Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
#ዓድዋ_127 ‼️

የዓድዋ ድል በዓልን ለማክበር የተለያዩ አገራት ወታደራዊ አታሼዎች በመስቀል አደባባይ ተገኝተዋል
*****************
(ኢ ፕ ድ)

የጀግኖች ኢትዮጵያዊያንን ተጋድሎ ውጤት የሆነውን የዓድዋ ድል በዓል ለማክበር በመስቀል አደባባይ የተለያዩ አገራት ወታደራዊ አታሼዎች ተገኝተዋል።

የነጭ ወራሪን በማንበርከክ አኩሪ ገድል ስለፈጸሙ የአድዋ ድል ጀግኖች ከአውሮፖና ከተለያዩ አህጉራት ለመጡ ወታደራዊ አታሼዎች ገለጻ ተደርጓል።

ብርጋዴር ጄኔራል ካሳዬ ጨመዳና ሌሎች የቀድሞ ጦር ሠራዊት አመራሮችና አባላት በበዓሉ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።

ዓድዋ አፍሪካውያንን ያነቃቃ የነፃነት ደወል ነው፤ የአያት ቅድመ አያቶቻችን ተጋድሎ በትውልድ እየተዘከረ ይኖራል የሚሉ ሀሳቦች ከመድረኩ በጽሁፍ ተዘጋጅተዋል።

በበዓሉ ላይ ከተተያዩ አገራት ወታደራዊ አታሼዎች በተጨማሪ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በመስቀል አደባባይ ዓድዋን አስመልክቶ ወታደራዊ ትርዒት እንደሚደረግ ይጠበቃል።

በጌትነት ተስፋማርያም
#ዓድዋ_127‼️

የዓድዋ ድል በዓል በዓድዋ ከተማ በሶሎዳ ተራራ ስር እየተከበረ ነው
**************
(ኢ.ፕ.ድ)

127ኛው የዓድዋ ድል በዓል በዓድዋ ከተማ በሶሎዳ ተራራ ስር እየተከበረ ነው።

በበዓሉ ላይ ህፃናት ስለ ዓድዋ ድል የሚተርክ ህብረ ዝማሬ አቅርበዋል።

የከተማው ነዋሪዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በዓሉን ለመታደም ማልደው በሥፍራው ተገኝተዋል።

በጌትነት ምህረቴ (ዓድዋ)
#ዓድዋ_127

127ኛው የዓድዋ ድል በዓል በመስቀል አደባባይ "አንድነት ጀግንነት እና ፅናት" በሚል መሪ ሃሳብ በከፍተኛ ድምቀት እየተከበረ ነው።

በበዓሉ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት አመራሮች፣ አርበኞች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ተማሪዎች እንዲሁም ከተለያዩ አከባቢዎች የመጡ የማህበረሰብ ክፍሎች ታድመዋል።

መርሃ ግብሩ በመከላከያ ሰራዊት የማርች ባንድ ታጅቦ እየተከናወነ ነው።

በመክሊት ወንደወሰን