"የሰው ሀይል ምርታማነትን ማረጋገጥ ካልተቻለ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ከፍላጐት ያለፈ አይሆንም"
ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል-የስራና ክህሎት ሚኒስትር
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የሰው ሀይል ምርታማነትን ማረጋገጥ ካልተቻለ የኢኮኖሚ እድገት ከፍላጐት ያለፈ አይሆንም ሲሉ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ገለጹ።
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ምርታማነት ላይ የተኮረ ምክክር ከሚመለከታቸው ባለ ደርሻ አካላት ጋር እያካሄደ ነው።
ሚኒስሯ በምክክር መድረኩ ባቀረቡት ንግግር፣ "ለአንድ አገር ትልቁ ሀብቱ የሰው ሀይል ነው። የሰው ሀይልን ምርታማነት ማረጋገጥ ካልቻልን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት ከፍላጐት ያለፈ አይደለም" ብለዋል።
አንደ አገር ከኢኮኖሚ እድገት ጋር የተሳሰረ ክህሎት ተኮር የስራ እድል ፈጠራ እንደሚያስፈልግ ሚኒስትሯ ገልጸዋል። ለኢኮኖሚው እድገት ዜጐችን በእውቀትና በክህሎት በማልማት ማስተዳደር እንደሚገባም አመላክተዋል።
ዜጐቿ ደስተኛ ሆነው የሚኖሩባትን አገር ማየት የማይፈልግ የለም ያሉት ሚኒስትሯ፣ ይህ የጋራ መሻት እውን እንዲሆን እንደ ተቋም ለብቻ መስራት እንደማይቻል ጠቅሰው፣ ማልማት፣ ማብቃትና ማስተዳደር ላይ ጠንካራ አጋርነት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዜጐች አገራዊ ጸጋዎችን በመጠቀም የስራ ፈጣሪነት አስተሳሰባቸው እንዲጐለብት እያደረገ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
በምክክሩ የሚዲያ ባለሙያዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ባለ ድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ሰኔ 23 ቀን 2015 ዓም
በአዲሱ ገረመው

የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ስምንት ሚሊየን ወጣቶች ተሳታፊ የሚሆኑበት የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ሊያስጀምር ነው
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ስምንት ሚሊዮን ወጣቶች ተሳታፊ የሚሆኑበት የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በአሶሳ ከተማ በነገው እለት ያስጀምራል።
በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ወጣቶች ተሣታፊ የሚሆኑበት የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎትን በተመለከተ የሊጉ ምክትል ፕሬዝዳንትና የፅ/ቤት ሀላፊ ወጣት አባንግ ኩሙዳን መግለጫ ሰጥታለች።
በበጎ ፍቃድ አገልግሎቱ የአቅመ ደካሞች ቤት የማደስ፣ የደም ልገሳና የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር እንደሚከናወን ወጣት አባንግ ገልጻለች።
አራት መቶ ሚሊዬን ችግኞች እንደሚተከሉ በመግለጫው ተገልጿል፡፡
ሰኔ 23 ቀን 2015 ዓም
አማን ረሺድ
(ፎቶ ፋይል

የኦሮሚያ ክልል ከ323 ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለማስፈተን መዘጋጀቱን አስታወቀ
*****************
-484 ሺህ 994 የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ይፈተናሉ
የኦሮሚያ ክልል 323 ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለማስፈተን መዘጋጀቱን አስታወቀ። በተመሳሳይም 484 ሺህ 994 የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና ይወስዳሉ።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ሀላፊ ዶክተር ቡልቶሳ ሂርኮ የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ፈተናዎች ዝግጅትን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፤ በክልሉ ከ323 ሺህ በላይ የ12ኛ እና 484 ሺህ 994 የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ለፈተና ተመዝግበዋል፡፡
እንደ ዶክተር ቡልቶሳ ገለጻ የ8ኛ ክፍል ፈተና በአንድ ሺህ 441 የፈተና ጣቢያዎች ላይ ሰኔ 26 እና 27 ይሰጣል፡፡
ለ12ኛ ክፍል ፈተና በማህበራዊ ሳይንስ እና በተፈጥሮ ሳይንስ በአጠቃላይ ከ323 ሺህ በላይ ተማሪዎች ይፈተናሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል፡፡
የ12ኛ ክፍል ፈተና በ22 ዩነቨርሲቲዎች ይሰጣል ያሉት ዶክተር ቡልቶሳ፤ 17 በክልሉ በሚገኙና 5 አጎራባች ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ፈተናው ይሰጣል ብለዋል፡፡
ፈተናው ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከሐምሌ 19 እስከ 21 የሚሰጥ መሆኑን ጠቅሰው ለተፈጥሮ ሳይንስ ከሐምሌ 25 እስከ 28 እንደሚሰጥ ገልፀዋል፡፡
ፈተናው የተሳካ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ግብረሀይል ተቋቁሞ ወደ ትግበራ ተገብቷል፤ በዚህም ከባለፈው ዓመት ልምድ በመነሳት ፈተናውን ተማሪዎች አንዳች ችግር ሳይገጥማቸው ለመስጠት ዝግጅት ተደርጓልመ ብለዋል።
ሰኔ 23 ቀን 2015 ዓም
በማርቆስ በላይ

በፌዴራል መንግሥት ለክልሎች የሚሰጠው በጀትና ድጎማ በፌዴራል ዋና ኦዲተር ስር ኦዲት ሊደረግ ነው
************
(ኢ.ፕ.ድ)
ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ ሁሉንም ክልሎች ከፌደራል መንግሥት የተሰጣቸውን በጀትና ድጎማ መሠረት በማድረግ በዋና ኦዲተር ስር ኦዲት ለማድረግ እንደሚሠራ ተገለጸ።
ዋና ኦዲተር ወይዘሮ መሠረት ዳምጤ ሰኔ 20 ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበውን ዓመታዊ የኦዲት ሪፖርት አስመልክቶ ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት፤ እስካሁን የክልል ዋና ኦዲተሮች በየክልላቸው ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኪን ይጫኑ
https://press.et/?p=103842

በሦስት ክልሎች ከ8 ሚሊዮን በላይ ለሆኑ ተፈናቃዮች 4 ሚሊዮን ኩንታል የምግብ ድጋፍ ተደርጓል
************
(ኢ.ፕ.ድ)
ባለፉት ሰባት ወራት በአማራ፣ በትግራይና በአፋር ክልሎች በሰው ሠራሽና በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ከ8 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ተፈናቃዮች 4 ሚሊዮን ኩንታል የምግብ ድጋፍ መደረጉን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ከፍተኛ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አታለል አቡሃይ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ባለፉት ሰባት ወራት ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=103847

በመላው ሃገሪቱ በተገነቡት ኢንዱስትሪ ፓርኮች በተፈጠረ የገበያ ትስስር ከ300ሺ በላይ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ ተገለጸ
*****
(ኢ ፕ ድ)
በመላው ሃገሪቱ በተገነቡት የአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርኮች አካባቢ ያሉ አርሶ አደሮች የግብርና ምርቶቻቸውን በኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ላሉ አምራቾች እንዲያቀርቡ በማድረግ ሰፊና ዘላቂ የገበያ ትስስር በመፍጠር ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ ተገለጸ።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የማርኬቲንግና ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘመን ጁነዲን እንደገለጹት፤ በገበያ ትስስሩ ከ 15 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች በጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የአቮካዶ ዘይት ምርት በማምረት ለተሰማራ ኩባንያ የአቮካዶ ፍራፍሬ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።
እንደ ኃላፊው ገለጻ፤ በደብረ ብርሃን እና ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ደግሞ ለቢራ አምራች ካምፓኒዎች ብቅል የማቅረብ ስራ ለሚሰሩ አምራቾች የቢራ ገብስ በማቅረብ በኩል ከ280 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች የገበያ ትስስር ተፈጥሮላቸዋል፡፡
በኢንዱስትሪ ፓርኮቹ የአካባቢውን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ያስገባ ስራዎችን በመሰራት ላይ እንደሚገኙ የገለጹት አቶ ዘመን በቅርቡም በአፋር አካባቢ ያለውን የግመል ወተት በግብዓትነት የሚጠቀም ካምፓኒ በሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ እንዲሁም አማራ ክልል አካባቢ ያለውን የበቆሎ ምርት በግብዓትነት የሚጠቀም አምራችም እንዲሁ በባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ ገብተው ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ፈጽመው ግንባታ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተልባ እግርን በግብዓትነት የሚጠቀም ካምፓኒ ጋር የገበያ ትስስር ስራዎች ለመስራት የዘር ብዜትና የምርምር ስራዎች በመሰራት ላይ እንደሚገኙ የገለጹት ኃላፊው በቀጣይም የዘር ብዜቱን ለአርሶ አደሩ በማሰራጨት በስፋት ወደ ምርት እንዲገቡ የማድረግ ስራዎች እንደሚሰሩ አብራርተዋል፡፡
በኢንዱስትሪ ፓርኮች በአልባሳትና ጨርቃ ጨርቅ፤በአግሮ ፕሮሰሲንግ፤በፋርማሲዩቲካል ዘርፎች ተሰማርተው እንደሚገኙ የገለጹት አቶ ዘመን በተለይም ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በኋላ ያለው የኢንቨስትመንት ፍሰት በከፍተኛ ሁኔታ መነቃቃቱንና የባለሃብቶች ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎትም በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር መቻሉን ተናግረዋል፡፡
በኮርፖሬሽኑ አሁን ላይ 11 ኢንዱስትሪ ፓርኮች ሙሉ በሙሉ በስራ ላይ የሚገኙ ሲሆን የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክን ወደ ስራ ለመመለስም የተለያዩ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውን የተናገሩት አቶ ዘመን በተለይም ፓርኩን ወደ ነበረበት ለመመለስ የነበሩ ባለሃብቶችን የማወያየት እና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ መድረስ መቻሉን አቶ ዘመን ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል፡፡