Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በሙስና ምክንያት ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ሀብት ለብክነት መዳረጉን የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ
*****************************
(ኢ ፕ ድ)
በሙስና ምክንያት ከ2 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር የህዝብና የመንግስት ሀብት ለብክነት መዳረጉን የፀረ ሙስና ብሔራዊ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገልፀዋል።
እስካሁን በተከናወኑ የሙስና ተግባር 759 የሙስና ወንጀሎች ከህብረተሰቡ ጥቆማ የቀረበ ሲሆን፤ ከተጠቆሙት መካከል 175 የሙስና ወጀሎች በመለየት ምርመራ እየተደረገበት እንደሆነ ገልፀዋል።
25 ሺህ 885 ካ.ሜ በምርመራ የሙስና ወንጀል ተፈፅሞ መገኘቱን ጠቁመዋል። የክልሎች ሲጨመር ምን ያክል እንደሚሆን ለመረዳት ይቻላል ሲሉ ተደምጠዋል።
የሙስና ወንጀልን ለመቀነስ የትስሰር ገመድን መበጠስ ይገባል፤ ችግሩ የፖሊሲ የማስፈፀም አቅም የሚያዳክም ነው ብለዋል።
በመሆኑም ችግሩን ዳር ለማድረስ ህብረተሰቡ ከፀረ-ሙስና ኮሚቴው ጎን በመቆምና የተጀመረውን ጥቆማ የመስጠት ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የኮሚቴው ሰብሳቢና የኢፈድሪ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ መልክት አስተላልፈዋል።
ውይይቱ በፌደራል፣ በክልልና በከተማ መስተዳድር የተቋቋመው የፀረ-ሙስና አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት እየተካሄደ ያለው።
እስካሁን የተከናወኑ ተግባራትን የጋራ ግምገማ ለማካሄድና የቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ያለመ መሆኑ ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት አመራር ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ተካሂዷል
***********************
(ኢ ፕ ድ)

ብሔራዊ የአደጋ ሥጋት አመራር ምክር ቤት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን ሰብሳቢነት በዛሬው ዕለት አስቸኳይ ስብሰባ ተካሂዷል።

በዋነኛነት በአየር ሁኔታ መዛባት መንሥኤነት በተለይም ላለፉት አምስት የዝናብ ወቅቶች በተፈጠረው ከፍተኛ የዝናብ እጥረት የተነሣ በሀገራችን ድቡባዊ፣ ደቡብ ምስራቃዊና ደቡብ ምእራባዊ ክፍሎች ድርቅ ተከሥቶ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን አስከትሏል።

የፌደራል መንግሥትና ክልሎች ከሕዝብ እና ከአጋር ተቋማት ጋር በመሆን ለችግሩ ተገቢ ምላሽ ለመስጠት ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል።

በሌላ አንጻር በሰው ሰራሽ አደጋዎች መንስኤነት ተፈናቅልው የሚገኙ ዜጎች ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረትን የጠየቀ ስራ ሆኗል።

ምክር ቤቱ የድርቁን ዝርዝር ሁኔታ፣ የደርሰውን የጉዳት መጠን፣ የተከናወኑ የአደጋ ምላሽ ሥራዎችን የሚያሳዩ ሪፖርቶችን በሚገባ ገምግሟል። ጥንካሬዎችና ጉድለቶችን ለይቷል።

በአጭርና በረጅም ጊዜ ሊከናወኑ የሚገባቸውን የአደጋ ምላሽ እና የዘላቂ ልማት ሥራዎች በመለየት በቅንጅትና በርብርብ ለመተግበር አቅጣጫ ተቀምጧል።

በመጭዎቹ አራት ወራት በልዩ ትኩረት ቅድሚያ ተሠጥቷቸው የሚሰሩ ሥራዎችን የለየ ሲሆን ፈጣን ምላሸ ለመስጠት ሥራዎችን በቅርበት እየገመገመ እንደሚሠራ አስታውቋል።
በሶማሌ ክልል በተከሰተ ድርቅ 3 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዜጎች ለተረጂነት ተጋልጠዋል
***************
(ኢ ፕ ድ)
በሶማሌ ክልል ባሉ 11 ዞኖች በተከሰተው ድርቅ 3 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሕዝብ ለተረጂነት መጋለጡን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።
የሶማሌ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር ረሺድ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፣ ድርቁ በክልሉ ሁሉም ዞኖች የተከሰተ ሲሆን አደጋው በሸበሌ፣ በዳዋና በአፍዴር ዞኖች የከፋ ሆኗል። በድርቁ ምክንያት ለተረጂነት ከተጋለጡት ከ3 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዜጎች አሁን ላይ እርዳታ እያገኙ ያሉት 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ያህሉ ብቻ ናቸው። 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዜጎች አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94088
👉 "በከተማዋ በቂ የጤፍ አቅርቦት የለም" - ነጋዴዎች
👉 "የጤፍ ዋጋ መናር ፈተና ሆኖብናል" -የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች
👉 "የኑሮ ውድነት ጉዳይ የእኛ ኃላፊነት አይደለም" -የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር
*********************
(ኢ ፕ ድ)
በቂ የጤፍ አቅርቦት ባለመኖሩ እና በጤፍ ዋጋ ላይ ከፍተኛ ጭማሪ በመደረጉ ጤፍ ገዝተን እንጀራ መብላት አልቻልንም ሲሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለጹ።
ጤፍ ሲገዙ ያገኘናቸው የአዲስ አበባ ነዋሪ ወይዘሮ አረጉ ጥፍጤ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ የጤፍ ዋጋ በጣም ጨምሯል፤ በወፍጮ ቤቶች ጤፍ የለም።
በአንዳንድ ወፍጮ ቤቶች ቢገኝም እንደጤፉ ዓይነት እስከ ስምንት ሺህ አምስት መቶ ብር ድረስ እየተሸጠ ይገኛል።
25 ኪሎ ጤፍ በሁለት ሺህ ብር .....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94085
ዲጂታል የእንግሊዝኛ ቋንቋ መማሪያ መተግበሪያ ደረጃና ተደራሽነት ሊሻሻል ነው
***************
(ኢ ፕ ድ)
ዲጂታል የእንግሊዝኛ ቋንቋ መማሪያ መተግበሪያ ተገልጋዮችን በዕውቀት ደረጃ በመለየት ግልጋሎት መስጠት እንደሚጀምር እና ተደራሽነቱን ለማስፋት እንደሚሠራ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
በትምህርት ሚኒስቴር የሶፍትዌር ቀማሪ አቶ አለምሁሉ አወቀልኝ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት፤ ዲጂታል የእንግሊዝኛ ቋንቋን ያለምንም የበይነ መረብ ክፍያ ለማስተማር የሚያስችል መተግበሪያ ከወራት በፊት ይፋ ሆኗል። ይህ መተግበሪያ ሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍል የሚያሳትፍ ሲሆን ብዙዎች ቋንቋው ላይ ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94120
ከድርጅቱ ሰርቨር ላይ አራት ሚሊዮን የሚጠጉ ሰነዶች እንዲጠፉ ተደርጓል
**************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ከሰርቨሩ ላይ እስከ አራት ሚሊዮን የሚደርሱ ሰነዶች ሆንተብሎ እንዲጠፉ ተደርጎ እንደነበርና ይህም ለሂሳብ ሥራ አስቸጋሪ ሁኔታ መፍጠሩ ተገለፀ።
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የሂሳብ አያያዝም ልዩ ትኩረት እንደተሰጠው ተጠቁሟል።
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሐብታሙ ኃይለሚካኤል በተለይም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94099
20 ኢንቨስተሮች በስኳር ኢንዱስትሪ ለመሰማራት ፍላጎት አሳይተዋል
*****************
(ኢ ፕ ድ)
20 የአገር ውስጥ ባለሀብቶችና የውጭ አገር ኢንቨስተሮች ወደ ግል ሴክተር የሚዞሩ ስምንት የስኳር ፋብሪካዎችን በመግዛት በዘርፉ ላይ ለመሰማራት ፍላጎት ማሳየታቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በሚኒስቴሩ የለውጥ ሥራዎች አማካሪ ወ/ት ሂንጃት ሻሚል ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በስኳር ኢንዱስትሪው ዘርፉ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው የግል ኢንቨስተሮች መሳተፍ እንደሚችሉ በተደረገው ጥሪ መሠረት ከ20 በላይ የሚሆኑ የግል ተቋማት መሳተፍ እንደሚፈልጉ ከወዲሁ አሳውቀዋል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94091
ፎረሙ ዘላቂ ሰላም በማረጋገጥና በመልሶ ግንባታ ላይ በትኩረት ይሠራል
**************
(ኢ ፕ ድ)
ተጋሩ ኢትዮጵያውያን ለዘላቂ ሰላም ፎረም ሰላምን ለማረጋገጥና በጦርነት የወደሙ አካባቢዎችን መልሶ ማልማት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ ገለጸ።
ፎረሙ በትናንትናው ዕለት ሲመሰረት ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የማህበሩ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ከበደ አሰፋ እንዳስታወቁት፤ ሕዝብና አገርን ዓላማ የሚያደርግ ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ፣ ሲቪክ ማኅበር፣ የንግድ ማኅበረሰብ፣ ዳያስፖራ ማህበር እና ግለሰቦችም ጭምር በአንድነት በመሆን እና ልዩነታቸውን ወደ ጎን በመተው በአገርና ሕዝብ ላይ ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94098
በወረዳው በበጋ መስኖ ስንዴ 52 ሺህ ኩንታል ምርት ይጠበቃል
***************
(ኢ ፕ ድ)
ከበጋ መስኖ ልማት ሥራዎች 52 ሺህ ኩንታል የስንዴ ምርት እንደሚጠበቅ በሰሜን ወሎ ዞን የግዳን ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
የግዳን ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ካሳሁን ሞላ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በአጠቃላይ በወረዳው በበጋ መስኖ ልማት ከተሸፈነው 1ሺህ 936 ሄክታር መሬት 52 ሺህ ኩንታል ስንዴ ምርት ይጠበቃል።
በወረዳው በሚገኙ 12 ቀበሌዎች ላይ በ52 ክላስተር የለማውን ስንዴ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94111