Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ጉዳት የደረሰበት የደሴ ሙዚየም የመልሶ ግንባታ ስራ ተጀመረ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ጉዳት የደረሰበት የደሴ ሙዚየም የመልሶ ግንባታ ስራ መጀመሩን የደሴ ከተማ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ።

የደሴ ከተማ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ትዕግስት አበበ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በእንግሊዝ መንግሥት የገንዘብ ድጋፍ የደሴ ሙዚየምን የማደስና የመልሶ ግንባታ ፕሮጀክት ተጀምሯል።

የደሴ ሙዚየም መልሶ ግንባታ ስራ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የመምሪያ ኃላፊዋ ጠቁመዋል። በቱሪዝም ዘርፍ የወደሙ መሰረተ ልማቶችንና ቅርሶችን መልሶ የመገንባት ስራ በተደራጀ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል።

ስራው በቀጣይ የቱሪዝም ዘርፍ ገቢን ለማሳደግ ይረዳል ሲሉም ወ/ሮ ትዕግስት ተናግረዋል። ለመልሶ ግንባታና....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94330
ፓርኩ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ አድኗል
***************
(ኢ ፕ ድ)

የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ባለፉት ስምንት ወራት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ማዳኑን አስታወቀ። ባለፉት ስምንት ወራት ምርቶችን ለውጭ ገበያ በማቅረብ ከ48 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ማግኘቱንም አስታውቋል።

በፓርኩ እያለሙ የሚገኙ ባለሀብቶች ከሀገር ውስጥ ምርትና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር በፈጠሩት የገበያ ትስስር፤ በስምንት ወራት የሁለት ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር የምርትና አገልግሎት ትስስር መፈጠሩንም አስታውቋል። የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ትንሳኤ ይማም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ በተያዘው በጀት ዓመት የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት በርካታ ሥራዎችን ሲሰራ ቆይቷል። በዚህም ፓርኩ ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባ ምርትን በሀገር ውስጥ መተካት ችሏል።

ለዚህም ሱፍሌት ማልት የብቅል ፋብሪካ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል። ይህ ፋብሪካ ከውጭ የሚገባውን የብቅል ምርት ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ምርት መተካት ችሏል። ይህም 54 ሺህ ለሚሆኑ አነስተኛ የእርሻ መሬት ያላቸው አርሶ አደሮች ተጠቃሚ እንዲሆኑ
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94324

(ፎቶ ኢፕድ ፋይል)
በአፍሪካ ቀንድ የሚታየውን የሰራተኞች ፍልሰት ለመቆጣጠር የሚያስችል የቀጠናው አገራት የሚኒስትሮች ፎረም እየተካሄደ ነው
******************
(ኢ ፕ ድ)

በምስራቅና በአፍሪካ ቀንድ የሚታየውን የሰራተኞች ፍልሰት ለመቆጣጠር የሚያስችለው አራተኛው የቀጠናው አገራት የሚኒስትሮች ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

የአለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት በኢትዮጵያ ምክትል ሃላፊ ጂያን ዣን በፎረሙ መክፈቻ ላይ እነዳሉት፤ ፍልሰትን ለመቆጣጠር እና የስደተኛ ሰራተኞችን ደህንነት ለመጠበቅ ፖሊሲዎችን እና ልምዶችን ለማስማማት ጠቃሚ መድረክ ነው።

የስራና ክህሎት ሚኒስትር ድኤታ አቶ አሰግድ ጌታቸው በበኩላቸው አራተኛው የሚኒስትሮች ፈረም በሰራተኞች መብት አያያዝ፣ ጉልበት ብዝበዛን በመከላከል፣ ህገወጥ ፍልሰትን ለመቆጣጠር አገራት ያላቸው ልምዶችና ተሞክሮዎችን የሚለዋወጡበት ነው።

ኢትዮጵያ በሰራተኞች አያያዝና በስራ እድል ፈጠራ ላይ ያላትን ልምድና ትሞክሮ እንደምታካፍል ገልጸዋል።

ፎረሙ 11 አገራትን ማለትም ኢትዮጵያ፣ ኬንያያ፣ ብሩንዲ፣ ኤርትራ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ሩዋንዳ፣ ሶማሊያ፣ ታንዛኒያና ኡጋንዳን የያዘ ሲሆን በአለም አቀፍ የሰራተኞች ድርጅት፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ ተወካዮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ፎረሙ ለሚቀጥሉት አራት ቀናት የሚቆይ ነው።

በሞገስ ተስፋ
ክልሎች ለውሃ ልማት የተበደሩትን አምስት ቢሊዮን ብር ለመመለስ ፈቃደኛ አልሆኑም
**************
(ኢ.ፕ.ድ)

ክልሎችና ከተማ መስተዳደሮች ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ውሃ ለማልማት የተበደሩትን አምስት ቢሊዮን ብር በላይ ለመመለስ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በንጹህ የመጠጥ ውሃ ተደራሽነት ላይ እንቅፋት መፍጠሩ ተገለጸ።

መመለስ ከነበረባቸውም የመለሱት ገንዘብም አንድ ከመቶ በታች መሆኑም ተገልጿል።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ሃብታሙ ኢተፋ ለኢትዮጵያ ፕሬሰ ድርጅት እንደገለጹት፤ የውሃ ልማት ፈንድ በሚኒስቴሩ ስር ሲቋቋም የተገኘውን ገንዘብ ከተሞች ተበድረው የመጠጥ ውሃ ግንባታ አከናውነው ለህብረተሰቡ ከሚሰጡት የመጠጥ ውሃ ደግሞ የሚገኘውን ገቢ በመሰብሰብ እዳቸውን የሚከፍሉበትን...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94373
የዓይን ብሌንለመለገስ ቃል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው
👉 223 ዜጎች የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ተደርጎላቸዋል፣
**************
(ኢ ፕ ድ)
የዓይን ብሌን ለመለገስ ቃል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል እያሳየ መምጣቱን የዓይን ባንክ አስታወቀ፡፡ በፈረንጆቹ ባለፈው አንድ ዓመት 223 ዜጎች የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ እንደተደረገላቸው ተገልጿል::
የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ የግንዛቤ ማስጨበጫ አስተባባሪ አቶ ነጋ ደምሴ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በፈረንጆቹ ባለፈው ዓመት 191 ዜጎች ለመለገስ ቃል ገብተዋል:: በተለይም ከታዋቂው አርቲስት ታሪኩ ብርሀኑ ህልፈት በኋላ
ባንኩ የማህበረሰብ ተቋም በመሆኑ ህልፈት ካጋጠመ በኋላ የዓይን ብሌንን....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94417
በኦሮሚያ ክልል በመጪው የክረምት ወቅት አምስት ቢሊዮን የሚጠጉ ችግኞች ይተከላሉ
**************
(ኢ ፕ ድ)
በኦሮሚያ ክልል በመጪው የክረምት ወቅት አራት ነጥብ ዘጠኝ ቢሊዮን ችግኞች እንደሚተከሉ የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ::
የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በክልሉ በመጪው የክረምት ወቅት አራት ነጥብ ዘጠኝ ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እስከ አሁን ድረስ ሦስት ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ችግኞች ተዘጋጅተዋል::
ባለፈው የክረምት ወቅት አራት ነጥብ ሦስት ቢሊዮን ችግኞች መተከላቸውን ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94451