Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የዓድዋ ድል በዓል በአድዋ ከተማ በድምቀት ተከበረ
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
127ኛው የዓድዋ ድል በዓል በተለያዩ ትርኢቶች በዓድዋ ከተማ በሶለዳ ተራራ ግርጌ በደመቀ መልኩ ተከብሯል።
የዓድዋ ከተማ ነዋሪዎች በሥፍራው ለሚገኙት የኢፕድ ዘጋቢዎች እንደገለጹት፤ የዓድዋ ድል ቀደምት አባቶች ብሄር ሀይማኖት ቋንቋ ሳይለዩ ሆ ብለው በአንድነት ተፋልመው ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላው ለጥቁር ህዝቦች አኩሪ ድል የተቀናጁበት ነው።
"እኛም ኢትዮጵያውያን የተፈጠረውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ በአንድነት አገራችንን ሰላም መጠበቅ አለብን" ብለዋል።
አቶ አሰፋ አብርሃ የተባሉት የአድዋ ከተማ ነዋሪ፤ "ዓድዋ የጀግኖች አባቶቻችን አኩሪ የድል ታሪክ ነው። እኛም ኢትዮጵያዊያን ከእነሱ የተግባር አንድነትን መማር ይኖርብናል። በትግራይ ብሎም በኢትዮጵያ የተፈጠረውን ሰላም ሁላችንም መጠበቅ አለብን። ሰላም በመፈጠሩ ነው ዓድዋን ድል በዓል በደመቀ ሁኔታ ያከበርነው። የሰላም ዋጋ ተነግሮ አያልቅም። ይህንን ጅምር ሰላም መንከባከብ ይገባል" ነው ያሉት።
የአድዋ ከተማ አሉላ ቀበሌ ነዋሪ መምህር ትብለጽ አማሃ ታሪካዊው የአድዋ ድል አስተማሪና ታላቅ ነው ትላለች። "ከዚህ ድል ብዙ መማር አለብን በተለይ አድነትን ፍቅርን መተባበር የታየበት ድል ስለሆነ እኛም በተፈጠረው ሰላም ያንን ማስቀጠል አለብን" ብላለች።
በዓሉ የዓድዋ ከተማ ነዋሪዎች፣ የፌዴራል ፓሊስ አባላት በተገኙበት በታሪካዊው ሶሎዳ ተራራ ግርጌ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል ።
በጌትነት ምህረቴ (ዓድዋ)
የዓድዋ ድልን የሚያጎሉ ጠንካራ የኪነጥበብ ስራዎችን ማብዛት ይገባል
**************
(ኢ ፕ ድ)
የዓድዋ ድልን የአንድነት ስሜት የሚያጎሉ ጠንካራ የኪነጥበብ ስራዎችን ማብዛት ይገባል ሲሉ አርቲስቶች ተናገሩ።
አርቲስትና ደራሲ ማህተመ ኃይሌ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጸው፤ ዓድዋን አስቦ ከመዋል ባለፈ ትውልዱን ለመቅረጽ ልንጠቀምበት ይገባል። በተለይ የኪነጥበብ ስራዎችን በማስፋፋት የሀገር ፍቅር ስሜትና አንድነት እንዲጎለብት ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93454
“ዓድዋ ኢትዮጵያውያን በጥቁር ሕዝቦች ልብ ውስጥ በደማቅ ቀለም እንድንጻፍ ምክንያት ሆኗል”
- አቶ ወንደሰን ግርማ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር
******************
(ኢ ፕ ድ)
ዓድዋ የቅኝ ገዢዎችን ህልም በማምከን ኢትዮጵያ በጥቁር ሕዝቦች ልብ ውስጥ በደማቅ ቀለም እንድትጻፍ ምክንያት ሆኗል ሲሉ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ወንደሰን ግርማ ተናገሩ።
ዳይሬክተሩ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳሉት የዓድዋ ድል የፓን አፍሪካኒዝም ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93466
የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት‼️

በትጋት፣ በትዕግሥት እና ብሔራዊ ሕጎችን በማክበር የጋራ ጥረታችን ታክሎበት ከድህነት ነጻ የሆነች ሀገር መፍጠር እንችላለን። የታክስ እና የጉምሩክ ሕግ ተገዢነት ሀገራዊ ንቅናቄ ዛሬ ስናስጀምር ሀገራዊ ግዴታቸውን በእውነት ሲወጡ ለነበሩ ግብር ከፋዮች ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋል።
ክብረ በዓሉ አስደናቂ እንደነበር የአንጎላ መከላከያ አዛዥ ተናገሩ
************
(ኢ ፕ ድ)
127ኛው የዓድዋ ድል በዓል ደማቅና መርሃግብሩ የተዘጋጀበት መንገድም አስደናቂ እንደነበር የአንጎላ መከላከያ ሠራዊት አዛዥ ኮሎኔል ጆሴ ፎንሴካ ተናሩ። ኮሎኔል ጆሴ ፎንሴካ በመስቀል አደባባይ የዓድዋ ድል ክብረ በዓል ላይ ታድመዋል።
ኮሎኔል ጆሴ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ ዝግጅቱ በጦርነቱ ወቅት የነበረውን የኢትዮጵያውያን አንድነትና ጀግንነት ያሳያል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93552