Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ስንዴን ወደ ውጭ ገበያ መላክ ጠንካራ ኢኮኖሚን ለመገንባት ዕድል ይሰጣል
************
(ኢ.ፕ.ድ)
ኢትዮጵያ በበጋ መስኖ በስፋት ያለማችውን ስንዴን ኤክስፖርት ማድረግ መጀመሯ ጠንካራ ኢኮኖሚን መገንባት የሚያስችላት ትልቅ ጅማሮ እንደሆነ የምጣኔ ሀብት ምሁር ገለጹ፡፡
በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህርና በ‹‹ፍሮንቲየርአይ (Frontieri)›› ጥናትና አማካሪ ድርጅት ከፍተኛ ተመራማሪ ዶክተር ሞላ አለማየሁ ለኢፕድ እንደተናገሩት፤ አሁን...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93762
ክልሉ ለ215 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ ሰጠ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
ባለፉት ስድስት ወራት ለ215 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ መስጠቱን የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አስታወቀ፡፡
የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሐልጌዮ ጂሎ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፣ በክልሉ ባለፉት ስድስት ወራት የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለጠየቁ 215 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጥቷል፡፡
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93761
አዲስ አበባ በቀን 1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ ቢያስፈልጋትም እያመረተች ያለችው 725 ሺህ ብቻ ነው
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
በአዲስ አበባ ከተማ በቀን ከሚያስፈልገው አንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ አሁን ላይ እየተመረተ ያለው 725ሺህ ሜትር ኪዩብ ብቻ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታወቀ::
በ570 ሚሊዮን ብር በጀት ተጨማሪ 75ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ እየለማ እንዳለ ተገልጿል::

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93752
ብሔራዊ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ አማራጮች ላይ የሚመክር ጉባኤ እየተካሄደ ነው
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
ብሔራዊ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ አማራጮች ላይ የሚመክር ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።
በፍትህ ሚኒስቴር አስተባባሪነት እየተካሄደ በሚገኘው የምክክር መድረክ ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሠብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ፣ ሚኒስትሮችና የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ተገኝተዋል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ባደረጉት ንግግር፤ ባለፉት ጊዜያት በነበሩ ግጭቶች የተፈጠሩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በሕግ ለመፍታት ተገቢው ትኩረት ባለመሰጠቱ የበዳይ ተበዳይ ትርክትና ቁርሾ ተበራክቷል ብለዋል።
በተለያዩ ጊዜያት የተፈጸሙ ጉልህ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችንና ቁርሾዎችን አግባብነት ባለው መልኩ ለመፍታት ብሔራዊ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ አስፈላጊ በመሆኑ ለውጤታማነቱ መስራት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
ግጭት ወቅት የተከሰቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተገቢው መንገድ ለመፍታት በሀገራችን ብሔራዊ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ የሚያስፈልግበት ወቅት ላይ ነን ሲሉም ነው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የተናገሩት።
በጌትነት ተስፋማርያም
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፓኪስታን የኢንቨስትመንትና የንግድ ልኡክ ጋር ውይይት እያደረጉ ነው
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፓኪስታን የኢንቨስትመንትና የንግድ ልኡክ ጋር ውይይት እያደረጉ ነው። ውይይቱ ለቀጣይ አምስት ቀናት የሚቆይ ነው ተብሏል።
በውይይቱ ወቅት ንግግር ያደረጉት በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር በኢትዮጵያ በርካታ የኢንቨስትመንት አማራጮች መኖራቸውን ገልጸዋል።
ይህ መድረክ የኢትዮጵያና የፓኪስታንን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር አዲስ ምእራፍ ነው ያሉት አምባሳደሩ፣ ኢትዮጵያ ካላት የኢንቨስትመንት አማራጭ በተጨማሪ ያለችበት ስትራቴጂያዊ አቀማመጥ ተመራጭ እንደሚያደርጋት ገልጸዋል።
ኢትዮጵያና ፓኪስታን ከፍተኛ የሆነ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አላቸው። እንዲሁም በአለም አቀፍ መድረክ ያላቸው ግንኙነት ጠንካራ ነው፣ ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
በሰላምና ደህንነት፣ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲና በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ሁለቱ ሀገራት ጠንካራ ዲፕሎማሲ ግንኙነት እንዳላቸው አምባሳደር ጀማል ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የፓኪስታን አምባሳደር ሻዛብ አባስ እንደተናገሩ፣ ኢትዮጵያ የአለም አቀፍ የዲፕሎማሲ መናከሪያ ናት። ሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ግንኙነት ተፈጥሯል። ኢትዮጵያ የሁሉም የስልጣኔ ምልክት ናት ብለዋል።
በኢትዮጵያ ያሉ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮችም ለፓኪስታን ልኡካን ቀርበዋል።
በሞገስ ጸጋዬ
«በአህጉሪቱ ዘላቂ ሰላምና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለመፍጠር ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ያስፈልጋል» አቶ ትዕግስቱ አወሉ
***************
(ኢ ፕ ድ)
በአህጉሪቱ ዘላቂ ሰላምና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለመፍጠር ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ያስፈልጋል ሲሉ አቶ ትዕግስቱ አወሉ ተናገሩ።
የምሥራቅ አፍሪካ የጂኦፖለቲካል ተንታኝ የሆኑት አቶ ትዕግስቱ አወሉ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ በአህጉሪቱ ዘላቂ ሰላምና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለመፍጠር ፖለቲካዊ መሪዎቹም የፖለቲካ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ትስስር በመፍጠር ሕዝባቸውን ከድህነት ለማላቀቅ በቁርጠኝነት ሊቆሙ ይገባል፡፡
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93799
ቻይና ለኢትዮጵያ ከቀረጥ ነፃ ንግድ መፍቀዷ የውጭ ምንዛሬ እንዲያድግ ይረዳል
**************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ በቻይና ገበያ ምርቶቿን ከቀረጥ ነፃ ለማቅረብ ፈቃድ ማግኘቷ ያለባትን የውጭ ምንዛሬ ክምችት ክፍተት ለመሙላት ያስችላታል ሲሉ የምጣኔ ሀብት መምህር ዶክተር ይንገስ አለሙ ተናገሩ::
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93788
ተቋሙ ታራሚዎችን በመልካም ባህሪ ለማነጽ በትኩረት እየሠራ ነው
***********
(ኢ ፕ ድ)

