ችግኞችን በጋራ እንደተከልን ሁሉ ሰላማችንን በጋራ በመጠበቅ ደህንነቷ የተረጋገጠባት ዲሞክራሲያዊት አገር እንገነባለን- ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)
“ችግኞችን በጋራ እንደተከልን ሁሉ ሰላማችንን በጋራ በመጠበቅ ደህንነቷ የተረጋገጠባት ዲሞክራሲያዊት አገር እንገነባለን” ሲሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ ገለጹ።
በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል በተያዘው መርሐ-ግብር መሰረት ኢትዮጵያዊያን በነቂስ ወጥተው ችግኝ እየተከሉ ነው።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ(ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት ኢትዮጵያዊያን ዝናቡ ሳይበግራቸው ችግኝ በመትከል ላይ ይገኛሉ።
ችግኝ መትከል የሕልውና ጉዳይ መሆኑን አመልክተዋል።
ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ በድርቅ የምትጠቃ አገር በመሆኗ አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ከመትከል ባለፈ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ጉዳይ ነው ብለዋል።
“ችግኞችን በጋራ እንደተከልን ሁሉ ሰላማችንን በጋራ በመጠበቅ ደህንነቷ የተረጋገጠባት ዲሞክራሲያዊት አገር እንገነባለን” ብለዋል ሚኒስትሩ።
ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓም