Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የባጃጅ አሽከርካሪዎች በቅርቡ ወደ ስራቸው እንደሚመለሱ ተገለጸ
*******************
(ኢ.ፕ.ድ)

የባጃጅ አሽከርካሪዎች በቅርቡ ወደ ስራቸው እንደሚመለሱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ።

በቅርቡ እየተነሳ ካለው የባጃጅ አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ መግለጫ ሰጥቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ምትኩ አስማረ እንደተናገሩት፤ የከተማ አስተዳደሩ የባጃጅ አገልግሎትን የተሻለ ለማድረግ የአሰራር ማስተካከያ እያደረገ ሲሆን ይህ ተግባራዊ እስከሚሆን ድረስ የባጃጅ አሽከርካሪዎችና ተጠቃሚዎች በትግስት እንዲጠብቁ አሳስበዋል።

የባጃጅ ትራንስፓርት መንግሥት የትራንስፖርት አገልግሎትን ማድረስ በማይችልበት የከተማ ዳርቻዎች፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ አገልግሎት መሰጠት እንደተጀመረ አስታውሰው፤ አሁን ላይ አገልግሎቱ እየተስፋፋ ሄዶ በከተማይቱ ውስጥ ከሚገኙ 11ክፍለ ከተሞች መካከል በስምንቱ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

ከተማ አስተዳደሩ አገልግሎቱን ወደ አሰራር ለማስገባት ባደረገው ጥረት 9ሺህ 950 የባጃጅ አገልግሎት ሰጪዎች በ123 ማህበራት ተደራጅተው በስምንቱ ክፍለ ከተሞች ላይ እንደሚሰሩ ተናግረው ብዛት ያላቸው ግን እንዳልተመዘገቡ ጠቁመዋል። የከተማ አስተዳደሩም መሰራት ያለባቸውን ስራዎች እንዳጠናቀቀ በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚመለሱ ተናግረዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ትራንስፖርት ቢሮ የባጃጅ ትራንስፖርት የአገልግሎት አስፈላጊነት በዝርዝር ተጠንቶ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ ከየካቲት 30/2015 ጀምሮ በከተማዋ በየትኛውም አከባቢ ላልተወሰነ ጊዜ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት የታገደ መሆኑን ቢሮው መግለፁ የሚታወስ ነው።

በቃልኪዳን አሳዬ
ምርትን በመያዝ ለፖለቲካ መጠቀሚያ በሚያደርጉ ላይ ቁጥጥር ይደረጋል
👉 የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ ወደ ሥራ ገብቷል፣
👉 የጤፍ ዋጋ ዝቅ እንዲል እንሠራለን፣
*****************
(ኢ ፕ ድ)
ምርትን በመያዝ ለሌላ የፖለቲካ ቀውስ መጠቀሚያ ለማድረግ የሚደረጉ ሙከራዎች ላይ መንግሥት ጠንካራ ቁጥጥር እንደሚያደርግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።
የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱንና የጤፍ ዋጋ ከተጋነነው ጭማሪ ዝቅ እንዲል እንደሚሠራ ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር ዓባይ ከወቅታዊው የኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94255
በሶማሌ ክልል ለድርቅ ተጎጂዎች ሰብዓዊ ድጋፍ እየቀረበ ነው
👉 4 ነጥብ 3 ሚሊዮን ተረጂዎች ተለይተዋል
******************
(ኢ ፕ ድ)
በሶማሌ ክልል ለሚገኙ የድርቅ ተጎጂዎች የዓለም ምግብ ፕሮግራም ድጋፍ እያቀረበ መሆኑን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ።
የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ በክልሉ ከሚገኙ 11 ዞኖች መካከል ዘጠኙ ዞኖች በድርቅ የተጠቁ ናቸው ያሉት አቶ ደበበ፤ ለደረሰው የድርቅ አደጋ ጉዳት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ድጋፍ እያቀረበ ይገኛል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94258
በደቡብ ኦሞ ዞን 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን እንስሳት ለመኖና ውሃ እጥረት ተጋልጠዋል
******************
(ኢ ፕ ድ)
በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን በተከሰተው ድርቅ ከሁለት ነጥብ ሦስት ሚሊዮን በላይ እንስሳት ለመኖና ውሃ እጥረት መጋለጣቸውን የደቡብ ኦሞ ዞን አስታወቀ።
በተከሰተው ድርቅ ተጎጂ ለሆኑ 337 ሺህ 923 በላይ ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ እየተደገ መሆኑ ተገልጿል።
የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጋቱ ዳንሳ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በዞኑ በተለይ ቆላማ በሆኑ አካባቢዎች ባለፉት ሦስት ዓመታት የዝናብ እጥረት በመኖሩ ድርቅ ተከስቷል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94279
“የትምህርትሥርዓቱን ለማሻሻል የትምህርት ሕጎችን ማክበርና የመምህራን ብቃት ላይ መሰራት አለበት”
-የሥርዓተ ትምህርት ባለሙያዎች
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
በኢትዮጵያ ያለውን የትምህርት ሥርዓት ለማሻሻል በሕገ-መንግሥቱ የተቀመጡ የትምህርት ሕጎችን ማክበርና የመምህራንን ብቃት ማሻሻል አስፈላጊ መሆኑን የሥርዓተ ትምህርት ባለሙያው ገለጹ።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ጥናትና ምርምር ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶክተር ፍርዲሳ ጀቤሳ ለኢትዮጵያ ፕሬስ እንደገለጹት፤ ሀገራዊ የሆነ ሕገመንግሥታዊ የትምህርት ግቦች እና ዓላማዎችን ወደ ተቋማት በማውረድ እና በመተግበር የትምህርት ሥርዓቱን ለማሻሻል መሰራት አለበት።

