የኢፌዴሪ አየር ሃይል በቦረና ዞን በድርቁ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የምግብ ቁሳቁስ እና የእንስሳት መኖ ድጋፍ አደረገ
******************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢፌዴሪ አየር ሃይል በቦረና ዞን በድርቁ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የምግብ ቁሳቁስ እና የእንስሳት መኖ ድጋፍ አደረገ፡፡
ድጋፉን የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ በተገኙበት ለዞኑ የአገር ሽማግሌዎች እና የስራ ኃላፊዎች አስረክበዋል።
የአየር ኃይል የሰራዊት አባላት በራሳቸው ተነሳሽነት ድጋፉን ማሰባሰባቸውንና ለእንስሳት መኖነት በአየር ኃይሉ ግቢ ውስጥ የተመረተ መሆኑን ሌተናል ጄኔራል ይልማ ገልጸዋል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ፤ ከመኖው በተጨማሪ ስንዴ እንዲሁም የእንስሳት ምግብ እንደሚገኝበት እና በቀጣይ አየር ኃይሉ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖችን የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመልክተዋል።

ለቴክኒክና ሙያ ስልጠና መግቢያ ውጤት ይፋ ሆነ
***************
(ኢ ፕ ድ)
በ2014 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ለቴክኒክና ሙያ ስልጠና የሚያስገባቸውን መቁረጫ ነጥብ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ይፋ አደረገ።
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈራያት ካሚል በሰጡት መግለጫ፤ በተፈጥሮ ሳይንስ ደረጃ 5 ወንድ 246ና ከዚያ በላይ፣ ለታዳጊ ክልልና አርብቶ አደር አከባቢ ወንድ 203ና ከዚያ በላይ፣ ሴቶች 218 ከዚያ በላይ፣ ለታዳጊ ክልልና አርብቶ አደር አከባቢዎች 202 ከዚያ በላይ እንዲሆን ተወስኗል ብለዋል።
ለሁሉም ክልሎች አካል ጉዳተኛ 149ና ከዚያ በላይ መሆኑን ገልጸዋል።
ለማህበራዊ ሳይንስ በደረጃ 5 ለወንዶች 203ና ከዚያ በላይ፣ ለታዳኪ ክልሎችና አርብቶ አደር አከባቢ ወንዶች 173ና ከዚያ በላይ፣ ለሴቶች 179ና ከዚያ በላይ፣ ለታዳጊ ክልልና አርብቶ አደር አከባቢ ሴቶች 171ና ከዚያ በላይና ለሁሉም ክልሎች አካል ጉዳተኞች 149ና ከዚያ በላይ መሆኑን ገልጸዋል።
በሄለን ወንድምነው
ዝርዝር መረጃውን ከሰንጠረዡ ይመልከቱ

#ዓድዋ_127‼️
127ኛው የዓደዋ ድል በዓል በምኒልክ አደባባይ መከበር ጀምሯል
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
127ኛውን የዓደዋ ድል በዓል በምኒልክ አደባባይ የመከላከያ ሠራዊት እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ማርች ባንድ ሀገራዊ ዝማሬዎችን በማሰማት መከበር ጀምሯል።
ዝግጅቱን ለመታደም የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ወደ ምኒልክ አደባባይ እያቀኑ መሆኑን በሥፍራው የሚገኙት የኢፕድ ዘጋቢዎች ተመልክተዋል።
በውብሸት ሰንደቁ

#ዓድዋ_127 ‼️
የዓድዋ ድል በዓልን ለማክበር የተለያዩ አገራት ወታደራዊ አታሼዎች በመስቀል አደባባይ ተገኝተዋል
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የጀግኖች ኢትዮጵያዊያንን ተጋድሎ ውጤት የሆነውን የዓድዋ ድል በዓል ለማክበር በመስቀል አደባባይ የተለያዩ አገራት ወታደራዊ አታሼዎች ተገኝተዋል።
የነጭ ወራሪን በማንበርከክ አኩሪ ገድል ስለፈጸሙ የአድዋ ድል ጀግኖች ከአውሮፖና ከተለያዩ አህጉራት ለመጡ ወታደራዊ አታሼዎች ገለጻ ተደርጓል።
ብርጋዴር ጄኔራል ካሳዬ ጨመዳና ሌሎች የቀድሞ ጦር ሠራዊት አመራሮችና አባላት በበዓሉ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።
ዓድዋ አፍሪካውያንን ያነቃቃ የነፃነት ደወል ነው፤ የአያት ቅድመ አያቶቻችን ተጋድሎ በትውልድ እየተዘከረ ይኖራል የሚሉ ሀሳቦች ከመድረኩ በጽሁፍ ተዘጋጅተዋል።
በበዓሉ ላይ ከተተያዩ አገራት ወታደራዊ አታሼዎች በተጨማሪ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በመስቀል አደባባይ ዓድዋን አስመልክቶ ወታደራዊ ትርዒት እንደሚደረግ ይጠበቃል።
በጌትነት ተስፋማርያም

የዓድዋ ድል በዓል በዓድዋ ከተማ በሶሎዳ ተራራ ስር እየተከበረ ነው
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
127ኛው የዓድዋ ድል በዓል በዓድዋ ከተማ በሶሎዳ ተራራ ስር እየተከበረ ነው።
በበዓሉ ላይ ህፃናት ስለ ዓድዋ ድል የሚተርክ ህብረ ዝማሬ አቅርበዋል።
የከተማው ነዋሪዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በዓሉን ለመታደም ማልደው በሥፍራው ተገኝተዋል።
በጌትነት ምህረቴ (ዓድዋ)