Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
344 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
3ኛው ዓመታዊ የፓርላማ ጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው
****
(ኢ ፕ ድ)

የኢፌድሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛው ዓመታዊ የፓርላማ ጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ "ህግ አወጣጥ፣ ክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም የሕዝብ ውክልና" በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ነው፡፡

በኮንፍረንሱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ፤ ምክር ቤቱ የተጣለበትን ከፍተኛ ኃላፊነት ለመወጣት በጥናትና ምርምር ላይ የተመሰረቱ ተግባራት ማከናወን ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት ምክር ቤቱ በጥናትና ምርምር ላይ የተመሠረተ ውሳኔዎች እያስተላለፈ ይገኛል ያሉት አቶ ታገሰ፤ በዘንድሮ ዓመትም ከ60 በላይ ጥናት ቀርቦ 13 የሚሆኑት መሥፈርቱን አሟልተው ተገኝተዋል ብለዋል፡፡

አቶ ታገሰ አክለውም፤ የሚደረጉ ጥናትና ምርምሮች ምክር ቤቱ ለሚያከናውናቸው ተግባራት ትልቅ ግብዓት እንደሚሆኑና ምክር ቤቱ ትክክለኛና በእውነታ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ እንዲያስተላልፍ እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡

የኢፌድሪ ፍትህ ሚኒስትር ጌዲዖን ጢሞቲዎስ (ዶክተር) በበኩላቸው፤ ምክር ቤቱ በህዝብ የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ የጥናትና ምርምር ሥራዎች በእጅጉ ጠቃሚ ናቸው ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ አክለውም ፓርላማው በጥናትና መርምር ሥራዎች ላይ መድረክ መፍጠሩ ለተመራማሪዎችና ለሙሁራን ለወደፊት ስራቸው እንዲጠናከርና አዳዲስ የጥናትና ምርምር ሥራዎች እንዲፈጠሩ እድል እንደሚፈጥር ጠቁመዋል፡፡

በኮንፍረንሱ የኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ ሚኒስትሮች፣ የክልልና የከተማ አስተዳደር አፈጉባዔዎች፣ የዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንቶች፣ የቀድሞ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ሰኔ 24 ቀን 2015 ዓም
በልጅዓለም ፍቅሬ
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ከፍተኛ አመራሮች ከዓለም ባንክ የፕሮግራሞች ገለልተኛ ግምገማ ቡድን ጋር ተወያዩ
****************
(ኢ.ፕ.ድ)

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ከፍተኛ አመራሮች ከዓለም ባንክ የፕሮግራሞች ገለልተኛ ግምገማ ቡድን ጋር ተወያዩ፡፡

ገለልተኛ ቡድኑ የባንኩን ከ2012-2022 በኢትዮጵያ የነበረዉን ተሳትፎ ለመገምገም የመጣ ሲሆን ከተለያዩ ዘርፎች ጋር እንደሚገናኝም ይጠበቃል፡፡

ከግምገማዉ በኋላም ቀጣይ እቅዶችን በማዘጋጄት የልማት ትብብር መስኮችን ይለያል ፡፡
ግምገማዉ ባንኩ በኢትዮጵያ የሰራቸዉ የልማት ትብብር ስራዎች ከሚመለከታቸዉ የመንግስት አካላት ጋር በመሆን በዝርዝር የሚገመግም ሲሆን ለአብነትም የአየር ንብረት ለዉጥ ጋር የተገናኙ ተግባራት እንዲሁም የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ ረገድ የተሰሩ ስራዎችም ይጠቀሳሉ፡፡

ባንኩ በኢትዮጵያ ያለዉን የልማት ትብብር ተሳትፎ በተመለከተ ከፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍጹም አሰፋ እንዲሁም ሚኒስትር ዲኤታዉ ዶ/ር ነመራ ገበየሁ ጋር ሰፈ ዉይይት አድርገዋል፡፡

ከግምገማዉ ቀጥሎ በሚዘጋጁ እቅዶች ላይ ባንኩ የኢትዮጵያን የልማት የትኩረት መስኮችና ቅድሚ የሚሰጣቸዉን ፍላጎቶች በመለዬት የትብብር ማዕቀፉ እንደሚዘጋጅ ይጠበቃል፡፡

የባንኩ የፕሮግራሞች የግምገማ ቡድን አባላት ከተለያዩ አካላት ጋር በመገናኘት የሚወያዩ ሲሆን ካለፉት አስር ዓመታት ተሞክሮዎችን በመዉሰድና የቀጣይ የኢትዮጵያ የልማት መስኮች በማገናዘብ አዲስ የልማት ትብብር ማዕቀፍ ይቀርጻል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተሳተፉበት የእግር ኳስ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ይታያል
************
(ኢ.ፕ.ድ)

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተሳተፉበት የእግር ኳስ ጨዋታ ዛሬ ምሽት በተለያዩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ይታያል።

ጨዋታው የኢቢሲ ሚዲያ ኮምፕሌክስ ምርቃትን ምክንያት በማድረግ የተደረገ እንደሆነ ተቋሙ አስታውቋል።

ጨዋታው ዛሬ ምሽት 1 ሰዓት ላይ በኢቲቪ ዜና ቻናል፣ በኢቲቪ መዝናኛ ቻናል እና በኢቢሲ የዩቲዩብ ገጽ የሚተላለፍ ሲሆን፤ ኢፕድም ይህንኑ ጨዋታ በማህበራዊ ገጾቹ የሚያጋራ መሆኑን ከወዲሁ ያሳውቃል።
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት
8.2 ኪ.ሜ ርዝመት እና ከ10 እስከ 40 ሜትር የጎን ስፋት ያለውን የኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም ቤቶች የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ አጠናቅቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል።

ህዳር 2013 ዓ.ም የመንገዱን ግንባታ ባስጀመርንበት ወቅት የአካባቢው መህበረሰብ እና የጋራ መኖርያ ቤት ባለዕድለኞች “ቶሎ ገንቡልን” ሲል ጋቢ አልብሰው አደራ ሰጥተውን ነበር።

እኛም መንገዱ በአካባቢው ያለውን የመንገድ መሰረተ ልማት እጥረት የሚቀርፍ እና የጋራ መኖርያ ቤት ባለዕድለኞች ወደ ቤታቸው ሲገቡ የሚሰጣቸውን ፋይዳ በመገንዘብ ግንባታውን ባስጀመርንበት ወቅት በገባነው ቃል መሰረት በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቅቀን ዛሬ ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል።

በዚህ በጀት አመት የያዝናቸው ትልልቅ ተሻጋሪ ድልድዮች እና የመንገድ ፕሮጀክቶችም እየተጠናቀቁ ነው።