪፖርት የሚያቀርብ ቡድን ወደ ስፍራው የሚሰማራ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ ባለሀብቱን በማቋቋም ረገድ የተለያዩ ድጋፎች በመስጠት ታቅዶ እንቅስቃሴ የተጀመረበት ሁኔታ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ጎርፉ ባደረሰው ኪሳራ የጥጥ ግብዓት ከውጭ በማስገባት በመጠቀም ችግሩን ለመቅረፍ ጥረት እንደሚደረግ የጠቆሙት ኃላፊው፤ በቀጣይ የግብዓት አቅርቦት እጥረት ሊያስከትል የሚችል መሆኑን አመልክተዋል፡፡ ለዚህም የጨርቃ ጨርቅ ዘርፉ ግብዓት ከሚያቀርቡ አቅራቢ ድርጅቶች ጋር በቅንጅት የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አዲስ ዘመን መስከረም 18/2013
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የበረሃ አንበጣን ለመቆጣጠር እየሰሩ ላሉ የፌደራል ተቋማት ምስጋና አቀረቡ
**********
(ኢ.ፕ.ድ)

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በአንዳንድ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ጉዳት እያደረሰ ያለውን የበረሃ አንበጣ ለመቆጣጠር ከክልሎች ጋር በትብብር እየሰሩ ላሉ የፌደራል ተቋማት ምስጋና አቀረቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፦

"በሀገር ደረጃ ዓለም አቀፉን የጤና ቀውስ እንዲሁም በርካታ የተፈጥሮ አደጋዎችን ለመቋቋም እየተረባረብን ነው፤ በዚህ ወቅት፣ ከክልል አቻዎቻቸው ጋር ተባብረው የበረሃ አንበጣን ለመከላከል በከፍተኛ ጥረት ላይ ለሚገኙት የፌደራል ተቋማት ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ" ብለዋል
አሜሪካ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረገች
******************
(ኢ ፕ ድ)
የአሜሪካ መከላከያ ሰራዊት ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት 2 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዶላር ግምት ያላቸው የተለያዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገች፡፡
ይህ ድጋፍ ሰራዊቱ በቀጠናው የሚስተዋለውን ሽብርተኛነትንና የአልሸ ባብን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር እያደረገው ላለው ጥረት የሚያግዝ መሆኑን በአዲስ አበባ የአሜሪካን ኤንባሲ አስታውቋል፡፡
ድጋፍ የተደረጉት ቁሳቁሶችም አምቡላንስ፣ የጭነትና የነዳጅ ማጓጓዣ ተሸከርካሪዎች፣ ለኦፕሬሽን ማዕክል የሚያገለግሉ ዘመናዊ ኮምፒተሮች፣ የሰራዊቱ መንቀሳቀሻ መኪናና ሌሎች ናቸው ተብሏል፡፡
ይህ ድጋፍ የአሜሪካ ሰራዊት ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጋር ሽብርተኝነትን ለመከላከል በጋራ እየሰሩ እንዳሉ የሚያሳይ መሆኑንም ኤንባሲው አስታውቋል።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚፈጸሙ ጥቃቶች በክልሉ የመንግስት መዋቅር ክፍተት መሆኑ ተገለጸ
************************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ:- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚፈጸሙ ጥቃቶች በክልሉ የመንግስት መዋቅር ክፍተት እና በአንዳንድ አመራሮች ችግር ምክንያት መሆኑን የአማራ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት በበኩሉ ችግሮችን ለይቶ እርምጃ መውሰዱን ገልጿል።
የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ትናንት ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመንግስት መዋቅር ክፍተት አለ ፤ ይህንን ክፍተት የክልሉ መንግስት በአቋም ደረጃ ወስዶ አልሰራበትም። በዚህም ምክንያት በአማራና በአገው ብሄረሰቦች ላይ ጥቃት ሊደርስ ችሏል።
