Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ያልተጠናቀቁ የጋራ መኖርያ ቤቶች ግምባታ እስከ ሰኔ ወር ድረስ እንዲጠናቀቅ ከንቲባ አዳነች አሳሰቡ
****************
(ኢ ፕ ድ)

የጋራ መኖርያ ቤቶችን ግንባታ በተያዘላቸው ጊዜ ያለማጠናቀቅ ክፍተት መኖሩን የገመገሙት ከንቲባ አዳነች፣ ለዚህ ክፍተት የሲሚንቶ እጥረት፣ የተለያዩ የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ ልዩነት እንዲሁም የወሰን ማስከበር ችግር መኖሩን ተገንዝበናል ብለዋል

ሆኖም እነዚህን ችግሮች በመቅረፍ፣ የጋራ መኖርያ ቤቶችን መሰረታዊ ግንባታ መንግስት በአፋጣኝ በማጠናቀቅ፣ ቀሪውን ተጠቃሚው እንዲያሟላ የሚደረግ ሲሆን የመሰረተ ልማት አቅራቢ ተቋማት ቀሪ ስራዎችን በቅንጅትና በፍጥነት እንዲያጠናቅቁ አቅጣጫ የሰጡ ሲሆን ይህንንም የሚከታተሉ ተቋማትና ኮሚቴዎች በየሳምንቱ የግንባታውን ሂደት ይከታተላሉ ብለዋል።

የተነሱት የግብዓት እጥረትና የዋጋ ልዩነቶችም አፋጣኝ እልባት አግኝተው እስከ ሰኔ ወር ባለው ግዜ ግንባታዎች ተጠናቅቀው ለተጠቃሚው ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ አቅጣጫ መቀመጡን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት ገልጸዋል።
የጠቅላይ ሚነስትር ዶከተር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት‼️

ዛሬ ከሼክ ተሚም ኢብን ሀማድ አልታኒ ጋር በመገናኘታችን ደስተኛ ነኝ። የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን ጨምሮ በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይም ተወያይተናል። #ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ዘርፎች ለኳታር ኢንቨስትመንቶች ብዙ ዕድሎች አሉ።
በቶክዮ ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል
******
(ኢ.ፕ.ድ)

ሌሊት በተካሄደው የ2023 የቶክዮ ማራቶን ላይ የተሳተፉ ወንድና ሴት ኢትዮጵያዊን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።

በወንዶች ውድድር አትሌት ደሶ ገልሚሲ አንደኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ፤ አትሌት መሀመድ ኢሳ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቋል። አትሌት ፀጋዬ ጌታቸው ደግሞ የሶስተኛ ደረጃን ይዞ ፉክክሩን ጨርሷል ።

በሴቶች በተደረገው ውድድር አትሌት ፀሀይ ገመቹ በኬንያዊቷ ሮዝመሪ ዋንጂሩ ተቀድማ በሁለተኝነት ውድድሯን ስታጠናቅቅ አሸቴ በከሬ ሶስተኛ አትሌት ወርቅነሽ ኢዶሳ ደግሞ በአራተኝነት ውድድራቸውን ፈፅመዋል።
የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሀብት ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ ተሻግሯል
****************
(ኢ ፕ ድ )
የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ በማንቀሳቀስ በአገሪቱ ምጣኔ ሀብት ዕድገት ላይ ጉልህ ሚና እየተወጡ መሆኑን የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር አስታወቀ፡፡

