Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሴት አብራሪዎች ብቻ  የተመራ በረራ ወደ ዛንዚባር አደረገ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እየተከበረ ያለውን አለም  አቀፉን የሴቶች ቀን ምክንያት በማድረግ በሴት አብራሪዎች ብቻ  የተመራ በረራ ወደ ዛንዚባር ማድረጉን አስታወቀ።

ዛሬ "እኔም የእህቴ ጠበቃ ነኝ" በሚል እየተከበረ ያለውን የዓለም የሴቶች ቀን ምክንያት በማድረግ በሴት አብራሪዎች ብቻ የተመራ በረራ ወደ ዛንዚባር ማድረጉን በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።
የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር የአምስት አመት የስራ ዘመን ክብረ በዓልና የእውቅና መርሃግብር እየተካሄደ ነው
*******************
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮ- ጅቡቲ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የአምስት አመት የስራ ጉዞ ክብረ በአልና ለጉዞው ስኬታማነት አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላት የእውቅና መርሃግብር እየተካሄደ ነው።

የኢትዮ ጀቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ አብዲ ዘነበ (ዶክተር) በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ እንደገለጹት፣ የኢቶ ጅቡቲ የምድር ባቡር አክሲዮን ማህበር የሁለቱን አገሮች የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ትስስር በከፍተኛ ደረጃ አሳድጓል።

ምድር ባቡሩ በማድንና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እየተደረገ ላለው ስራ ምርቶችን በማጓጓዝ ጉልህ ሚና ተወጥቷል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው፣ በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ የምታገኝባቸውን ቡናንና ሌሎች ምርቶችን ወደ ውጭ ለመላክ በመጓጓዝ ትልቅ ድርሻ እንደተውጣ ገልጸዋል።

በዚህ በአምስተኛ የስራ ዘመኑ ያከናወናቸው ስኬታማ የስራ እንቅስቃሴው የሚቀርቡ ሲሆን በእነዚህ አመታት የምድር ባቡር አክሲዮን ማህበሩ ላከናወናቸው ስኬታማ ስራዎች አስተዋጽኦ ላደረጉ ባለድርሻ አካላት እውቅና ይሰጣል።

የኢትዮ ጀ ቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ አብዲ ዘነበ(ዶክተር)፣ የገንዘብ ሚኒስትሩና የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አህመድ ሽዴ፣ የሎጂስቲክና ትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ፣ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር፣ የጅቡቲ የመሰረተ ልማት ሚኒስትር ሀሰን ሆምድ ኢብራሂም፣ በኢትዮጵያ የጂቡቲ አምባሳደር አብዲ መሃመድ፣ የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ(ዶክተር)፣ የሲሲኢሲሲ- ሲአር ኢሲ ጄቲ ማኔጀር ጉዮ ቾንግፍርግ ተገኝተዋል።

በሞገስ ተስፋ
ሴቶች በትምህርት ዘርፍ እኩል የመሳተፍ ዕድል እንዲፈጠርላቸው እየተሠራ ነው
***************
(ኢ ፕ ድ)
ሴቶች በትምህርት ዘርፍ እኩል የመሳተፍ ዕድል እንዲፈጠርላቸው የሚረዳ ሥራ እያከናወነ መሆኑን የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶች ጥቃት ጥበቃ እና ምላሽ ዴስክ ኃላፊ ወይዘሮ ህሊና ላቀው ለኢትዮጵያ ፕሬስ እንደገለጹት፤ የችሎታ እና ብቃት ማነስ ሳይኖርባቸው ባለው የግንዛቤ እጥረት ምክንያት ለሴቶች የትምህርት ዕድል ያለመስጠት ችግር በስፋት ይስተዋላል።
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94017
"ኢትዮጵያ ብዙና አመቺ የኢንቨስትመንት አማራጮች ያሏት አገር ነች" – የፓኪስታን ኢንቨስተሮች
*****************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ከሌሎች አገራት በተሻለ ብዙ አማራጮች ያሏት አገር መሆኗን በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደረጉት የፓኪስታን ኢንቨስተሮች ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ገለጹ፡፡
የግሊትስ መድኃኒት ድርጅት ዳይሬክተር ቻውዳርይ ቢላል፤ በጉብኝቴ ኢትዮጵያውያን እንግዳ ተቀባይ ከመሆናቸው በተጨማሪ አገሪቱ ለኢንቨስትመንት የምትመች አገር መሆኗን ተመልክቻለሁ ብለዋል፡፡
ድርጅታቸው ግሊትዝ ፋርማሲ በዓለም ላይ ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=94003
ኢትዮጵያ እና ኬንያ በጋራ ድንበር አካባቢ የሚከሰቱ የጸጥታ ስጋቶችን በቅንጅት ለመከላከል ተስማሙ
********************
(ኢ ፕ ድ)
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ የተመራ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ ከኬንያ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በናይሮቢ መወያየታቸውን በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ ገልጸዋል፡፡
ሁለቱ አገራት በጸጥታው ዘርፍ በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አስታውቀዋል፡፡
ኢትዮጵያ እና ኬንያ የጋራ ድንበር አካባቢ የሚከሰቱ የጸጥታ ስጋቶችን በጋራ ለመከላከል የሚያስችል ስምምነት መፈራረማቸውን አምባሳደሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።
"ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከተመድ የአዳጊ ሀገራት ጉባኤ ጎን ለጎን ውጤታማ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ውይይት አድርገዋል" --የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
***********************
(ኢ ፕ ድ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከ5ኛው ከተመድ የአዳጊ ሀገራት ጉባኤ ጎን ለጎን ውጤታማ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ውይይት ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ዲፕሎማሲ እንቅስቃሴን በተመለከተ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
ባለፉት ሁለት ዓመታት ከነበርንበት የግጭት ዐዉድ ወጥተን ወደ ኢኮኖሚ ግንባታ ተሸጋግረናል ብለዋል።
የቻይና፣ ኳታር፣ እንግሊዝ፣ አሜሪካና ሌሎች አገራት ባለሀብቶች መዋዕል ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል ብለዋል።
በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የኳታር ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት መስክ ላይ በሚሰማሩበት ሁኔታ መክረዋል ብለዋል።
የኳታር ከፍተኛ አቅም ያላቸው ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በማምረቻውና በኮንስትራክሽን ዘርፎች ለመሰማራት ፍላጎት ማሳየታቸውን ገልጸዋል።
ከሰባ በላይ የሚሆኑ የፓኪስታን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ለመሰማራት በአዲስ አበባ እንደሚገኙም ገልጸዋል።
የኢትዮ-ካናዳ የቢዝነስ ፎረም የካናዳ ባለሀብቶች በግብርና ዘርፎች ለመሰማራት ፍላጎት ያሳዩበት መድረክ እንደነበር አስታውሰዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
በሙስና ምክንያት ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ሀብት ለብክነት መዳረጉን የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ
*****************************
(ኢ ፕ ድ)
በሙስና ምክንያት ከ2 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር የህዝብና የመንግስት ሀብት ለብክነት መዳረጉን የፀረ ሙስና ብሔራዊ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገልፀዋል።
እስካሁን በተከናወኑ የሙስና ተግባር 759 የሙስና ወንጀሎች ከህብረተሰቡ ጥቆማ የቀረበ ሲሆን፤ ከተጠቆሙት መካከል 175 የሙስና ወጀሎች በመለየት ምርመራ እየተደረገበት እንደሆነ ገልፀዋል።
25 ሺህ 885 ካ.ሜ በምርመራ የሙስና ወንጀል ተፈፅሞ መገኘቱን ጠቁመዋል። የክልሎች ሲጨመር ምን ያክል እንደሚሆን ለመረዳት ይቻላል ሲሉ ተደምጠዋል።
የሙስና ወንጀልን ለመቀነስ የትስሰር ገመድን መበጠስ ይገባል፤ ችግሩ የፖሊሲ የማስፈፀም አቅም የሚያዳክም ነው ብለዋል።
በመሆኑም ችግሩን ዳር ለማድረስ ህብረተሰቡ ከፀረ-ሙስና ኮሚቴው ጎን በመቆምና የተጀመረውን ጥቆማ የመስጠት ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የኮሚቴው ሰብሳቢና የኢፈድሪ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ መልክት አስተላልፈዋል።
ውይይቱ በፌደራል፣ በክልልና በከተማ መስተዳድር የተቋቋመው የፀረ-ሙስና አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት እየተካሄደ ያለው።
እስካሁን የተከናወኑ ተግባራትን የጋራ ግምገማ ለማካሄድና የቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ያለመ መሆኑ ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት አመራር ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ተካሂዷል
***********************
(ኢ ፕ ድ)

ብሔራዊ የአደጋ ሥጋት አመራር ምክር ቤት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን ሰብሳቢነት በዛሬው ዕለት አስቸኳይ ስብሰባ ተካሂዷል።

በዋነኛነት በአየር ሁኔታ መዛባት መንሥኤነት በተለይም ላለፉት አምስት የዝናብ ወቅቶች በተፈጠረው ከፍተኛ የዝናብ እጥረት የተነሣ በሀገራችን ድቡባዊ፣ ደቡብ ምስራቃዊና ደቡብ ምእራባዊ ክፍሎች ድርቅ ተከሥቶ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን አስከትሏል።

የፌደራል መንግሥትና ክልሎች ከሕዝብ እና ከአጋር ተቋማት ጋር በመሆን ለችግሩ ተገቢ ምላሽ ለመስጠት ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል።

በሌላ አንጻር በሰው ሰራሽ አደጋዎች መንስኤነት ተፈናቅልው የሚገኙ ዜጎች ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረትን የጠየቀ ስራ ሆኗል።

ምክር ቤቱ የድርቁን ዝርዝር ሁኔታ፣ የደርሰውን የጉዳት መጠን፣ የተከናወኑ የአደጋ ምላሽ ሥራዎችን የሚያሳዩ ሪፖርቶችን በሚገባ ገምግሟል። ጥንካሬዎችና ጉድለቶችን ለይቷል።

በአጭርና በረጅም ጊዜ ሊከናወኑ የሚገባቸውን የአደጋ ምላሽ እና የዘላቂ ልማት ሥራዎች በመለየት በቅንጅትና በርብርብ ለመተግበር አቅጣጫ ተቀምጧል።

በመጭዎቹ አራት ወራት በልዩ ትኩረት ቅድሚያ ተሠጥቷቸው የሚሰሩ ሥራዎችን የለየ ሲሆን ፈጣን ምላሸ ለመስጠት ሥራዎችን በቅርበት እየገመገመ እንደሚሠራ አስታውቋል።