ትምህርት ለአንድ ሀገር መሰረት ነው ያሉት ባለሙያው፤ ነጻና ገለልተኛ የትምህርት መመሪያ በመስጠት ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ያለው መዋቅር ከሕገመንግሥቱ እንዲሁም ከተቋማዊ ግቦችና ዓላማዎች አንፃር የሚመራ እና የሚደግፍ አመራር መፈጠር ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94365
በአዲስ አበባ ደረቅ ቆሻሻን ጥቅም ላይ በማዋል ሥራ ከ16 ሺህ በላይ ዜጎች እየተሳተፉ ነው
*************
(ኢ.ፕ.ድ)

በአዲስ አበባ ከ16 ሺህ በላይ ዜጎች በደረቅ ቆሻሻ ሽያጭና ተያያዥ ስራዎች እንደሚተዳደሩ የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ የመልሶ መጠቀምና ኡደት ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ፀጋዬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ በአዲስ አበባ ከተማ ከ16 ሺህ በላይ ዜጎች በማህበር ተደራጅተው ቆሻሻን ከተለያዩ ስፍራዎች ሰብስበው በመሸጥ ላይ ናቸው።

እንደ አቶ ካሳሁን ገለፃ፤ በየመንደሩ ተጠራቅሞ የሚገኘውን ደረቅ ቆሻሻ በመሰብሰብ መልሶ ለአገልግሎት እንዲውል የሚረዳ ስራ የሚያከናውኑ ዜጎች የአካባቢ ብክለትን....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94359
በዞኑ ባለፉት ስምንት ወራት ከቱሪዝም ዘርፉ ከ94 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኝቷል
************
(ኢ.ፕ.ድ)
ባለፉት ስምንት ወራት ከሀገር ውስጥና ከውጭ ጎብኚዎች ከ94 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ፡፡

በዞኑ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ የቱሪዝም መስኮች ጥናትና ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከተማ አለሙ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፣ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ምክንያት የውጭ ገብኚዎች ቁጥር የቀነሰ ቢሆንም የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ቁጥር ጥሩ መሻሻል ያሳየ ነው፡፡

በዞኑ ባለፉት ስድስት ወራት ከአንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን በላይ የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች እንዲሁም ከሁለት ሺ በላይ የውጭ ሀገር ገብኚዎች ወደ ዞኑ ሄደው የጎበኙ ሲሆን በዘርፉ ከ94 ሚሊዮን ብር በላይ ማግኘት እንደተቻለ ገልጸዋል፡፡ ጉራጌ ዞን ብዙ ለሀገር ውስጥና...
https://www.press.et/?p=94333
ጉዳት የደረሰበት የደሴ ሙዚየም የመልሶ ግንባታ ስራ ተጀመረ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ጉዳት የደረሰበት የደሴ ሙዚየም የመልሶ ግንባታ ስራ መጀመሩን የደሴ ከተማ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ።

የደሴ ከተማ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ትዕግስት አበበ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በእንግሊዝ መንግሥት የገንዘብ ድጋፍ የደሴ ሙዚየምን የማደስና የመልሶ ግንባታ ፕሮጀክት ተጀምሯል።

የደሴ ሙዚየም መልሶ ግንባታ ስራ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የመምሪያ ኃላፊዋ ጠቁመዋል። በቱሪዝም ዘርፍ የወደሙ መሰረተ ልማቶችንና ቅርሶችን መልሶ የመገንባት ስራ በተደራጀ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል።

ስራው በቀጣይ የቱሪዝም ዘርፍ ገቢን ለማሳደግ ይረዳል ሲሉም ወ/ሮ ትዕግስት ተናግረዋል። ለመልሶ ግንባታና....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94330
ፓርኩ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ አድኗል
***************
(ኢ ፕ ድ)

የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ባለፉት ስምንት ወራት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ማዳኑን አስታወቀ። ባለፉት ስምንት ወራት ምርቶችን ለውጭ ገበያ በማቅረብ ከ48 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ማግኘቱንም አስታውቋል።

በፓርኩ እያለሙ የሚገኙ ባለሀብቶች ከሀገር ውስጥ ምርትና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር በፈጠሩት የገበያ ትስስር፤ በስምንት ወራት የሁለት ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር የምርትና አገልግሎት ትስስር መፈጠሩንም አስታውቋል። የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ትንሳኤ ይማም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ በተያዘው በጀት ዓመት የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት በርካታ ሥራዎችን ሲሰራ ቆይቷል። በዚህም ፓርኩ ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባ ምርትን በሀገር ውስጥ መተካት ችሏል።

ለዚህም ሱፍሌት ማልት የብቅል ፋብሪካ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል። ይህ ፋብሪካ ከውጭ የሚገባውን የብቅል ምርት ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ምርት መተካት ችሏል። ይህም 54 ሺህ ለሚሆኑ አነስተኛ የእርሻ መሬት ያላቸው አርሶ አደሮች ተጠቃሚ እንዲሆኑ
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94324

(ፎቶ ኢፕድ ፋይል)
በአፍሪካ ቀንድ የሚታየውን የሰራተኞች ፍልሰት ለመቆጣጠር የሚያስችል የቀጠናው አገራት የሚኒስትሮች ፎረም እየተካሄደ ነው
******************
(ኢ ፕ ድ)

በምስራቅና በአፍሪካ ቀንድ የሚታየውን የሰራተኞች ፍልሰት ለመቆጣጠር የሚያስችለው አራተኛው የቀጠናው አገራት የሚኒስትሮች ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

የአለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት በኢትዮጵያ ምክትል ሃላፊ ጂያን ዣን በፎረሙ መክፈቻ ላይ እነዳሉት፤ ፍልሰትን ለመቆጣጠር እና የስደተኛ ሰራተኞችን ደህንነት ለመጠበቅ ፖሊሲዎችን እና ልምዶችን ለማስማማት ጠቃሚ መድረክ ነው።

የስራና ክህሎት ሚኒስትር ድኤታ አቶ አሰግድ ጌታቸው በበኩላቸው አራተኛው የሚኒስትሮች ፈረም በሰራተኞች መብት አያያዝ፣ ጉልበት ብዝበዛን በመከላከል፣ ህገወጥ ፍልሰትን ለመቆጣጠር አገራት ያላቸው ልምዶችና ተሞክሮዎችን የሚለዋወጡበት ነው።

ኢትዮጵያ በሰራተኞች አያያዝና በስራ እድል ፈጠራ ላይ ያላትን ልምድና ትሞክሮ እንደምታካፍል ገልጸዋል።

ፎረሙ 11 አገራትን ማለትም ኢትዮጵያ፣ ኬንያያ፣ ብሩንዲ፣ ኤርትራ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ሩዋንዳ፣ ሶማሊያ፣ ታንዛኒያና ኡጋንዳን የያዘ ሲሆን በአለም አቀፍ የሰራተኞች ድርጅት፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ ተወካዮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ፎረሙ ለሚቀጥሉት አራት ቀናት የሚቆይ ነው።

በሞገስ ተስፋ