Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
343 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
#አረንጓዴዐሻራ

የአረንጓዴ አሻራ ተሳታፊ ለመሆን ከኬንያ የመጡት የዜድቲኢ- ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ

ኢትዮ ቴሌኮም ከአመራርና ሠራተኞች በተጨማሪ የሥራ አጋሮቹንም የችግኝ ተከላው አካል አድርጓል።

የዜድቲኢ- ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክሪስ ይ ለኢፕድ፤ የዛሬው ችግኝ ተከላ እንዳያመልጣቸው ከኬንያ ተነስተው ንጋት 10:00 አዲስ አበባ መግባታቸውን ገልጸዋል።

የመርሃግብሩ ተሳታፊ በመሆኔም በጣም ተደስቻለሁ ብለዋል።

ኢትዮጵያ ላይ በቴክኖሎጂው ዘርፉ ከምናደርገው አስተዋጽኦ ባለፈ አረንጓዴ አሻራን ጨምሮ በሌሎችም ዘርፎች የበኩላችንን ሚና ለመወጣት ዝግጁ ነን ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ በዛሬው ዕለት እንደ ተቋም 300 የሚጠጋ ችግኝ ተክለናል ብለዋል።

ኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ ላይ እየሠራች ያለችው ሥራ ለሌሎችም አገራት ተምሳሌት የሚሆን በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።

በፋንታነሽ ክንዴ

ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓም
#አረንጓዴዐሻራ ድሬደዋ

በድሬዳዋ አስተዳደር የ500 ሺህ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር‼️
#አረንጓዴዐሻራ

የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በዛሬው የአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ መረሐግብር ተሳትፎ ‼️
#አረንጓዴዐሻራ #በትግራይ‼️

በትግራይ ክልል በአንድ ቀን 500 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሀ ግብር የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ እና የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ፕሮፌሰር እያሱ ኤሊያስን ጨምሮ ሌሎች በተገኙበት ተጀምሯል።

የችግኝ መትከል መርሀ ግብሩም በክለሉ በጽራህ ወንበርታ ወረዳ በሚካኤል እንባ ቀበሌ እየተካሄደ ነው።

በመርሀ ግብሩ ላይ አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ ባደረጉት ንግግር፤ የትግራይ ክልል በተፋሰስ ልማትና ችግኝ ተከላ የታወቀ መሆኑን በመጥቀስ፤ አሁን የተገኘውን ሰለም በማጽናት የበለጠ የልማት ስራ እነደሚሰራ ገልጸዋል።
ሰላሙን ለማጽናት የፌዴራል ምንግስት ጠንክሮ እየሰራ መሆኑን በመጥቀስም፤ ችገሮች ካሉ በውይይት በመፍታት መጓዝ እንደሚገባ ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው፤ ሰላም ሰፍኖ ወደዚህ አይነት ተግባር መመለሳቸው መልካም ተግባር መሆኑን በመጠቀስ፤ የተገኘውን ሰላም ለማጽናት ጠንክረው እንደሚሰሩ አብራርተዋል።

በመላው አገሪቱ ከጠዋቱ 12 ሰአት ጀምሮ እስከ 5:30 ባለው ሰዓት በመላው ኢትዮጵያ 247 ሚሊዮን ችግኞች መተከላቸውን የመንግስት ኮምንኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ድኤታ ሰላማዊት ካሳ መግለጻቸው ይታወሳል።
ሀምሌ 10 ቀን 2015 ዓም
በማዕረግ ገብረእገዚአብሔር
#አረንጓዴዐሻራ

በሸገር ከተማ የአካኮ መነ አብቹ ወረዳ በእንጦጦ የህዋ ሳይንስ ምርምር ማዕከል አካባቢ የሸገር ከተማ አመራሮች ፣ የመነ አብቹ ክፍለ ከተማውና ወረዳው አመራሮች፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላትና ነዋሪዎች አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።

በዋቅሹም ፈቃዱ
ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓም