Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
343 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል መልዕክት‼️

በሁሉም የክልላችን አካባቢ ያከናወነውን የአንድ ጀንበር አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በስኬት አጠናቀናል። የመልማት ትልቁ አቅማችን አንድነታችንና ትብብራችን ነው። የዛሬ ስኬታችንም ከተባበርን ለድል እንደምንበቃ ታላቅ ማሳያ ነው። አንድ ከሆን የማንፈታው ችግር የለም። አንድነታችንና ትብብራችንን በዘላቂነት ማጽናት አለብን።

በጋራ ጥረታችን ዛሬ የተከልነው ችግኝ ለመጭው ትውልድ የምናስረክበው የጋራ ሃብት ነው። ቅርስና ጌጥም ነው። የችግኝ ተከላ የአንድ ወቅት ተግባር ብቻ ሳይሆን ባሕል ሆኖ እንዲቀጥል ማድረግ ያስፈልጋል። ተከላውን ማከናወን ብቻ ሳይሆን ተንከባክቦ ለቁም ነገር ማብቃት ከሁላችንም የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው፡፡

የችግኝ ተከላ መርሃ ግብራችን በቀጣይ የክረምት ወራትም የሁላችንም የቤት ስራ ሆኖ መቀጠል ይኖርበታል። የአንድ ጀንበር ድሉን በክረምት እቅዳችን ለመድገም ርብርብ ማድረግ ይኖርብናል።

ከችግኝ ተከላው ጎን ለጎን ሰላማችን ማረጋገጥ ይጠይቀናል። የሰላም ዋጋው የሚታወቀው ሰላም ሲደፈርስ ነው። ሰላም በሌለበት አልምቶ መቀየር አይኖርም። ከምናልመው ስኬትም መድረስ አይታሰብም። ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ሁሉም አካል ከክልሉ መንግስት ጎን በመሆን የራሱን አስተዋጽኦ ማበርከት አለበት።

ለአንድ ጀንበር አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ እቅድ ስኬታማነት አሻራችሁን በማሳረፍ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ላበረከታችሁ ሁሉ በራሴና በክልሉ መንግሥት ስም ከፍ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ።
“ችግኞችን በጋራ መትከል ሥነምህዳሩን ከማስተካከል ባለፈ አብሮነታችንን ለማጎልበት ያግዛል” ረዳት ፕሮፌሰር አህመድ ዘካሪያ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞችን በጋራ መትከል የተዛባውን ሥነምህዳር ከማስተካከል ባለፈ አብሮነታችንን በማጎልበት ረገድ የጎላ ጠቀሜታ ይኖረዋል ሲሉ ረዳት ፕሮፌሰር አህመድ ዘካሪያ ገለጹ።

ረዳት ፕሮፌሰር አህመድ ዘካሪያ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በህብረት ወጥቶ የአረንጓዴ ዐሻራ የማሳረፍ ሂደቱ በራሱ ትብብርንና ሕብረትን የሚፈልግ ተግባር ነው፡፡ አንዱ ኢትዮጵያዊ ከሌላው ጋር ይበልጥ የሚግባባበትና የሚተሳሰብበትን ስሜት ይፈጥራል፡፡

በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ከፊሉ የችግኝ መትከያ ጉድጓድ ሲያዘጋጅ ከፊሉ ደግሞ ችግኞችን በማፍላት ይዘጋጃል፤ በመጨረሻም ሁሉም በአንድነት ለትውልዱ የሚተርፍ ሕይወትን ይዘራል።

ይህ ሂደት በራሱ ቅብብሎሽንና አንድነትን የሚያሳይ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን በስፋት በመሳተፍ ይበልጥ ….

