Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
343 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
#አረንጓዴዐሻራ በኢትዮጵያ ‼️
በአንድ ጀንበር የ500 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐ ግብር በአየር ሃይል ጠቅላይ መምሪያ ተከናወነ
*****
(ኢ.ፕ.ድ)

በአንድ ጀምበር የ500 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐ-ግብር በአየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ተከናውኗል።

በአየር ኃይል ደረጃ በተከናወነው ችግኝ የመትከል መርሐግብር የፌዴራልና የክልል የስራ ኃላፊዎች ከቢሾፍቱ ከተማ የተውጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎችና የአየር ኃይል አባላት ተገኝተዋል።

በችግኝ ተከላው ላይ ተገኙት የትምህርት ሚንስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንደተናገሩት ለነገው ትውልድ የምትሆን የለማች ጠንካራ ሀገር ለመገንባት ለተያዘው ራዕይና ግብ የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሠማ በበኩላቸው አለም በአየር ንብረት መዛባት በጦርነት በወረርሽኝና በሌሎች ችግሮች መወጠሯንና ይህም ከበረሃማነት ጋር ተያይዞ የሚከሰት ችግር መሆኑን ጠቅሰው ችግሩን ከምንጩ ለማድረቅ ለተያዘው ሀገራዊ የአረንጓዴ ልማት ንቅናቄ ችግኝ መትከል አሥፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ ፍቃዱ ሰራዊቱ ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን ተንከባክበው ለታለመለት ዓላማ ከግብ በማድረሱ ረገድም እንደ ከዚህ ቀደሙ ጥረታቸውን መቀጠል አለበት ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
#አረንጓዴዐሻራ
በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ 500 ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀምበር የመትከል መርሀ ግብር 566 ሚሊዮን 971 ሺህ 600 ችግኝ መተከሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ።

ይህ ችግኝ በ302 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የተተከለ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

ይህ ቁጥር በጂኦስፓሻል መረጃ መሰረት የተጠናቀረ መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በጂኦስፓሻል ያልተካተቱ አከባቢዎች የተተከሉ ችግኞች መኖሩንና ቁጥሩ ከዚህም በላይ እንደሚሆን ገልጸዋል።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"ዛሬ ለኢትዮጵያም፣ ለአፍሪካም ለመላው ዓለም ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ እጅግ የሚያኮረ ተግባር ፈጽመናል፤ ለዚህም እንኳን ደስ ያለን ማለት እፈልጋለሁ"

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት‼️

ታሪክ ሠርታችኋል

500 ሚልዮን ዛፎችን በመትከል የራሳችንን ሪከርድ እንድንሰብር የቀረበውን ጥሪ ተቀብላችሁ የወጣችሁ ሁሉ ምስጋና ይገባችኋል። አረንጓዴ ታሪክ ሠርታችኋል። አረንጓዴ ታሪክ ጽፋችኋል። 

የተዛባ አየር፣ የተራቆተ ምድር ለትውልድ አናወርስም ብላችሁ፤ ጎሕ ሳይቀድ ወደ ተራሮችና ሸለቆዎች፣ ወደ ሜዳዎችና ሸንተረሮች ተሠማርታችሁ  566 ሚልዮን ዛፎች ተክላችኋል። ሪከርዳችሁን ሰብራችኋል።

በሁሉም ክልሎች፣ ዞኖችና ወረዳዎች  ዛፎች ተተክለዋል።  ከ9 ሺ በላይ የተለዩ ቦታዎች  ተዘጋጅተው ነበር። ከ3600 በላይ የሚዲያ ባለሞያዎች በመላ ሀገሪቱ ተሠማርተው ነበር። የቴሌና የግብርና ባለሞያዎች የመረጃ አያያዙ ዘመናዊ እንዲሆን ሠርተዋል። የአዲስ አበባ ታክሲዎች ነጻ ትራንስፖርት ለችግኝ ተካዮች  ተሰጥተዋል። ሕጻናት፣ እናቶች፣ አባቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ በነቂስ ወጥተው ተክለዋል።  በኢትዮጵያውያን አረንጓዴ ታሪክ ተሠርቷል።

ኢትዮጵያውያን ከተባበርን የማንሰብረው ሪከርድ የለም።
ሐምሌ 11 ቀን 2015 ዓ.ም የስራ ማስታወቂያ‼️
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል መልዕክት‼️

በሁሉም የክልላችን አካባቢ ያከናወነውን የአንድ ጀንበር አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በስኬት አጠናቀናል። የመልማት ትልቁ አቅማችን አንድነታችንና ትብብራችን ነው። የዛሬ ስኬታችንም ከተባበርን ለድል እንደምንበቃ ታላቅ ማሳያ ነው። አንድ ከሆን የማንፈታው ችግር የለም። አንድነታችንና ትብብራችንን በዘላቂነት ማጽናት አለብን።

በጋራ ጥረታችን ዛሬ የተከልነው ችግኝ ለመጭው ትውልድ የምናስረክበው የጋራ ሃብት ነው። ቅርስና ጌጥም ነው። የችግኝ ተከላ የአንድ ወቅት ተግባር ብቻ ሳይሆን ባሕል ሆኖ እንዲቀጥል ማድረግ ያስፈልጋል። ተከላውን ማከናወን ብቻ ሳይሆን ተንከባክቦ ለቁም ነገር ማብቃት ከሁላችንም የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው፡፡

የችግኝ ተከላ መርሃ ግብራችን በቀጣይ የክረምት ወራትም የሁላችንም የቤት ስራ ሆኖ መቀጠል ይኖርበታል። የአንድ ጀንበር ድሉን በክረምት እቅዳችን ለመድገም ርብርብ ማድረግ ይኖርብናል።

ከችግኝ ተከላው ጎን ለጎን ሰላማችን ማረጋገጥ ይጠይቀናል። የሰላም ዋጋው የሚታወቀው ሰላም ሲደፈርስ ነው። ሰላም በሌለበት አልምቶ መቀየር አይኖርም። ከምናልመው ስኬትም መድረስ አይታሰብም። ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ሁሉም አካል ከክልሉ መንግስት ጎን በመሆን የራሱን አስተዋጽኦ ማበርከት አለበት።

ለአንድ ጀንበር አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ እቅድ ስኬታማነት አሻራችሁን በማሳረፍ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ላበረከታችሁ ሁሉ በራሴና በክልሉ መንግሥት ስም ከፍ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ።