Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የዓለም ጤና ድርጅት በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው የጤና ተቋማት የሚውል 70 ሜትሪክ ቶን የመድኃኒትና የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
*******************
(ኢ.ፕ.ድ)
የዓለም ጤና ድርጅት በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው የጤና ተቋማት የሚውል 70 ሜትሪክ ቶን የመድኃኒትና የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
የድርጅቱ ድጋፍም በጦርነት ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው የአፋር፣ የትግራይ እና የአማራ ክልል ጤና ተቋማት የሚውል መሆኑን በሽረ ቅርንጫፍ የዓለም የጤና ድርጅት አስተባባሪ ዶክተር ቦኒፈስ አምባኒ ገልጸዋል።
መንግስት እነዚህ አስቸኳይ መድኃኒትና የህክምና መሳሪያዎች ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆኑ ያደርጋልም ብለዋል።
ድጋፋም ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተደራሽ እንደሚሆን ተመልክቷል።
በጌትነት ምህረቴ
እስራኤል በጤናው ዘርፍ ለኢትዮጵያ ሙያዊ ድጋፍ እንደምታደርግ ተገለጸ
***********
(ኢ ፕ ድ)
የእስራኤል የጤና ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ልምድ በማካፈል፣ የእውቀት ሽግግር በማድረግና የኢትዮጵያ ባለሙያዎች በእስራኤል እንዲማሩ በማድረግ የጤና ዘርፍ እንዲዘምን እየሠራች መሆኑን በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ አስታወቁ።
በቅርቡ ከእስራኤል የመጡ ሁለት የጤና ምሑራን የአመራር ችሎታንና ልሕቀትን ለማሳደግ ‹‹የጤና እንክብካቤ አመራር›› በሚል ርዕስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ 50 የሕክምና ዶክተሮች ልምዳቸውን ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93610
“ አፍሪካውያንን ከፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ ጎን ለማሰለፍ ኢትዮጵያኒዝምን ማጠናከር ያስፈልጋል”- ፕሮፌሰር ሹመት ሲሻኝ የታሪክ ተመራማሪ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
አፍሪካውያንን ኢትዮጵያ ከያዘችው የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ ጎን ለማሰለፍ ቅድሚያ ኢትዮጵያኒዝምን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ተመራማሪና መምህሩ ፕሮፌሰር ሹመት ሲሻኝ ገለጹ።
ፕሮፌሰር ሹመት ሲሻኝ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በዓድዋ ድል ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93608
ለ20 ወራት የኤሌክትሪክ አገልግሎት በመቋረጡ መቸገራቸውን የሐራ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ
👉 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበኩሉ በቅርቡ አገልግሎቱን አስጀምራለሁ ብሏል
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ለአንድ ዓመት ከስምንት ወራት የተቋረጠው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለበርካታ ችግር እንደዳረጋቸው በሰሜን ወሎ ዞን የሐራ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበኩሉ ለህዝብ መገልገያ ተቋማት ቅድሚያ በመስጠት አገልግሎቱን ለማስጀመር እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።
የሐራ ከተማ ነዋሪ አቶ መላኩ ምስጋናው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ ለአንድ ዓመት ከስምንት ወራት የተቋረጠው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለበርካታ ችግር ዳርጓቸዋል።
ኤሌክትሪክ በመቋረጡ ምክንያት ከፍተኛ ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93605
በአርቲስት ዓሊ ቢራ ስም በቢሾፍቱ ከተማ አዲስ የባንክ ቅርንጫፍ ተከፈተ
*****************
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢሾፍቱ ከተማ ድሬ ጂቱ ቀበሌ በክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ ስም ‘’ዓሊ ቢራ ቅርንጫፍ’’ በይፋ አስመርቆ ስራ አሰጀመረ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞች አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ወጋየሁ ገብረማርያም፣ የባንኩ ማዕከላዊ ሪጅን የዲስትርክቶች ኦፕሬሽን ዳይሬክተር አቶ አንዷለም ግዛቸውና አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ በጋራ ቅርንጫፉን መርቀው ስራ አሰጀምረዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማዕከላዊ ሪጅን የዲስትርክት ኦፕሬሽን ዳይሬክተር አቶ አንዷለም ግዛቸው እንደተናገሩት፤ አርቲስት አሊ ቢራ ከዚህ በላይ ይገበዋል፤ ተሰጦውን ሳይሰስት ለኢትዮጵያውያን ያበረከተና ለጥበብ የተሰጠ ሰው እንደሆነ ተናግረዋል።

