Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
#ዓድዋ_127‼️

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንትን ጨምሮ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናትና አርበኞች በምኒልክ ሃውልት ስር የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል
**********************
(ኢ ፕ ድ)

በአዲስ አበባ ምኒሊክ አደባባይ እየተከበረ ባለው 127ኛው የዓድዋ ድል በዓል የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንትን ጨምሮ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናትና የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች በምኒልክ ሃውልት ስር የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።

አንድነት ጀግንነት እና ፅናት በሚል መሪ ሃሳብ በሚከበረው የድል በዓል ላይ
በምኒልክ ሃውልት ሥር የአበባ ጉንጉን ያስቀመጡት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፤ የጥንታዊት ኢትዮጵያዊ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንዔል ጆቴ እና ሌሎች የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ናቸው።

የድል በዓሉ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ አርበኞች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እና ተማሪዎች እንዲሁም ለልዩ ልዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች በተገኙበት እየተከበረ ነው።

መርሃ ግብሩ በመከላከያ ሰራዊት፣ በፌዴራል ፖሊስ እና በአዲስ አበባ ፖሊስ ማርች ባንዶች ታጅቦ እየተከናወነ ነው።

በውብሸት ሰንደቁ
#ዓድዋ_127 ‼️
127ኛው የአድዋ ድል በዓል በመስቀል አደባባይ‼️
127ኛው የአድዋ ድል በዓል የኤፌድሪ ፕሬዝዳንት ሳለወርቅ ዘውዴ፣ ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፣ የተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክርቤቶች አፈጉባኤዎች፣ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትሮች፣ አምባሳደሮች፣ የመከለከያና የፌዴራል ፓሊስ አባላትና አመራሮች፣ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተገኙበት በመስቀል አደባባይ እየተከበረ ነው።
የአባት አርበኞችን የአድዋ ክተት ዘመቻ የሚያሳይ ትርዒትን ጨምሮ የተለያዩ ትርኢቶች እየቀረበ ነው።
በትርዒቱ የንጉስ ምኒልክንና የንግስት ጣይቱ የጦርነት አዋጅ ጥሪ በድራማዊ ተውኔት ለታዳሚው ቀርቧል።
በርካታ ፈረሰኞች በዓሉት በልዩ ትርዒት አድምቀዋል።
የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ ቀጄላ መርዳሳ ባደረጉት ንግግር የዓድዋ በዓል በደማቅ ሁኔታ እንዲከበር ላደረጉ ሁሉ ምስጋና ማቅረብ እወዳለሁ ብለዋል።
በመክሊት ወንድወሰን እና ጌትነት ተስፋማርያም
#ዓድዋ_127 ‼️
የዓድዋ የድል በዓልን በማስመልከት ወታደራዊ ትርዒት በመሰቀል አደባባይ ቀርቧል
127ኛውን የዓድዋ ድል በዓልን ምክንያት በማድረግ በሀገር መከላከያ ሠራዊት የተመራ ወታደራዊ ትርዒት በመስቀል አደባባይ ቀርቧል።
የጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ምድር ኃይል ሠልፈኞች፣ የአየር ኃይልና የባህር ኃይል አባላት እንዲሁም የተለያዩ የፀጥታ አካላት በረድፍ በአደባባዩ በማለፍ ትርዒት አሳይተዋል።
በበዓሉየኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ፣ የሕዝብተወካዮች ምክርቤት አፈጉባኤ ታገሠ ጫፎ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላና ጄነራል አበባው ታደሰ እንዲሁም የተለያዩ እንግዶች ተገኝተዋል።
ሞተረኞች፣ የፌዴራል ፖሊስ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም የተለያዩ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችና ዘመናዊ ትጥቆች የትርዒቱ አካል ናቸው።
በጦር ጄት እና ተዋጊ ሄሊኮፍተሮች የታጀበ የአየር ላይ ትርዒትም ቀርቧል።
የጦር ጄቶቹ በመገለባበጥ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ተነስተው በአዲስ አበባ አየር ላይ የተለያዩ ትርኢት አሳይተዋል።
በጌትነት ተስፋማርያም