Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት‼️

በትጋት፣ በትዕግሥት እና ብሔራዊ ሕጎችን በማክበር የጋራ ጥረታችን ታክሎበት ከድህነት ነጻ የሆነች ሀገር መፍጠር እንችላለን። የታክስ እና የጉምሩክ ሕግ ተገዢነት ሀገራዊ ንቅናቄ ዛሬ ስናስጀምር ሀገራዊ ግዴታቸውን በእውነት ሲወጡ ለነበሩ ግብር ከፋዮች ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋል።
ክብረ በዓሉ አስደናቂ እንደነበር የአንጎላ መከላከያ አዛዥ ተናገሩ
************
(ኢ ፕ ድ)
127ኛው የዓድዋ ድል በዓል ደማቅና መርሃግብሩ የተዘጋጀበት መንገድም አስደናቂ እንደነበር የአንጎላ መከላከያ ሠራዊት አዛዥ ኮሎኔል ጆሴ ፎንሴካ ተናሩ። ኮሎኔል ጆሴ ፎንሴካ በመስቀል አደባባይ የዓድዋ ድል ክብረ በዓል ላይ ታድመዋል።
ኮሎኔል ጆሴ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ ዝግጅቱ በጦርነቱ ወቅት የነበረውን የኢትዮጵያውያን አንድነትና ጀግንነት ያሳያል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93552
ከ760 ሺህ በላይ ሠልጣኞች ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ይገባሉ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 760 ሺህ 832ቱ ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ገብተው እንደሚሰለጥኑ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ። በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚሰጠው ሥልጠና ወደ ደረጃ ስምንት ከፍ እንዲል ተደርጓል።
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለፁት...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93546
ብሔራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ የሀገሪቱን አጠቃላይ የኢኮኖሚ ሁኔታና እንቅስቃሴ ግምገማ እያካሄደ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አሰታወቀ‼️
ኢትዮጵያ ከሌሎች አገራት ጋር የሚኖራትን የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከር በሚያስችል ውይይት ተካሄደ
*****
(ኢ ፕ ድ)

አዘርባጃን ባኩ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የገለልተኛ አገራት ንቅናቄ ጉባኤ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ካዛኪስታንና ከሰርቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በውይይቱ የካዛኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካኔት ቱመሽ በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የተካሄዱ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ለውጦችን አድንቀዋል።

ከሁለቱ አገሮች በቱሪዝምና በኢንሸስትመንት አቅሞች ላይ ለመስራት ፍላጎት እንደላቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ በቢዝነስ ስራዎች የተሰማሩ ባለሃብቶች በካዛኪስታን ጉብኝት እዲያደርጉም ጠይቀዋል። ካዛኪስታን ለተማሪዎች ነፃ የስኮላርሺፕ እድሎች እንደምታመቻችም ተናግረዋል።

አቶ ደመቀ በኢትዮጵያ  የነበረውን ውስጣዊ ችግር ለመፍታት በሰላም ስምነቱ አፈፃፀም ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።  በውስጥ አቅም ችግሮችን ለመፍታት የተደረጉ ጥረቶችና ወደ ተግባር የተገባበትን ሂደት አብራርተዋል።

የሁለቱን አገሮች የንግድና የቢዝነስ ትብብር በሚፈለገው ደረጃ ማሳደግ እንደሚገባ ተናግረዋል። ካዛኪስታን እ.ኤ.አ. 2017/2018 በተባበሩት መንግሥት የፀጥታው ምክርቤት የተለዋጭ ቆሚ ኮሚቴ አባል በነበረችበት ወቅት ኢትዮጵያ በቅርበት ስትሰራ እንደነበር አስታውሰዋል።

በተመሳሳይ አቶ ደመቀ ከሰርቢያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አይቨክ ዳሴክ ጋር ውይይት አድርገዋል።

የሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን ጠንካራ ታሪካዊ ግንኘነት ማሳደግ እንደሚገባም ገልፀዋል።

ካዛኪስታን እና ሰርቢያ የገለልተኛ አገራት ንቅናቄ አባል ሲሆኑ ከኢትዮጵያ ጋር በአለምአቀፍ መድረኮች፣ በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ በትብብር ይሰራሉ ።
ወጪ ንግድንና ምርታማነትን ማሳደግ የዕዳ ጫናን ለማቃለል ያስችላል የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች
***************
(ኢ ፕ ድ)
ወጪ ንግድን ማሳደግና ምርትና ምርታማነትን መጨመር ሀገራዊ የዕዳ ጫናን ለማቃለልና ኢኮኖሚውን ለማሳደግ የሚደረገውን ጥረት የሚያሳካ መሆኑን የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ገለጹ።
የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዶክተር ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ሀገራዊ የዕዳ ጫናው ካልተቃለለ ድሃ ተኮር የልማት ሥራዎችን ያስተጓጉላል። በመሆኑም ወጪ ንግድን ማሳደግና ምርትና ምርታማነትን መጨመርን ጨምሮ ሌሎችንም አስፈላጊ እርምጃዎችን በመውሰድ ሀገራዊ የዕዳ ጫናን ለማቃለል የሚደረገውን ጥረት ማጠናከር ይገባል ።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93623
መቄዶንያ አንድ ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማሰባሰብ ጥሪ አቀረበ
*************
(ኢ ፕ ድ)
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር የፊታችን እሁድ በዶንኪ ቲዩብ አማካኝነት በሚደረገው አንድ ሚሊዮን ዶላር ገቢ የማሰባሰብ መርሐግብር ዜጎች እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረበ።
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ብንያም በለጠ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ የፊታችን እሁድ በኮሚዲያን እሸቱ አማካኝነት በዶንኪ ቲዩብ ለሚደረገው የአንድ ሚሊዮን ዶላር ገቢ የማሰባሰብ ፕሮግራም በመላ ዓለም የሚገኙ ዜጎች እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
ማኅበሩ አዲስ አበባ አያት ፀበል መድኃኒዓለም አጠገብ በሚገኘው ግቢ ውስጥ ሦስት ሺህ 600 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ከሁለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ዘመናዊ ሕንፃ እየገነባ መሆኑን....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93619
ክልሉ ባለፉት ስድስት ወራት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቱሪስቶችን አስተናግዷል
***************
(ኢ ፕ ድ)
የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ባለፉት ስድስት ወራት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሚጠጉ የሀገር ውስጥ ቱሪስቶችን ማስተናገዱ ተገለጸ።
የክልሉ ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይለማርያም ተስፋዬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ባለፉት ስድስት ወራት 1 ሚሊዮን 490 ሺ የአገር ውስጥ ጎብኚዎች ክልሉን ጎብኝተዋል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93615