Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
343 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
#አረንጓዴዐሻራ

የመስኖና ቆላማ ሚኒስትር የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በማከናወን ላይ ይገኛል
****************
(ኢ ፕ ድ)

የመስኖና ቆላማ ሚኒስትር መስሪያ ቤት አመራሮችና ሠራተኞች ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሶስት ጋር በጋራ በመሆን በጎተራ ማሳለጫ አቅራቢያ የአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በማከናወን ላይ ይገኛሉ።

ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓም
በቃልኪዳን አሳዬ
#አረንጓዴዐሻራ_በአርባምንጭ‼️

በአንድ ጀምበር 500 ሚሊየን ችግኝ ተከላ መርሐግብር በአርባምንጭ‼️
#አረንጓዴዐሻራ_በአፋር‼️

በአንድ ጀምበር 500 ሚሊየን ችግኝ ተከላ መርሐግብር በአፋር‼️
"ዛሬ የምንተክለው ችግኝ የነገ ጥላችን ነው" ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
ከንቲባ አዳነች በጉለሌ እፅዋት ማዕከል በመገኘት አረንጓዴ አሻራቸውን ካኖሩ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት፥ በዛሬው ዕለት በከተማዋ በ140 የተለያዩ ቦታዎች ላይ ችግኞች እየተተከሉ መሆኑን ገልፀዋል።

"ዛሬ የምንተክለው ችግኝ በአየር መዛባት ምክንያት የሚመጣውን ችግር መከላከያ ጋሻችን ነው፤ ዛሬ የምንተክለው ችግኝ የነገው ጥላችን ነው" በማለትም የመርሐ-ግብሩን አስፈላጊነት በአፅንዖት ገልፀዋል።

የአረንጓዴ ዐሻራ ሂደት ከተባበርን ተዓምር መሥራት እንደምንችል ያሳየንበት እና የምናሳይበት ነውም ብለዋል ከንቲባዋ።