የኮሮናቫይረስ እየተስፋፋ ቢሆንም ተገቢው ጥንቃቄ እየተደረገ የትምህርት ዝግጅት እና እንቅስቃሴ መጀመር አስፈላጊ ነው - ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ
***********************
የኮሮናቫይረስ እየተስፋፋ ቢሆንም ተገቢው ጥንቃቄ እየተደረገ የትምህርት ዝግጅት እና እንቅስቃሴ መጀመር አስፈላጊ በመሆኑ በ2013 የትምህርት ዘመን ተማሪዎች ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ እንዳይሆኑ እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ገለጹ።
የቀጣዩ ዓመት ትምህርት ምዝገባ ከነገ ነሐሴ 20 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በመንግሥት እና በግል ትምህርት ቤቶች እንደሚጀመር የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶችን በመተግበር ምዝገባ እንዲያከናውኑ ተፈቅዷል ብለዋል።
የበሽታው ሁኔታ እየተስፈፋ ቢሆንም የትምህርት ዝግጅት እና እንቅስቃሴ መጀመር አስፈላጊ ሆኑ መገኘቱን ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት።
ወደ መማር ማስተማር ተግባር በሚገባበት ወቅት ለተማሪዎች ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እንደሚሠራ ገልጸው፣ ማስክ፣ የእጅ ማፅጃ እና መሰል አቅርቦቶችን ከባላድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለማቅረብ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በግልም ሆነ በመንግሥት ትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እንዳይከሰት ተማሪዎች ማስክ በማድረግ፣ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ እና እጅን በመታጠብ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚኖርባቸው ሚኒስትሩ አሳስበዋል።
ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉት ተማሪዎች በ2012 የትምህርት ዘመን በ2ኛ ሴሚስተር ያለፋቸውን ትምህርቶች ማካካሻ ለመስጠት መታሰቡንም ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ገልጸዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል ።

በሀሰተኛ የብር ኖቶች 20 ኩንታል ጤፍ የገዙት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
********************************
(ኢፕድ)
በምስራቅ ጎጃም ዞን ጎዛምን ወረዳ ሊቫኖስ ቀበሌ ልዩ ቦታው ሮቢት እየተባለ በሚጠራው ስፍራ ነሐሴ 18/2012 ዓ.ም በሀሰተኛ የብር ኖት 20 ኩንታል ጤፍ ለመግዛት የሞከሩት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅትም 90ሺ 1 መቶ ሀሰተኛ የብር ኖት፤ 13ሺ 7 መቶ ህጋዊ የብር ኖት፤ ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ ከ6 መሰል ጥይት፤ ስድስት ተንቀሳቃሽ ስልክ እንደተገኘባቸው የጎዛምን ወረዳ ፖሊስም ገልጿል።
የወረዳው የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ፀጋዬ ጋሹ እንደገለፁት በመጭው አዲስ ዓመት በዓል ወቅት ህብረተሰቡ ልዩ ልዩ ግብይቶችን ሲያከናውን ለእንዲህ አይነቱ የወንጀል ድርጊት ሰለባ እንዳይሆን አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግና አጠራጣሪ ሁኔታ ሲያጋጥምም ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት ወንጀልን የመከላከል ተግባሩን እንዲወጣ ጥሪ አስተላልፈዋል ሲል ከጎዛምን ወረዳ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኔዘርላንድ የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ቀዳሚ መዳረሻ አገር ሆነች
************************
(ኢ ፕ ድ)
በ2012 በጀት ዓመት ኔዘርላንድ የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ቀዳሚ መዳረሻ አገር መሆኗ ተገለጸ፡፡
ኢትዮጵያ በ2012 በጀት አመት አበባ ፣ ቡና፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ጨርቃጨርቅና አልባሳት የኤሌክትሪክ ውጤቶች፣ ጫማ ፣ ቆዳ ማርና ሰም፣ የቅባት እህሎች የአልኮል መጠጦች፣ ጫት፣ ሻይ ብረትና የመሳሰሉትን ወደ ኔዘርላንድስ ልካለች።
ከተላኩት የወጪ ንግዶችም ኢትዮጵያ 320 ሚሊዮን 162 ሺህ የአሜሪካን ዶላር አግኘታለች።
ጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ ቡና ጫማ፣ አበባ፣ የቆዳውጤቶችን፣ የቅባት እህሎችን እና ሌሎች ኢትዮጵያ ወደ ውጪ የምትልካቸውም ምርቶች በመቀበል አሜሪካ በሁለተኛነት ስትቀመጥ፤ በተጠቀሰው በጀት አመት 295 ሚሊዮን 809 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ማግኘት ችላለች፡፡
ከሶማሊያ 291 ሚሊዮን 855 ሺህ ዶላር፣ ከሳውዲ አረቢያ 214 ሚሊዮን 652 ሺህ፣ ከጀርመን 174 ሚሊዮን 283 ሺህ ዶላር መገኘቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1545 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ የ 17 ሰዎች ህይወት አለፈ
****************************
(ኢፕድ)
በ24 ሰዓታት ለ18 ሺህ 778 ሰዎች በተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ 1545 ሰዎች በኮሮና መያዛቸው ተረጋግጧል።
17 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው ሲያልፍ በቫይረሱ የሞቱት ቁጥር 709 ደርሷል።
በዛሬው እለት 534 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን አጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች
ቁጥር 15 ሺህ 796 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስቡክ ገጻቸው አስታውቀዋል።
ሌሎች 290 ሰዎች በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ እንደሚገኙም ተገልጿል።
አጠቃላይ እስካሁን ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 43 ሺህ 688ሲሆኑ በአሁኑ ሰአት ቫይረሱ ያለባቸው
ሰዎች ቁጥር 27 ሺህ 181 ደርሷል።

ከነገ ጀምሮ የሚተገበር የኢንተርኔት እና የድምፅ ጥቅል ቅናሽ ተደረገ
***************************
(ኢፕድ)
ኢትዮ ቴሌኮም ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ በኢንተርኔት ጥቅል እና በድምፅ ጥቅል አገልግሎቶቹ ላይ ቅናሽ ማድረጉን አስታወቀ።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ የተቋሙን የ3 አመት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ እና የ2013 በጀት አመትን ዋና የትኩረት አቅጣጫ በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸውም በኢንተርኔት ጥቅል ላይ 35 በመቶ እንዲሁም በድምፅ ጥቅል ላይ የ29 በመቶ ቅናሽ መደረጉን ገልፀዋል።
የሞባይል ድምጽ እና ዳታ ጥምር አገልግሎት 28 በመቶ እንዲሁም በፕሪሚየም ያልተገደበ የድምጽ ጥቅል አገልግሎት 21 በመቶ ቅናሽ ተደርጓልም ብለዋል፡፡
በፕሪሚየም ያልተገደበ የዳታ ጥቅል አገልግሎት 21 በመቶ እንዲሁም በፕሪሚየም ያልተገደበ የድምጽ እና ዳታ ጥቅል አገልግሎት 20 በመቶ ቅናሽ ተደርጓል፡፡
በፕሪሚየም ፕላስ ያልተገደበ የጥቅል አገልግሎት 16 በመቶ እንዲሁም በሳተላይት አገልግሎት ላይ እስከ 61 በመቶ ቅናሽ መደረጉም ተገልጿል፡፡
በቤትዎ ይቆዩ የጥቅል አገልግሎት ላይ የ59 በመቶ ቅናሽ የተደረገ ሲሆን እስከ ፈረንጆቹ አዲስ ዓመት የመጀመሪያ ቀን ድረስ ባለበት እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
ከዚህ ባለፈም የኢትዮጵያውያንን አዲስ ዓመት ምክያት በማድረግ ለአዲስ አመት የአደይ አበባ ጥቅል አገልግሎት 53 በመቶ እና በዓለም አቀፍ አየር ሰአት አገልግሎት ላይ የ100 ፐርሰንት የአየር ስጦታ ለደንበኞች አቅርቧል ሲል ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጥገና ባለሙያዎች በአፍሪካ አቪየሽን ታሪክ የመጀመሪያ ሊባል የሚችል የአውሮፕላን ክንፍ ላይ የምህንድስና ማሻሻያ አደረጉ
*********************************
(ኢፕድ)
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን ጥገና ባለሙያዎች በአፍሪካ አቪየሽን ታሪክ የመጀመሪያ ሊባል የሚችል የአውሮፕላን ክንፍ ላይ የምህንድስና ማሻሻያ /winglet modification/ አደረጉ።
ማሻሻያው የተደረገው አየር መንገዱ በሚያበራቸው የቦይንግ 767 አውሮፕላኖች ላይ ሲሆን፣ ይህም በአመት እስከ 500 ሺህ ጋሎን ነዳጅ እንዲቆጥብ ያስችለዋል ተብሏል።
ከዚህም በተጨማሪ ማሻሻያው 277 ሺህ ሜትሪክ ቶን የካርበን ልቀትንም የሚያስቀር በመሆመኑ አየር መንገዱ በአካባቢ ጥበቃ የሚያደርገውን ጥረት የሚያግዝ ነው።
69 የሚሆኑ የአየር መንገዱ የአውሮፕላን አካል ጥገና ባለሙያዎች ሌት ተቀን እና በእረፍት ቀናቸውም በመስራት ጭምር ፕሮጀክቱን በስኬት ማጠናቀቃቸው ተገልጿል።