ለችግሩ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ዘላቂ መፍትሄ እየተሰጠ አይደለም፤ እሳት የማጥፋት ስራ ነው እየተሰራ ያሉት አቶ ግዛቸው፤ ከዘላቂ መፍትሄ አንጻር ከክልሉ አመራሮች ጋር በመድረክ ስምምነት የተደረሰበት አማራው፣ አገው እና ሁሉም ዜጋ በአፈጻጸሙና በብቃቱ ተመርጦ በየአካባቢው መደራጀትና የአካባቢውን ጸጥታ መጠበቅ እንዳለበት አመልክተዋል።
“የክልሉ መንግስት አመራሮች በመድረክ ደረጃ የሌላውን ብሄር አደረጃጀት በመዋቅር ውስጥ ለማስገባት ፈቃደኛ ናቸው፤ ምክንያቱም ችግሩ የጋራ ነውና፤ ግድያው አማራን እና አገውን አነጣጥሮ ቢፈጸምም አልተባበር ያለውን ጉሙዝን እና ሺናሻንም ያካተተ ነው ጥቃት አድራሹ ጽንፈኛ ቡድን የክልሉን መንግስትም አዳክሞ ወደ ስልጣን የመምጣት ፍላጎት ያለው እንደሆነም አመልክተዋል።
“የቤኒሻንጉል ጉሙዝ መንግስት ይሄንን ያውቃል። ስለዚህ ይሄን አልቀበልም አይልም፤ ችግሩ ያለው ቁርጠኛ ሆኖ መፈጸም ላይ ነው፤ ይሄ ደግሞ የሆነው መሃላቸው ላይ የዚህ ጽንፈኛ አመለካከት ተጋሪዎች ስላሉ ነው። ይሄንን ማረም አለባቸው” ብለዋል።
አማራ እና አገውን ከሚሊሻ፣ ከቀበሌና ከወረዳ አደረጃጀት ውስጥ ያገለለ ነው ያሉት አቶ ግዛቸው፤ በዚህም ምክንያት የጥቃቱ ሰለባ የሚሆኑ ወገኖች ራሳቸውን የመከላከል አቅም እንዳጡ አመልክተዋል።
በአማራና በአገው ብሄር ተወላጆች ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት መድረሱን ያስታወሱት አቶ ግዛቸው በሰሞኑ ጥቃት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የአማራ ክልላዊ መንግስት የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
ከአጭር ጊዜ መፍትሄ አንጻር በጥቃቱ ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ የማድረግና የማረጋጋት ስራ እየተሰራ መሆኑን ያነሱት ዳይሬክተሩ፤ በዚህም አስፈላጊው የእለት ደራሽ ሰብአዊ ድጋፍ እየቀረበላቸው መሆኑን አስታውቀዋል።
በጉዳይ ዙሪያ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ መለሰ በየነ በበኩላቸው፤ “የተፈጠረው ችግር ሁላችንንም አሳስቦናል፤ በእኛ መዋቅር ድክመት የተፈጠረ ችግር ነው፤ ያንን ችግር እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በአብሮነት በጋራ መፍታት እና በጀመርነው ልክ መሄድ አንድ መፍትሄ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
ቀደም ብሎ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የክልሉን መዋቅር መልሶ የማየትና የማስተካከል ስራ መከናወኑን የገለጹት አቶ መለሰ፤ በሁሉም ወረዳዎችና ዞኖች ላይ የአመራር ሁኔታ ተፈትሾ ፤ በሂስና በግለ ሂስ ውጤት መሰረት ከሃላፊነት የሚነሱት በሙሉ ተነስተዋል፤ በህግ የሚጠየቁም አመራሮች ተለይተዋል ብለዋል።
“ጥቃቱን እያደረሱት ያሉት የትኛውንም ማህበረሰብ የማይወክሉ ሽፍታዎች ናቸው፤ እነዚህን ሽፍታዎች ደግሞ በጋራ በመሆን የመደምሰስ ስራ ይሰራል፤ አሁንም በተጨባጭ እየተካሄደ ያለው ይሄው ነው” ያሉት አቶ መለሰ፤ የችግሩ ዘላቂ መፍትሄ የጋራ ልማት ማከናወን መሆኑን በማንሳት፤ ከዚህ አንጻር ሁለቱ ክልሎች የጋራ የልማት ትብብር እንዳላቸው አመልክተዋል።
የሁለቱ ክልሎች የ3 ዓመት የጋራ የልማት ፕሮጀክት ይፋ ሆኗል፤ ይሄንን በይበልጥ ለማጠናከር የጋራ ጽ/ቤትና መዋቅር ለማቋቋም ስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል።
ከአደረጃጀት አንጻር የእኛ ክልል ምሳሌ መሆን የሚችል ነው፤ የአማራ ብሄረሰብ በሚበዛባቸው አካባቢዎች ከቀበሌ ጀምሮ የመዋቅሩ አካል የሚሆኑበት አሰራር አለ ያሉት አቶ መለሰ፣ በክልል ደረጃም ከህዝቡ ቁጥር አንጻር እየታየ በመዋቅር ውስጥ የሚሳተፉበት አሰራር ተግባራዊ እንደሆነ አመልክተዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት በትናንትናው እለት በ45 የክልሉ አመራሮች ላይ እርምጃ መውሰዱ ታውቋል። ከነዚህም ውስጥ አስሩ አመራሮች በህግ እንዲጠየቁ ተወስኗል።
አዲስ ዘመን መስከረም 19/2013
የፌዴራል ፖሊስ ነገ መስከረም 20 ቀን በመስቀል አደባባይ በሚያካሂደው ትርኢት ሳቢያ ለትራፊ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች
ነገ መስከረም 20 ቀን 2013 ዓ/ም ከጠዋቱ 1፡30 እስከ 6፡30 ሰዓት በመስቀል አደባባይ የመንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የፌዴራል ፖሊስ የሰልፍ ትርኢት ይካሄዳል፡፡
በዚህመሰረት
• ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ኦሎምፒያ አደባባይ
• ከመገናኛ፣በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኒያለም፣በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያ አካባቢ
• ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባሻ ወልዴ ችሎት ወይም ፓርላማ መብራት
• ከቸርችል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ አገር አስተዳደር መብራት ወይም ኢሚግሬሽን መ/ቤት አካባቢ
• ከተክለሀይማኖት በሜትሮሎጂ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ
• ከተክለሀይማኖት፣በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣ኢሚግሬሽን ጥቁር አንበሳ የኋላ በር
• ከጌጃ ሰፈር፣ጤና ጥበቃ፣ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ
• ከሳሪስ በጎተራ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር አካባቢ
• ከጦር ኃይሎች፣ልደታ፣ፖሊስ ሆስፒታል ሜክሲኮ አደባባይ
• ከጦር ኃይሎች፣ልደታ፣ፖሊስ ሆስፒታል፣ሜክሲኮ፣ለገሀር መብራት የሚወስደው ለገሃር መብራት
የይለ ፍፈቃድ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ዝግ መሆኑን አሽከርካሪዎች ተገንዝበው የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን አስተላልፏል፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር ሁለት የግል ትምህርት ቤቶችን አገደ
*************************
(ኢ ፕ ድ)
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን የክፍያ መመሪያ ተላልፈው የተገኙ ሁለት የግል ትምህርት ቤቶች ለግዜው መታገዳቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
እገዳው የተላለፈባቸው ትምህርት ቤቶች አንድነት ኢንተርናሽናል እና ሄሌኒክ-ግሪክ ማህበረሰብ ት/ቤት ናቸው፡፡
በትምህርት ቤቶቹ ላይ ውሳኔ የተላለፈው ትምህርት ቤቶቹ የተቀመጠውን መመሪያ ተግባራዊ ባለማድረጋቸው የወላጅ ኮሚቴዎች ተደጋጋሚ አቤቱታ በማቅረባቸው መሆኑም ተገልጿል፡፡
ትምህርት ቤቱ ከዛሬ ጀምሮ መንግስት( ትምህርት ሚኒስቴር) ያወጣውን መመሪያ ከወላጅ ኮሚቴ ጋር በመነጋገር ፈጥኖ ሪፖርት እስኪያደርጉ ድረስ ትምህርት ቤቶቹ ምንም አይነት የትምህርት ስራ እንዳይሰሩ መታገዳቸውን ተገልጿል፡፡
የኢሬቻ በዓልን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር የተለያዩ ዝግጅቶችን እያደረገ መሆኑን በአዲስ አበባ ከተማ የኦሮሚያ ወጣቶች ማህበር አስታወቀ
**************************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ የኢሬቻ በዓልን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር የተለያዩ ዝግጅቶችን እያደረገ መሆኑን በአዲስ አበባ ከተማ የኦሮሚያ ወጣቶች ማህበር አስታወቀ።
ማህበሩ በበአሉ ዋዜማና በእለቱ በአዲስ አበባ ከተማ የፀጥታ ማስከበር ስራዎችን እንደሚያከናውንም ዛሬ በአዲስ አበባ በተደረገ የውይይት መድረክ ላይ አስታውቋል።
