Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
343 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
#አረንጓዴዐሻራ

በአዳማ በከሰዓት በኋላ መርሀ ግብሩ ችግኝ ተከላው ቀጥሏል
***********
(ኢ.ፕ.ድ)

በአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከሉ መርሀ ግብር በአዳማ ከተማ ቀጥሏል።

በኢሬቻ ቀበሌ እየተካሄደ የሚገኘውን መርሀ ግብር የኢፕድ ዘጋቢ እየተመለከተ ይገኛል።

ሕብረተሰቡ በበራሱ ወጪ ሳይቀር የገዛውን ችግኝ በመትከል ላይ ይገኛሉ።

ችግኝ መትከል ብቻውን በቂ እንዳልሆነ ተናግረው አስፈላጊውን እንክብካቤ ለማድረግም በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በዋሲሁን ተክሌ (አዳማ)
ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም
#አረንጓዴዐሻራ

የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በጅማ ከተማ በተለያዩ ቀበሌዎች ከሰአትም ቀጥሏል

በአገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኞችን የመተከል መርሃ ግብር በጅማ ከተማ ቀጥሏል።

በከሰአት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ በግንጆ ጉዱሩ ፣ በህርማታ መንቲና እና እግንጆ ቀበሌዎች ቀጥሏል።

በዳግማዊት አበበ (ጅማ)
#አረንጓዴዐሻራ በኢትዮጵያ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ፣በዕለቱ ለሦስተኛ ጊዜ ከአረጋውያን እናቶችና አባቶች ጋር አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አሰታወቀ።