Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
343 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
#አረንጓዴዐሻራ

የኢንዱስትሪ ሚንስትር አቶ መላኩ አለበል፣ የኢንዱስትሪ ሚንስትር ድኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ እና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት በቢሾፍቱ ደካካ ተራራ ላይ አረንጓዴ አሻራቸዉን አሳርፈዋል።
#አረንጓዴዐሻራ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) ከተማሪዎች ጋር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ አካሂደዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በየካ ተራራ ከሚገኙ የአንደኛ ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ጋር በመሆን የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ላይ መሳተፋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

“በዕለቱ ለሁለተኛ ጊዜ ባደረጉት ችግኝ ተከላ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በየካ ተራራ ከሚገኙ የአንደኛ ደረጃና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ጋር በመሆን የ500 ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ቀን አረንጓዴ ዐሻራ ተከላ ላይ ተሳትፈዋል።
#አረንጓዴዐሻራ

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐግብር በማከናወን ላይ ይገኛል
****************
(ኢ ፕ ድ)

በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኝ ተከላን እውን ለማድረግ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በዛሬው ዕለት በዳግማዊ ምኒልክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐግብር አከናውነዋል።

የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳሬክተር ዶክተር ጌታሁን ጋርደው፤ ችግኞችን መተከል የተፈጥሮ ሀብትን ለመጠበቅ ከፍተኛ ጥቅም ይሰጣል ብለዋል።

በአንድ ጀበር 500 ሚልዮን ችግኝ በመትከል ታሪክ እንስራለን ፤ አለምን እያስጨነቃት ያለውን የአየር ንብረት ለውጥ እንቀንሳለን ሲሉ አብራርተዋል። ለችግኞችን አሰፈላጊውን እንክብካቤ በማድረግ ለትውልድ ማስተላለፍ ይገባልም ብለዋል።

ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓም
በታደሰ ብናልፈው
#አረንጓዴዐሻራ

የአማራ ክልል ርዕስ መስተዳድር አርሶ አደሮች በአረንጓዴ አሻራ ላሳዩት ተሳትፎ አመሰገኑ
********************
(ኢ ፕ ድ)
በዘንድሮው የአረንግዴ ዐሻራ መርሀ ግብር 500 ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀምበር የመትከል መርሀ ግብር ላይ ለተሳተፉ የአማራ ክልል አርሶአደሮች የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ምስጋና አቀረቡ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ዛሬ በክልሉ በተካሄደው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር፤ “ነገን ዛሬ እንትከል የሚለው መልዕክት ለአርሶ አደሮቻችን እጥፍ ድርብ መልዕክት አለው” ብለዋል።

አርሶ አደሮቻችን ምርታማ እንዲሆኑ የመሬቱ ለምነት እንዲጠበቅ በየአከባቢው ዛፎች መኖራቸው ከፍተኛ ዋጋ እንዳለው አርሶ አደሮቻችን ብለዋል፤ ርዕሰ መስተዳድሩ።

"ችግኝ መትከል ከግብርና ስራችን ጋር የተቆራኘ የማይለያይ ተግባር ነው፤ ይህን ተግባር አርሶ አደሮች በነቂስ ወጥታችሁ አብራችሁን በመሳተፋችሁ በዋናነትም የእናንተ ስራ ጠቃሚ መሆኑን ተገንዝባችሁ የዚህ በአል ተሳታፊ በመሆናችሁ አመሰግናለሁ” ብለዋል።

ይህን ችግኝ በዘመቻ እንተክላላን፤ መትከል አንድ ነገር ነው፤ የመጨረሻውና ዋናው ነገር የተከልነው ችግኝ ፀድቆ ለአከባቢው ጥቅምና አገልግሎት የሚሰጥበት ደረጃ ላይ ማድረስ ነውም ብለዋል።

“የፍራፍሬ ከሆነ ከፍሬው ለመቋደስ መስራት መቻል አለብን፤ የተከልነው ዛፍ ከሆነም የአከባቢውን ስነ ምህዳር እንዲጠብቅ ማድረግ አለብን፤ ይህ ካልሆነ ከንቱ ልፋት ነው” ሲሉም ነው የተናገሩት።

“ችግኞቹን ከብዙ ንክኪ በመጠበቅ እንክብካቤ ተደርጎላቸው ፀድቀው እናንተን እንዲጠቅሙ የበኩላችሁን አስተዋፅኦ እንድታደርጉ አደራ እላላሁ” ሲሉም ነው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት።

በሀይማኖት ከበደ
ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓም