#አረንጓዴዐሻራ #በትግራይ‼️
በትግራይ ክልል በአንድ ቀን 500 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሀ ግብር የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ እና የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ፕሮፌሰር እያሱ ኤሊያስን ጨምሮ ሌሎች በተገኙበት ተጀምሯል።
የችግኝ መትከል መርሀ ግብሩም በክለሉ በጽራህ ወንበርታ ወረዳ በሚካኤል እንባ ቀበሌ እየተካሄደ ነው።
በመርሀ ግብሩ ላይ አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ ባደረጉት ንግግር፤ የትግራይ ክልል በተፋሰስ ልማትና ችግኝ ተከላ የታወቀ መሆኑን በመጥቀስ፤ አሁን የተገኘውን ሰለም በማጽናት የበለጠ የልማት ስራ እነደሚሰራ ገልጸዋል።
ሰላሙን ለማጽናት የፌዴራል ምንግስት ጠንክሮ እየሰራ መሆኑን በመጥቀስም፤ ችገሮች ካሉ በውይይት በመፍታት መጓዝ እንደሚገባ ተናግረዋል።
አቶ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው፤ ሰላም ሰፍኖ ወደዚህ አይነት ተግባር መመለሳቸው መልካም ተግባር መሆኑን በመጠቀስ፤ የተገኘውን ሰላም ለማጽናት ጠንክረው እንደሚሰሩ አብራርተዋል።
በመላው አገሪቱ ከጠዋቱ 12 ሰአት ጀምሮ እስከ 5:30 ባለው ሰዓት በመላው ኢትዮጵያ 247 ሚሊዮን ችግኞች መተከላቸውን የመንግስት ኮምንኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ድኤታ ሰላማዊት ካሳ መግለጻቸው ይታወሳል።
ሀምሌ 10 ቀን 2015 ዓም
በማዕረግ ገብረእገዚአብሔር

#አረንጓዴዐሻራ‼
በሸገር ከተማ የአካኮ መነ አብቹ ወረዳ በእንጦጦ የህዋ ሳይንስ ምርምር ማዕከል አካባቢ የሸገር ከተማ አመራሮች ፣ የመነ አብቹ ክፍለ ከተማውና ወረዳው አመራሮች፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላትና ነዋሪዎች አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።
በዋቅሹም ፈቃዱ
ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓም

#አረንጓዴዐሻራ
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ
*************
(ኢ ፕ ድ)
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በየካ ተራራ ላይ አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ።
ቀዳማዊት እመቤቷ ከተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ማዕከላት ከመጡ ሕፃናት ጋር በርካታ ችግኞችን በመትከል ተሳትፈዋል።
የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ሠራተኞች ከላቭ ኤንድ ኬር የበጎፈቃድ ቡድን ጋር በስፍራው የፍራፍሬ ችግኞችን ተክለዋል።
ሀምሌ 10 ቀን 2015 ዓም
በጌትነት ተስፋማርም

የኢንዱስትሪ ሚንስትር አቶ መላኩ አለበል፣ የኢንዱስትሪ ሚንስትር ድኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ እና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት በቢሾፍቱ ደካካ ተራራ ላይ አረንጓዴ አሻራቸዉን አሳርፈዋል።