የሕግ ታራሚዎችን በመልካም ባህሪ ለማነጽ ቤተ መጽሐፍት ላይ በትኩረት እየሠራ መሆኑን የወላይታ ሶዶ ማረሚያ ተቋም አስታወቀ፡፡

የወላይታ ሶዶ ማረሚያ ተቋም ኃላፊ ኮማንደር ደጀኔ ዳርጮ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አንደገለጹት፤ ማረሚያ ተቋሞች በተለያዩ ወንጀሎች በሕግ ተከሰው የእስር ቅጣት የሚፈረድባቸውን የሕግ ታራሚዎች ተረክበው የማነፅ፣ የማስተማርና አመለካከታቸውን በመልካም የመቀየር ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ይህን ከባድ ኃላፊነት ለመወጣት ታራሚዎች ላይ ትኩረት ተደርጎ መሥራት ይገባዋል፡፡
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93802
“የኢትዮጵያንና ፓኪስታንን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር እየተሰራ ነው”
አቶ ደመቀ መኮንን
********************
(ኢ ፕ ድ)
የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የስራ ሃላፊዎች ጋር በመሆን ከፓኪስታን የኢንቨስትመንትና የንግድ ልኡክ ጋር ውይይት እያደረጉ ነው።
በውይይቱ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ ደመቀ መኮንን፤ የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት በጣም እየተጠናከረ የመጣ መሆኑን ተናግረዋል።
አቶ ደመቀ የኢትዮጵያ መንግሥት ምቹ የሆነ የኢንቨስትመንት ሁኔታን ለመፍጠር እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል።
ፓኪስታን እና ኢትዮጵያ የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነት ያላቸው መሆኑን የገለጹት አቶ ደመቀ፤ ይሄንን ግንኙነት የበለጠ በኢኮኖሚ እና በተለያዩ ዘርፎች ለማጠናከር ጠንካራ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል ።
በቅርቡም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራውን ወደ ፓኪስታን ያደርጋል ብለዋል።
የፓኪስታን ባለሀብቶች በግብርና፣ ቱሪዝም፣ ኬሚካል፣ ጨርቃጨርቅ ፣ ማዕድን ፣ እና በተለያዩ ዘርፎች መሰማራት የሚያስችል ገለፃ ተደርጐላቸዋል ።
በሞገስ ፀጋዬ