የህወሓት/ ትህነግ አመራሮችና ጥቅመኞቻቸው በራያ ወረዳዎች የመሬት ወረራ እያካሄዱ ነው ሲል የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አስታወቀ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
"የህወሓት/ ትህነግ አመራሮችና ጥቅመኞቻቸው በትግራይ ክልል በተካለሉት የራያ ወረዳዎች ላይ ስልታዊና ዓይን ያወጣ የመሬት ወረራ እያካሄዱ ነው" ሲል የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ራዴፓ) አስታወቀ።
“መሬታችን ያለ ሕጋዊ መንገድ አንሰጥም” ያሉ ገበሬዎች እየታሰሩ ነው ያለው ፓርቲው፤ በዚህ ምክንያትም በወፍላ ወረዳ 50፣ በራያ ዓዘቦ ወረዳ በወራባዬ ቀበሌ 13 ገበሬዎች መታሰራቸውን፤ በራያ-አላማጣ ወረዳም 110 ገበሬዎችን ያለ ካሳ ክፍያ መፈናቀላቸውን ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መግለጫ አስታውቋል።
ይህን ሕገ-ወጥ የመሬት ወረራና የሕዝባችን እስርና እንግልት አጥብቆ ያወግዛል ያለው ፓርቲው፤ የፌዴራል መንግሥትና የሚመለከታቸው የሰዓአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችም መፍትሔ እንዲሰጡ፤ የሚዲያ ተቋትም ተግባሩን እንዲያወግዙ ጥሪ አቅርቧል።
በሃገራችን የሰሜን ምሥራቁ ክፍል በተደጋጋሚ የአንበጣ መንጋ መከሰት በራያ አከባቢዎች በሰብልና በአዝርእት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል ያለው ፓርቲው፤ የክልሉ መንግሥት/ትህነግ እንደ ኮሮናው ሁሉ ይህን የተፈጥሮ አደጋ ከመከላከል ይልቅ በዝምታ እየተመለከተው ይገኛል። ይባስ ብሎም ገበሬዎችና ወጣቶች በጋራ በመሆን በሰው ኃይል የአንበጣ መንጋውን መከላከል እንዳይችሉ በምርጫ ምዝገባና ካርድ ማውጣት ሰበብ በተስፋና በጉጉት የሚጠበቁ የሰብልና የአዝርዕት ቡቃያዎች ለከፍተኛ ውድመት እንዲጋለጡ አድርጓል ብሏል።
“ይህ የትህነግ ተግባር በራያ ሕዝብ ላይ ያለውን የጠላትነትና የማደህየት ደባ በግልጽ ያሳየ ሆኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም ሕዝባችን ይህ ሕገ_ወጥ ድርጅት መቸም ጊዜ ቢሆን ለደኅንነቱና ለዕድገቱ በየማያግዝ መሆኑን ዐውቆ እስከመጨረሻው እንዲቃወመውና ለመብቱና ማንነቱ መከበር ከሚታገለው ፓርቲያችን ጎን ይቁም” ሲል ጠይቋል።
እንደ ፓርቲው መግለጫም፤ የክልሉ መንግሥት/ትህነግ ለሥራ አጦች የሚሰጥ ሥልጠና በሚል ማታለያ መዝግቦ ለውትድርና ወጣቶችን በአስገዳጅ ሁኔታ እየመለመለ ይገኛል። እንዲሁም በየቀበሌው ከ300 እስከ 500 የሚደርሱ ሰዎችን፣ ዕድሜያቸው ያልደረሱ ታዳጊ ወጣቶችን ጭምር ለአስገዳጅ ውትድርና በቀበሌ አስተዳዳሪዎች አማካኝነት በመመልመል ወደ እርስበርስ ጦርነት ለመማገድ እያዘጋጃቸው ይገኛል።
የልማት ተግባራትን በመተው ቁጥር ስፍር የሌላቸው የክልል ልዩ ኃይሎችንና ሚሊሻዎችን አስታጥቀው የሚሰጧቸው ሬሽን ቢያጡ በግድ ገንዘብ፣ ዱቄት፣ ምግብ፣ እህል ወዘተ አዋጡ እያሉ ሕዝባችንን ለቀውስ መዳረጋቸው አጥብቀን እናወግዛለን ያለው ፓርቲው፤ “የሕዝባችንን ያለ አግባብ መጨቆንና መንገላታት በመገንዘብ የፌደራል መንግሥት እንዲደርስለትና ከሚደርስበት ብዝበዛ እና አስገዳጅ ውትድርና እንዲታደገው” ሲል ጥሪ አቅርቧል።

የፀረ-ኤች አይ ቪ መድሃኒት የሚወስዱ ሰዎች የበሽታ የመከላከል አቅማቸው ስለሚቀንስ ከሌሎች ሰዎች በበለጠ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ይመከራል፡፡
በመሆኑም:-
1. ወደ ጤና ተቋም የሚያደርጉትን ምልልስ በመቀነስ የቀጠሮ ጊዜ እንዲረዝም ማድረግ
2. መድሃኒታቸውን በትክክልና ሳያቋርጡ መውሰድ
3. ከአደገኛ ሱሶች መራቅ
4. እራስን አለማጨናነቅ፣ የአካልብቃትእንቅስቃሴ ማድረግ
5. ሌሎች ለኮቪድ 19 መከላከያዎችን መተግበር
6. ህመም ከተሰማ ወዲያውኑ ወደ አቅራቢያ ጤና ተቋም መሄድ እና ሪፖርት ማድረግ፡፡
7. የጸረ-ኤችአይቪ ህክምና የምናገኝበትንና መድሃኒት የምንወስድበትን ጤና ተቋም እንዲሁም የባለሙያ ስልክ ቁጥር መያዝ፣ በስልክ የጤና ባለሙያዎችን ምክር መጠየቅ፣ ማማከር ተገቢ ነው።
የጤና ሚኒስቴር

በአዲስ አበባ የሚገኘው የብሪታንያ ኤምባሲ፣ በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲና ዲፕሎማቶች ላይ ለተፈጸመው ጥቃት ይቅርታ ጠየቀ
************************************
(ኢፕድ)
በአዲስ አበባ የሚገኘው የብሪታንያ ኤምባሲ በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲና ዲፕሎማቶች ላይ በቅርቡ ለተፈጸመው አግባብ ያልሆነ ድርጊት ይቅርታ ጠየቀ።
የኤምባሲው ከፍተኛ ባለስልጣን አሌክስ ካሜሮን እንዳሉት በቅርቡ በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ በተፈጠረው ሁከትና በዲፕሎማት ላይ ለተፈጸመው ጥቃት ይቅርታ ጠይቀው፣ በቀጣይ እንዲህ ያሉ ሁኔታዎች እንደማይደገሙ፤ የእንግሊዝ መንግስትም በቬናው ስምምነት መሰረት ለኤምባሲውም ሆነ ለዲፕሎማቶች ተገቢውን ጥበቃ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በበኩላቸው በቬና ኮንቬንሽን መሰረት ማንኛውም አገር ኤምባሲዎችና ዲፕሎማቶችን ከሁከት፣ ጣልቃ ገብነት ወይም የአመጽ ተግባር የመከላከል ሃላፊነት እንዳለበት አስታውሰው፤ በቅርቡ በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲና ዲፕሎማቶች ላይ የተፈጸመው ድርጊት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ቅሬታ አሳድሯል። በመሆኑም ይላሉ አምባሳደሩ በቀጣይ እንዲህ ያለ ነገር እንዳይከሰት የእንግሊዝ መንግስት ተገቢውን ጥበቃ የማድረግ ሃላፊነት አለበት ብለዋል።

በትግራይ ይካሄዳል በተባለው ህገ-ወጥ ምርጫ አንሳተፍም ያለው የራያ ሕዝብ እየታሰረና እየተሰደደ ነው ሲል የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ራዴፓ) አስታወቀ
***********************
(ኢ ፕ ድ)
በትግራይ በሚካሄደው ህገ-ወጥ ምርጫ ላይ አንሳተፍም ያሉ የራያ ሕዝቦች እየታሰሩና እየተሰደዱ መሆናቸውን የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ራዴፓ) አስታወቀ።
ፓርቲው ወቅታዊ የራያ አካባቢና ሃገራዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፤ ህወሓት/ትህነግ ሊያካሂድ ላሰበው ህገ ወጥ ምርጫ ካርድ እያደለ ይገኛል። በዚህ ህገ-ወጥ ክልላዊ ምርጫ ላይ መብቴ/ማንነቴ ሳይከበርና ጥያቄዎቼ ሳይመለሱ አልሳተፍም ያለው የራያ ሕዝብ እንዲሁም ለውጡን የሚደግፉ ሰዎች፣ የተለያዩ የተፎካካሪ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች እየታሰሩና እየተሰደዱ ይግኛሉ።
“ለምርጫ አንመዘገብም፣ የምርጫ ካርድም አንወስድም ያሉ ነዋሪዎች እስር፣ እንግልትና ድብደባ ጭምር እየደረሰባቸው ነው” ያለው የፓርቲው መግለጫ፤ በዚሁ ምክንያትም በራያ- መኾኒ፣ በራያ-ኮረምና በራያ-ጨርጨር እስከ ዛሬው ቀን ድረስ 105 ወጣቶችና አዛውንቶች መታሰራቸውን አመልክቷል ።
የራያ ወገኖቻችንን ላይ ድብደባና ከፍተና የአካልና የሥነ-ልቡና ጉዳት እየደረሰ ነው ያለው ፓርቲው፤ “የራዴፓ አባል ናችሁ” እንዲሁም “ስበር ራያ”ን ትደግፋላችሁ እያሉ ወጣቶችንና አዛውንቶችንም ጭምር ያለ ፍርድ ቤት ፈቃድ መኖረያ ቤቶቻቸውን ይበረብራሉ፤ ያሸማቅቋቸዋል ነው ያለው። ለአብነት ያህልም በዚህ ሳምንት ብቻ በአላማጣ በ6 ወጣቶች ላይ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ፓርቲው አስታውቋል።
ከዚህ በከፋ መንገድ በማንነታቸው ምክንያት ጥያቄ ሊያነሡ ይችላሉ በሚል መሠረተ ቢስ ሰበብ በራያ አላማጣ ብቻ 20 የመንግሥት ሠራተኞች ከሥራ ገበታቸው ተሰናብተዋል ያለው ፓርቲው፤ እነዚህ ተግባሮች በሕገ-መንግሥቱ የተደነገጉትን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን የሚፃረሩ በመሆናቸው በአስቸኳይ እንዲቆሙ አሳስቧል።
“ሕዝባችን የመንግሥት ውሳኔን አክብሮ፣ በዚህ ሕገ-ወጥ ምርጫ አልሳተፍም፣ አልመርጥም በማለቱ ከፍተኛ የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶች እየደረሰበት ነው” ያለው የፓርቲው መግለጫ፤ “የፌዴራል መንግሥት በአስቸኳይ ጣልቃ ገብቶ ደኅንነቱና ህልውናው እንዲጠብቅልን፤ ከኮሮና በሽታ እልቂት እንዲታደግልን እንዲሁም ሕጋዊ ምርጫ እስኪደረግ ድረስ መላው የራያ አካባቢ በገለልተኛ አካል ወይም በሃገር መከላከያ ሠራዊት ጥበቃ ሥር እንዲቆይ” ሲል ጠይቋል።
በትግራይ ይካሄዳል የተባለው ክልላዊ ምርጫ ህጋዊ እንዳልሆነና እንደማያውቀው ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ማስታወቁ፤ በተመሳሳይም የፌዴሬሽን ምክር ቤትም ምርጫው ህገ ወጥና ተቀባይነት እንደሌላው መግለጹ ይታወሳል።

ደቡብ አፍሪካ ፡ 'የአናብስቱ አባት' በሚንከባከቧቸው አንበሶች ተበሉ
ዌስት ማቲውሰን ይባላሉ። እውቅ የአካባቢ ተንከባካቢ ነበሩ። በተለይም ከደቦሎች ጋር ባላቸው ቅርበት 'የደቦል አንበሶች አባት' የሚል ቅጽል አስገኝቶላቸዋል።
እኚህ እውቅ የደቡብ አፍሪካ የዱር እንሰሳት ተንከባከባቢ የነበሩት ሰው ታዲያ በሚንከባከቧቸው አንበሶች መበላታቸው ተሰምቷል።
ክስተቱ ያልተመለደና ያልተጠበቀ ነበር።
ሚስተር ማቲውሰን በአናብስቱ ሲበሉ ባለቤታቸው አብረዋቸው በቅርብ ርቀት ነበሩ።
ሚስተር ማቲውሰን ነጫጭ አናብስቱን ለማለዳ የእግር ጉዞ ነበር ከጥበቃ ጎሬያቸው ይዘዋቸው የወጡት። ትንሽ እግራችንን አፍታተን እንመለስ ብለው።
ሆኖም ሳይመለሱ ቅርተዋል።
ባላቸውንና ለእግር ጉዞ ይዘዋቸው የወጡትን አናብስት በመኪና ከኋላ ኋላ ሲከተሏቸው የነበሩት የሟች ሚስት ነገሮች መልካቸውን እየለወጡ እንደሆነ ሲረዱ አንበሶችን ትኩረት ለማስቀየር ሙከራ ቢያደርጉም አልተሳካላቸውም።
የ68 ዓመት ባላቸውንም ከመበላት አላስጣሏቸውም።
ዌስት ማቲውሰን በደቡብ አፍሪካ ታዋቂውን የሳፋሪ ሎጁ ያስተዳድሩ ነበር። ስሙም ላየን ትሪ ቶፕ ሎጅ ተብሎ ነው የሚጠራው። የሚገኘውም በደቡብ አፍሪካ፣ ምዕራብ ጆሐንስበርግ፣ ሊምፖፖ ግዛት አካባቢ ነው።
አንበሶቹ ከዚህ ቀደም ወደ አንድ ሌላ ሎጅ ተወስደው የነበረ ሲሆን በቅርብ ጊዜ ወደ ዱር ተመልሰው ሊወሰዱ እንደነበር ተዘግቧል።
አንዷ ሴት አንበሳ ያልተጠበቀ ባህሪ ማሳየቷ ነው ነገሮችን የለወጣቸው።
በወቅቱ ሴቷ አንበሳ ባልተለመደ መልኩ በሌላኛዋ አንበሳ ላይ ጨከን የማለት ባህሪ ታይቶባት ነበር።
ከዚያ ወዲያው ደግሞ ፊቷን መልሳ ከእኚህ ከተጠባቂያቸው ጋር ልፍያ ጀመረች። ሳይታሰብ ጠባቂዋን መቦጫጨቅ እንደጀመረች ተነግሯል።
የሟች ዘመዶች እንደሚሉት የሰውየው ለሞት መዳረግ ምናልባት አንበሶቹ እርስበርስ መቦጫጨቅና ኃይል የተቀላቀለበት ልፍያ ማድረጋቸው ያመጣው መጥፎ አጋጣሚ ሊሆን ይችላል።
የሚገርመው ሰውየው አናብስቱን ከሚታደኑበት ስፍራ አውጥተው በሕይወት እንዲቆዩ ማድረጋቸው ነው።
መካነ አደን (canned hunting) እንሰሳት በአንድ ክልል ሆነው ሰዎች በሕጋዊ አደን እንዲገድሏቸው የሚደረግበት ክልል ነው።
እነዚሁ አናብስት በ2017 እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ክልላቸውን ጥሰው በመውጣት አንድ በአካባቢው የሚጎራበታቸውን ሰው ገድለዋል።
እኚህን ጠባቂያቸውን ሲገድሉ ታዲያ ይህ ሁለተኛ ጊዜያቸው መሆኑ ነው።
ሚስተር ማቲውሰን አናብስቱን ያሳደጓቸው ገና ደቦል ሳሉ ነበር። ሰውየው ከአናብስቱ ጋር አብረዋቸው ሲላፉና ሲጫወቱ በርከት ያሉ ዘጋቢ ፊልሞች አሏቸው።
ምንጭ ቢቢሲ

የህክምና ማዕከሉ የኮሮና ታማሚዎችን ያልተገባ ድርጊት አወገዘ
**************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ፡- በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሰባት የኮሮና ህክምና ማእከል በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ከገቡ ታማሚዎች አንዳንዶች በህክምና ክትትል ወቅት የሚያደርጓቸው ያልተፈቀዱ ድርጊቶች ተገቢ ባለመሆናቸው መታረም እንዳለባቸው ማዕከሉ አሳሰበ፡፡
የማእከሉ “ኬዝ ማናጀር“ ዶክተር ወርቅነህ ነጮ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ማዕከሉ አስቀድሞ ለለይቶ ማቆያ የተዘጋጀ ሲሆን ወደ ለይቶ ማከሚያ ከተቀየረ ደግሞ አንድ ወር አልፎታል፡፡ የህክምና ማዕከል ከሆነ ጊዜ ጀምሮም ከ200 በላይ የኮሮና ተጠቂዎችንም አስተናግዷል፡፡
የህክምና ክትትል ሲያደርጉ ከነበሩት ታማሚዎች አንዳንዶቹ በማዕከሉ ውስጥ በድብቅ ጫት መቃም፣ ሲጋራ ማጨስና መሰል ድርጊቶችን ሲፈጽሙ እንደነበር ተደርሶበታል ያሉት ማናጀሩ፣ እነዚህንና መሰል ድርጊቶችን በህክምና ማዕከላት ውስጥ መፈጸም ያልተገባና የሚኮነን ተግባር በመሆኑ ለወደፊቱ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች እንደሚያሳዩት ባህሪ የሚገቡበት የህክምና ማእከላት ይለያያሉ ያሉት ዶክተሩ፣ በየካ ወረዳ ሰባት የሚስተናገዱት ምንም አይነት ምልክት ያልታየባቸውና ቀላል ምልክት ያሳዩ ታማሚዎች እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ሆኖም ቫይረሱን አቅልሎ በማየትና ለህክምና ተቋሙ ተገዢ ባለመሆን አንዳንዶች እንደ ጫት ሲጋራና መሰል ያልተፈቀዱ ነገሮችን በማስገባት በድብቅ ይጠቀሙ እንደነበር ተናግረዋል፡፡
ድርጊቱ የተፈጸመው ታማሚዎች ከቤተሰብ እቃ ሲላክላቸው በድብቅ በማስገባታቸው ሲሆን፤ ይህ አይነት ድርጊት ይኖራል ተብሎ ባለመታሰቡ የሚገቡት እቃዎች ላይ በወቅቱ ጠበቅ ያለ ፍተሻ አልነበረም ብለዋል፡፡
ድርጊቱ መፈጸሙን የህክምና ባለሙያዎች የህክምና ክትትል ለማድረግ በየክፍሎቹ ሲዞሩ ማረጋገጣቸውንም ዶክተር ወርቅነህ ገልጸው ሆኖም ደርጊቱ መፈጸሙ ከተረጋገጠ ወዲህ ጥብቅ ክትትልና ፍተሻ በማድረግ ማስቀረት መቻሉንም አስታውቀዋል፡፡
ዶክተር ወርቅነህ እንዲህ አይነት ተግባራትን በተለይ በህክምና ሥፍራዎች ውስጥ መፈጸም ህገ ወጥ መሆኑን ጠቅሰው፤ በማዕከሉ የሚገቡት ታካሚዎች ምንም እንኳን ጤነኛ መስለው ቢታዩም በውስጣቸው ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተረጋግጦ ስለገቡ በሽታው ይበልጥ እንዳይበረታባቸው፤ እንዲሁም በህክምና ማእከላት ያሉትን መመሪያዎችና ባለሙያዎችን በማክበር ጭምር ራሳቸውን ከመሰል ድርጊት መቆጠብ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በማዕከሉ ለ15 ቀናት ክትትል አድርጎ የወጡት አቶ ጎሳዬ ልመነህ በበኩላቸው ፤ የጤና ባለሙያዎች ሰዎች በቫይረሱ እንዳይያዙ ቀድመው መጠንቀቅ ይገባቸዋል ሲሉ የሚመክሩት ተግባራዊ አለማድረግ አንድ ጥፋት ሆኖ ሳለ በቫይረሱ ተይዘው ወደ ማገገሚያ ማዕከላት የሚገቡ ሰዎች መሰል አስጸያፊ ተግባራትን ማድረጋቸው ተገቢ አይደለም ሲሉ ድርጊቱን ተገቢ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡
አቶ ጎሳዬ በየካ ወረዳ ሰባት የኮሮና ህክምና ማእከል በተለይ ወጣቶች ወደ ማዕከሉ ከገቡ በኋላ ተደብቀው ጫት ሲቅሙ፣ ሲጋራ ሲያጨሱ፣ አልኮል መጠጦችን ከሀይላንድ ጋር በመቀላቀል ወደ ማዕከሉ በድብቅ ሲያስገቡና መሰል ያልተገቡ ድርጊቶችን ሲያከናውኑ መታዘባቸውን በመናገር፤ ተደጋጋሚ ድርጊት እንዳይፈጸም የማዕከሉ ሠራተኞች በዕቃዎች ላይ ጥብቅ ክትትል ማድረግ እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡
አዲስ ዘመን ነሐሴ 22/2012

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1 ሺህ 733 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው
***********
(ኢ.ፕ.ድ)
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 18 ሺህ 766 የላቦራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 733 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በትናንትናው ዕለት 586 ሠዋች ያገገሙ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በአገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 17 ሺህ 415 ሆኗል።
ካለፉት 24 ሰዓታት ምርመራ የ13 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ በኮሮናቫይረስ የተነሣ የሟቾች ቁጥር 758 ደርሷል።
በአሁኑ ወቅት 358 ሰዎች በጽኑ ሕክምና ላይ ሲገኙ፣ 29 ሺህ 965 ደግሞ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች መሆናቸው ተገልጿል።
በአጠቃላይ በአገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 48 ሺህ 140 ደርሷል።

"የፌዴራል መንግሥት ህውሓት እየሠራ ያለውን ግፍና በደል ሊቀለብስ የሚችል ሥራ እየሠራ አይደለም" - ዶክተር ሲሳይ መንግስቴ የፌዴራሊዝም መምህር
****************************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ፦ ህውሓት እየሠራ ያለው ግፍና በደል በጣም ሰፊ ቢሆንም የፌዴራል መንግሥት ይህንን ሊቀለብስ የሚችል ሥራ እየሠራ አይደለም ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌዴራሊዝም ትምህርት ክፍል መምህር ዶክተር ሲሳይ መንግስቴ አስታወቁ።
«የራያ ህዝብ የማንነት ጥያቄና የማዕከላዊ መንግሥታዊ ምላሽ ከአፄ ዮሐንስ እስከ ኢህአደግ» እና «በሴራ የተፈተነች ህይወት›› መፃሐፍ ደራሲና የፌዴራሊዝም መምህሩ ዶክተር ሲሳይ መንግስቴ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ህውሓት እየሠራ ያለው ግፍና በደል በጣም ሰፊ ቢሆንም የፌዴራል መንግሥት ይህንን ሊቀለብስ የሚችል ሥራ እየሠራ አይደለም ሲሉ አመልተዋል።
‹‹በጉዳዩ የፌዴራል መንግሥት ብዙ ጊዜ ጥያቄና ወቀሳ ቀርቦበታል። ዝምታው ግን ለምን እንደሆነ አይገባኝም።በተለይም የትግራይ ክልል የተደራጀ ኃይል ያለው እንደመሆኑ ያንን መመከት የሚያስችል እንቅስቃሴ እየተደረገ አይደለም›› ብለዋል።
ዝምታው ህዝቡ እንዳይጎዳ ከማሰብ የተነሳ ቀስ በቀስ አመራሩን ማዳከም የፈለገ እንደሚመስል በመጠቆምም፤ ሂደቱ በአንድ በኩል ትክክል ነው። ነገር ግን አንድ ቦታ ላይ ከሚወሰደው ዕርምጃ አኳያ አድሎ ሊመስል እንደሚችል አመልክተዋል።
የቀድሞ የሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አብዲ መሀመድ ኡመር በሱማሌ ክልል ችግር በፈጠረበት ጊዜ ወዲያውኑ ዕርምጃ መወሰዱን በምሳሌነት አስታውሰው፤ ትግራይ ላይ እንዲህ ዓይነት ችግር ሲፈጠር ለምንድን ነው ዝም የሚባለው? ሲሉም ጠይቀዋል።
ህወሓት በራያና በወልቃይት ህዝብን እያፈነ ይገኛል፣ እየተፈፀመ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው፤ ጉልበት ያለው እንዳሻው እያፈነ ሊቀጥል፤ ብዙም ጉልበት የለውም ተብሎ የሚታሰበውን ዕርምጃ የሚወሰድበት ሁኔታ መኖር የለበትም ብለዋል።
የህውሓት አክራሪ አመራር ላይ ጠበቅ ያለ ህጋዊ፣ አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ ዕርምጃ መወሰድ አለበት። በሂደት ደግሞ እያዳከመ ሄዶ ህዝብንና ድርጅቱን ለይቶ ጠንከር ያለ ዕርምጃ የሚወሰድበትን ሁኔታ ማሰብ በጣም አስፈላጊ እንደሆነም አመልክተዋል።
ህወሓቶች ምርጫ እናደርጋለን ብለው እያደረጉት ያለው የማዋከብ ሥራ በህዝቡ ላይ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሚባለው ሁሉ ሌላ ተጨማሪ የጎን ውጋት ሆኖበታል። በምርጫ ያልተመዘገበ ሰው በክልሉ መኖር እንደማይችል ተነግሮታል። በተለይም ፍቃደኛ ያልሆነ ወጣት በቤተሰቡ በኩል በግድ እንዲመዘገብ እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል።
እንደ ዶክተር ሲሳይ ማብራሪያ፤ የምርጫ ባህሪ ማንም ሰው በፍላጎት የሚመርጥበትን መብት ይሰጣል። ይሁን እንጂ ህወሓት ይህንን መብት በመጋፋት ከፍተኛ ተፅእኖ እያደረሰ ይገኛል። ተጽዕኖው በተለይ ራያና ወልቃይት ላይ በጣም በከፋ መልኩ የሚታይበት ሁኔታ አለ።
‹‹ምርጫውን ልክ የትግራይ ህዝብ የነፃነት መገለጫ አድርገው ነው እየቆጠሩት ያሉት። ህወሓት የአገሪቱን ህገመንግሥት ብቻ ሳይሆን የራሳቸውን ህገመንግሥት ጭምር የሚጥስ ሥራ እየሠራ ነው›› ሲሉም ነው የተናገሩት።
የክልሉን ልዩ ኃይል ቁጥር በመጨመር የማሳፈንና የማሰር ሁኔታ ተስፋፍቷል ያሉት ዶክተር ሲሳይ፤ በተለይ ሰሞኑን ‹‹ምርጫውን ይቃወማሉ፣ ያደናቅፋሉ ብለው የሚያስቧቸውን በርካታ ቁጥር ያላቸውን ወጣቶችን እያሰሩና እያስፈራሩ ናቸው። ማሳደዱና እንግልቱ በጣም በሚያስፈራ ሁኔታ የበለጠ ጨምሯል ብለዋል።
ወደትግራይ ክልል ለመሄድ በየአምስት ኪሎ ሜትሩ ባሉ ኬላዎች ላይ አስፈሪ ፍተሻ ይደረጋል፤ በገዛ አካባቢሽ ላይ ደርግ ያደርገው እንደነበረው ገበያ ቦታ ሳይቀር መታወቂያ ይጠየቃል። ከአንዱ ቀበሌ ወደ ሌላኛው ቀበሌ ለመንቀሳቀስ መታወቂያ ካልያዝሽ ከፍተኛ እንግልት ይደርሳል ሲሉም ተናግረዋል።
ራያ ቆቦና ራያ አላማጣ የተዋሃደ ቤተሰብ ቢሆንም በሁለት ክልሎች የሚተዳደሩ ናቸው። በመሆኑም የራያ ቆቦ አካባቢ ነዋሪ የአማራ ክልል መታወቂያ ይዞ ከተገኘ ተጨማሪ እንግልት ይገጥመዋል። እንዲህ ዓይነት ግፍና በደል በጣም ጎልቶ ወጥቷል። በመሆኑም ምርጫው ህገወጥ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ህዝቡን እያንገላቱበትና እያሰቃዩበት ያለ በመሆኑ በእጅጉ የሚወገዝና በእዚህ መልክ መቀጠል የማይገባው ነው ሲሉም አመልክተዋል።
አዲስ ዘመን ነሀሴ 23/2012

ዳያስፖራው ከ800 ሺ ዶላር በላይ ለህዳሴው ግድብ ድጋፍ አደረገ
*****************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ፡- በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የዳያስፖራው ማህበረሰብ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ከ800 ሺ ዶላር በላይ የቦንድ ግዢ ማከናወኑንና በስጦታ ማበርከቱን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት ዳያስፖራው ማህበረሰብ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ሲጀመር ጀምሮ ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት ቦንድ በመግዛት ስጦታ በማበርከትና በሙያው ድጋፉን ሲያደርግ ቆይቷል። በእነዚህም ዓመታት ከ42 ሚሊየን ዶላር በላይ ማስገባት የተቻለ ሲሆን፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ብቻ ሙሌቱ እስከተጀመረበት ቀን ደረስ ከ800 ሺ ዶላር በላይ የቦንድ ግዢና ስጦታ አከናውኗል።
ሀብት የማሰባሰቡ ሥራ በዘመቻ መልክ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በመጠቆምም በቀጣይ ዓመትም ከ200 ሚሊየን ብር በላይ ለማሰባሰብ አቅድ የተያዘ ሲሆን፤ ዘንድሮ ሙሌቱ ከተጀመረ በኋላ ኢትዮጵያ እያደረገችው ያለውን የድርድር ሂደትም በመላው ዓለም በእንግሊዝኛ፤ በፈረንሳይኛና በአረብኛ ቋንቋዎች የተለያዩ ሚድያዎችን በመጠቀም ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በስፋት ድጋፍ እየሰጡበት መሆኑን ገልጸዋል።
የኮሮና ቫይረስ መከሰትንም ተከትሎ ዳያስፖራው የተቻለውን ሲያደርግ ቆይቷል ያሉት ወይዘሮ ሰላማዊት እስከአሁን ከ300 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን፤ ይህም በሽታው እስከሚጠፋ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል ሃሳብን በነፃነት መግለጽም ሆነ መንግሥትን መቃወም መብት ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንዳንድ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ኤንባሲዎች አካባቢ እየተከናወኑ ያሉት ተግባራት ግን ከኢትዮጵያዊነት ስነ ምግባር ያፈነገጡ ብቻ ሳይሆን በህግ የሚያስጠይቁም ናቸው ብለዋል። በመሆኑም ማንኛውም ሰው ያለውን ጥያቄም ሆነ ተቃውሞ ስርዓት በጠበቀና የሀገርን ክብርና ሉአላዊነት በማይነካ መልኩ ማቅረብ እንዳለበት አሳስበዋል።

