Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
343 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
#አረንጓዴዐሻራ

ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አስጀምረዋል።

የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው በክልሉ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አስጀመሩ በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በመከናወን ላይ ይገኛል።
#አረንጓዴዐሻራ ‼️
"የኢትዮጵያ መንግስት ለነገ ትውልድ የሚሰራውን ሥራ አጠናክሮ ይቀጥላል"- አቶ አደም ፋራህ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)

የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ዘንዘልማ ቀበሌ ገላድ ተፋሰስ ችግኝ በመትከል አርንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።

ምክትል ፕሬዝዳንቱ በወቅቱ እንደተናገሩት፤ "የኢትዮጵያ መንግስት ባለፋት ጊዜያት ለነገ ትውልድ የሚጠቅሙ በርካታ ሥራዎችን ሲሰራ ቆይቷል። ከነዚህም ውጥ አንዱ የአርንጓዴ ዐሻራ ነው። ይህም ለሀገር ብቻ ሳይሆን ለምድር ገፀ በረከትን የሚያላብስ ነው።

መንግስት ለነገ ትውልድ የሚሰራውን ሥራ አጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፤ የአርንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በሌሎች ሀገራት ላይ በጎ ተፅዕኖ ለመፍጠር ይረዳናል ብለዋል።

መርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ በታሪክ ለዓለም ያበረከተቻቸው አስተዋፅዖ እንዲታወሱ የሚያደርግ ሲሆን በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል መርሃ ግብሩም ኢትዮጵያ ለዓለም የምታበረክተው አስተዋፅኦን አጠናክራ እንደምታስቀጥል የሚያሳይ ነው ሲሉም ገልፀዋል።

ከዚህም ባለፈ የአየር ንብረት ለውጥ በሰው ልጆች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው። ይህም የንፁህ መጠጥ ውሃ መጠን እንዲቀንስ እና የአፈር መሸርሸርን አስከትሏል። ስለዚህ መርሃ ግብሩ ይህንን ጉዳት ለመቀነስ ያስችላል ብለዋል።

በሳሙኤል ወንድወሰን (ባህርዳር)
ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም
#አረንጓዴዐሻራ

የአረንጓዴ አሻራ ተሳታፊ ለመሆን ከኬንያ የመጡት የዜድቲኢ- ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ

ኢትዮ ቴሌኮም ከአመራርና ሠራተኞች በተጨማሪ የሥራ አጋሮቹንም የችግኝ ተከላው አካል አድርጓል።

የዜድቲኢ- ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክሪስ ይ ለኢፕድ፤ የዛሬው ችግኝ ተከላ እንዳያመልጣቸው ከኬንያ ተነስተው ንጋት 10:00 አዲስ አበባ መግባታቸውን ገልጸዋል።

የመርሃግብሩ ተሳታፊ በመሆኔም በጣም ተደስቻለሁ ብለዋል።

ኢትዮጵያ ላይ በቴክኖሎጂው ዘርፉ ከምናደርገው አስተዋጽኦ ባለፈ አረንጓዴ አሻራን ጨምሮ በሌሎችም ዘርፎች የበኩላችንን ሚና ለመወጣት ዝግጁ ነን ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ በዛሬው ዕለት እንደ ተቋም 300 የሚጠጋ ችግኝ ተክለናል ብለዋል።

ኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ ላይ እየሠራች ያለችው ሥራ ለሌሎችም አገራት ተምሳሌት የሚሆን በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።

በፋንታነሽ ክንዴ

ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓም
#አረንጓዴዐሻራ ድሬደዋ

በድሬዳዋ አስተዳደር የ500 ሺህ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር‼️
#አረንጓዴዐሻራ

የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በዛሬው የአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ መረሐግብር ተሳትፎ ‼️