የማህበሩ ሰብሳቢ ወጣት ባጫ ጂሬኛ በዚሁ መድረክ ላይ ባደረገው ንግግር፤ ማህበሩ ከ68 ሺህ በላይ አባላት ያሉትና ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ አደረጃጀቱን በማጠናከር በልማት ስራዎች ላይ አበክሮ ሲሳተፍ መቆየቱን ገልጿል።
"ወጣቶች የሀገሪቱ የማህበረ-ኢኮኖሚው ዋልታ በመሆናቸው መደራጀታቸው የራሳቸውን ችግር ከመፍታት አልፈው ለሀገር ችግር ቁልፍ መፍቻ ናቸው" ሲል ተናግሯል።
በአሁኑ ሰዓትም ማህበሩ በአዲስ አበባ ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር በመሆን እየሰራ እንደሆነ የገለጸው ሰብሳቢው፤ የዘንድሮውን የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓልን በሰላማዊ መንገድ ለማክበር በእነሱ በኩል አሰፈላጊው የቅድመ ጥንቃቄ ዝግጅት ስራዎች መሰራቱን አስታውቋል።
ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ በማያደርግ መልኩ የገዳ አባቶች በሚያስቀምጡት አቅጣጫ መስረት በአሉ እንደሚከበርም ነው የእለቱ መድረክ ተሳታፊዎችም ያስታወቁት፡፡
በውይይት መድረኩም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ አባ ገዳዎችና ወጣቶች መገኘታቸውን ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በወንድማሸኝ አሸብር
ምርጫ ቦርድ ለ6ተኛው አገራዊ ምርጫ እያደረገ ያለውን ዝግጅት ለሚዲያ አካላት ሊያስጎበኝ ነው
*******************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ6ተኛው አገራዊ ምርጫ ኦፕሬሽን እያደረገ ያለውን ዝግጅት ለሚዲያ አካላት ሊያስጎበኝ ነው።
ቦርዱ ለሚዲያዎች ባወጣው ጥሪ፤ በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የተመዘገቡ ሚዲያዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ6ተኛው አገራዊ ምርጫ ኦፕሬሽን እያደረገ ያለውን ዝግጅት እንዲጎበኙ ጋብዟል።
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ማናቸው?
በ1922 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ነው የተወለዱት።
ዕድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እትጌ መነን ተምረዋል።
ከ1955 ዓ.ም ጀምሮ በለንደንና በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከፍተኛ ትምህርት ተከታትለዋል። እንዲሁም በመምህርነት አገልግለዋል።
ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ መንግሥታትን በመተቸትና ሂስ በመስጠት የሚታወቁ የፖለቲካ ሰው ናቸው።
ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲን ከመሰረቱት ሰዎች አንዱ ናቸው።
በተለይም ኢህአዴግን ፊት ለፊት በመቃወም ይታወቃሉ።
አንጋፋው ምሁርና የሰብዓዊ መብት ተሟጓቹ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም መጋቢት 7ቀን 2011 ዓም ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ሰፋ ያለ ቆይታ አድርገው ሃሳባቸውን አጋርተዋል።
በፕሮፌሰሩ ህልፈተ ህይወት የተሰማንን ሃዘን እየገለጽን በወቅቱ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ በድጋሜ እንድታነቡት አቅርበናል።
ሊንኩን ተጭነው መረጃዉን ማግኘት ይችላሉ!
https://www.press.et/Ama/?p=6932...
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ለቤተሰቦቻቸው ፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን ተመኝተዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሙሉ መልዕክት ....
"የሐሳብ ልዕልና ምልክት፤ የሰላማዊ ትግል አርአያ፣ ላመኑበት ነገር እስከ መጨረሻቸው ሞጋች፣ ላመኑበት እውነት ብቻ የሚቆሙት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም በማረፋቸው ጥልቅ ኀዘን ተሰምቶኛል። ለቤተሰቦቻቸው ፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን እመኛለሁ"
“የእነ ዶክተር ዐብይ አህመድ ለውጥ የተለየ የሆነው ከነበረው አስተሳሰብ አፈንግጠው መውጣታቸው ነው። ራሳቸውን ነፃ አድርገው በነፃነት ለመምራት መነሳታቸው ከሌሎቹ የተለየ ያደርጋቸዋል”። በየመድረኩ የሚናገሩትም በጣም የሚያስደንቅ ንግግር ሆኖ ነው ያገኘነው። ስለዚህ እነዚህ ሰዎች ችሎታ ያላቸው ከመሆናቸው በላይ ዋናው ነገር ወኔያቸው፤ ራሳቸውን ነፃ አድርገው ሌላውን ነፃ ማድረጋቸው፤ እስረኞችን መፍታታቸውና ሌሎችም ተግባራት አስደሰተኝ”
የኢሬቻ በዓልን ለመረበሽ የተዘጋጁ 503 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
**********
(ኢ.ፕ.ድ)

መስከረም 23 እና 24 የሚከበረውን የኢሬቻ በአል ለመረበሽ የተዘጋጁ 503 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ኮማንደር አራርሳ መርዳሳ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለፁት፤ የኢሬቻ በዓል ላይ የሚሳተፉ የበዓሉ ታዳሚዎች በሰላም ወጥተው እንዲገቡ ኮሚሽኑ በጥብቅ እየሰራ ነው።

የግል ፍላጎታቸውን ለማሳካት በተለያየ አቅጣጫ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ሀይሎች እንዳሉና ኮሚሽኑም እንደደረሰባቸው የገለፁት ኮማንደሩ፤ እስካሁን ድረስ 503 ሰዎች፣14 ክላሽ ፣ 26 ቦምብ እና 103 ሽጉጦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል፡፡

ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የኢሬቻ በዓል በኮረና ምክንያት እንደ ከዚህ ቀደሙ በርከት ባለ ሰው የማይከበር ሲሆን በገዳ አባቶች የተላለፈውን ውሳኔን ህብረተሰቡ ስራ ላይ ማዋል እንዳለበትም ጄኔራል ኮማንደር አራርሳ ተናግረዋል፡፡

ህብረተሰቡ ከፀጥታ ሀይሉ ጋር በመሆን ከህወሓት እና ከሸኔ የተሰጣቸውን ግዳጅ በመውሰድና ኦሮሚያን የጦርነት አውድማ ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ሀይሎችን በማጋለጥ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የስልጣን ጥም ያላቸው አካላት "ከመስከረም 25 በኋላ መንግስት የለም" እያሉ ህብረተሰቡን ለማወክ የሚፈልጉ አካላት በምንም ሁኔታ እንደማይሳካላቸው ጄኔራል ኮማንደር አራርሳ ተናግረዋል፡፡

የኦሮሚያ ፖሊስ የህዝቡን ሰላም የሚያውኩትን በመከታተል ህግ ለማስከበር በቁርጠኝነት መዘጋጀቱንም ኮማንደሩ አስታውቀዋል፡፡

በሐይማኖት ከበደ
በእንጦጦ ጫካ ለአመታት እንጨት በመልቀም ኑሯቸውን ሲገፉ የኖሩ ሴቶች በእንጦጦ ፓርክ ውስጥ አዲስ ስራ እንደተፈጠረላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አስታወቁ
**************************
(ኢ ፕ ድ)
በእንጦጦ ጫካ ለአመታት እንጨት በመልቀም ኑሯቸውን ሲገፉ የኖሩ ሴቶች በእንጦጦ ፓርክ ውስጥ አዲስ ስራ ተፈጥሮላቸው እየሰሩ መሆናቸውን የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ገጻቸው ላይ፤ "ጠንካራዎቹ የእንጦጦ ሴቶች ከአዳዲሶቹ ሥራዎቻቸው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ" በሚል ከምስል ጋር ባሰፈሩት መልዕክት እንዳሉት፤ የእንጦጦ ሴቶች ለዓመታት ወገብ ከሚያጎብጥ የማገዶ እንጨት ለቀማና ሸክም ተሠማርተው ኖረዋል፡፡
እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፤ አሁን ግን በእንጦጦ ፕሮጀክት አማካይነት በመቶዎች የሚቆጠሩት ሠልጥነው በአዲሱ መናፈሻ ውስጥ ለተከፈቱ ንግድ ሥራዎች በግብዓት አቅራቢነት ተደራጅተዋል፡፡
ዶ/ር አብይ በመልዕክታቸውም፤ "ትራንስፎርሜሽን በሂደቱ ውስጥ ሌሎችን ማንሣትን ይጠይቃል" ሲሉ ተናግረዋል።
ሁለተኛው የኢሬቻ ፎረም በሸራተን አዲስ በመካሄድ ላይ ነው
***********************
(ኢ ፕ ድ)
ሁለተኛው የኢሬቻ ፎረም በሸራተን አዲስ ሆቴል በመካሄድ ላይ ነው።
በፎረሙ ላይም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፣የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ዲፕሎማቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡
በፎረሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እንደተናገሩት፤ የኦሮሞ ህዝብ በብዙ ችግሮች ውስጥ አልፎ ዛሬ ላለበት ድል ደርሷ ብለዋል፡፡
የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ በሆራ ፊንፊኔ እንዲከበር የጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አመራር ከፍተኛ አስተዋፆኦ እንደነበረው ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በኋላ ቀጣዩ ትውልድ የገዳ ስርአቱን እየኖረበት ሊያስተዋውቀውም ይገባል ብለዋል፡፡
በአሉ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ እየተጉ ላሉ አካላት ምስጋናቸውን በማቅረብ ሰላምን ለማደፍረስ የሚጥሩ ቡድኖች መቼም እንደማይሳካላቸውም አስታውቀዋል፡፡
ኢሬቻ ስጋት እንዲሆን የሚፈልጉ አካላት ቢኖሩም የሰላምና የይቅርታ በአል የሆነው ኢሬቻ ግን ስጋት ሊሆን አይችልም ነው ያሉት አቶ ሽመልስ።
ያለፈው አመት የኢሬቻ በአል በሰላም ተከብሮ ማለፉን ያስታወሱት ፕሬዝዳንቱ፤ ዘንድሮ በኮቪድ ምክንያት በውስን ሰው ለማክበር መገደዳቸውን አስታውቀዋል።
በሀይማኖት ከበደ
መጪው መስከረም 30 ቀን 2013 ዓ.ም ብቻ አይደለም የወደፊቶቹም
መስከረሞች በሰላም ይቀጥላሉ፤ የሚያስቆምም የሚገታም ኃይል
የለም፤
👉 ኢትዮጵያ ሰላሟ ተጠብቆ ብዙ መስከረሞችን ታልፋለች፤ መከላከያ
ሠራዊቱ፣ ሕዝቡ፣ ሀገሪቱም ትቀጥላለች፤
👉 አንዳንድ ሰዎች ያልሆነ መልዕክት አስተላልፈዋል በሚል
ኅብረተሰቡ መረበሽ የለበትም፤
👉 ምንም የሚፈጠር ረብሻና ሁከት አይኖርም፤ ሕግና ሥርዓት ተከብሮ
ይቀጥላልም ብለዋል፤
ጀነራል ብርሃኑ ጁላ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም በሰኔ ወር 2012 ዓ.ም ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቆይታ ያስተላለፉት መልዕክት ሲሆን፤ ሙሉ ቃለ መጠይቁን ከታች ካለው ሊንክ ማግኘት ይችላሉ።
https://www.press.et/Ama/?p=34383
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እና ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ በኮሮና ተያዙ
***********
(ኢ.ፕ.ድ)
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እና ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ።
ዶናልድ ትራምፕ የቅርብ አማካሪያቸው በኮሮናቫይረስ መያዟን ተከትሎ እርሳቸው እና ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ የኮሮናቫይረስ ምርመራ አድርገው ውጤቱን በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን ብለው ነበር።
የምርመራውን ውጤቱን ተከትሎ እርሳቸው እና ባለቤታቸው በቫይረሱ መያዛቸውን ዶናልድ ትራምፕ በትዊተር ገጻቸው ላይ ይፋ አድርገዋል።
ኢሬቻ የፍቅር፣ የይቅርታ፣ የምስጋና፣ የሰላም እና የአንድነት በዓል ነው። በሆራ ፊንፊኔ እየተከበረ ባለው የኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ አባገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ የኃይማኖት አባቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።