“የእንጦጦና ሸራተን አካባቢ ፓርኮች ለሌሎች ፕሮጀክቶች የልምድ ማሳያ መሆን ይችላሉ" አምባሳደር ደግፌ ቡላ
*****************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ፡- ሸገርን የማስዋብ አካል የሆኑት የአንጦጦ የሸራተን አካባቢ ፓርክ ግንባታዎች በመላ ኢትዮጵያ ተግባራዊ ለሚደረጉ ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ የልምድ ማሳያ መሆን እንደሚችሉ አምባሳደር ደግፌ ቡላ ተናገሩ።
የፌዴራል የፍትህ፤ የህግ ጥናትና ምርምር ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ደግፌ ቡላ አንድነት እና እንጦጦ ፓርኮችን ከጎበኙ በኋላ እንደገለጹት፤ በሸገር ማስዋብ ፕሮጀክት ስር ያሉት የሸራተን አካባቢ አረንጓዴ ፓርክን እና እንጦጦ ፓርክ በአጭር ጊዜያት ተጠናቀው ጎብኚዎችን ማስተናገድ በመቻላቸው በተለያየ መንገድ በቀጣይ ሊገነቡ ለታሰቡ ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች የልምድ ማሳያ በመሆን ማገልገል ይችላሉ።
ፓርኮቹ በአጭር ጊዜ በመጠናቀቃቸው በአንድ በኩል በግንባታ ፍጥነት ረገድ ተሞክሮ ለማካፈል እንደሚረዱ የገለጹት አምባሳደር ደግፌ፤ በሌላ መልኩ ደግሞ ተፈጥሮን እና ሰው ሠራሽ መዝናኛዎችን በአንድ መያዝ በመቻላቸው በቱሪዝም ዘርፉ ያሉ አማራጮችን በሌሎች ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ለማድረግ በር ከፋች መሆናቸውን ተናግረዋል።
እንጦጦ ከዚህ ቀደም በባህር ዛፍ የተሸፈነ በመሆኑ በአካባቢው ያሉ እናቶቻችን እንጨት እና ቅጠል የሚለቅሙበት ቦታ መሆኑን አስታውሰው፤ ማንም ሰው እስከአሁን ዞር ብሎ ያላየው ልዩ ሀብት ያለበት ቦታ እንደነበረ ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ለውጥ ከመጣ በኋላ ግን ዶክተር አብይ አህመድ በወሰዱት ዕርምጃ ለትውልድ የሚተላለፍ መዝናኛ ማልዕከል መገንባቱ በዘርፉ ትልቅ ልምድ ያስገኘ መሆኑን አስረድተዋል።
በተመሳሳይ የሸራተን አካባቢ እና የአንድነት ፓርኮች ከአዲስ አበባ ውጪ ሊገነቡ ለታሰቡ ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች በሥራ ጥራት እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ረገድ ትልቅ ተሞክሮ ማካፈያ መሆን እንደሚችሉ ገልጸዋል።
እንደ አምባሳደር ደግፌ ከሆነ፤ ገበታ ለሀገር በሚል ምዕራፍ ሊገነቡ ለታቀዱ በኦሮሚያ ክልል ለሚገኘውን የወንጪ ሐይቅ ፤ በአማራ ክልል የሚገኘውን ጎርጎራን እና በደቡብ ኢትዮጵያ ለሚገኘውን የኮንታ ኮይሻ ፕሮጀክቶች ውጥን መሳካት ከሸገር ማስዋብ ፕሮጀክት ተግባራዊ ልምድ መውሰድ ይቻላል።
በተመሳሳይ በመላ ኢትዮጵያ መልማት የሚችሉ አካባቢዎች ላይ ፕሮጀክቶችን በማዘጋጀት ለነዋሪው ንጹህ አየርን ማስገኘት ብቻ ሳይሆን ሀብት መሰብሰብ እንደሚቻል የሸገር ፕሮጀክቶች በአይን የሚታይ ትምህርት ሰጪ ናቸው ብለዋል።
ከዚህ ቀደም ባለው ልምድ የውጭ ሀገራት ጎብኚዎች በተለይም የአፍሪካ መሪዎች አዲስ አበባ ሲመጡ በቅርበ የሚያገኙትን ሉሲን ብቻ ጎብኝተው እንደሚመለሱ ያስታወሱት አምባሳደር ደግፌ፤ ከዚህ በኋላ ግን በመዲናዋ ሊጎበኙ የሚችሉ በርካታ አማራጮች በመስፋፋታቸው የዲፕሎማቶችም ሆነ የጎብኚዎችን የቆይታ ጊዜ በማራዘም ተጨማሪ ገቢ ለሀገር ማስገባት የሚያስችል ዕድል እንደተፈጠረ ገልጸዋል።
በመሃል ከተማ የተገነቡትን ፓርኮች እና እንጦጦ ፓርክን መመልከት ቢቻል በአጭር ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ ምን ያክል ለቱሪዝም ምቹ የሆነች ሀገር እንድትሆን እየተሠራ እንዳለ መገንዘብ እንደሚቻል ተናግረዋል። በዚህ ረገድ ፓርኮቹን እንደእራስ ሀብት በመንከባከብ ለቀጣዩ ትውልድ የሚተላለፉበትን መንገድ ማሰብ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።
የእንጦጦ እና ሸገር ፓርኮች ጥሞናን ለሚፈልጉ የህግና ጥናትና ምርምሮች ወሳኝ ቦታዎች መሆናቸውን የተናገሩት አምባሳደር ደግፌ፤ በዚህ ረገድ የሀገር ውስጥ ምሁራንም ሆነ በኢንስቲትዩቱ በኩል ከውጭ ሀገራት ለጥናት የሚመጡ ምሁራንን ወደፓርኮቹ በመጋበዝ አዳዲስ ሃሳቦችን እንዲያፈልቁ ጥረት እንደሚደረግ ገልጸዋል።
መጥፎ ሃሳብ ለሰው ልጅ ውድቀት ምክንያት እንደሚሆን ሁሉ ፓርኮቹን ለመገንባት የቻሉ ሃሳቦች ደግሞ ልማትን በመፍጠራቸው ሊደነቁ ይገባቸዋል። በዚህ ረገድ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ለዚህ ሥራ የጣሩ የሥራ ባልደረቦች በሙሉ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
አዲስ ዘመን ነሀሴ 23/2012
ጌትነት ተስፋማርያም

