Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
343 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
#አረንጓዴዐሻራ በአፍር‼️

በአገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኞችን የመተከል መርሃ ግብር በአፋር‼️
የዛሬውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር ሁነት ለመዘገብ ከሶስት ሺህ በላይ ጋዜጠኞች ተሰማርተዋል
*****************
(ኢ ፕ ድ)

የዛሬውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር ሁነት ለመዘገብ በመላ አገሪቱ ከሶስት ሺህ በላይ ጋዜጠኞች ተሰማርተዋል።

የመንግስት ኮምንኬሽን አገልገሎት ሚኒስትር ድኤታ ሰላማዊት ካሳ እንዳስታወቁት፤ በሁለተኛው ምዕራፍ የመጀመሪያ ዙር የአረጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር በአንድ ቀን 500 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ሁነትን ለመዘገብ ከሶስት ሺህ በላይ ጋዜጠኞች ስራ ላይ ናቸው።

ኢትዮጵያን አረንጓዴ የማልበሱ ተግባር ከዘጠኝ ሺህ በላይ ቦታዎች ላይ እየተከናወነ መሆኑን የጠቀሱት ሚንስትር ድኤታዋ፤ ሁነቱን አዲስ አበባ ከሚገኝ የሁነት መከታተያ ማዕከል በሳተላይት ከመከታተል ባሻገር ጋዜጠኞች ከቦታው ሆነው መረጃዎችን በማድረስ ላይ ናቸው ብልዋል።

በጌትነት ምህረቴ
ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓም
"የአረንጓዴ አሻራ መረሐግብር የሀገር ጉዳይ በመሆኑ ሳንታክት አጠናክረን ልናስቀጥለው ይገባል" -ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ
*********************
(ኢ ፕ ድ)

የአረንጓዴ አሻራ መረሐግብር የሀገር ጉዳይ በመሆኑ ሳንታክትና ሳንሰለች አጠናክረን ልናስቀጥለው ይገባል ሲሉ የፓሊሲ ጥናት ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ተናገሩ።

በልደታ ክፍለከተማ 500 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀንበር የማስጀመሪያ መረሐግብር ላይ ተገኝተው አሻራቸውን ያሳረፉት ኢፌዴሪ ፓሊሲ ጥናት ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፤ አረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ለሀገራችን ወሳኝ ጉዳይ በመሆኑ በተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች ሳንገደብ አጠናከረን ልናስቀጥል ይገባል ብለዋል።

ችግኝ መትከል የሕልውና ጉዳይ ነው ያሉት ፕሮፌሰር በየነ፤ ዝናብና ሌሎች ምክንያቶች ሳያሸንፉን አሻራችንን በማስቀመጥ የታቀደውን ማሳከት እንደሚገባ አስታውቀዋል፡፡

ሁሉም ማህበረሰብ አቅሙን፣ ጉልበቱን እና ጌዜውን ሳይቆጥብ ሀገሪቱን አረንጓዴ ጠማድረግ መልካም ጅማሮ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አመላክተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ በድርቅ እና በርሃብ የምትጠቃ አገር ናት የሚለውን ሃሳብ በአረንጓዴ አሻራ መረሐግብር ታሪክ ለማድረግ ተረባርበን ልንሰራ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

አረንጓዴ አሻራ ሀገሪቱን አረንጓዴ ከማድረግ ባለፈ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ጉልህ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡
ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓም
በሄለን ወንድምነው
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️

የዛሬዋ ማለዳ ታሪካዊ ናት። ከከተማችን ነዋሪዎች ጋር የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችንን በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል ጥሪ ተቀብለን በከተማችን 4 ሚሊዮን ችግኞችን በ140 ቦታዎች መትከል ጀምረናል።

ከአምናው እና ከካቻምናው ይበልጥ ብዙ ችግኞችን ደጋግመን መትከል ጀምረናል። አንድ ሆነን በአንድ ልብ መስራት ስንጀምር ችግሮቻችን በኛ ፊት አቅም ይከዳቸዋል። ተባብረን ስንሰራ ችግሮቻችን ቀልለው፤ የራቀ የመሰለው ስኬት እየቀረበ በርካቶችን ጠቃሚ ያደረጉ ስራዎችን ሰርተናል።
ውድድሩን ከራሳችን ጋር አድርገን የዛሬውን ስራችንን ከትናንትናው በጥራትም፣ በብዛትም የተሻለ በማድረግ ችግሮቻችንን እየቀደምን የዛሬው ስኬታችን ለተሻለው የነገው ድል እያሻገረን እንቀጥላለን። ዛሬ የምንተክለው ችግኝ ነገ ምግባችን፣ መጠለያ ጥላችን እንዲሁም የነገ የአየር ብክለት መከላከያ ጋሻችን ነው።

መላው የከተማችን ነዋሪዎች በአዲስ አበባ ደረጃ ለመትከል የታቀደውን የአንድ ጀምበር ከ4 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን የመትከል መርሀ ግብር ላይ እየተሳተፋችሁ ስለሆነ እያመሰገንኩ፣ ከመትከል በተጨማሪ በመንከባከቡም ረገድ እንድትሳተፉ ጥሪዬን አቀርባለሁ። አዲስ አበባን እየተባበርን በመፍጠር፣ እየፈጠንን ችግሮቻችንን በመርታት ለነዋሪዎቿና ለጎብኚዎቿ የምትመች ውብ ከተማ ለማድረግ በትጋት መስራታችንን እንቀጥላለን።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