Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ሞትን አይቼ ተመለስኩ
የ27 ዓመት ወጣት ነኝ፤ በአዲስ አበባ ከተማ ሽሮ-ሜዳ አካባቢ ነው የምኖረው፡፡ አስታውሳለሁ ቀኑ ሰኔ 16 ሐሙስ ዕለት ነው፤ ካለወትሮዬ ምቾት የሚነሳ ስሜት ተሰማኝ፡፡ ቀኑን ሙሉ እንዲሁ ስረበሽ ነበር የዋልኩት፡፡ ማታ ላይ ምግብ ባያሰኘኝም በግድ ቀምሼ ተኛሁ፡፡
እኩለ ሌሊት ብን ብን የሚል ደረቅ ሳል ድንገት ከእንቅልፌ ቀሰቀሰኝ፤ ሰውነቴም በሚነድ እሳት ውስጥ እንዳለ ሆኖ አገኘሁት፡፡ ባኞ ቤት ገባሁና በቀዝቃዛ ውሃ ፊቴን ታጠብኩ ሊበርድ አልቻለም፡፡ አፌ ስለደረቀና ስለመረረኝ በውሃ ተጉመጠመጥኩት፤ እንደማቅለሽለሽ አለኝ፡፡
ተከራይቼ ስለምኖር በወቅቱ አጠገቤ የሚረዳኝ ሰው አልነበረምና እማደርገው አጣሁ፡፡ ቆይቼ ለጓደኛዬ ደውዬ እንደታመመኩ ነገርኩት፡፡ መኪና ይዞ መጣና ወደ አቅራቢያዬ ወደሚገኝ ጤና ጣቢያ ወሰደኝ፤ እነሱም ሁኔታውን አይተው ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ላኩኝ፡፡ የሆስፒታሉ ሃኪሞችና ነርሶች ተረባረቡና አስገቡኝ፡፡ ወዲውኑ ምርመራ ታዞልኝ ናሙና እንድሰጥ ተደረገ፡፡ ትኩሳቱ እየጨመረ መጣ፤ አጠገቤ የሚረዱኝን የጤና ባለሙያዎች ጭምር የሰውነቴ ግለት ይታወቃቸው ነበር፡፡ ቀስ በቀስ እየደከመኝ እየደከመኝ መጣ፡፡
የምርመራ ውጤቴ ደረሰ፤ ውጤቱም የኮሮና ቫይረስ በሽታ መሆኑ ተረጋገጠ፡፡ ከዚያ በኋላ የሆንኩትን ሁሉ በውል አላቀውቅም ነበር፡፡
ከ7 ቀናት በኋላ ከሰመመን ስሜቴ ወጥቼ ራሴን ሳውቅ በአፍንጫዬ ቱቦ እና በእጄ ላይ ደግሞ ግሉኮስ ተተክሎልኛል፤ በዙሪያዬ ደግሞ መላ አካላቸውን በተሸፈኑ ጤና ባለሙያዎች ተከብቤ አገኘሁት፡፡ ድንጋጤ አይሉት የመረበሽ ሰሜት ተሰማኝ፤ ከአጠገቤ የነበረ ሃኪም ሊያረጋጋኝ ሞከረ፡፡ አይኖቼ በእምባ ተሞሉ፡፡
ቀስ በቀስም ራሴን እያወቅሁ ስሄድ ወደኋላ እንደህልም ያየሁትን ማስታወስ ጀመርኩ፤ ነጭ የለበሱ የለበሱ ሰዎች አጅበውኝ ይዘውኝ ሲሄዱ ያየሁት ታወሰኝ፡፡ ሰፊ አዳራሽ ያለው ዙሪያ ገባው በአበቦች ያጌጠ ውብ ቦታም ይታወሰኛል፡፡ እንዲህ አይነት ስፍራ በምድር ላይ ስለመኖሩ እጠራጠራለሁ፤ ምንድን ነው ነገሩ ብዬም ራሴን ጠየኩ፡፡
በተደረገልኝ ህክምናና እንክብካቤ ራሴን በደንብ እያወኩኝ ስመጣ ያ ያየሁት ነገር በሞትና በህይወት መካከል የነበርኩበትን ወቅት በማስታወስ ላይ እንደነበርኩ ተረዳሁ፡፡ ሳልሞት ሞትን አይቼ እንድመለስ የረዳኝን ፈጣሪ እጅግ አድርጌ አመሰግነዋለሁ፡፡
እኛ የምናውቀው በሽታ ሲያመን ሰው እንዳያስታምመንና እንዳይጠይቀን እስከ መከልከል የሚያደርስ አልነበረም፡፡ ኮሮና ግን የተለየ ነው፤ ቤተሰብ እንኳ ከጎኔ ሆኖ እንዲያስታምመኝ ያለፈቀደልኝ ጨካኝ በሽታ ነው፡፡
ከምንም በላይ ግን የህክም እርዳታና እንክብካቤ ያደረጉልኝን የጤና ባለሙያዎች በእጅጉ ላመሰግናቸው እወዳለሁ፤ በህይወት ዘመናቸው ሁሉ ክፉ አይንካቸው፡፡
ቀድሞ ያልታዬኝ ስህተቴ አሁን ላይ ቁልጭ ብሎ ታይቶኛል፤ ለበሽታው የነበረኝ ግዴለሽነት ዋጋ አስከፍሎኛል፡፡ እኔ እድሉን አግኝቼ ታክሜ መዳኔ ቢያስደስተኝም አሁን ላይ ጤና ተቋማት ወደ መጨናነቅ ደረጃ እየደረሱ መሆኑን ስሰማ በእጅጉ አሳዝኖኛል፤ ችግሩን ቀምሸዋለሁና፡፡ እናም ወገኖቼ ከእኔ ተማሩ፤ በተቻለ መጠን ጥንቃቄ በማድረግ ከኮሮና በሽታ ራሳችንና ቤተሰባችንን እንጠብቅ መልዕክቴ ነው፡፡
(ከኮሮና ቫይረስ በሽታ ያገገመ ግለሰብ ታሪክ፤ ስሙ በግል ጉዳዩ ምክንያት ያልተጠቀሰ)
በክፍል ውስጥ የተማሪዎችን ቁጥር በመመጠንና ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም ትምህርት ለማስጀመር ጥናት ተደርጓል - አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ የትምህርት ሚኒስተር ዴኤታ
*****************************
(ኢፕድ)
ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሊያጋልጥ በማይችልና ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ የመማር ማስተማር ሂደቱን በአዲሱ ዓመት ለማስጀመር ጥናት መደረጉን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ እንዳለው በአንድ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎችን ቁጥር በመመጠንና ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም ትምህርት ማስጀመር በሚቻልበት መንገድ ላይ ጥናት ተደርጓል።
የትምህርት ሚኒስተር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ የ2013 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ መጀመሩን አመልክተዋል።
ኮሮናቫይረስ በፖለቲካ፣ በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ ዘርፍ በሳደረው ጫና ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ውጭ እንዲሆኑ መደረጉንም አስታውሰዋል።
አቶ ሚሊዮን እንዳሉት ትምህርት መቋረጡ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመግታት አስተዋፅኦ ቢኖረውም በተማሪዎች በተለይም ከህጻናት እድገት አንጻር ከፍተኛ ጫና አሳድሯል።
በተለይ ህጻናት ትምህርት ዝግ ሆኖ ቤት በመዋላቸው ለአስገድዶ መደፈርና ያለዕድሜ ጋብቻ መዳረጋቸውን ሚኒስቴር ዴኤታው ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ባሉ ከ42 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች ከ700 ሺህ በላይ መምህራንና ከ26 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ይገኛሉ።