በአሁኑ ትውልድ ይበልጥ እንዲታወቅና በመጪው ትውልድ እንዳይዘነጋ ታስቦ ቅርንጫፉ እንደተከፈተ ጠቁመዋል።

ለክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ የህይወት ዘመን ትሩፋቶች የተዘጋጀ መታሰቢያ እንደሆነም ተገልጿል።

በምረቃ ሥነሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተለያዩ ቅርንጫፍ ማናጀሮች፣ የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ ተወካይ፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎችና በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ያልተጠናቀቁ የጋራ መኖርያ ቤቶች ግምባታ እስከ ሰኔ ወር ድረስ እንዲጠናቀቅ ከንቲባ አዳነች አሳሰቡ
****************
(ኢ ፕ ድ)

የጋራ መኖርያ ቤቶችን ግንባታ በተያዘላቸው ጊዜ ያለማጠናቀቅ ክፍተት መኖሩን የገመገሙት ከንቲባ አዳነች፣ ለዚህ ክፍተት የሲሚንቶ እጥረት፣ የተለያዩ የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ ልዩነት እንዲሁም የወሰን ማስከበር ችግር መኖሩን ተገንዝበናል ብለዋል

ሆኖም እነዚህን ችግሮች በመቅረፍ፣ የጋራ መኖርያ ቤቶችን መሰረታዊ ግንባታ መንግስት በአፋጣኝ በማጠናቀቅ፣ ቀሪውን ተጠቃሚው እንዲያሟላ የሚደረግ ሲሆን የመሰረተ ልማት አቅራቢ ተቋማት ቀሪ ስራዎችን በቅንጅትና በፍጥነት እንዲያጠናቅቁ አቅጣጫ የሰጡ ሲሆን ይህንንም የሚከታተሉ ተቋማትና ኮሚቴዎች በየሳምንቱ የግንባታውን ሂደት ይከታተላሉ ብለዋል።

የተነሱት የግብዓት እጥረትና የዋጋ ልዩነቶችም አፋጣኝ እልባት አግኝተው እስከ ሰኔ ወር ባለው ግዜ ግንባታዎች ተጠናቅቀው ለተጠቃሚው ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ አቅጣጫ መቀመጡን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት ገልጸዋል።
የጠቅላይ ሚነስትር ዶከተር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት‼️

ዛሬ ከሼክ ተሚም ኢብን ሀማድ አልታኒ ጋር በመገናኘታችን ደስተኛ ነኝ። የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን ጨምሮ በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይም ተወያይተናል። #ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ዘርፎች ለኳታር ኢንቨስትመንቶች ብዙ ዕድሎች አሉ።
በቶክዮ ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል
******
(ኢ.ፕ.ድ)

ሌሊት በተካሄደው የ2023 የቶክዮ ማራቶን ላይ የተሳተፉ ወንድና ሴት ኢትዮጵያዊን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።

በወንዶች ውድድር አትሌት ደሶ ገልሚሲ አንደኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ፤ አትሌት መሀመድ ኢሳ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቋል። አትሌት ፀጋዬ ጌታቸው ደግሞ የሶስተኛ ደረጃን ይዞ ፉክክሩን ጨርሷል ።

በሴቶች በተደረገው ውድድር አትሌት ፀሀይ ገመቹ በኬንያዊቷ ሮዝመሪ ዋንጂሩ ተቀድማ በሁለተኝነት ውድድሯን ስታጠናቅቅ አሸቴ በከሬ ሶስተኛ አትሌት ወርቅነሽ ኢዶሳ ደግሞ በአራተኝነት ውድድራቸውን ፈፅመዋል።
የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሀብት ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ ተሻግሯል
****************
(ኢ ፕ ድ )
የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ በማንቀሳቀስ በአገሪቱ ምጣኔ ሀብት ዕድገት ላይ ጉልህ ሚና እየተወጡ መሆኑን የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር አስታወቀ፡፡

ቀደም ሲል በኪሣራ ውስጥ የነበሩ የልማት ድርጅቶች ወደ ትርፋማነት ተሸጋግረዋል ተብሏል፡፡ https://www.press.et/?p=93690
ማህበሩ በ52 ፓርኮች ከ24 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን እየተንከባከበ ነው
***************
(ኢ.ፕ.ድ)
👉 6 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል እየተዘጋጀ ነው
በ52 ፓርኮች ከ24 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን መትከል መቻሉን የኦሮሚያ ልማት ማህበር አስታወቀ፡፡
ማህበሩ በመጪው ክረምት ስድስት ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል የዝግጅት ሥራ እያከናወነ መሆኑንም አስታውቋል፡፡
የኦሮሚያ ልማት ማህበር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ደጀኔ ኢቲቻ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93759