ብሔራዊ ሙዚየም በኮሮና ምክንያት 150 ሺ ጎብኚዎችን አጥቷል
***************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ:- ኮሮና ወረርሽኝ ወደ ኢትዮጵያ ከገባ ጀምሮ የጉብኝት አገልግሎቱ በመቋረጡ በአምስት ወራት ውስጥ 150 ሺ ጎብኚዎችን ማጣቱን ብሔራዊ ሙዚየም አስታወቀ።
በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን የብሔራዊ ሙዚየም ዳይሬክተር አቶ ኤፍሬም አማረ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ የኮሮና በሽታ ወደኢትዮጵያ ከገባ ከመጋቢት 15 ቀን 2012 ጀምሮ የብሔራዊ ሙዚያም ለጥንቃቄ ሲባል ለጎብኚዎች ዝግ ሆኖ ቆይቷል። በዚህም ምክንያት ባለፉት አምስት ወራት ሙዚየሙን ሊጎበኙ ለሚችሉ 150ሺህ ሰዎች አገልግሎት መስጠት አልተቻለም።
ቀደም ባለው ጊዜ ባለው ልምድ መሰረት ብሔራዊ ሙዚየምን በየቀኑ የሚጎበኙ ሰዎች ቁጥር በአማካይ አንድ ሺ ይደርሳል። በተለይ በክረምት ወቅት ከትምህርት ቤቶች እና ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙዚየሙን ለመጎብኘት የሚመጡ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጨምር አመልክተው፣ የውጭ ሃገራት ጎብኚዎችም በብዛት ወደኢትዮጵያ እንደሚመጡ የሚጠበቅበት ወቅት እንደነበር አስታውቀዋል።
ሙዚየሙ በኮሮና በሽታ ምክንያት ሲዘጋ አገልግሎቱን ማግኘት ካልቻሉ 150 ሺህ ሰዎች መካከል 45ሺህ የሚሆኑት ከውጭ ሀገራት የሚመጡ ጎብኝዎች እንደሚሆኑ ይገመታል ያሉት አቶ ኤፍሬም፤ ጎብኚዎቹ በመቅረታቸው የባህል እቃዎች እና አልባሳት አቅራቢዎችን
ገቢ ክፉኛ እንደጎዳው ተናግረዋል።
በተለይ ከዚህ ቀደም በነበረው ልምድ መሰረት አብዛኛዎቹ ሙዚየሙን የጎበኙ የውጭ ዜጐች በመቀጠል የሃገር ባህል አልባሳትን ለመግዛት ወደሽሮ ሜዳ እና አካባቢው ያቀኑ እነደነበር አስታውሰዋል። አሁን ላይ ግን ጎብኚዎቹም ባለመኖራቸው የሽሮሜዳ ነጋዴዎችም ገቢ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳሳደረ ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅተ በተለያዩ ዓለማት የሚገኙ ሙዚየሞች የኮሮናን በሽታ ባገናዘበ ሁኔታ ጥንቃቄ እያደረጉ በከፊል አገልግሎት ወደመስጠት መሸጋገራቸውን የተናገሩት አቶ ኤፍሬም ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየምም በቀጣይ በቁጥር የተወሰኑ ጎብኚዎችን እያስተናገደ እንዲሠራ ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቄ መቅረቡን አስታውቀዋል።
በጉዳዩ ላይ ውይይት እየተደረገ በመሆኑ በ2013 ዓ.ም መስከረም ወር አጋማሽ ጀምሮ ሙዚየሙ በከፊል አገልግሎት ሊጀምር እንደሚችል ቅድመ ግምት መቀመጡን ገልጸዋል። ሙዚየሙ እስኪከፈት ድረስ ግን ለዝግጅት የሚረዱ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመዋል።
ብሔራዊ ሙዚየም ዝግ በሆነባቸው ጊዜያት መጠነኛ ጥገና እንደተረገለት የገለጹት አቶ ኤፍሬም፤ ፍሳሽ ያስገባ የነበረው ጣሪያው ሙሉ እድሳት እንደተደረገለት ተናግረዋል። ለእድሳቱም ከ300ሺ ብር በላይ ወጪ መሆኑንም ገልጸዋል።
በተጨማሪ ሙዚየሙ በሳምንት አንድ ጊዜ እየተከፈተ አስፈላጊው የፅዳት አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ጠቁመው፤ በሙዚየሙ ብቻ የሚገኙ ከሁለት ሺ በላይ ቅርሶችም ያለምንም ጉዳት በመልካም ይዞታ ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።
እንደ አቶ ኤፍሬም ከሆነ፤ የሉሲ ቅሪተ አካል እና ሌሎችም ቅሪት አካላት ጉዳት ቢደርስባቸው ምንም መተኪያ ስለሌላቸው በሳይንሳዊ ዘዴ የተሠራላቸው አምሳያ /ሳይንቲፊክ ሪፕሊካ/ በሙዚየሙ ውስጥ ተቀምጧል። ትክክለኛዎቹ ቅሪት አካላት ግን ለጥንቃቄ ሲባል በቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ሕንፃ ውስጥ ተቀምጠው ለወሳኝ ጥናትና ምርምር ሥራ ሲፈለጉ ብቻ ክፍት ይደረጋሉ ብለዋል።

ከጣና የሚገኘው የዓሣ ምርት በ1 ሺ 700ቶን ቀንሷል
****************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ፡- በእንቦጭ አረም እና ተያያዥ ችግሮች የተነሳ ከጣና ሐይቅ በዓመት ይገኝ የነበረው የዓሣ ምርት በ1 ሺ 700ቶን መቀነሱ ተገለጸ። እንቦጭ አረም በዓሣ ሀብትና አጥማጆች ሕይወት ላይም በከፍተኛ ደረጃ እያዛባ መሆኑም ተገልጿል። ከ9,000 ወደ 7,000 ቶን መቀነሱ የባህርዳር የዓሣና ሌሎች የውሃ ውስጥ ህይወት ምርምር ማዕከል ተመራማሪና የማዕከሉ ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ተዋበ በተለይም ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ በጣና ሐይቅ ላይ የዓሣ አስጋሪዎች ቁጥርና የምርቱ ተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ ቢሆንም ከሐይቁ የሚገኘው ምርት በከፍተኛ ደረጃ እየነቀሰ ነው።
ተመራማሪ ጥናቶችን ዋቢ አድርገውእንዳስታወቁት፤ በቅርቡ በተካሄደው ጥናት 5 ሺ 4,000 ዓሣ አስጋሪዎች በዓመት 7 ሺ 300 ቶን ዓሣ አምርተዋል። እ.ኤ.አ በ2013 በፈረንጆች አቆጣጠር 3 ሺ 114 አስጋሪዎች በነበሩበት ወቅት ግን 9,000 ቶን አምርተው ነበር። ይህ የሚያሳያው የዓሣ አጥማጆች ቁጥር እና የምርቱ ተጠቃሚዎች ፍላጎት እየጨመረ ሲሄድ ዓሣ ሀብቱ እየቀነሰ ነው።
ለምርቱ መቀነስ አንዱ ምክንት የእንቦጭ አረም መስፋፋት እንደሆነ ተመራማሪው አመልክተው፤ እንቦጭ በባህሪው በፍጥነት እና በስፋት የሚራባና የሚባዛ መሆኑን አስታውቀዋል።
"አረሙ በቅድሚያ የዓሣ መራቢያ ቦታ ይይዛል፣ የዓሣ ዕንቁላልም ለመራባት ምቹ ሁኔታ አያገኝም። በተጨማሪም የፀሐይ ብርሃን ወደ ውሃ ውስጥ እንዳይገባ ያደርጋል። እንቦጩ ሲወገድና ሲሞት በሐይቁ ውስጥ ሌላ ኬሚካል የሚለቅ በመሆኑ በውሃ ውስጥ ያለውን የአየር ዝውውር ያዛባል" ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት በጣና ሐይቅ ላይ የተከሰተው እንቦጭ አረም የዓሣ ዋንኛው የመራቢያ ስፍራ የሆነውን ቦታ መያዙን ያመለከቱት ተመራማሪው፣ ይህም በቀጥታ በዓሣ መራባትና ሀብት ዕድገት ላይ ተፅዕኖ እየፈጠረ እንደሚገኝ አመልክተዋል።
ከሐይቁ ምሥራቃዊ ክፍል በእንቦጭ ክፉኛ መጠቃቱን ያመለከቱት ተመራማሪው፤ አካባቢው በታንኳ ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ እየሆነ በመምጣቱ የዓሣ ማስገር ሥራውን አስቸጋሪ አድርጎታል ብለዋል። ዓሣ ማስገሪያ መረቦች ዓሣ ከመያዝ ይልቅ በእምቦጭ እየተሞሉ መሆኑንም አስታውቀዋል።
እንቦጭ ዓሣን ጨምሮ ሌሎች ሃይቅ ውስጥ የሚኖሩ እንስሳት የሚመገቧቸውን ዕጽዋት በማጥፋትቀዳሚ እንደሆነ ያመለከቱት ተመራማሪው፣ ችግሩ የዓሣ ዝርያ እና መጠንን በመቀነስ አደጋ መፈጠሩን ገልጸዋል።
በበጋ ወቅት ጣና ውሃ ሲቀንስ አርሶ አደሩ ጣና ዙሪያ (ባህረ ሸሽ) እርሻ የሚያካሂድ ሲሆን፤ ቀደም ሲል አንድ አርሶ አደር ብቻውን 0 ነጥብ 25 ሄክታር መሬት ለማረስ ይችል ነበር ብለዋል። የእቦጭ አረም ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ ግን 0 ነጥብ 25 ሄክታር መሬት ለማረስ 9 ሰው ማስፈለጉን አመልክተዋል። ይህም እንቦጭ እያስከተለ ያለውን ዘርፈ ብዙ ችግር ተጨማሪ አንድ ማሳያ እንደሆነ ጠቁመዋል።
የባህርዳር የዓሣና ሌሎች የውሃ ውስጥ ህይወት ምርምር ማዕከል በ1992 ዓ.ም የተመሰረተ ማዕከል ሲሆን፤ ዘርፈ ብዙ የምርምር ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል።
አዲስ ዘመን ነሀሴ 23/2012
ክፍለዮሐንስ አንበርብር

