Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
#ዓድዋ_127‼️

የአድዋ ድል በዓል አከባበር በአድዋ ድልድይ
*****************
(ኢ ፕ ድ)

127ኛው የአድዋ ድል በዓል በአድዋ ድልድይ በድመቀት እየተከበረ ነው።

በክብር በዓሉ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የትምህርትና ስልጠና መመሪያ ሀላፊ ብርጋዴር ጀነራል ሙልጌታ አምባቸው እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያውያን ባህር አቋርጦ የመጣውን የጠላት ጦር ተጋፍጦ ለማሸነፍ ተማምለው ቃል የተገባቡበት ስፍራ ነው ብለዋል። የ

አድዋ ታሪክ የተፀነሰበት ቦታ እንደሆነም አስታውሰዋል።

በስፍራውም ጀግናው የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ወታደራዊ ሰልፍ ያሳየ ሲሆን፤ ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች አድዋን የሚገልጹና ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነፃነት ተምሳሌት መሆኑዋን አመላካች መፈክሮችን በመያዝ ለበዓሉ ድምቀት ሰጥተዋል።

127ኛው የአድዋ ድል በዓል" አንድነት፣ ጀግንነት እና ጽናት" በሚል መሪ ቃል በመላው ኢትዮጵያ በመከበር ላይ ይገኛል።

በቃልኪዳን አሳዬ
#ዓድዋ_127‼️

127ኛው የዓድዋ ድል በዓል በዓድዋ ከተማ‼️
#ዓድዋ_127‼️

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንትን ጨምሮ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናትና አርበኞች በምኒልክ ሃውልት ስር የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል
**********************
(ኢ ፕ ድ)

በአዲስ አበባ ምኒሊክ አደባባይ እየተከበረ ባለው 127ኛው የዓድዋ ድል በዓል የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንትን ጨምሮ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናትና የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች በምኒልክ ሃውልት ስር የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።

አንድነት ጀግንነት እና ፅናት በሚል መሪ ሃሳብ በሚከበረው የድል በዓል ላይ
በምኒልክ ሃውልት ሥር የአበባ ጉንጉን ያስቀመጡት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፤ የጥንታዊት ኢትዮጵያዊ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንዔል ጆቴ እና ሌሎች የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ናቸው።

የድል በዓሉ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ አርበኞች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እና ተማሪዎች እንዲሁም ለልዩ ልዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች በተገኙበት እየተከበረ ነው።

መርሃ ግብሩ በመከላከያ ሰራዊት፣ በፌዴራል ፖሊስ እና በአዲስ አበባ ፖሊስ ማርች ባንዶች ታጅቦ እየተከናወነ ነው።

በውብሸት ሰንደቁ