Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
343 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️

በጉለሌ ክፍለ ከተማ በአስከፊ ችግር ውስጥ ለሚገኙ የሃገር ባለውለታዎች አቅመ ደካሞች እንዲሁም ለአካል ጉዳተኛ ነዋሪዎቻችን 133 የመኖሪያ ቤቶች ቁልፍ አስረክበናል::

እነዚህን አላግባብ ተይዘዉ የነበሩ ቤቶች ህብረተሰቡን በማሳተፍ ለሚገባዉ ሰው ያስተላለፍን ሲሆን ይህም የክፍለ ከተማዉ ነዋሪዎች የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ምላሽ ነው::
ለነዋሪዎችዋ የምትመች ማህበራዊ ፍትህ የነገስባት አዲስ አበባን እውን ለማድረግ ህዝባችንን በላቀ ትጋት ማገልገላችንን እንቀጥላለን!!
ሐምሌ 12 ቀን 2015 ዓ.ም የስራ ማስታወቂያ‼️
የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር መደበኛ ጉባዔውን ጀመረ
***
(ኢ.ፕ.ድ)

የአማራ ክልል ምክር ቤት ከሐምሌ 12 እስከ 14/2015 ዓ.ም የሚካሄደውን 6ኛ ዙር፣ 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 6ኛ መደበኛ ጉባዔውን ጀምሯል።

በጉባዔው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ የተከበሩ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋየ በበጀት ዓመቱ በክልሉ የተያዙ የልማት ሥራዎች አፈጻጸም የሚያበረታታ ነበር ብለዋል።

የክልላችንን ብሎም የሀገርን ኢኮኖሚ ለማሳደግ በስንዴ ልማት፣ በእርሻ ሜካናይዜሽን እንዲሁም በአረንጓዴ አሻራ እና በትምህርቱ ዘርፍ በከፍተኛ ንቅናቄ የተሠራበት ዓመት እንደነበርም ገልጸዋል።

የማዳበሪያ እጥረት የወለደው የሕገወጦች መበራከት በክልሉ አርሶ አደሮች በኩል ቅሬታን የፈጠረ መኾኑን የገለጹት አፈ ጉባዔዋ ለጉዳዩ ዘላቂ እልባት ለመስጠት የጋራ ርብርብ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

አፈ ጉባዔዋ "የክልሉ ሕዝብ የመጀመሪያ ጥያቄ ልማት እና የሕግ የበላይነት መከበር ነው" ሲሉ ገልጸዋል።

መንግሥት የመሪነቱን ተግባር በትክክል በመወጣት የሕዝቡን ጥያቄ ፈጥኖ መመለስ አለበት ሲሉም ተናግረዋል። በተለይም ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት በመኾኑ መላ የክልሉ ሕዝብ ከመንግሥት ጎን በመቆም ሰላሙን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ነው ያሉት።

ምክር ቤቱ በሦስት የጉባዔ ቀናት ልዩ ልዩ ተግባራትን የሚያከናውን ሲኾን ከነዚህም መካከል:-

👉 የመደበኛ ጉባዔውን አጀንዳዎች እና ቃለ ጉባዔ መርምሮ ማጽደቅ
👉 የክልሉን አስፈጻሚ አካላት የ2015 በጀት ዓመት የ11 ወር እቅድ አፈጻጸም የተጠቃለለ ሪፖርት መርምሮ ማጽደቅ
👉 የክልሉን ፍርድ ቤቶችን የ2015 በጀት ዓመት የ11 ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት መርምሮ ማጽደቅ
👉የአማራ ክልል የ2016 በጀት ዓመት ጥቅል የበጀት ጣሪያ አመዳደብ እና የወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች የድጎማ በጀት ቀመር እና የ2016 በጀትን ለማጽደቅ የበጀት አስተዳደሩን ለመወሰን የወጣ አዋጅን መርምሮ ማጽደቅ
👉 የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች የ2016 በጀት ዓመት በጀትን መርምሮ ማጽደቅ
👉 የክልሉን ኦዲት መሥሪያ ቤት የ2016 በጀት ዓመት በጀቱን መርምሮ ያጸድቃል
👉የምክር ቤቱን የ2016 በጀት ዓመት በጀቱን መርምሮ ማጽደቅ እና
👉 ልዩ ልዩ ሹመቶችን መርምሮ ማጽደቅ በአጀንዳነት ተይዘዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል።

ሐምሌ 12 ቀን 20115
በኦሮሚያ ክልል የ600 ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ተጀመረ
****************
(ኢ ፕ ድ)

በኦሮሚያ ክልል የትምህርት ንቅናቄውን መሠረት በማድረግ 600 የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ግንባታ መጀመሩን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለፀ። ከ86 በመቶ በላይ የክልሉ ትምህርት ቤቶች ደረጃቸውን ያልጠበቁ መሆናቸው ተመልክቷል።

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ግርማ ባይሳ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻል ንቅናቄ መሠረት 600 የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች በሁሉም ገጠር አካባቢዎች ለመገንባት ታቅዶ ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=104876
አገልግሎቱ ከአንድ ሺ 700 በላይ ሀሰተኛ ማስረጃዎች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ አድርጓል
****************
(ኢ ፕ ድ)

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት በተጠናቀቀው 2015 በጀት ዓመት አንድ ሺ 733 ሀሰተኛ ማስረጃዎች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ በማድረግ ሊደርስ የነበረ ጉዳት ማስቀረት መቻሉን አስታወቀ፡፡

ተቋሙ በበጀት ዓመቱ አንድ ሚሊዮን 524 ሺ 583 ተገልጋዮችን አስተናግዶ አንድ ነጥብ 77 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉንም ገልጿል፡፡

የአገልግሎቱ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዓለምእሸት መሸሻ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ አንድ ሺ 733 ሀሰተኛ ማስረጃዎች ጥቅም ላይ ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=104871
የካፒታል ገበያ ምጣኔ ሀብታዊ ትሩፋቶች
*************
(ኢ ፕ ድ)

በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያን በ2016 ዓ.ም ለማስጀመር ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል። በአሁኑ ወቅትም አብዛኛው የዝግጅት ሥራ እየተጠናቀቀ መሆኑን ባለሥልጣኑ በቅርቡ አስታውቋል። ይህ የገበያ ሥርዓት በኢትዮጵያ መጀመሩ በምጣኔ ሀብት ላይ ብዙ ትሩፋት እንዳለው የዘርፉ ምሁራን ይናገራሉ። ።

በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማርኬቲንግ ማኔጅመንት ምሁር ፕሮፌሰር ብርሃ ቡርጂ እንደሚሉት፤ በተለይ የካፒታሊስት ሀገራት የሚባሉት የካፒታል ገበያን በሰፊው ይጠቀማሉ። ሕንድ ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=104886
የጋምቤላ ክልል ከመኸር እርሻ 4 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት እየሠራ ነው
*************************
(ኢ ፕ ድ)

በ2015/16 ዓ.ም የመኸር ምርት ዘመን አራት ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት አቅዶ እየሠራ መሆኑን የጋምቤላ ክልል የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ኃላፊ አቶ አጃክ ኡቻላ ኝጌሎ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በ2015/16 ዓ.ም የመኸር ምርት ዘመን ከ156 ሺህ 226 ሔክታር በላይ መሬት በዘር በመሸፈን አራት ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ኩንታል ምርት ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=104889
የአጣጥ ማዞሪያ – ሌራ የመንገድ ፕሮጀክት ከተያዘለት ጊዜ አስቀድሞ ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው
*******************
(ኢ ፕ ድ)
በጉራጌ ዞን ከአጣጥ ማዞሪያ – ጉንችሬ – ቆሴ – ጌጃ – ሌራ ድረስ እየተሠራ ያለው የመንገድ ፕሮጀክት ከተያዘለት ጊዜ ቀድሞ ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አስታወቀ።

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የቡታጅራ አካባቢ ግንባታ ፕሮጀክት ማኔጅመንት ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ገዛኸኝ ዋክቶሌ እንደገለፁት፤ የአጣጥ ማዞሪያ – ጉንችሬ – ቆሴ – ጌጃ – ሌራ የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት በሦስት ዓመታት ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=104896
"የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ከኢትዮጵያ ባሻገር አለም አቀፍ አጀንዳ ሆኗል" - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
********************
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር አለም አቀፍ አጀንዳ እየሆነ ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ገለፁ። ከኢትዮጵያ ባሻገር የአፍሪካ ጉዳይ ስለመሆኑም ጠቁመዋል።

የአረንጓዴ ዲፕሎማሲና በኬንያ ናይሮቢ የተካሄደው 43ኛው የአስፈጻሚዎች ስብሰባ ስኬታማ ነበር ብለዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ዲፕሎማሲ ክንውኖችን አስመልክቶ ለአገር ውስጥና ለውጭ አገር መገናኛ ብዙሃን በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ለአገር የገጽታ ግንባታ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር አለም አቀፍ አጀንዳ እየሆነ ነው። ከኢትዮጵያ ባሻገር የአፍሪካ ጉዳይ ስለመሆኑም ጠቁመው የአረንጓዴ አሻራ በአገር ደረጃ ታሪክ የተሰራበት ነውም ብለዋል።

ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ ያደረጉ ኤምባሲዎች፣ አለም አቀፍ ተቋማትና ድርጅቶች በአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር መሳተፋቸውን ጠቅሰው ለተሳትፏቸውም ምስጋና አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር የተባበሩት መንግስታት አጀንዳ እንደነበር አስታውሰዋል። በጥቅሉ አለም አቀፍ ተቀባይነት እያገኘ መንጣቱን ተናግረዋል። ።

የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ተጠናክሮ እንዲቀጥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የገንዘብ ማፈላለግ ሃላፊነቱን እንደተወጣም ገልጸዋል።

በሞገስ ጸጋዬ

ሐምሌ 12 ቀን 2015 ዓ.ም