Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
343 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
አብሮ ታሪክ መስራት ትልቅ ድል ነው-አቶ ደመቀ መኮንን
***************
(ኢ ፕ ድ)

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሃግብርን በአዲስ አበባ አስጀምረዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ባደረጉት ንግግር የዛሬው ቀን ኢትዮጵያን ፀጋ በማልበስ ትልቅ ታሪክ እየተሰራበት ያለ ቀን መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኝ በመትከል ሀገራችን ለማልበስ ለትውልድ የተመቸ ሁኔታ ለመፍጠር በመላ ሀገሪቱ ታሪክ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት ካሳካነው በላይ ሪከርዳችንን በማሻሻል ውጤት የምናሳይበት ቀን ነውም ብለዋል፡፡

500 ሚሊየን ችግኝ በአንድ ጀንበር መትከል ማለት የመስራት አቅማችንን የበለጠ የሚያነሳሳ እና ለተሻለ እንድንዘጋጅ የሚያደርገን ነው ብለዋል አቶ ደመቀ፡፡

ትውልዱ የራሱን ታሪክ የሚሰራና ለመጪው ትውልድ የተመቸች ኢትዮጵያን ለማስረከብ እየሰራ ነው ያሉት አቶ ደመቀ በዚህም እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

እንደ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዘገባ “ስናብር ያምርብናል፤ አብሮ ታሪክ መስራት ትልቅ ድል ነው ”ሲሉም ገልጸዋል፡፡ የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ እንትጋ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
#አረንጓዴዐሻራ

የመስኖና ቆላማ ሚኒስትር የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በማከናወን ላይ ይገኛል
****************
(ኢ ፕ ድ)

የመስኖና ቆላማ ሚኒስትር መስሪያ ቤት አመራሮችና ሠራተኞች ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሶስት ጋር በጋራ በመሆን በጎተራ ማሳለጫ አቅራቢያ የአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በማከናወን ላይ ይገኛሉ።

ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓም
በቃልኪዳን አሳዬ