Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በአፍሪካ ቀንድ የሚታየውን የሰራተኞች ፍልሰት ለመቆጣጠር የሚያስችል የቀጠናው አገራት የሚኒስትሮች ፎረም እየተካሄደ ነው
******************
(ኢ ፕ ድ)

በምስራቅና በአፍሪካ ቀንድ የሚታየውን የሰራተኞች ፍልሰት ለመቆጣጠር የሚያስችለው አራተኛው የቀጠናው አገራት የሚኒስትሮች ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

የአለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት በኢትዮጵያ ምክትል ሃላፊ ጂያን ዣን በፎረሙ መክፈቻ ላይ እነዳሉት፤ ፍልሰትን ለመቆጣጠር እና የስደተኛ ሰራተኞችን ደህንነት ለመጠበቅ ፖሊሲዎችን እና ልምዶችን ለማስማማት ጠቃሚ መድረክ ነው።

የስራና ክህሎት ሚኒስትር ድኤታ አቶ አሰግድ ጌታቸው በበኩላቸው አራተኛው የሚኒስትሮች ፈረም በሰራተኞች መብት አያያዝ፣ ጉልበት ብዝበዛን በመከላከል፣ ህገወጥ ፍልሰትን ለመቆጣጠር አገራት ያላቸው ልምዶችና ተሞክሮዎችን የሚለዋወጡበት ነው።

ኢትዮጵያ በሰራተኞች አያያዝና በስራ እድል ፈጠራ ላይ ያላትን ልምድና ትሞክሮ እንደምታካፍል ገልጸዋል።

ፎረሙ 11 አገራትን ማለትም ኢትዮጵያ፣ ኬንያያ፣ ብሩንዲ፣ ኤርትራ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ሩዋንዳ፣ ሶማሊያ፣ ታንዛኒያና ኡጋንዳን የያዘ ሲሆን በአለም አቀፍ የሰራተኞች ድርጅት፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ ተወካዮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ፎረሙ ለሚቀጥሉት አራት ቀናት የሚቆይ ነው።

በሞገስ ተስፋ
ክልሎች ለውሃ ልማት የተበደሩትን አምስት ቢሊዮን ብር ለመመለስ ፈቃደኛ አልሆኑም
**************
(ኢ.ፕ.ድ)

ክልሎችና ከተማ መስተዳደሮች ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ውሃ ለማልማት የተበደሩትን አምስት ቢሊዮን ብር በላይ ለመመለስ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በንጹህ የመጠጥ ውሃ ተደራሽነት ላይ እንቅፋት መፍጠሩ ተገለጸ።

መመለስ ከነበረባቸውም የመለሱት ገንዘብም አንድ ከመቶ በታች መሆኑም ተገልጿል።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ሃብታሙ ኢተፋ ለኢትዮጵያ ፕሬሰ ድርጅት እንደገለጹት፤ የውሃ ልማት ፈንድ በሚኒስቴሩ ስር ሲቋቋም የተገኘውን ገንዘብ ከተሞች ተበድረው የመጠጥ ውሃ ግንባታ አከናውነው ለህብረተሰቡ ከሚሰጡት የመጠጥ ውሃ ደግሞ የሚገኘውን ገቢ በመሰብሰብ እዳቸውን የሚከፍሉበትን...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94373
የዓይን ብሌንለመለገስ ቃል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው
👉 223 ዜጎች የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ተደርጎላቸዋል፣
**************
(ኢ ፕ ድ)
የዓይን ብሌን ለመለገስ ቃል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል እያሳየ መምጣቱን የዓይን ባንክ አስታወቀ፡፡ በፈረንጆቹ ባለፈው አንድ ዓመት 223 ዜጎች የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ እንደተደረገላቸው ተገልጿል::
የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ የግንዛቤ ማስጨበጫ አስተባባሪ አቶ ነጋ ደምሴ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በፈረንጆቹ ባለፈው ዓመት 191 ዜጎች ለመለገስ ቃል ገብተዋል:: በተለይም ከታዋቂው አርቲስት ታሪኩ ብርሀኑ ህልፈት በኋላ
ባንኩ የማህበረሰብ ተቋም በመሆኑ ህልፈት ካጋጠመ በኋላ የዓይን ብሌንን....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94417
በኦሮሚያ ክልል በመጪው የክረምት ወቅት አምስት ቢሊዮን የሚጠጉ ችግኞች ይተከላሉ
**************
(ኢ ፕ ድ)
በኦሮሚያ ክልል በመጪው የክረምት ወቅት አራት ነጥብ ዘጠኝ ቢሊዮን ችግኞች እንደሚተከሉ የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ::
የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በክልሉ በመጪው የክረምት ወቅት አራት ነጥብ ዘጠኝ ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እስከ አሁን ድረስ ሦስት ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ችግኞች ተዘጋጅተዋል::
ባለፈው የክረምት ወቅት አራት ነጥብ ሦስት ቢሊዮን ችግኞች መተከላቸውን ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94451
በደቡብ ክልል ከበጋ መስኖ ስንዴ ከ500 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል
*************
(ኢ ፕ ድ)
በክልሉ በዘር ከተሸፈነው የበጋ መስኖ ስንዴ ከ500 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ የደቡበ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡
በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከ13 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በስንዴ መሸፈኑ ተገልጿል፡፡
በክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በክልሉ 13 ሺህ 400 ሄክታር መሬት በመስኖ ስንዴ ተሸፍኗል፡፡
በአጠቃላይ ከ36 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች በመስኖ ልማቱ እየተሳተፉ ሲሆን ከ500 ሺህ ኩንታል በላይ.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94442
በአማራና አፋር ክልሎች ከ90 በመቶ በላይ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ጥገና ተደርጓል
************
(ኢ ፕ ድ)
በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ተከስቶ በነበረው ጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሥራ ለማስጀመር አስፈላጊው በጀትና የሰው ኃይል በመመደብ ከ90 በመቶ በላይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት እንደጀመረ ተገለፀ፡፡
የአማራ ክልል የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰለሞን ጣሰው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94444
በ2015/16 የመኸር ምርት ዘመን12.8ሚሊዮን ኩንታል የማዳበሪያ ግዥ ተፈጸማል
*************
(ኢ ፕ ድ)

በ2015/16 የመኸር ምርት ዘመን 12 ነጥብ 8ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዥ መፈጸሙን የግብርና ሚኒስቴር አሰታወቀ።

የግብርና ሚኒስትር ዶክተር ግርማ አመንቴ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት በ2015/16 የመኸር ምርት ዘመን 12 ነጥብ 8ሚሊዮን ኩንታል የማዳበሪያ ግዥ ተፈጽሟል።

ከዚህ ውስጥ 4 ነጥብ 8 ሚሊዮኑ ጂቡቲ ወደብ ደርሷል። ወደብ ከደረሰው 4 ነጥብ 5 ሚሊዮኑ ወደ ክልሎች ተጓጉዟል። ይህም ለአርሶ አደሩ በፋጥነት ተደራሽ ይደረጋል ብለዋል።

መንግስት የማዳበሪያ ዋጋን ለማረጋጋትም 21 ቢሊዮን ብር አድጎ ማድረጉን ጠቅሰው፣ ይህም በአንድ ኩንታል ማዳበሪያ 1566 ብር ድጎማ መደረጉን ተናግረዋል።

በጌትነት ምህረቴ
ከተማዋን የኢንቨስትመንትና የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ እየተሠራ ነው
************
(ኢ ፕ ድ)

የደብረ ታቦር ከተማን የኢንቨስትመንት እና የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን የከተማዋ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ መምሪያ ገለጸ።

የደብረ ታቦር ከተማ የኢንቨስትመንት እና የኢንዱስትሪ መምሪያ ኃላፊ አቶ አባይነው አሸብር ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ከተማዋ የኢንቨስትመንት፣ የንግድና የኢንዱስትሪ ባለቤትነቷን አጥታ ቆይታለች። ይሁንና መምሪያው አሁን ላይ ከተማዋን የሚመጥኑ የልማት ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል።

በንጉሡ እና በደርግ ዘመን የነበረውን የአውሮፕላን ማረፊያ እንደገና በማስፋፋት በአዲስ መልክ ሥራ ለማስጀመር ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህም ኢንቨስትመንትን ወደ ከተማዋ ለመሳብ የራሱ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡

እንደ አቶ አባይነው ገለጻ፤ የአካባቢውን የተፈጥሮ ጸጋ በመጠቀም የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት ለመሳብ እየተሠራ ነው። በተለይ በእንጨት፣ አግሮ ፕሮሰሲንግ፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ ስጋና ወተት፣ ሲሚንቶ እና የቢራ ብቅል፣ ማዕድንና መሰል ዘርፎች ላይ የሚሰማሩ ባለሀብቶችን ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል።

ከተማዋ በተለያዩ ዘርፎች ለሚሰማሩ ባለሀብቶች እና ጥያቄ ለሚያቀርቡ ሁሉ አገልግሎት ለመስጠት...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94456