“ወቅቱ ኮሮናቫይረስ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ያለበት በመሆኑ ትምህርት ቤቶች መከፈታቸው ህብረተሰቡን እያነጋገረ ነው” ያሉት አቶ ሚሊዮን፣ ወረርሽኙ የሚቆምበት ጊዜ ባለመታወቁ ትምህርት እንደሚጀመርና ይህም የጤና ጥበቃ የሚያስቀምጠውን መስፈርት ተግባራዊ በማድረግ እንደሚከናወን ገልጸዋል።
ባለፈው የመማር ማስተማር ሂደት በአማካይ ከ60 እስከ 80 ተማሪዎች በአንድ ክፍል ውስጥ ይማሩ የነበረበት ሁኔታ እንደነበር አቶ ሚሊዮን አስታውሰዋል።
በቀጣይ ትምህርት ሲከፈት በቅድመ መደበኛ 14 በመቶ የሚሆኑትን ትምህርት ቤቶች ከ20 እስከ 25 ተማሪዎችን ብቻ በአንድ ክፍል እንዲያስተምሩና አንድ ተማሪ በአንድ ዴስክ ብቻ እንዲቀመጥ ለማድረግ መታቀዱን አስረድተዋል።
አቶ ሚሊዮን እንዳሉት ቀሪዎቹ 80 በመቶ ተማሪዎች በፈረቃ እንዲማሩና 6 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ደግሞ ትምህርት ቤት በመገንባትና አማራጭ ማህበራዊ ተቋማትን በመጠቀም ለማስተማር ታቅዷል።
በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 24 በመቶ ወይም ከ20 እስከ 25 ተማሪዎች በአንድ ከፍል ውስጥ እንዲማሩ፣ 56 በመቶ በፈረቃ እንዲሁም 20 በመቶ ተጨማሪ ክፍል በመገንባት እንዲማሩ ተወስኗል።
በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 19 በመቶ ተማሪዎች ወይም ከ20 እስከ 25 የሚሆኑት በአንድ ክፍል ውስጥ እንዲማሩ እንዲሁም 50 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ በፈረቃ የሚማሩ ይሆናል።
ሌሎች 31 በመቶ ተጨማሪ ክፍሎችን በመገንባትና አማራጭ ማህበራዊ ተቋማትን በመጠቀም ለማስተማር መታቀዱንም አመልክተዋል።
በሽታን በመከላከል የትምህርት ተቋማትን ስራ ለማስጀመር ተቋማቱን ማስፋት እንደሚገባም አቶ ሚሊዮን ተናግረዋል።
ኦሮሚያ ክልል ሃብት በማሰባሰብ 30 ሺህ አዳዲስ ክፍሎችን መገንባቱን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው፣ “አማራ ክልልም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ያለውን የክፍል እጥረት ችግር ለመቅረፍ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው” ብለዋል።
ተማሪዎች በተረጋጋ ሁኔታ እንዲማሩ የቀደመው የመማር ማስተማር ስልት በአዲስ መልክ እንደሚሆን ጠቁመው፣ ይህም የቡድን ስራን ጨምሮ የተማሪዎችን አካላዊ ንክኪን ሊያስቀር በሚችል መልኩ እንደሚሰጥ ተናግረዋል።
አቶ ሚሊዮን እንዳሉት የትምህርት ቤቶች አከፋፈት ጥናቱን መሰረት ያደረገ ይሆናል።
ትምህርት ቤቶች በተመሳሳይ ወቀት አንድ ላይ ሊከፈቱ እንደማይችሉና ደረጃ በደረጃ የመክፈት ሂደት እንደሚኖር ገልጸው፣ አጀማመሩ ከክልል ክልልና ከዞን ዞን ሊለያይ እንደሚችል አመልክተዋል።
ይህንን ተከትሎ አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ጭማሪ እየጠየቁ መሆኑን ገልጸው፣ ይህን በሚያደርጉ ተቋማት ላይ ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ቤቶችን እስከመዝጋት የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድ አመልክተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ጠቅላይ ሚኒስትሬን ላለማመስገን ምክንያት የለኝም፤ አመሰግናለሁ !
በተንቀሳቃሽ ስልኬ የማኅበራዊ ትስስር ገጼን ከፍቼ መረጃ ፍለጋ እጆቼን ከላይ ወደታች እያንሸራተትኩ ድንገት አንድ ተንቃሳቃሽ ምስል እይታዬን ገታው። ያየሁትን በቀላሉ ለማመንም ከበደኝ። ምክንያቱ ደግሞ ያየሁት ሰው ሙሉ ገጽታው በፊት መሸፈኛ ምክንያት ሙሉ ለሙሉ መለየት ቢያስቸግረኝም ድምፁ ግን ቁርጥ እሱን ነው። የእኔን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ።
እኔ ደስም ግርምም ብሎኛል። ይህ በኢትዮጵያ ተደርጎ አላየሁም። ይህንን ብቻ በማድረጉ እኮ ምን ያህል ወደ ህዝብ መቅረብ እንደሚፈልግ መረዳት ይቻላል። ያዩትና ያናገራቸው እንደመዝለልም እንደመደንገጥም አርጓቸዋል። እኔን እንዲህ አጋጥሞኝ ቢሆን ኖሮ ስል አሰብኩ፤ እኔ እንጃ! እጮህ ነበር። ታድያ ይህን ድንቅ መሪ እንዴት ነው አለማመስገን የሚቻለው።
መሪዬ የትራፊክ ፍሰቱ የተሳለጠ ይሆን ዘንድ በአንድ በኩል ሲያስተናብር በሌላ በኩል ደግሞ በፍቅር በተሞላ አንደበት መልካም ዘመንን ለወገኖቹ ሲመኝና የፍቅርም ስጦታ ሲያበረክት ላየ በእርግጥ ልብን በሐሴት ይሞላል። እኔ ሁሌም አንድ ነገር በአገሬ ኢትዮጵያ ይሆን ዘንድ እመኝ የነበረውን ድርጊት በመፈጸሙም ላመሰግነው ወደድኩ። በእርግጥም ብዙዎቻችሁ ልክ እንደ እኔው ተመሳሳይ ግርምታን ሳያጭርባችሁ እንዳልቀረ አስባላሁ።
ወርዶ ጫማ ለመጥረግ በቂ የሞራል ስንቅ ያለው! እንዳለመታደል ሆኖ ነው እንጂ እ ይህን ማን አድርጎ አይተናል? ማንም፤ እንዲያው ግን መመሰጋገን ምን ወጪ አለው? ምንም፤ መልካምና ልብን በሐሴት የሚሞላ ተግባር ለፈጸመ ቢመረንም ቢጣፍጠንም ማመስገንን መልመድ አለብን።
እርግጥ ነው ብዙዎቻችን በልባችን አድንቀን አሊያም ደግሞ ገርሞንም ይሆናል። ነገር ግን አድናቆቱንም ሆነ ምስጋናውን ከአንደበታችን ሲወጣ ድል እንነሳበታልና ይልመድብን። ስናመሰግን እናከብራለን።
እንከበራለን፤ ተመስጋኝም አመስጋኝም ዋጋቸው ከፍ ያለ ነውና።
የአንዳንድ አገር መሪዎች ኧረ እንዲያውም የጥቂት አገር መሪዎች ድንገት በህዝባቸው መካከል በመከሰት የህዝቡን እውነተኛ ስሜት ሲያስተውሉና ወደህዝቡ ወረድ ብለው የልቡን ሲያዳምጡ ሳይ በእጅጉ እቀና እንደነበር አልሸስግም። አንዳንዶቻችሁ ይህ ምን ያስደንቃል ትሉ ይሆናል፤ በኛ ባለ ስልጣናት ስለልቦና ለዚያውም በጠቅላይ ሚኒስትር ደረጃ !
እኔ ጠቅላይ ሚኒስትሬን የትራፊክና የፖሊስን የደንብ ልብስ ለብሶ ሰዎችን ስላናገረ ብቻ ሳይሆን ከዚህ ቀደምም ሲያደርጋቸው በነበሩ ሰው ሰው በሚሸቱ ድርጊቶቹ አለማመስገን አይቻለኝም። ለማመስገን ብዕሬን የቀሰርኩት ባደረጋቸው በርካታ ማህበረሰባዊ ትርጉማቸው ከፍ ባሉ ዘመን ተሸጋሪ ጉዳዮች ነው።
ፖለቲካዊ የሆኑ ነገሮቹን ለጊዜው ወደጎን እናደርጋቸው፤ ስብዕናው ለእኔ ከምገምተው በላይ ነው። በእርግጥም መሪዬን በቅርብ ሆኖ ላየው ፍጹም የሆነ ፈገግታና ትህትና ስለማይለየው ማንንም ቢሆን በዚያ ፍቅሩ መሸነፉ አይቀርም። ከትልልቆቹ ጋር እንደትልቅ፣ ከሕፃናቱ ጋር እንደእነርሱ፣ ከጎዳና ተዳዳሪውም ሆነ ከየትኛውም ሰው ጋር የሚያሳየው ትህትና የሚገርም ነው።
የልብን መዝገብ አንደበት ይተርከዋል እንዲል እኔ ጠቅላይ ሚኒስትሬን እንዲህ አመሰገንኩ። እናንተም አመስግኑ፤ የምስጋና ንፉጋን አትሁኑ እናመስግን፤ በምስጋና አለማመስገንን። በምስጋና ውስጥ በረከትም ኃይልም አለ።
አዲስ ዘመን ጳጉሜን 4/2012
ቅድስት ሶሎሞን ከሽሮ ሜዳ
የኢትዮጵያ የምንጊዜም ባለውለታ የጦር ሜዳ ጀግኖቻችን በያላችሁበት ታላቅ ምስጋና ይደረሳችሁ !!
ለኢትዮጵያ ሀገራችን ባላውለታ ለሆናችሁ በደምና በአጥንታችሁ ክስካሽ ታላቅ መስዋእትነት ከፍላችሁ የተሰነዘረብንን ጥቃት መክታችሁ ኢትዮጵያን በክብር ላስረከባችሁን የኢትዮጵያ ጀግኖች በሙሉ ያለእናንተ ታላቅ ተጋድሎ የዛሬዋን ሀገር አናገኛትም ነበርና በዚህ የምስጋና ቀን የሀገር ባለውለታ ናችሁና ታላቅ ምስጋና ይድረሳችሁ !!
በጠላት ወረራ ዘመን የኢጣሊያን ፋሽስት ወረራ መክታችሁ በዱር በገደል ተንከራታችሁ ያለበቂ ስንቅና ትጥቅ ኢትዮጵያዊ ቁርጠኝነትንና ጀግንነትን ሰንቃችሁ እምቢ ለሀገሬ ብላችሁ ተዋግታችሁ ድል አድርጋችሁ የተፈራች የተከበረች ሀገር ላስረከባችሁን አባቶቻችንና አያቶቻችን በሕይወት ላላችሁትም ለሌላችሁትም ጀግኖች በዚህ የምስጋና ቀን ታላቅ ምስጋና ይድረሳችሁ !!
በሶማሊያ ወረራ ወቅት የእናት ሀገር ጥሪ ሲደረግልህ የእርሻ ማሳህን ጦሙን አድሮ አንተ ሞፈርና ቀንበርህን ሰቅለህ፤ ትዳርህን ልጆችህን ትተህ፤ ቅሌን ማቄን ሳትል ዘምተህ ታላቅ ተጋድሎ በማድረግና መስዋእትነት በመክፈል ኢትዮጵያን ላስከበርካት የቀድሞው የኢትዮጵያ መደበኛ ሰራዊትና የሚሊሽያው ሰራዊት አባላት በህይወት ላላችሁትም ለሌሉትም ያለእናንተ ታላቅ መስዋእትነት ይህችን ውብ ሀገር መረከብ አይቻልም ነበርና በዚህ የምስጋና ቀን ታላቅ ምስጋና ይድረሳችሁ !!
ለኢትዮጵያ የቀድሞውም የአሁኑም የጦር መሪ ጀነራሎች ከፍተኛ መኮንኖች፤ መስመራዊ መኮንኖች፤ ባለሌላ ማዕረጎች፤ ጀግናው ተዋጊ ሰራዊት፤ የኢትዮጵያ የምድር ጦር፤ የአየር ኃይል፤ የባሕር ኃይል፤ የፖለስ ሠራዊት አባላት በሕይወት ላላችሁትም በመስዋዕትነታችሁ ታላቅ የተከበረች ሀገር ላስረከቡንም ጀግኖች፤ ኢትዮጵያን በደማችሁ አጽንታችሁ ላስረከባችሁን ውድ ጀግኖች በዚህ የምስጋና ቀን ለጀግኖቻችን ታላቅ ምስጋና እናቀር ባለን!!
ከመርደቂዮስ
አዲስ ዘመን ጳጉሜን 4/2012
ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ አዲስ አመትን አስመልክተው ካስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ከተናገሯቸው የተወሰዱ፤
- ምንም ያልተነካ አንድ ዓመት ሙሉ ከፊታችን አለን፤ብልህ ይመጥቅበታል ሞኝ ይወድቅበታል እኛ ግን ከብልሆዎች ወገን ልንሆን ይገባል፤
- ባገኘናቸው ድሎች ረክተን አንቀርም ባሳለፍናቸው ድሎች ታስረን አንቆምም ወደ ልዕልና እንመጥቃለን፤
“መምጠቅ ወደ ከፍታ መዝለቅ ነው፤ ልክ እንደ መንኩራኩር፣ ልዕልና ከከፍታ ይለያል ክብር አለው፤ በቀላሉ ከሚደረስበት መዳረሻ ወደላይ እጅግ መላቅን ይፈልጋል፤
- እንመጥቃለን ገና ወደ ልዕልና ስንል መታፈርና መከበር ወዳለው ከፍታ እንደ ምድር ስበት የሚስቡን ችግሮቻችንን አልፈን ለዚህ በተዘጋጁ እና በቆረጡ መጣቂዎች እና ባዘጋጀነው የ10 ዓመት ፍኖተ ብልፅግና መንኩራኩርነት ህብረ ብሄራዊነት በተሰኘ ማምጠቂያ ስፍራ ብልፅግና ወደተባለ ደርሰንበት ወደ ማናውቀው የመንፈስ፣ የቁስ እና የኢኮኖሚ ከፍታ እንመጥቃለን ማለታችን ነው”
- 2012 በደስታና ሀዘን፣ በክብርና ውርደት፣ በኩራትና ሀፍረት የተሞላ ዓመት ነበር፤
-የኢትዮጵያ ፈታኞች አሉን ያሉትን ድንጋዮች ሁሉ ወርውረዋል፤ ሆኖም የኢትዮጵያ ጀግኖች የቻሉትን ሁሉ ለሀገራቸው ሰውተዋል፤ ትርፍ ነብስ ያላቸው እስከሚመስል በጀግኖቿ ብርታት መከራውን ሁሉ አልፋ ኢትዮጵያችን ዛሬም አለች፤
- ኢትዮጵያ ጨለማ የማይበግራት የብርሃን ሀገር፣ የብርቱ ህዝብ የፅኑ ዜጋ ሀገር ናት፤
-ወደ ብልፅግና ማማ ሊያወጣ ራእይ የሰነቀው፣ ከፋፋይ እና ኋላ ቀር አስተሳሰቦችን በፍቅር እና በመተባበር የተካው፣ ሀገሪቱን ወደሚገባት ከፍታ ሊያወጣት የሰነቀው ብልጽግና ጥይት እንኳን ኮሽ ሳይል የነበረውን አሮጌ አስተሳሰብ አስወግዶ የተወለደው በዚህ ዓመት ነበር፤
- ከጨለማ በኋላ ብርሃን፣ ከፈተና በኋላ ተስፋ፣ ከመለያየት በኋላ መገናኘት፣ ከውድቀት በኋላ መነሳት አለ፤
- ከዘመን ወደ ዘመን የምናደርገው ሽግግር ትርጉም እንዲኖረው ካለፈው ዘመን ጋር አሮጌና ጎታች አስተሳሰባችንን ተሰናብተን አዲስ እና ተራማጅ አስተሳሰብን ልንላበስ ይገባል፤
- የፖለቲካ አሰራራችንን እና ባህላችንን በቅንነት ለማሻሻል፣ በመካከላችን የፈጠርነውን የልዩነት አጥር ለማፍረስ፣ የመለያየትን ገደል ለመሻገር ምን ያህል ተዘጋጅተናል፤
- መጪው ዓመት ስላለፈው የምንቆዝምበት፣ ስላለፈው ቂም ቋጥረን በቀልን የምናስብበት ሳይሆን በይቅርታ እና በእርቅ ሰላምን አውርደን በመተሳሰብና በመደማመጥ ልዩነታችንን አጥብበን ህዝባችንን እና ሀገራችንን በማስቀደም ወደ ልዕልና የምንመጥቅበት እንዲሆን ሁላችሁንም እጋብዛለሁ፤
----
ፍርድ ቤቶች በመስከረም ወር በከፊል ዝግ ሆነው ይቆያሉ ተባለ
***********
(ኢ.ፕ.ድ)

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በመስከረም ወር 2013 ዓ.ም በከፊል ዝግ ሆነው እንደሚቆዩ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

ይህም ፍርድ ቤቶች የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል ከመጋቢት 10 - እስከ ሐምሌ 10 ቀን 2012 ዓ.ም በከፊል ዝግ ሆነው ከቆዩበት ሁኔታ ለመውጣትና ተቋርጠው የነበሩት አገልግሎቶችን ደረጃ በደረጃ ለማስጀመር ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሐምሌ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ባወጣው መመሪያ መሰረት ዳኞች በመስከረም ወር እረፍት አንዲያደርጉ በመወሰኑ ነው ተብሏል፡፡

ዳኞች ዓመታዊ እረፍታቸውን በነሃሴ እና በመስከረም ወር የሚወስዱ በመሆኑ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አስቸኳይነት ያላቸውን ጉዳዮች ብቻ በተረኛ ችሎቶች በማስተናገድ በከፊል ዝግ ሆነው እንደሚቆዩ ማድረግ የተለመደ አሰራር መሆኑን ያስታወሰው ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በዚህ ዓመት ዳኞች አጭር የእረፍት ጊዜ እንደሚኖራቸው ገልጿል፡፡

ከፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ እንዳመለከተው ፍርድ ቤቶቹ በከፊል ዝግ ሆነው በሚቆዩባቸው የመስከረም ወር 20 የስራ ቀናት አስቸኳይና ጊዜ የማይሰጡ ከዜጎች መሰረታዊ መብቶች እንዲሁም ከአገር ሰላምና ፀጥታ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ጉዳዮች እንደሚመለከቱ ተገልጿል፡፡

ለአብነትም እንደ የጊዜ ቀጠሮ፣ የዋስትናና የዕግድ ጥያቄዎች፣ የመያዣና የብርበራ ትዕዛዞች፣ በተፋጠነ ስነ-ስርዓት የሚታዩ የእጅ ከፍንጅ ወንጀሎች እንዲሁም ከቤተሰብና ከሕፃናት ቀለብና አስተዳደግ ጋር የተያያዙ አጣዳፊ መሰረታዊ ጉዳዮች በተረኛ ችሎቶች የሚስተናገዱ መሆኑ ተነግሯል፡፡

የአዲሱ ዓመት የመጀመሪያው ወር ለዳኞች የእረፍት ጊዜያቸው አንዲሆን የተወሰነ ቢሆንም በፍርድ ቤቶች የተለመደ አሰራር አብዛኛዎቹ ዳኞች በፈቃዳቸው ውዝፍ መዛግብትን በማጥራት ስራ ላይ ይቆያሉ።
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሥራ አስፈጻሚ የድርጅቱን ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳን ከፓርቲው ማገዱን አስታወቀ
**********************-
(ኢ.ፕ.ድ)

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሥራ አስፈጻሚ የድርጅቱን ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳን ከፓርቲው ማገዱን አስታወቀ።

የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ቀጀላ መርዳሳ ዛሬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ አቶ ዳውድ በፓርቲው አንድነትና ሰላማዊ ትግል ላይ እየፈጠሩት የነበረውን ችግር ለመቅረፍ ተደጋጋሚ ጥረቶች ቢደረጉም ያሉባቸውን ችግሮች ከማስተካከል ይልቅ ፓርቲውን የመከፋፈልና አንጃ የመፍጠር አካሄዶችን ሲከተሉ ቆይተዋል። በመሆኑም ለፓርቲው ህልውናና ጥንካሬ ሲባል የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አቶ ዳውድ ኢብሳን ከፓርቲው አግዷቸዋል።

በቀጣይ በፓርቲው ህገ ደንብና አሰራር መሰረት የሚከናወኑ ተግባራት መኖራቸውን ያስታወቁት አቶ ቀጃላ፤ ሁሉንም ሂደቶች በተመለከተ ፓርቲው ለምርጫ ቦርድ አስፈላጊውን ሰነድና መረጃ ማስገባቱን አስታውቀዋል።

አቶ ዳውድ ላለፉት 20 አመታት በፓርቲው ላይ ተደጋጋሚ አደጋ መደቀናቸውን የተናገሩት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው፤ ቀደም ባሉት አመታት ሶስት ጊዜ ለፓርቲው መከፋፈል ዋናው ምክንያት እርሳቸው እንደነበሩና አሁንም ለአራተኛ ጊዜ ፓርቲውን ለመከፋፈል አንጃ ፈጥረው ሲንቀሳቀሱ ይተዋል። ይህንን ለማስተካከል ጥረት ሲደረግም በተጨባጭ የፓርቲውን ንብረትና ገንዘብ ወደግላቸው የማዘዋወር እንቅስቃሴ ውስጥ ገብተዋል። ስለሆነም ፓርቲውን ለመታደግ ሲባል እርምጃው ተወስዶባቸዋል።

አቶ ዳውድ በፓርቲው ውስጥ ችግር መፍጠር የጀመሩት ከሀምሌ ወር ጀምሮ እንደነበር የተናገሩት አቶ ቀጀላ፤ ችግሩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት ቢደረግም በእርሳቸው በኩል ችግሩን ለመፍታት ባለመተባበራቸው ፓርቲው ህጋዊ እና ፖለቲካዊ እርምጃ መውሰዱን አስታውቀዋል።

እንደ አቶ ቀጀላ ገለጻ፤ ፓርቲ ከአቶ ዳውድ ጋር ያለው ትልቅ ልዩነት በትግል አካሄድ ላይ ነው። ኦነግ ወደ አገር ቤት ከገባ በኋላ ሰራዊቱ በዓለም አቀፍ አሰራር መሰረት ወደ መንግስት የጸጥታ አካላት እንዲቀላቀል ስምምነት ቢደረግም፤ አቶ ዳውድ ግን በዚህ ላይ ግልጽ አቋም አልነበራቸውም፤ በአንድ በኩል ሰላማዊ ትግሉን ይፈልጋሉ፤ የትጥቅ ትግሉንም በኪስ አድርገው በድብቅ መሄድ ይፈልጋሉ።

በተጨባጭም በምዕራብና በደቡብ ጫካ ውስጥ ካሉ ሰዎች ጋር ግንኙነት ሲያደርጉ ቆይተዋል። ይሄ አካሄድ አግባብ አይደለም በሚል ስራ አስፈጻሚው ሲነጋገርበት ቆይቷል። ምክንያቱም የትጥቅና ሰላማዊ ትግል ድንበር ሊበጅለት ይገባልና ብለዋል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጠቅላላ ጉባዔ ተደርጎ አዲስ መሪ ኣስኪመረጥ ድረስ የድርጅቱ ተወካይና መሪ ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ አራርሶ ቢቂላ እንደሆኑ አቶ ቀጀላ ጠቅሰው፤ በአቶ ዳውድ በኩል እስከዛሬ የነበሩ የዲስፕሊን ጥሰቶችን በተመለከተ ፓርቲው ዝርዝር መግለጫ ማውጣቱን አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ ነባሮቹን የ10፣ የ50 እና የ100 ብር የገንዘብ ዓይነቶች ሙሉ ለሙሉ ለወጠች
**********
(ኢ.ፕ.ድ)
ኢትዮጵያ ነባሮቹን የ10፣ የ50 እና የ100 ብር የገንዘብ ዓይነቶች ሙሉ ለሙሉ መለውጧን የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አስታወቁ።

እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፤ ነባሮቹን የገንዘብ ኖቶች በመተካት ለግብይት የሚሆን አዲስ የገንዘብ ዓይነት መጠቀም እንደምትጀምር በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል።

አዲስ የ200 ብር ገንዘብ ኖትም ተጨማሪ ሆኖ መምጣቱን ገልጸዋል።

እነዚህ አዲስ የገንዘብ ዓይነቶች ለሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎች የሚደረግን ድጋፍ፣ ሙስናን እና የኮንትሮባንድ ሥራዎችን ለመቀልበስ ይረዳሉ ብለዋል።

በአዲሶቹ የገንዘብ ዓይነቶች ላይ የተካተቱ መለያዎች አመሳስሎ ገንዘብ ለማተም የሚደረጉ ሕገ ወጥ ጥረቶችንም ለማስቀረት ያግዛሉ ነው ያሉት።
የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ግብርና እና አርሶ አደሮች የሚውል የ80 ሚሊየን ዶላር እርዳታ አጸደቀ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ግብርና እና ለአርሶ አደሮች ድጋፍ የሚውል የ80 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ ማጽደቁን አስታወቀ።
ባንኩ በድረ ገጹ ላይ ይፋ ባደረገው መረጃ እንዳስታወቀው፤ እርዳታው የኢትዮጵያን ግብርና ምርት ለማሰደግ እና በእፕነስተኛ ማሳ ለሚተዳደሩ ለአርሶ አደሮች የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሚውል ነው።
የዓለም ባንክ የ 2019 የድህነት ምዘና በኢትዮጵያ የግብርናው ዘርፍ ባለፉት አስርት ዓመታት ለድህነት ቅነሳው ቁልፍ አንቀሳቃሽ ዘርፍ መሆኑን ጠቅሶ ለሁለተኛው የግብርና ልማት ፕሮጀክት (AGPII) ተግባራዊነት የሚያግዝ ተጨማሪ ፋይናንስ ማጽደቅ ለአገሪቱን የግብርናው ኢኮኖሚ ማሳደግ አቅም ይፈጥራል ብሏል።
በአለም ባንክ ከፍተኛ የግብርና ባለሙያ የሆኑት ቪካስ ቹድሃሪ እንዳሉት “ሁለተኛው የግብርና ልማት ፕሮጀክት (AGPII) በኢትዮጵያ ድህነት ቅነሳ ላይ የጎላ አስተዋፅዖ አድርጓል ፡፡ ፕሮጀክቱ በተጨባጭ በተለይም ምርታማነትን በማሳደግ እና የንግድ ሥራን በማጎልበት ረገድ ትልቅ አስተዋጽዖ አበርክቷል ፡፡ በተጨማሪም የመስኖ አጠቃቀምን በማስተዋወቅ አርሶ አደሩ በአንድ ዓመት ውስጥ ሁለት ወይም ሶስት ጊዜ ሰብሎችን ለመሰብሰብ አስችሎታል ፡፡ አርሶ አደሩ ዝናብ ላይ ጥገኝነት በመላቀቅ እሴት የሚጨምሩ የአትክልት ፍራፍሬዎችን ማምረት ጀምሯል።
በተለይም AGPII ወደ 1.4 ሚሊዮን የሚጠጉ አነስተኛ አርሶ አደሮች (37% ሴቶች የሆኑ ) የግብርና አገልግሎቶችን ተደራሽነት ለማሳደግ ረድቷል ፡፡ እንዲሁም በ 254 አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎች መጠቀም በመቻሉ በሰብል ምርታማነትን በማሳደግና በአየር ንብረት-ዘመናዊ ጥበቃ ላይ ውጤታማ መሆን ተችሏል ነው ያለው ባንኩ።
ፕሮጀክቱ አርሶ አደሮችን ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር እንዲላመዱ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከተ ሲሆን 2 ሺህ 299 አዳዲስ አነስተኛ የመስኖ እቅዶችን በማጠናቀቅ እና ነባር የመስኖ መሠረተ ልማቶችን በማሳደግ 23,290 ሄክታር የእርሻ መሬት በመስኖ እንዲለማ አስችሏል ተብሏል ፡፡
በፕሮጀክቱ ስር የተካሄዱት የገበያ መሰረተ ልማት እና የእሴት ሰንሰለት ኢንቬስትመንቶች አርሶ አደሮችን ከገበያዎች ጋር በማስተሳሰር እና ንግድን ለማሳደግ ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል ብለዋል ፡፡ እነዚህ ተግባራት በሄክታር ከፍተኛ የምርት መጠን እንዲጨምር በማገዛቸው የአርሶ አደሮችን ገቢ እንዲያድግ አግዘዋል፡፡ እንዲሁም ለአርሶ አደሮች የተሻሻሉ የአመጋገብ ውጤቶችን አስገኝተዋል፡፡
በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ደቡብ ሱዳን እና ለሱዳን ዳይሬክተር በበኩላቸው የኢትዮጵያ የግብርናው ዘርፍ ለጠቅላላ ምርቱ 45 ከመቶውን እንዲሁም 80 በመቶ የሚሆነውን የሰራተኛ ኃይል የሚቀጥር በመሆኑ ለአገሪቱ ኢኮኖሚ ወሳኝ ዘርፍ ነው ፡፡ በዘርፉ እስካሁን ድረስ አበረታች ውጤቶች የተገኙ ቢሆንም ቀሪ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ እና የምርታማነት ግኝቶችን ለማፋጠን ፣ ለተዛባ የአየር ንብረት ሁኔታ ተጋላጭነትን ለመቀነስ ፣ የመሬት መበላሸትን ለመቅረፍ እና በዘርፉ ላይ የተመረኮዘ የተፈጥሮ ሃብት መሰረትን ለማሳደግ ተጨማሪ ስራ ያስፈልጋል ብለዋል።
ይህ ተጨማሪ ፋይናንስ እነዚህን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ እና የኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ ሙሉ አቅሙን መጠቀም እንዲችል ይረዳዋል ብለዋል። ገንዘቡ እስካሁን የተገኙ ውጤቶችን ለማሳደግ እና የተለያዩ ተጨማሪ ቴክኒካዊ ጉዳዮችን ለማሳደግ የተመደበ መሆኑን ተጠቅሷል ፡፡
በተጨማሪም ገንዘቡ በከፍተኛ የዋጋ ግሽበት የተፈጠሩትን ያልተጠበቁ የፋይናንስ ክፍተቶችን የሚሞላ እና ከፍተኛ ወጪ በመጠየቃቸው ምክንያት የዘገዩ የፕሮጀክት ሥራዎች አፈፃፀም ያፋጥናል ተብሏል፡፡
ለሁለተኛው የግብርና ልማት ፕሮጀክት በ 167 ወረዳዎች በአማራ ፣ በኦሮሚያ ፣ በደቡብ ፣ በትግራይ ፣ በቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ፣ በጋምቤላ እና በሐረሪ ክልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ይተገበራል ፡፡ ፕሮጀክቱ በቀጥታ ለግብርና ዕድገት ከፍተኛ አቅም ባላቸው አካባቢዎች ለሚኖሩ 1.6 ሚሊዮን አነስተኛ አርሶ አደሮችን በቀጥታ ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል ፡፡
“የፓርቲዎች የውይይት ባህል እየጎለበት ከሄደ ቀጣዩን ምርጫ በተሻለ መግባባት ማካሄድ እንችላለን “ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ
**************************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ፡- የፓርቲዎች የውይይት ባህል እየጎለበት ከሄደ ቀጣዩን ምርጫ በተሻለ መግባባት ማካሄድ እንደሚቻል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ ። ፓርቲዎች ተቀራርበው መወያየታቸውን ተከትሎ እየተገኙ ያሉ ስኬቶችን ማስቀጠል እንደሚገባም ተገለጸ ።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የተካሄዱትን ውይይቶች ትናንት ከፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር በጋራ በገመገሙበት ወቅት ፤ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚካሄደው የውይይት ባህል እየተጠናከረ የሚሄድ ከሆነ ለብዙ ችግሮች መፍትሄ የሚሰጥ ይሆናል።
ይበልጥ ስንተዋወቅ፣ ስንደጋገፍ ቀጣዩን ምርጫ በተሻለ መግባባት ማካሄድ ያስችላል ብለዋል ።
“ምን አልባት ምርጫውን የሚያሸንፈው ሀይል በርከት ያለ ከሆነ ይህንኑ የትብብር መንፈስ ካስቀጠልነው በጋራ ሆኖ አገር መምራት የሚያስችል አውድ ይፈጥራል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በአገራዊ አጀንዳዎች የሚካሄዱ ውይይቶች በጋራ መግባባት ላይ በተመሠረተ ሁኔታ ቀጣይ መንገዶችን ለማበጀት የታለሙ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ሙሳ አደም በበኩላቸው፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አማካኝነት የሚካሄዱ ውይይቶች ፍሬያማ እንደነበሩ አስታውቀዋል። በተለይ ብሄራዊ መግባባት ዙሪያ በምክር ቤቱ አማካኝነት የተካሄደው ውይይትም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በመድረኩ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አመልክተዋል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ እያካሄዱት ያሏቸው ውይይቶች ቅርርብንና መግባባትን ለማጠናከር ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የገለጹት ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር ተወክለው የመጡት አቶ ኡመር መሃመድ፤ መሰል ውይይቶች አጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል።
ትግራይ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሰብሳቢ ዶክተር አረጋዊ በርሄ በበኩላቸው ፤ “የፖለቲካ ባህላችን ኋላ ቀር ነው” ፤ በፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አማካኝነት በብሄራዊ መግባባቱ ዙሪያ የተደረጉና በቀጣይ የሚካሄዱ ውይይቶች በፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ዘንድ ጥሩ መንፈስና መቀራረብ የሚፈጥሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በወቅቱም የፖለቲካ ፓርቲዎቹ የጋራ መድረክ አማካኝነት የፖለቲካ ፓርቲዎች አደረጃጀት፣ የኢትዮጵያ ትልቁ የቅራኔ ምንጭ ምንድነው? ህገ መንግስትና ህገ መንግስታዊነት፣ ጥሩ ምርጫ ምን ማለት ነው? የሚሏቸው አጀንዳዎች ዙሪያ በቀጣይ ውይይት ለማድረግ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
ከፖለቲካ ፓርቲዎቹ የተመረጡ አራት ሰዎች ከ10 ወይም ከ15 ቀናት በኋላ በሚያካሂዱት ውይይት መድረኮች ላይ ጹሁፋቸውን አቅርበው ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሏል።ፓርቲዎች ተቀራርበው መወያየታቸውን ተከትሎ እየተገኙ ያሉ ስኬቶችን ማስቀጠል እንደሚገባም በውይይት መድረኩ ላይ ተጠቁሟል።
አዲስ ዘመን መስከረም 6/2013
ጌትነት ምህረቴ
በኦሮሚያ ክልል ከ32 ሺህ በላይ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች መገንባታቸው ተገለፀ
***********************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ፦ የኮሮና ቫይረስን በመከላከል ትምህርትን ለማስቀጠል እንዲቻል 32 ሺህ 108 ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች መገንባታቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቶላ በሪሶ ትናንት በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ በክልሉ ተጨማሪ 30 ሺህ ክፍሎችን ለመገንባት ታቅዶ ከእቅዱ በላይ 32 ሺህ 108 መገንባቱን አስታውቀዋል።
በተጨማሪም የተለያዩ የውሃ እና የመፀዳጃ ቤት ግንባታዎችም መከናወኑንም አመልክተዋል።
ከመፅሃፍት ጋር በተያያዘም 1 ሚሊየን መጽሃፍት ለመሰብሰብ ታቅዶ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን የተለያዩ አይነት መጽሃፍቶችን መሰብሰብ መቻሉን ጠቁመዋል።
በቀጣይም የ2013 የትምህርት ዘመን ትምህርት ለማስቀጠል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ያመለከቱት ዶክተር ቶላ፤ የተማሪዎች ምዝገባም እየተካሄደ ነው ብለዋል ። በቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታትም ምዝገባው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
መምህራንን በተመለከተ በክልሉ ከሚገኙ 13 የመምህራን ኮሌጆች 25 ሺ 300 የ3ኛ ዓመት ተማሪዎችን የማጠቃለያ ቲቶሪያል በመስጠት ወደ ቅጥር ይገባሉ ብለዋል።
በክልሉ በዚህ የትምህርት ዘመን 11 ነጥብ 2 ሚሊየን ተማሪዎችን መዝግቦ ለማስተማር እቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሚገኝም አመልክተዋል።
በወቅቱም የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ሰራተኞች ለገበታ ለሀገር የአንድ ወር ደመወዛቸውን 1 ሚሊየን 249 ሺህ ብር መለገሳቸው ተገልጿል በመግለጫው።
አዲስ ዘመን መስከረም 6/2013
325 አዳዲስ የገጠር ከተሞች እና መንደሮች ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ማድረግ ተቻለ
*************************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ፡- በ2012 ዓ.ም ብቻ ምንም አይነት የኤሌክትሪክ ሃይል አግኝተው የማያውቁ 325 አዳዲስ የገጠር ከተሞች እና መንደሮች የኤሌክትሪክ ሃይል እንዲያገኙ ማድረግ መቻሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።
የአገልግሎቱ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታዬ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደተናገሩት፤ ተቋሙን በማዘመን ነባሩ ደንበኛ አስተማማኝ ኤሌክትሪክ እንዲያገኝ ከማስቻል በተጨማሪ ከኤሌክትሪክ ጋር ምንም አይነት ትውውቅ የሌላቸውን አካባቢዎች ኤሌክትሪክ በማዳረስ ትልልቅ ሥራዎች እየተሰሩ ናቸው። በተጠናቀቀው 2012 በጀት ዓመት 168ሺህ 751 አባወራዎች አዲስ ቆጣሪ እንዲያገኙ ተደርጓል።
የገጠር ኤሌክትሪፍኬሽን ፕሮግራም ሲጀመር 667 ከተሞች ብቻ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ እንደነበሩ ያስታወሱት አቶ መላኩ፤ አንዳንድ የዞን ከተሞች ሳይቀሩ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ እንዳልነበሩ ተናግረዋል። እስከ አሁን በገጠር ኤሌክትርፍኬሽን 6 ሺህ 759 የገጠር ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን አመልክተዋል።
እንደ አቶ መላኩ ገለፃ፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በአጠቃላይ የደንበኛው ቁጥር ከ3 ሚሊየን የዘለለ አይደለም። ከኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥም 44 በመቶ ብቻ ነው የኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚያገኘው። 66 በመቶው ህዝብ ማለትም ብዛት ያላቸው ከተሞች አሁንም ከኤሌክትሪክ ሃይል ጋር እንደማይተዋወቁም ጠቁመዋል። ተቋሙ ይህን ሁኔታ ለመቀየር አዳዲስ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ያልነበሩ የገጠር ከተሞች እና መንደሮች ተጠቃሚ እንዲሆኑ በከፍተኛ መዋለ ነዋይ ፕሮጀክቶች ነድፎ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ህዝቡ ፍትሃዊ በሆነ መልኩ የኤሌክትሪክ ሀይል እንዲዳረሰው ተቋማቸው ጠንክሮ የሚሰራ መሆኑን ተናግረው፣ ኤሌክትሪክ ሀይል ማስፋፋት ቢቻልም አሁንም ተጠቃሚ ያልሆኑ በርካታ የገጠር ከተሞች አሉ ሲሉ ተናግረዋል።
በተጨማሪ ነባሩ ደንበኛ በተለያዩ ምክንያቶች የሚዋዥቅ እና የሚቆራረጥ አገልግሎት ሲያገኝ ቆይቷል ያሉት አቶ መላኩ፤ አሁን ግን ኔትወርኩን በማሻሻል ነባሮቹ ደንበኞች በመደበኛነት ሃይል እንዲያገኙ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። ለእዚህ ማሳያውም በዚህ ዓመት ክረምት ከፍተኛ ዝናብ ቢጥልም ሃይል የሚቆረጥበት ክስተት ውስን እንደነበር ጠቅሰዋል።
አዲስ ዘመን መስከረም 6/2013
ምህረት ሞገስ
የብር ኖቶች መቀየራቸው ትክክለኛ እርምጃ መሆኑን ፖለቲከኞች አመለከቱ
***********************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ ፦ መንግስት ነባሮቹን የገንዘብ ኖት በአዲስ መቀየሩ ህገወጥነትን የሚከላከል ትክክለኛ እርምጃ መሆኑን ፖለቲከኞች ገለጹ።
የትግራይ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር አረጋዊ በርሄ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳሉት፤ መንግስት የገንዘብ ኖት መቀየሩ ትክክለኛ እርምጃ ነው። ምክንያቱም የቆየው የህወሀት አገዛዝ አገሪቷን የኮንትሮባንድ መናኸሪያ የደላላና የቀማኛ አገር አድርጓት ነበር።
እንደ ዶክተር አረጋዊ ገለጻ፤ ባለፉት ዓመታት በአገሪቱ በአንድ ጀምበር ሚሊየነር የሚሆኑ ፣ ከምንም ተነስተው ባለ በርካታ ህንጻ ባለቤቶች የሆኑ ህገወጦች የበዙባት ሆና ነበር፤ ይህንን ሁኔታ ለመቀየርና ህጋዊ መንገድን ለመፍጠር የገንዘብ ኖት መቀየር ትክክለኛ እርምጃ ነው ብለዋል።
ቀደም ባሉት ጊዜያት ኮንትሮባንድና ማጭበርበርን የማያውቁ በላባቸውና በወዛቸው የሚያድሩ ሰዎች ችግር ውስጥ ነበሩ ያሉት ዶክተር አረጋዊ ፤ አሁን የተፈጠረው እድል ህጋዊ ሆኖ የሰራ ሁሉ የሚያገኝበትና የሚለወጥበት መሆኑን ጠቅሰዋል።
በሌላ በኩልም ዘርፈው ባስቀመጡት ገንዘብ መሳሪያ በመግዛት የተለያዩ አደንዛዥ እጾችን በማመላለስና ህገወጥ በሆኑ ተግባራት ላይ በመሰማራት አገሪቱ እንድትተራመስ ሲሰሩ የነበሩ አካላት የገንዘብ ለውጡ አደብ እንደሚያስገዛቸው አመልክተዋል።
መንግስት እንደከዚህ ቀደሙ ህጋዊ ያልሆኑ የመበልጸግ ሂደቶችን የሚቆጣጠርበት ህጋዊ ሳይሆኑ ወደ አገር የሚገቡ መድሀኒቶችን ጨምሮ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችና የኮንትሮባንድ እቃዎች እይታ ውስጥ የሚያስገባበት ሁኔታ ስለሚፈጥር ፤ የገንዘብ ለውጥ ለአገሪቱ ትልቅ ጥቅም የሚሰጥና የኢኮኖሚ መረጋጋትን የሚያመጣ እንደሆነ አመልክተዋል።
ገንዘብን ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ሲያከማቹ የቆዩ ሰዎች መውጫ መንገዳቸውን እራሳቸው የሚያውቁት ቢሆንም ፤ እየተተገበሩ ያሉ አሰራሮች የሰራ ሰው የሚያገኝበት፣ በሀቅ ገንዘቡን በአገር ልማትና እድገት ላይ የሚያውልበት ነው ብለዋል ።በጠቅላላው ህግን የተከተለ ተጠቃሚ የሚሆንበት መሆኑንም አብራርተዋል።
በአገሪቱ ላይ ያለውን ያልተመጣጠነና ለሌባና ለቀማኛ የተመቸ አካሄድን በማስቀረት ኢኮኖሚው እንዲረጋጋ፣ የዋጋ ግሽበትም በቁጥጥር ስር እንዲውል፣ የተደበቁ ገንዘቦችም እንዲመክኑ በማድረግ በኩል ከፍተኛ ሚና ያለው እንደሆነም አስታውቀዋል።
አንድ አገር ደላላ የሚቆጣጠራት ከሆነ ፍትህ አይኖርም ዘራፊ ይበራከታል ፤ይህ ሲሆን ደግሞ እድገት አይደለም ወጥቶ መግባትም ይናፍቃል፤ በመሆኑም መንግስትም የሚሰራቸውን መሰረተ ልማቶች ተረጋግቶ እንዲሰራ አገርን የማልማት ስራውም የተሳለጠ እንዲሆን በጣም ጠቃሚ እረምጃ ነው ብለዋል ።
የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅና ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በበኩላቸው፤መንግስት ጥናት አስጠንቶ መረጃ ሰብስቦ የፋይናንስ ባለሙያዎች በጉዳዩ ላይ ጠለቅ ያለ ውይይት እንዲያደርጉበት አድርጎ የወሰነው ውሳኔ በመሆኑ ጥሩ እርምጃ ነው።
ህገ ወጥ ገንዘቦች በአገሪቱ ላይ መዘራታቸው አፍራሽ ሚና ያለው ነው፤ ግማሹም ፖለቲካውን ተገን በማድረግ ብዙ የብር ኖቶችን በየስርቻው ደብቆ ለእኩይ ተግባሩ ማስፈጸሚያነት ሲጠቀምበት የቆየ በመሆኑ ይህ ውሳኔ በመንግስት በኩል መወሰኑ ለኢኮኖሚያዊም ይሁን ፖለቲካዊ ሰላም መረጋገጥ ከፍተኛ ሚና ያለው መሆኑን አስታውቀዋል።
“ብዙ ኩንታል መቶ ብሮች አስቀምጠህ ከሆነና በፍጥነት ሄደህ ባንክ ካልቀየርክ ወረቀት ሆኖ ይቀራል ማለት እኮ በቂ ቁጥጥር ነው” ያሉት ፕሮፌሰር በየነ፤ አሁን ሁሉም ወደ ህጋዊነት የሚመጣበት ጊዜ ስለመሆኑም ጠቁመዋል ።
አዲስ ዘመን መስከረም 6/2013
እፀገነት አክሊሉ