"ዛሬ የምንተክለው ችግኝ የነገ ጥላችን ነው" ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
ከንቲባ አዳነች በጉለሌ እፅዋት ማዕከል በመገኘት አረንጓዴ አሻራቸውን ካኖሩ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት፥ በዛሬው ዕለት በከተማዋ በ140 የተለያዩ ቦታዎች ላይ ችግኞች እየተተከሉ መሆኑን ገልፀዋል።
"ዛሬ የምንተክለው ችግኝ በአየር መዛባት ምክንያት የሚመጣውን ችግር መከላከያ ጋሻችን ነው፤ ዛሬ የምንተክለው ችግኝ የነገው ጥላችን ነው" በማለትም የመርሐ-ግብሩን አስፈላጊነት በአፅንዖት ገልፀዋል።
የአረንጓዴ ዐሻራ ሂደት ከተባበርን ተዓምር መሥራት እንደምንችል ያሳየንበት እና የምናሳይበት ነውም ብለዋል ከንቲባዋ።

#አረንጓዴዐሻራ በባህርዳር ‼
ነፍሰጡሯ በአረንጓዴ ዐሻራ‼
በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ዘንዘልማ ቀበሌ ገላድ ተፋሰስ አካባቢ ችግኝ እየተከሉ ካሉ ዜጎች መካከል ነፍሰጡሯ ወይዘሮ ሃይማኖት ቢተው አንዷ ናቸው።
ወይዘሮዋ ለኢትዮጵያ ኘሬስ ድርጅት ፤ በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተሳታፊ በመሆኔ በጣም ተደስቻለሁ። በዚህም በርካታ ችግኞችን ለመትከል አቅጄ መጥቻለሁ ብለዋል።
"ይህንንም የማደርገው ለምወልደው ልጅ ምቹ፣ አረንጓዴ እና ለሁሉ የምትስማማ ሀገር ቀድሜ ለማዘጋጀት ነው" ብለዋል።
ችግኝ የሚተክሉ ነፍሰ ጡር እናቶች ለልጆቻቸው እና ለመጪው ትውልድ ቀጣይነት ያለው የወደፊት ሕይወት እንዲኖራቸው አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆኑን ሊገነዘቡ ይገባልም ብለዋል።
በሳሙኤል ወንድወሰን (ባህርዳር)
ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓም