Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የዓይን ብሌንለመለገስ ቃል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው
👉 223 ዜጎች የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ተደርጎላቸዋል፣
**************
(ኢ ፕ ድ)
የዓይን ብሌን ለመለገስ ቃል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል እያሳየ መምጣቱን የዓይን ባንክ አስታወቀ፡፡ በፈረንጆቹ ባለፈው አንድ ዓመት 223 ዜጎች የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ እንደተደረገላቸው ተገልጿል::
የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ የግንዛቤ ማስጨበጫ አስተባባሪ አቶ ነጋ ደምሴ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በፈረንጆቹ ባለፈው ዓመት 191 ዜጎች ለመለገስ ቃል ገብተዋል:: በተለይም ከታዋቂው አርቲስት ታሪኩ ብርሀኑ ህልፈት በኋላ
ባንኩ የማህበረሰብ ተቋም በመሆኑ ህልፈት ካጋጠመ በኋላ የዓይን ብሌንን....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94417
በኦሮሚያ ክልል በመጪው የክረምት ወቅት አምስት ቢሊዮን የሚጠጉ ችግኞች ይተከላሉ
**************
(ኢ ፕ ድ)
በኦሮሚያ ክልል በመጪው የክረምት ወቅት አራት ነጥብ ዘጠኝ ቢሊዮን ችግኞች እንደሚተከሉ የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ::
የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በክልሉ በመጪው የክረምት ወቅት አራት ነጥብ ዘጠኝ ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እስከ አሁን ድረስ ሦስት ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ችግኞች ተዘጋጅተዋል::
ባለፈው የክረምት ወቅት አራት ነጥብ ሦስት ቢሊዮን ችግኞች መተከላቸውን ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94451
በደቡብ ክልል ከበጋ መስኖ ስንዴ ከ500 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል
*************
(ኢ ፕ ድ)
በክልሉ በዘር ከተሸፈነው የበጋ መስኖ ስንዴ ከ500 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ የደቡበ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡
በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከ13 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በስንዴ መሸፈኑ ተገልጿል፡፡
በክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በክልሉ 13 ሺህ 400 ሄክታር መሬት በመስኖ ስንዴ ተሸፍኗል፡፡
በአጠቃላይ ከ36 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች በመስኖ ልማቱ እየተሳተፉ ሲሆን ከ500 ሺህ ኩንታል በላይ.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94442
በአማራና አፋር ክልሎች ከ90 በመቶ በላይ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ጥገና ተደርጓል
************
(ኢ ፕ ድ)
በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ተከስቶ በነበረው ጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሥራ ለማስጀመር አስፈላጊው በጀትና የሰው ኃይል በመመደብ ከ90 በመቶ በላይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት እንደጀመረ ተገለፀ፡፡
የአማራ ክልል የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰለሞን ጣሰው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94444
በ2015/16 የመኸር ምርት ዘመን12.8ሚሊዮን ኩንታል የማዳበሪያ ግዥ ተፈጸማል
*************
(ኢ ፕ ድ)

በ2015/16 የመኸር ምርት ዘመን 12 ነጥብ 8ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዥ መፈጸሙን የግብርና ሚኒስቴር አሰታወቀ።

የግብርና ሚኒስትር ዶክተር ግርማ አመንቴ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት በ2015/16 የመኸር ምርት ዘመን 12 ነጥብ 8ሚሊዮን ኩንታል የማዳበሪያ ግዥ ተፈጽሟል።

ከዚህ ውስጥ 4 ነጥብ 8 ሚሊዮኑ ጂቡቲ ወደብ ደርሷል። ወደብ ከደረሰው 4 ነጥብ 5 ሚሊዮኑ ወደ ክልሎች ተጓጉዟል። ይህም ለአርሶ አደሩ በፋጥነት ተደራሽ ይደረጋል ብለዋል።

መንግስት የማዳበሪያ ዋጋን ለማረጋጋትም 21 ቢሊዮን ብር አድጎ ማድረጉን ጠቅሰው፣ ይህም በአንድ ኩንታል ማዳበሪያ 1566 ብር ድጎማ መደረጉን ተናግረዋል።

በጌትነት ምህረቴ
ከተማዋን የኢንቨስትመንትና የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ እየተሠራ ነው
************
(ኢ ፕ ድ)

የደብረ ታቦር ከተማን የኢንቨስትመንት እና የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን የከተማዋ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ መምሪያ ገለጸ።

የደብረ ታቦር ከተማ የኢንቨስትመንት እና የኢንዱስትሪ መምሪያ ኃላፊ አቶ አባይነው አሸብር ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ከተማዋ የኢንቨስትመንት፣ የንግድና የኢንዱስትሪ ባለቤትነቷን አጥታ ቆይታለች። ይሁንና መምሪያው አሁን ላይ ከተማዋን የሚመጥኑ የልማት ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል።

በንጉሡ እና በደርግ ዘመን የነበረውን የአውሮፕላን ማረፊያ እንደገና በማስፋፋት በአዲስ መልክ ሥራ ለማስጀመር ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህም ኢንቨስትመንትን ወደ ከተማዋ ለመሳብ የራሱ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡

እንደ አቶ አባይነው ገለጻ፤ የአካባቢውን የተፈጥሮ ጸጋ በመጠቀም የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት ለመሳብ እየተሠራ ነው። በተለይ በእንጨት፣ አግሮ ፕሮሰሲንግ፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ ስጋና ወተት፣ ሲሚንቶ እና የቢራ ብቅል፣ ማዕድንና መሰል ዘርፎች ላይ የሚሰማሩ ባለሀብቶችን ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል።

ከተማዋ በተለያዩ ዘርፎች ለሚሰማሩ ባለሀብቶች እና ጥያቄ ለሚያቀርቡ ሁሉ አገልግሎት ለመስጠት...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94456
ዩኒቨርሲቲው በቴክኖሎጂና በሳይንስ ዘርፍ ተግባር ተኮር የምርምር ሥራዎችን እያከናወነ ነው
**************
(ኢ ፕ ድ)

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ካለፉት ሦስት ዓመታት ጀምሮ በቴክኖሎጂና በሳይንስ ዘርፍ ተግባር ተኮር የምርምር ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ::

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ታረቀኝ ብርሃኑ እንደገለጹት፤ ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94453
ከኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ከ48 ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል
*******************
(ኢ ፕ ድ)

ባለፉት ሰባት ወራት ከኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ከ48 ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።

ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን እንዳሉት፤ .
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94506
የሰንበት ቀን ገበያዎች ተደራሽነታቸው ሊሰፋ እንደሚገባ ነዋሪዎች ተናገሩ

👉 አስተዳደሩ ገበያዎቹን ለማስፋፋት በትኩረት እንደሚሠራ አስታውቋል
*******************
(ኢ ፕ ድ )

የሰንበት ቀን ገበያዎች የሸማቹን አቅም ያገናዘቡ በመሆናቸው ተደራሽነታቸው ሊሰፋ እና የግብይት ሥርዓታቸው ሊጠናከር ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ የሰንበት ቀን ገበያዎች ተደራሽነታቸው እንዲሰፋ እና የተሳለጡ እንዲሆኑ እንደሚሠራ አስታውቋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ የስድስት ኪሎ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ሃና ዮሐንስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የሰንበት ቀን ገበያ ማኅበረሰቡ የሚፈልገውን ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያገኝበት የገበያ ቦታ ሆኗል።

በስድስት ኪሎ የሰንበት ቀን ገበያ ለግብይት የሚቀርቡ ምርቶች ነጋዴዎች በመደበኛ የመሸጫ ማዕከላት ከሚሸጡበት ዋጋ በተመጣጣኝ ዋጋ ለገዥዎች ያቀርባሉ። በመሆኑም አሁን ያለውን ተደራሽነት ከዚህም በላይ ማስፋፋት ቢቻል የሚል ሀሳብ አቅርበዋል።

በየካ ክፍለ ከተማ የመገናኛ ነዋሪ የሆነችው ወይዘሪት ፍሬህይወት ጫንያለው በበኩሏ፤ የሰንበት ቀን ገበያ ሸቀጣቀጦችን፣ አትክልቶችንና የቤት አስቤዛዎችን ከሱቆች ዝቅባለ የግብይት ዋጋ እያቀረቡ ነው። የገበያ ተደራሽነቱን በማስፋፋት የተለያዩ የጥራጥሬ፣ የጤፍ፣ የበቆሎ፣ የገብስና የመሳሰሉ ምርቶችንም በገበያው በይበልጥ ለአቅርቦት የሚውሉበት መንገድ ቢፈጠር የኑሮ ውድነቱን ለማርገብ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94521
በበልግ ዝናብ የጎርፍ አደጋ እንዳይደርስ አስፈላጊው ቅድመ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል
****************
(ኢ ፕ ድ)

በቀጣዮቹ አሥር ቀናት የሚጥለው የበልግ ዝናብ የጎርፍ ተጠቂ በሆኑ የተፋሰስ አካባቢዎች ላይ አደጋ እንዳያስከትል አስፈላጊው ቅድመ ጥንቃቄ ከወዲሁ ሊደረግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

ኢንስቲትዩቱ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በሚቀጥሉት አስር ቀናት የሚስተዋለው የዝናብ ሁኔታ አብዛኛውን የበልግ ርጥበት ተጠቃሚ ተፋሰስ የሆኑ አካባቢዎችን የሚሸፍን ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሰሜን ምሥራቅ፣ የምሥራቅ፣ የደቡብና የደቡብ ምሥራቅ በመጠንም ሆነ በሥርጭት የተስፋፋና የተጠናከረ ርጥበት ያገኛሉ።

በዚህም ዝናቡ የጎርፍ ተጠቂ በሆኑ ተፋሰሶች ላይ ጉዳት እንዳያስከትል አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ ከወዲሁ ሊደረግ እንደሚገባ ተመላክቷል።

ኢንስቲትዩቱ የላከው መግለጫ እንደሚያትተው፤ አብዛኛው ኦሞ ጊቤ ስምጥ ሸለቆ፣ አዋሽ፣ ገናሌ ዳዋ፣ የላይኛውና መካከለኛው ዋቢ ሸበሌ፣ የላይኛው ባሮ አኮቦ፣ ተከዜና ዓባይ ተፋሰሶች ላይ ከመጠነኛ እስከ ከፍተኛ እርጥበት የሚያገኙ ናቸው። ይህም ሁኔታ በመጠኑም ቢሆን የገጸ ምድር የውሃ መጠንን ሊያሻሽል እንደሚችል...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94526
የስንብት የአገልግሎት ክፍያ አልተሰጠንም ሲሉ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች ቅሬታቸውን አሰሙ

👉 የደረሰበትን ዝርፊያ አጣርቶ ሲያጠናቅቅ ተገቢውን ክፍያ እንደሚፈጽም ፋብሪካው አስታውቋል
*********************
(ኢ ፕ ድ )
የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ የማስጠንቀቂያና የስንብት ደብዳቤ በወቅቱ ቢሰጠንም በሕግና በሥርዓቱ መሠረት የስንብት የአገልግሎት ክፍያ አልተሰጠንም ሲሉ የፋብሪካው ሠራተኞች ገለፁ።

በፋብሪካው ላይ የተፈጸመው ዝርፊያ ተጣርቶ ሲጠናቀቅ የአገልግሎት ክፍያቸውን እንደሚያገኙ ፋብሪካው አስታውቋል።

በተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ የውሃ አቅርቦት ቡድን መሪ አቶ ሽመልስ መገርሳ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ ፋብሪካው የስንብት ደብዳቤ ከሰጣቸው ሁለት ወር አልፏቸዋል። ነገር ግን በስንብት ደብዳቤው ሕግና ሥርዓት መሠረት የአገልግሎት ክፍያ አልተሰጣቸውም። በዚህም ቤተሰባቸው እና የሚደግፏቸው ሰዎች ለከፍተኛ ችግርና ለርሃብ እየተዳረጉ ነው። ስለዚህ ፋብሪካው በሠራተኛው ላይ እየደረሰ ያለውን ችግር ተረድቶ ጉዳዩን ሊፈታ ይገባል ብለዋል።

ሌላው የፋብሪካው ሠራተኛ አቶ ሽመልስ ደምሌ በበኩላቸው፤ ከፋብሪካው የስንብት ደብዳቤ ከተሰጠኝ በኋላ የአገልግሎት ክፍያ ከሁለት ወር በላይ ባለማግኘቴ አስቸጋሪ ሕይወት እየመራሁ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ተናግረዋል።

በተለይ አካባቢው በረሃ በመሆኑ ከሌላ አካባቢዎች በተለየ ሁኔታ ቤተሰብን....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94539
ኢትዮ ቴሌኮምና ሳምሰንግ ኩባንያ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን ለማቅረብ ስምምነት ፈጸሙ

👉 ኩባንያዎቹ አዲሱን የሳምሰንግ ጋላክሲ ስልክ ለገበያ ማቅረባቸውን አብስረዋል
******************
(ኢ ፕ ድ)

ኢትዮ ቴሌኮም እና ሳምሰንግ ኩባንያ ለደንበኞች የተለያዩ የሳምሰንግ ጋላክሲ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን በአጋርነት ለማቅረብ የሚያስችል ስምምነትም ፈጸሙ። ኩባንያዎቹ በአጋርነት አዲሱን የሳምሰንግ ጋላክሲ ኤስ 23 አልትራ ተንቀሳቃሽ ስልክ ለደንበኞች ማቅረባቸውን ትናንት በተካሄደው የማብሰሪያ መርሃ ግብር ላይ ይፋ አድርገዋል።

በማስተዋወቂያ መርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ማርኬቲንግ ኦፊሰር አቶ ሰይድ አራጋው እንደገለጹት፤ ጋላክሲ ኤስ 23 አልትራ (Galaxy S23 Ultra) ተንቀሳቃሽ ስልክ እጅግ ዘመናዊ ሲሆን በ140 ሺህ ብር ለሽያጭ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ

https://www.press.et/?p=94542
አትክልትና ፍራፍሬ እንዳይበላሽ የሚረዳ ማሸጊያ ማሽን ወደ ሥራ ይገባል
****************
(ኢ ፕ ድ)

የአትክልትና ፍራፍሬ ማሸጊያ ማሽን በተያዘው በጀት ዓመት ወደ ሥራ የሚገባ መሆኑን የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን አስታወቀ።

በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ ሥራ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ምህዲን አስፋው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ቄራ ላይ ሁለት የአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም የስኳር ምርት ማሸጊያ ማሽኖች የመትከል ሥራ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ የመስመር ዝርጋታ ሥራዎች በማሟላት በተያዘው በጀት ዓመት ወደ ሥራ ይገባል።

በስድስት ሚሊዮን ብር ወጪ የሚገነቡት የአትክልትና ፍራፍሬ ማሸጊያዎች ምርት እንዳይበላሽና ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ታሽጎ እንዲቀመጥ ይረዳሉ ያሉት ኃላፊው፣ በቀጣይ የሚገነባው የአትክልትና ፍራፍሬ የማቀዝቀዣ መጋዘን ሕንፃ ሲጠናቀቅ ደግሞ የተሻለ ጥራት ያላቸውን ምርቶች ለገበያ ለማቅረብ ይረዳል ብለዋል።

እንደ አቶ ምህዲን ገለጻ፤ ምርቶቹ ታሽገው ሲሸጡ በኅብረተሰቡ ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ ተደርጎ የተለያዩ ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94546
አቶ ደመቀ መኮንን ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
**************
(ኢ ፕ ድ)

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።