መስቀል አደባባይ ዓለም አቀፍ ደረጃን በጠበቀ መልኩ ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን ጠ/ር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
ታሪካዊውን መስቀል አደባባይ ዓለም አቀፍ ደረጃን በጠበቀ መልኩ ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታውቀዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ“ባለፉት ጥቂት ወራት በመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ያለ መታከት ሲደክሙ በቆዩት ወገኖች እጅግ ተደንቄያለሁ” ብለዋል፡፡
በዚህኛው ዙር በአጠቃላይ 5 ሺህ ያህል ሠራተኞች የተሳተፉ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህንን ታሪካዊ አደባባይ ዓለም አቀፍ ደረጃን በጠበቀ መልኩ ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን አስታውቀዋል።

“ድሮን እየኖሩ ትውልዱን ወደኋላ እየመለሱ መስዋዕት የሚያደርጉ ፖለቲከኞች ጡረታ ሊወጡ ይገባል”አቶ ሙሳ አደም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ
*********************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ፡- በድሮ አስተሳሰብ እየኖሩ በአዲሱ ኃይል ጉልበት፤ ዕጣ ፋንታ፤ የወደፊት ራዕይ ላይ በመጫወት መስዋዕትነት የሚያስከፍሉት ፖለቲከኞች ጡረታ መውጣት እንደሚገባቸው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ሙሳ አደም ገለጹ።
የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ሙሳ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት፤ የዓለም ፖለቲካ በጣም ተለዋዋጭ ነው። ትናንት የነበረው የፖለቲካ አረዳድ ዛሬ አይሠራም፤ የለምም። በእኛ አገር ፖለቲካ ትናንት የሁልጊዜ ውሎ ነው። ገና ኃይለስላሴና ምኒልክ ዘመንን ያልተሻገረ ፖለቲከኛ ይዘን ቀጥለናል። ይህ ሁኔታ አገርን ስለማያሻግር እነዚህ ፖለቲከኞች ጡረታ ሊወጡ ይገባል። በምትኩ የሚሠራ ኃይል ወንበሩን መረከብ አለበት።
እነዚህ አካላት በጊዜያቸው ወቅቱ የሚጠይቀውን መንገድ ሂደው ብዙ ሠርተዋል፤ ለአገርም ያበረከቱት ነገር አለ። ይሁንና ‹‹እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል›› አባባላቸው ዛሬም ቀጥሏል። ይህ ደግሞ ወጣቱን እንዳይሠራና አገሩን እነርሱ በሠሩት ላይ ጨምሮ እንዳያሻግር እንቅ ፋት ሆነውበታል ብለዋል። ሀገራዊ ፖለቲካውና ፖለቲከኛው እንዲሻሻል ከተፈለገ እነዚህ ዘመናቸው ያበቃ ፖለቲከኞች ለተተኪው ወንበር መለቀቅ እንደሚኖርባቸው አስታውቀዋል።
የቀድሞ ሀገራዊ የፖለቲካ አካሄድ መልካምም መጥፎም ታሪኮች እንደነበሩት የሚያነሱት አቶ ሙሳ፤ በዘመናቸው የነበረው የፖለቲካ አረዳድ ይህንን እንዲያደርጉ አስገድዷቸዋልና አድርገውት አልፈዋል። አገርንም ለዛሬው ትውልድ ሠርተውለታል። ሆኖም ያንን ታሪክ አድርገን እንጂ ኑሯችን አድርገን መቀጠል የለብንም። ታሪኩ እንደ ታሪክነቱ ይነበብ፤ ይታወቅ፤ እውነታውን ሁሉም ይረዳው፤ ነገር ግን በዚያ ታሪክ እንድንኖር ሊፈረድብን አይገባም ብለዋል።
ትውልዱ ነገው እንዲበላሽ መፍቀድ የለበትም የሚሉት ሰብሳቢው፤ ዛሬ ብዙ ነገሮች ተለውጠዋል። በዛሬው አካሄድ የዛሬው ትውልድ መሠራት አለበት። ነገን እያነሱ ትውልዱን ወደትናንት መውሰዱና ማበጣበጡ አገርን ወደኋላ ከመመለስ አይተናነስም። በተለይ ፖለቲከኛው የትናንቱን ለትናንት በመተው ዛሬ በራሱ መንገድ እንዲሻገር እና ለውጥ እንዲመጣ ለተተኪዎች ቦታውን መልቀቅ እንደሚኖርበት አመልክተዋል።
አገሪቱ በርከት ያሉ በእውቀት መምራትና መሥራት የሚችሉ ወጣት ፖለቲከኞች አሏት፤ እነዚህን ወደ ሥራ ማስገባት ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ የሚገልጹት አቶ ሙሳ፤ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ያለፉት ዓመታትን የምንኖርበት ሊሆን አይገባምና ተሠርታ ያለቀችውን ኢትዮጵያን እንዲሠሩ ለትውልዱ እንፍቀድ ብለዋል።
የቀደሙት የትናንት ፖለቲከኞች ሌላ ሰው እንዲመጣባቸው አይፈልጉም፤ ወጣት ፖለቲከኛን ማየት ያማቸዋል ያሉት አቶ ሙሳ ፤ ይህ ደግሞ በሀገሪቱ ፖለቲከኛም ሆነ ፖለቲካው እንዳይፈጠር ከማድረጉም በላይ ወጣቱን የእሳት እራት እንጂ ባለተስፋ አላደረጉትም ብለዋል። የመሥራት ባህልን እንዲያዳብር እንዳልረዱትም አመልክተዋል።
እንደ አቶ ሙሳ ገለጻ፤ የተማረና የተመራመረ፤ የተሻለውን ለአገር ለማምጣት የሚጥር፤ ጉልበት ያለው ሯጭ ፖለቲከኛ አገር ያስፈልጋታል። እንደውም ‹‹ የተማረ ይግደለኝ›› እንደሚባለው የአገር ፖለቲካ መፈጠር የሚጀምረው ፖለቲከኛውም ፖለቲካውም በእውቀትና በአዲስ አስተሳሰብ ሲቃኝ ብቻ ነው። ስለሆነም የወቅቱን የፖለቲካ ጽንሰሃሳብ ያልተረዱ ሰዎች እየመሩ ግራ ከሚያጋቡ ጡረታ መውጣቱ ለነሱም ለሀገርም እንደሚበጅ ጠቁመዋል።
ፓርቲ የሚባለውም በዘመድ ተሰባስቦ የሚመሰረት ነው። ይህ ደግሞ አገር ለመምራት ሳይሆን ቤተሰብ ለማስተዳደር ብቻ የሚያስብ የሚያደርገው ተግባር ነው። እናም መሰረታዊ የፓርቲ ቁመና ያለው በሃሳብ ልዕልና የሚያምን ፓርቲ ከሌለ ፖለቲካም ፖለቲከኛም ሊፈጠር አይችልም።
ሁለቱም ያለመኖራቸው መንስኤ ነው አሁን ለአገር ፈተናና ዋጋ ማስከፈል ያበቃው ብለዋል። ፓርቲው እንደ ፓርቲ የሚሠራው ሥራ የለም። ህዝቡም ከፓርቲው የሚጠብቀውን እያገኘ አይደለም። ስለዚህም ህዝብ ከመጠቀም ይልቅ በችግር ውስጥ ተዘፍቆ ዓመታትን ዋጋ እየከፈለ እንዲኖር መደረጉንም አመልክተዋል።
ዘመኑን ያልዋጀ፤ አገርን ከፍ ለማድረግ በማያስችል ጉዳይ ላይ መስዋዕት እየከፈልን ነው የሚሉት አቶ ሙሳ፤ ትውልዱን በማደንቆር የተካኑ ፖለቲከኞች ጡረታ ይውጡና አዳዲስ የፖለቲካ አስተሳሰብና እውቀቱ ያላቸው አካላት ወንበሩን ይረከቡ ብለዋል።
ሀገራዊ የፖለቲካ አካሂዶች በመርህ፤ በፖሊሲ ላይ የተመሰረቱና ከአገርና ከህዝብ ጥቅም አንጻር የተቃኙ መሆን መቻልም አለባቸው። በዚህ ላይም በስፋት መሥራት መጀመር አለብን ሲሉም ተናግረዋል።
አዲስ ዘመን ነሐሴ 24/2012