Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
343 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
"በአረንጓዴ አሻራ ያመጣነውን ስኬት በሌሎች የልማት ዘርፎች መቀጠል አለበት"አምባሳደር ብርቱካን አያኖ
******
(ኢ ፕ ድ)

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች በድሬደዋ የነጻ ንግድ ቀጠና ውስጥ በዛሬው ዕለት አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።
በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ላይ አምባሳደር ቡርቱካን አያኖ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች ችግኞች ተሳትፈዋል።

አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በአረንጓዴ አሻራ ያመጣነውን ስኬት በሌሎች የልማት ዘርፎች መቀጠል አለበት ብለዋል ።

አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ይህ ልዑክ የመጣንበትን አላማ ያሳካ እና የመስተጋብሩን ያጠናከረ መሆኑን ገልፀው በቀጣይነት የተተከሉ ችግኞች እንዲፀድቁ ክትትል እናደርጋለን ብለዋል ።

ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ እና ጥበቃ እየሰራች ያለችው ተግባራ ለመጭው ዘመን ትውልድ አኩሪ እና በታሪክ ውስጥ ሲጠቀስ ይኖራል ብለዋል ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት ፣ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ኢኒስቲትዩት ሰራተኞች አምባሳደሮች ፣ ዲፕሎማቶች እና ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ከትናንት ጀምሮ ሐረር ከተማ እና በዛሬው እለትም በድሬዳዋ ከተማ ችግኝ ተክለዋል።
ከአረንጓዴ አሻራ መረሃግብሩ በተጨማሪ በድሬደዋ የነጻ ንግድ ቀጠና ውስጥ የሚገኝ የመኪና መገጣጠሚያን እና የደረቅ ወደብን የልዑካን ቡድኑ ጎብኝቷል።

ሐምሌ 11 ቀን 2015 ዓም
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የባህል ሙዚየም ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ
********************
(ኢ ፕ ድ)

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ‘ከመደመር ትውልድ መጽሀፍ’ በተሰበሰበ ገቢ የባህል ሙዚየም ለመገንባት በአቶ አሻድሊ ሀሰን የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ።

‘የመደመር ትውልድ መጽሀፍ’ በቤኒሻንጉል ክልል በሚኖረው ሽያጭ የሚገኘው ገቢ የክልሉን ባህላዊ እና ታሪካዊ ዕሴቶች የሚያንጸባርቅ ደረጃውን የጠበቀ የባህል ሙዚዬም ለመገንባት እንዲውል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሀሳብ መስጠታቸው ይታወሳል።

በዚሁ መሠረትም ከመጽሀፉ ሽያጭ በተገኘው ገቢ ደረጃውን የጠበቀ የባህል ሙዚዬም ለመገንባት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን የመሠረት ድንጋይ አሶሳ ከተማ ላይ አስቀምጠዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ከመደመር መጽሀፍ እስካሁን ድረስ ከ42 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን ገልጸዋል።

የሚገነባው የባህል ሙዚዬም የክልሉን ማህበረሰብ ባህላዊ እና ታሪካዊ ዕሴቶች ለለማበልጸግ ያግዛል ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ ።

ከአምስት ሺህ በላይ ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፈው የባህል ሙዚዬም ጥራቱን ጠብቆ በተያዘለት ጊዜ ተገንብቶ ስራ እንዲጀምር የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ያደርጋል ብለዋል አቶ አሻድሊ ሀሰን።

የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ እንዲሁም የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የሙዚዬሙን ግንባታ በበላይነት የሚያስፈጽሙ ይሆናል።

በሙዚዬሙ የመሠረት ድንጋይ ማኖር ስነ-ስርዓት ላይ የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈጉባዔ ወ/ሮ አለምነሽ ይባስ፣ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢስሀቅ አብዱልቃድር፣ የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዱልከሪም አብዱረሂም እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

ሐምሌ 11 ቀን 2015 ዓም
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️

በጉለሌ ክፍለ ከተማ በአስከፊ ችግር ውስጥ ለሚገኙ የሃገር ባለውለታዎች አቅመ ደካሞች እንዲሁም ለአካል ጉዳተኛ ነዋሪዎቻችን 133 የመኖሪያ ቤቶች ቁልፍ አስረክበናል::

እነዚህን አላግባብ ተይዘዉ የነበሩ ቤቶች ህብረተሰቡን በማሳተፍ ለሚገባዉ ሰው ያስተላለፍን ሲሆን ይህም የክፍለ ከተማዉ ነዋሪዎች የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ምላሽ ነው::
ለነዋሪዎችዋ የምትመች ማህበራዊ ፍትህ የነገስባት አዲስ አበባን እውን ለማድረግ ህዝባችንን በላቀ ትጋት ማገልገላችንን እንቀጥላለን!!
ሐምሌ 12 ቀን 2015 ዓ.ም የስራ ማስታወቂያ‼️
የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር መደበኛ ጉባዔውን ጀመረ
***
(ኢ.ፕ.ድ)

የአማራ ክልል ምክር ቤት ከሐምሌ 12 እስከ 14/2015 ዓ.ም የሚካሄደውን 6ኛ ዙር፣ 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 6ኛ መደበኛ ጉባዔውን ጀምሯል።

በጉባዔው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ የተከበሩ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋየ በበጀት ዓመቱ በክልሉ የተያዙ የልማት ሥራዎች አፈጻጸም የሚያበረታታ ነበር ብለዋል።

የክልላችንን ብሎም የሀገርን ኢኮኖሚ ለማሳደግ በስንዴ ልማት፣ በእርሻ ሜካናይዜሽን እንዲሁም በአረንጓዴ አሻራ እና በትምህርቱ ዘርፍ በከፍተኛ ንቅናቄ የተሠራበት ዓመት እንደነበርም ገልጸዋል።

የማዳበሪያ እጥረት የወለደው የሕገወጦች መበራከት በክልሉ አርሶ አደሮች በኩል ቅሬታን የፈጠረ መኾኑን የገለጹት አፈ ጉባዔዋ ለጉዳዩ ዘላቂ እልባት ለመስጠት የጋራ ርብርብ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

አፈ ጉባዔዋ "የክልሉ ሕዝብ የመጀመሪያ ጥያቄ ልማት እና የሕግ የበላይነት መከበር ነው" ሲሉ ገልጸዋል።

መንግሥት የመሪነቱን ተግባር በትክክል በመወጣት የሕዝቡን ጥያቄ ፈጥኖ መመለስ አለበት ሲሉም ተናግረዋል። በተለይም ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት በመኾኑ መላ የክልሉ ሕዝብ ከመንግሥት ጎን በመቆም ሰላሙን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ነው ያሉት።

ምክር ቤቱ በሦስት የጉባዔ ቀናት ልዩ ልዩ ተግባራትን የሚያከናውን ሲኾን ከነዚህም መካከል:-

👉 የመደበኛ ጉባዔውን አጀንዳዎች እና ቃለ ጉባዔ መርምሮ ማጽደቅ
👉 የክልሉን አስፈጻሚ አካላት የ2015 በጀት ዓመት የ11 ወር እቅድ አፈጻጸም የተጠቃለለ ሪፖርት መርምሮ ማጽደቅ
👉 የክልሉን ፍርድ ቤቶችን የ2015 በጀት ዓመት የ11 ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት መርምሮ ማጽደቅ
👉የአማራ ክልል የ2016 በጀት ዓመት ጥቅል የበጀት ጣሪያ አመዳደብ እና የወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች የድጎማ በጀት ቀመር እና የ2016 በጀትን ለማጽደቅ የበጀት አስተዳደሩን ለመወሰን የወጣ አዋጅን መርምሮ ማጽደቅ
👉 የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች የ2016 በጀት ዓመት በጀትን መርምሮ ማጽደቅ
👉 የክልሉን ኦዲት መሥሪያ ቤት የ2016 በጀት ዓመት በጀቱን መርምሮ ያጸድቃል
👉የምክር ቤቱን የ2016 በጀት ዓመት በጀቱን መርምሮ ማጽደቅ እና
👉 ልዩ ልዩ ሹመቶችን መርምሮ ማጽደቅ በአጀንዳነት ተይዘዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል።

ሐምሌ 12 ቀን 20115