የክልሉ ህዝብ ነገ በሚካሄደው የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራ መርሃግብር በነቂስ እንዲሳተፍ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ጥሪ አቀረቡ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ነገ ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም በአንድ ጀምበር 500 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል በሚካሄደው ዘመቻ የክልሉ ህዝብ በነቂስ እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።
በአረንጓዴ አሻራ መርሃግብሩ መሳተፍ የተሻለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር እና ለትውልድ ለማስተላለፍ እጅግ አስፈላጊ ተግባር መሆኑን ጠቁመው በመርሃግብሩ ላለፉት አመታት እንዳደረግነው ሁሉ ነገም የሀይማኖት፣ የብሔርና የፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ሳይገድበን በነቂስ በመውጣት ስለሀገራችን ብለን የምንሳተፍበት ተግባር ነው ብለዋል።
በክልላችንም በአንድ ጀምበር ለሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር አስፈላጊውን ዝግጅት ያጠናቀቅን በመሆኑ ነገ ሐምሌ 10 ከማለዳው 12:00 ጀምሮ በተዘጋጁ የችግኝ የመትከያ ስፍራዎች እንዲሁም በየአካባቢው ችግኝ በመትከል ሀገራዊ ሀላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል።
ሐምሌ 9 ቀን 2015 ዓ.ም

ሙሽሮቹ የጋብቻ ስነ-ስርዓታቸውን ችግኞችን በመትከል አከበሩ
*****
(ኢ ፕ ድ)
በሀድያ ዞን ሾኔ ከተማ ጋብቻቸውን ዛሬ የፈፀሙት ጥንዶች የጋብቻ ስነ-ስርዓታቸውን ችግኞችን በመትከል አሳልፈዋል።
ጥንዶቹ የችግኝ ተከላውን ከሚዜዎቻቸው ቤተሰቦቻቸውና አጃቢዎቻቸው ጋር "ነገን ዛሬ እንትከል" የሚለውን መርህ በመከተል መሆኑም ተገልጿል።
በሾኔ ከተማ ሊቻ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው ሙሽራው አቶ ረታ ወልቃ ለኢዜአ በሰጠው አስተያየት እንደገለጸው ችግኝ መትከል የሰው ልጆችን ህይወት ጤናማ እንደሚያደርግ ነው።
“በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ትግበራ የሀገሪቱን የግሪን ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ከማሳደግ በተጨማሪ ሁለንተናዊ ጉዞዋን ለማሳለጥ የሚያግዝ በመሆኑ በተግባሩ በመሳተፍ ላይ ነኝ” ሲል ገልጿል።
ነገ በሀገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀምበር የሚተከለውን አምስት መቶ ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርሀ-ግብርን በማሰብ ዛሬ የሰርግ ስነ-ስርዓቱን ችግኞችን በመትከል ለማሳለፍ መነሳሳቱን አብራርቷል።
ሙሽሪት ወይዘሮ ፍሬህይወት ብርሃኑ በበኩሏ የሀገርን ልዕልና አስጠብቆ ለማስቀጠል ቅድሚያ መሰጠት እንዳለበትና የጊዜና የቦታ ወሰን ሊገድብ እንደማይገባ ተናግራለች።
አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የሀገራችንን ከፍታ ለማረጋገጥ ታቅዶ በመተግበር ላይ ያለ በመሆኑ የሰርግ ስነ-ስርዓታቸውን ከሚዜዎቻቸው፣ ከአጃቢዎቻቸውና ከቤተሰቦቻቸዉ ጋር ችግኝ በመትከል ለማሳለፍ ከባለቤቷ ጋር ቀድመው የተተስማሙበት መሆኑን ተናግራለች።
የተከሉትን ችግኝ በመንከባከብ ለታቀደው ዓላማ እንዲውል የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ ገልጸዋል።
የሾኔ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አበራ በዶሬ በከተማው በአንድ ጀምበር ከ 100 ሺህ በላይ የተለያየ ዝርያ ያላቸውን ችግኞች ለመትከል ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ተናግረዋል።
ዛሬ የጋብቻ ስነ-ስርዓታቸውን የፈፀሙት ጥንዶች በሰርጋቸው ላይ የተለያየ ዝርያ ያላቸውን ችግኞች በሾኔ ከተማ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ በመትከል ማሳለፋቸውን ተናግረዋል።
የጥንዶቹ ድርጊት ለአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ትግበራ የሰጡትን ትኩረት የሚያመላክት ከመሆኑ በተጨማሪ የጋራ ሃሳቡ ሊጠናከር እንደሚገባም ገልጸዋል።

#አረንጓዴዐሻራ
በአንድ ጀምበር 500 ሚሊየን ችግኞች የሚተከሉበት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ዛሬ ይካሄዳል
"ነገን ዛሬ እንትከል"በሚል መሪ ሀሳብ ዛሬ ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን ችግኞች የሚተከሉበት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ይካሄዳል።
እርስዎስ ተዘጋጅተዋል?

በመላው ኢትዮጵያ በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሃ ግብር ተጀመረ
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
በአገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኞችን የመተከል መርሃ ግብር በይፋ ተጀምሯል።
የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ እንደገለፁት፤ ኢትዮጵያዊ ን ከጫፍ እስከ ጫፋ በመነሳት በአካባቢያቸው የአረጓዴ አሻራቸውን እያኖሩ ነው።
በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከጠዋቱ 12ሰዓት ጀምሮ በመላ አገሪቱ በይፋ መጀመሩን ገልፀዋል።
ይህ አረንጓዴ ዐሻራ የዛሬን ትውልድ ህይወቱን የሚድስ ለነገው ተስፋ የሚጭር መሆኑን ገልፀዋል።
ኢትዮጵያን አረንጓዴ የማልበሱን ሁነት ከሶስት ሺህ በላይ የሚዲያ ባለሙያዎች እየዘገቡ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል።
ከዘጠኝ ሺህ በላይ ቦታዎች የሚተከሉ ችግኞች በሳተላይት መከታተል የሚስችል ዝግጅትም ተደርጓል ብለዋል።
መላው ህዝብ በዚህ ታሪካዊ ዕለት የራሱን ዐሻራ በማኖር ዜጋዊ ድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
በአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳድሮች ጨምሮ 500 ሚሊዮን ችግኞች ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት 500ሚሊዮን ችግኞች የሚተከሉ ይሆናል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአንድ ጀምበር 500ሚሊዮን ችግኞችን ተክለን የራሳችንን ሪከርድ እንስበር ሲሉ ለመላው ህዝብ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።
ችግኞችን የሚተከሉበት አካባቢዎች ሁሉ መረጃ የሚሰበሰብበት ሲችዌሽን ክፍል ተዝጋጅቶ ሥራውን እያከናወነም ይገኛል።
ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም
በጌትነት ምሕረቴ