ቀደም ሲል በኪሣራ ውስጥ የነበሩ የልማት ድርጅቶች ወደ ትርፋማነት ተሸጋግረዋል ተብሏል፡፡ https://www.press.et/?p=93690
ማህበሩ በ52 ፓርኮች ከ24 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን እየተንከባከበ ነው
***************
(ኢ.ፕ.ድ)
👉 6 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል እየተዘጋጀ ነው
በ52 ፓርኮች ከ24 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን መትከል መቻሉን የኦሮሚያ ልማት ማህበር አስታወቀ፡፡
ማህበሩ በመጪው ክረምት ስድስት ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል የዝግጅት ሥራ እያከናወነ መሆኑንም አስታውቋል፡፡
የኦሮሚያ ልማት ማህበር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ደጀኔ ኢቲቻ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93759
ስንዴን ወደ ውጭ ገበያ መላክ ጠንካራ ኢኮኖሚን ለመገንባት ዕድል ይሰጣል
************
(ኢ.ፕ.ድ)
ኢትዮጵያ በበጋ መስኖ በስፋት ያለማችውን ስንዴን ኤክስፖርት ማድረግ መጀመሯ ጠንካራ ኢኮኖሚን መገንባት የሚያስችላት ትልቅ ጅማሮ እንደሆነ የምጣኔ ሀብት ምሁር ገለጹ፡፡
በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህርና በ‹‹ፍሮንቲየርአይ (Frontieri)›› ጥናትና አማካሪ ድርጅት ከፍተኛ ተመራማሪ ዶክተር ሞላ አለማየሁ ለኢፕድ እንደተናገሩት፤ አሁን...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93762
ክልሉ ለ215 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ ሰጠ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
ባለፉት ስድስት ወራት ለ215 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ መስጠቱን የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አስታወቀ፡፡
የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሐልጌዮ ጂሎ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፣ በክልሉ ባለፉት ስድስት ወራት የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለጠየቁ 215 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጥቷል፡፡
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93761
አዲስ አበባ በቀን 1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ ቢያስፈልጋትም እያመረተች ያለችው 725 ሺህ ብቻ ነው
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
በአዲስ አበባ ከተማ በቀን ከሚያስፈልገው አንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ አሁን ላይ እየተመረተ ያለው 725ሺህ ሜትር ኪዩብ ብቻ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታወቀ::
በ570 ሚሊዮን ብር በጀት ተጨማሪ 75ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ እየለማ እንዳለ ተገልጿል::

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93752
ብሔራዊ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ አማራጮች ላይ የሚመክር ጉባኤ እየተካሄደ ነው
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
ብሔራዊ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ አማራጮች ላይ የሚመክር ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።
በፍትህ ሚኒስቴር አስተባባሪነት እየተካሄደ በሚገኘው የምክክር መድረክ ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሠብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ፣ ሚኒስትሮችና የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ተገኝተዋል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ባደረጉት ንግግር፤ ባለፉት ጊዜያት በነበሩ ግጭቶች የተፈጠሩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በሕግ ለመፍታት ተገቢው ትኩረት ባለመሰጠቱ የበዳይ ተበዳይ ትርክትና ቁርሾ ተበራክቷል ብለዋል።
በተለያዩ ጊዜያት የተፈጸሙ ጉልህ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችንና ቁርሾዎችን አግባብነት ባለው መልኩ ለመፍታት ብሔራዊ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ አስፈላጊ በመሆኑ ለውጤታማነቱ መስራት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
ግጭት ወቅት የተከሰቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተገቢው መንገድ ለመፍታት በሀገራችን ብሔራዊ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ የሚያስፈልግበት ወቅት ላይ ነን ሲሉም ነው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የተናገሩት።
በጌትነት ተስፋማርያም
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፓኪስታን የኢንቨስትመንትና የንግድ ልኡክ ጋር ውይይት እያደረጉ ነው
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፓኪስታን የኢንቨስትመንትና የንግድ ልኡክ ጋር ውይይት እያደረጉ ነው። ውይይቱ ለቀጣይ አምስት ቀናት የሚቆይ ነው ተብሏል።
በውይይቱ ወቅት ንግግር ያደረጉት በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር በኢትዮጵያ በርካታ የኢንቨስትመንት አማራጮች መኖራቸውን ገልጸዋል።
ይህ መድረክ የኢትዮጵያና የፓኪስታንን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር አዲስ ምእራፍ ነው ያሉት አምባሳደሩ፣ ኢትዮጵያ ካላት የኢንቨስትመንት አማራጭ በተጨማሪ ያለችበት ስትራቴጂያዊ አቀማመጥ ተመራጭ እንደሚያደርጋት ገልጸዋል።
ኢትዮጵያና ፓኪስታን ከፍተኛ የሆነ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አላቸው። እንዲሁም በአለም አቀፍ መድረክ ያላቸው ግንኙነት ጠንካራ ነው፣ ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
በሰላምና ደህንነት፣ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲና በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ሁለቱ ሀገራት ጠንካራ ዲፕሎማሲ ግንኙነት እንዳላቸው አምባሳደር ጀማል ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የፓኪስታን አምባሳደር ሻዛብ አባስ እንደተናገሩ፣ ኢትዮጵያ የአለም አቀፍ የዲፕሎማሲ መናከሪያ ናት። ሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ግንኙነት ተፈጥሯል። ኢትዮጵያ የሁሉም የስልጣኔ ምልክት ናት ብለዋል።
በኢትዮጵያ ያሉ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮችም ለፓኪስታን ልኡካን ቀርበዋል።
በሞገስ ጸጋዬ