https://press.et/?p=104527
የዓባይ ሸለቆን በረሃማነት ለመከላከል የተጀመረው የቆላ ቀርከሃ ልማት ተጨባጭ ውጤት እያስገኘ ነው
******************
(ኢ ፕ ድ )
የዓባይ ሸለቆን በረሃማነት ለመከላከል በአማራ ክልል ደጀን ወረዳ የተጀመረው የቆላ ቀርከሃ ልማት ተጨባጭ ውጤት እያስገኘ መሆኑ ተገለጸ። የቀርከሃ ልማቱ የዓባን ግድብን ከደለል ለመከላከልም ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተጠቅሷል።

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር እና በደጀን ወረዳ እየተተገበረ ላለው የቆላ ቀርከሃ ፕሮጀክት የዩኒቨርሲቲው አስተባባሪ አቶ ደምሳቸው ሽታው ለኢፕድ እንደገለጹት፤ የዓባይ ሸለቆ ከፍተኛ የሆነ የበረሃማነት መስፋፋት እየተከሰተ የህዝቡ የኑሩ ሁኔታ እየወረደና የገቢ ምንጫቸው እየቀነሰ መሄዱ፤ ተዳፋት የሆኑ ስፍራዎች ለእርሻ አገልግሎት በመዋላቸውና ይህም አካባቢውን ለጎርፍና የመሬት መንሸራተት አደጋ ተጋላጭ በማድረጉ፤ ጎርፉ በቀጥታ ወደ ዓባይ ወንዝ በመግባት ከፍተኛ ደለል እየፈጠረ በመሆኑ የቆላ ቀርከሃ ልማት በአካባቢው እንዲጀመር ምክንያት ሆኗል።

ባለፉት ሦስት ዓመታት ትግበራውም የአካባቢው የደን ሽፋን.....

https://press.et/?p=104548
በግንባታ ቦታ የሚደርስ አደጋ የመድህን ሽፋን እንዲያገኝ ረቂቅ ደንብ ተዘጋጀ
*****************************
(ኢ ፕ ድ )
የግንባታ ሠራተኞች በሥራ ላይ ለሚደርስባቸው አደጋ የመድህን ሽፋን እንዲያገኙ የሚያስችል ረቂቅ ደንብ መዘጋጀቱ ተገለጸ።

በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር የሆኑት ተባባሪ ፕሮፌሰር በላይነህ አድማሱ ለኢፕድ እንደተናገሩት፤ የግንባታ ቦታዎች ከሥራ ላይ አደጋና ጤንነት ስጋት ነፃ ሊሆኑ ይገባል። የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ለሀገር ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ቢኖረውም የሥራ ላይ ደህንነት፣ ጤና እና የአካባቢ ደህንነት ሁኔታን በቀጥታ የሚመለከት የሕግ ማዕቀፍ የለውም።

ጉዳቱ እና አደጋው እያለ የሕግ ማዕቀፍ ባለመኖሩ በርካታ ሰዎች የሚገባቸውን ካሳ እያገኙ አይደለም ያሉት ተባባሪ ፕሮፌሰሩ፤ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የግንባታ ቦታ ደህንነት እና ጤና ደንብ፣ የሕግ ማዕቀፍና የትግበራ…..
https://press.et/?p=104565
"በአረንጓዴ አሻራ ያመጣነውን ስኬት በሌሎች የልማት ዘርፎች መቀጠል አለበት"አምባሳደር ብርቱካን አያኖ
******
(ኢ ፕ ድ)

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች በድሬደዋ የነጻ ንግድ ቀጠና ውስጥ በዛሬው ዕለት አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።
በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ላይ አምባሳደር ቡርቱካን አያኖ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች ችግኞች ተሳትፈዋል።

አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በአረንጓዴ አሻራ ያመጣነውን ስኬት በሌሎች የልማት ዘርፎች መቀጠል አለበት ብለዋል ።

አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ይህ ልዑክ የመጣንበትን አላማ ያሳካ እና የመስተጋብሩን ያጠናከረ መሆኑን ገልፀው በቀጣይነት የተተከሉ ችግኞች እንዲፀድቁ ክትትል እናደርጋለን ብለዋል ።

ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ እና ጥበቃ እየሰራች ያለችው ተግባራ ለመጭው ዘመን ትውልድ አኩሪ እና በታሪክ ውስጥ ሲጠቀስ ይኖራል ብለዋል ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት ፣ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ኢኒስቲትዩት ሰራተኞች አምባሳደሮች ፣ ዲፕሎማቶች እና ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ከትናንት ጀምሮ ሐረር ከተማ እና በዛሬው እለትም በድሬዳዋ ከተማ ችግኝ ተክለዋል።
ከአረንጓዴ አሻራ መረሃግብሩ በተጨማሪ በድሬደዋ የነጻ ንግድ ቀጠና ውስጥ የሚገኝ የመኪና መገጣጠሚያን እና የደረቅ ወደብን የልዑካን ቡድኑ ጎብኝቷል።

ሐምሌ 11 ቀን 2015 ዓም
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የባህል ሙዚየም ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ
********************
(ኢ ፕ ድ)

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ‘ከመደመር ትውልድ መጽሀፍ’ በተሰበሰበ ገቢ የባህል ሙዚየም ለመገንባት በአቶ አሻድሊ ሀሰን የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ።

‘የመደመር ትውልድ መጽሀፍ’ በቤኒሻንጉል ክልል በሚኖረው ሽያጭ የሚገኘው ገቢ የክልሉን ባህላዊ እና ታሪካዊ ዕሴቶች የሚያንጸባርቅ ደረጃውን የጠበቀ የባህል ሙዚዬም ለመገንባት እንዲውል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሀሳብ መስጠታቸው ይታወሳል።

በዚሁ መሠረትም ከመጽሀፉ ሽያጭ በተገኘው ገቢ ደረጃውን የጠበቀ የባህል ሙዚዬም ለመገንባት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን የመሠረት ድንጋይ አሶሳ ከተማ ላይ አስቀምጠዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ከመደመር መጽሀፍ እስካሁን ድረስ ከ42 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን ገልጸዋል።

የሚገነባው የባህል ሙዚዬም የክልሉን ማህበረሰብ ባህላዊ እና ታሪካዊ ዕሴቶች ለለማበልጸግ ያግዛል ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ ።

ከአምስት ሺህ በላይ ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፈው የባህል ሙዚዬም ጥራቱን ጠብቆ በተያዘለት ጊዜ ተገንብቶ ስራ እንዲጀምር የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ያደርጋል ብለዋል አቶ አሻድሊ ሀሰን።

የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ እንዲሁም የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የሙዚዬሙን ግንባታ በበላይነት የሚያስፈጽሙ ይሆናል።

በሙዚዬሙ የመሠረት ድንጋይ ማኖር ስነ-ስርዓት ላይ የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈጉባዔ ወ/ሮ አለምነሽ ይባስ፣ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢስሀቅ አብዱልቃድር፣ የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዱልከሪም አብዱረሂም እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

ሐምሌ 11 ቀን 2015 ዓም
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️

በጉለሌ ክፍለ ከተማ በአስከፊ ችግር ውስጥ ለሚገኙ የሃገር ባለውለታዎች አቅመ ደካሞች እንዲሁም ለአካል ጉዳተኛ ነዋሪዎቻችን 133 የመኖሪያ ቤቶች ቁልፍ አስረክበናል::

እነዚህን አላግባብ ተይዘዉ የነበሩ ቤቶች ህብረተሰቡን በማሳተፍ ለሚገባዉ ሰው ያስተላለፍን ሲሆን ይህም የክፍለ ከተማዉ ነዋሪዎች የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ምላሽ ነው::
ለነዋሪዎችዋ የምትመች ማህበራዊ ፍትህ የነገስባት አዲስ አበባን እውን ለማድረግ ህዝባችንን በላቀ ትጋት ማገልገላችንን እንቀጥላለን!!