74 የፌዴራል ተቋማት የፋይናንስ ግዥ ስርዓታቸውን በኤሌክትሮኒክስ በመፈፀም ላይ ናቸው
👉726 ጨረታዎች በኤሌክትሮኒክስ ተፈፅሟል፣
****
(ኢ ፕ ድ)
74 የፌዴራል ተቋማት የፋይናንስ ግዥ ስርዓታቸውን በኤሌክትሮኒክስ መፈፀማቸውን የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን አስታወቀ።
የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን የኤሌክትሮኒክ የመንግስት ግዥ ስረዓትን ተግባራዊ ከሚያደርጉ የፌዴራል ተቋማት ጋር ምክክር በማድረግ ላይ ይገኛል።
በምክክር መድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሃጂ ኢብሳ እንደተናገሩት፤ የኤሌክትሮኒክ የግዥ ስርዓት መንግስት ትኩረት ከሰጣቸው ዋነኛ የስራ ዘርፎች አንዱ ነው። ኢትዮጵያ በኤሌክትሮኒክ የግዥ ስርዓት በመተግበር ከአፍሪካ በስድስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
እንቅስቃሴዎች የተጀመሩት ከዛሬ አራት ዓመት በፍት ነው ምንም እንኳን አጭር ግዜ ቢሆንም አሁን ላይ 74 የፌዴራል ተቋማት የፋይናንስ ግዥ ስርዓታቸውን በኤሌክትሮኒክስ መፈፀማቸውን ተናግረዋል።
በያዝነው ዓመት ብቻ 726 ጨረታዎች በኤሌክትሮኒክስ መፈፀማቸውን ገልፀው። ጨረታዎችን ለመሳተፍ ከክልል ከተሞች ወይም ከሌሎች ሀገራት የሚደረገውን ጉዞና ለስራው ዜጎች ያባክኑ ከሁሉም በላይ በዘርፉ የሚካሄደውን የሙስና ሰንሰለት መቁረጥ እንደተቻለ ጠቁመዋል።
በመጀመሪያ ወቅት የኤሌክትሮኒክ የግዥ ስርዓት መንግስት ለመተግበር በሚሞክርበት ወቅት የተቋማት ፍቃደኝነት እንዳልነበረ አስታውሰው አሁን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሳይሆን እራሳቸው ወደ ተቋሙ በመምጣት የኤሌክትሮኒክ የግዥ ስርዓት እንዲዘረጋላቸው ጥያቄ እያቀረቡ እንደሆነ አብራርተዋል።
በቅርቡ የፌዴራል ተቋማትን አጠናቀን ወደ ክልሎች በመውረድ የኤሌክትሮኒክ የግዥ ስርዓት እንደምዘረጋ ተናግረዋል።
የኤሌክትሮኒክ የግዥ ስርዓት በመተግበር የተሻለ አፈፃፀሞ ያሳዩ አራት የፌዴራል ተቋማት የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቱ፣ የቅርስና ጥበቃ ባለስልጣን፣የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤትና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኒዎሎጂ ዩንቨርስቲ ተሞክሮዎቻቸውን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።
በውይይቱም የኢ-ጂፒ ፕሮጀክት አፈፃፀም ላይ ሰፊ ውይይቶች ይደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በቃልኪዳን አሳዬ

በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የሚስተዋሉ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት አቅጣጫ ተቀምጦ እየተሰራ መሆኑን የየክልሎቹ ኮምንኬሽን ቢሮ ኃላፊዎች አስታወቁ
******************
(ኢ.ፕ.ድ)
በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የሚስተዋሉ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት አቅጣጫ ተቀምጦ እየተሰራ መሆኑን የሁለቱም ክልሎች የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊዎች ዛሬ በጋራ በስጡት መግለጫ አስታወቀዋል።
የአማራ ክልል የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ትናንት የሁለቱም ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች በአገራዊ፣ ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።
በውይይቱ ከፍተኛ አመራሮች የተሳተፉበት መሆኑን የጠቀሱት አቶ ግዛቸው፤ መልካም የሆኑ የልማት ስራዎችን በጋራ ለማስቀጠል፣ ፈተናዎችና ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ውጤታማ ውይይት ተደርጓል ብለዋል።
የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ ሃይሉ አዱኛ በበኩላቸው፤ በሁለቱ ክልሎች መካከል የመልካም አስተዳደር፣ የልማት፣ የማህበራዊና ፖለቲካዊ ግንኙነትቶችን ለማጠናከር የሚያስችል ውይይት በከፍተኛ አመራሮች መካከል መካሄዱን አስታውቀዋል።
ሁለቱ ክልሎች በመናበብ የጋራ የሆኑ ፈተናዎችንና ችግሮችን ለመፍታት ስምምነት ላይ ተደርሷልም ብለዋል።
ውይይቱ በአመራሩ ብቻ የሚወሰን ሳይሆን በቀጣይም በምሁራን፣ በአገር ሽማግሌዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት መካከል ይደረጋል ተብሏል።
በሞገስ ተስፋ

የኢፌዴሪ አየር ሃይል በቦረና ዞን በድርቁ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የምግብ ቁሳቁስ እና የእንስሳት መኖ ድጋፍ አደረገ
******************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢፌዴሪ አየር ሃይል በቦረና ዞን በድርቁ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የምግብ ቁሳቁስ እና የእንስሳት መኖ ድጋፍ አደረገ፡፡
ድጋፉን የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ በተገኙበት ለዞኑ የአገር ሽማግሌዎች እና የስራ ኃላፊዎች አስረክበዋል።
የአየር ኃይል የሰራዊት አባላት በራሳቸው ተነሳሽነት ድጋፉን ማሰባሰባቸውንና ለእንስሳት መኖነት በአየር ኃይሉ ግቢ ውስጥ የተመረተ መሆኑን ሌተናል ጄኔራል ይልማ ገልጸዋል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ፤ ከመኖው በተጨማሪ ስንዴ እንዲሁም የእንስሳት ምግብ እንደሚገኝበት እና በቀጣይ አየር ኃይሉ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖችን የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመልክተዋል።

ለቴክኒክና ሙያ ስልጠና መግቢያ ውጤት ይፋ ሆነ
***************
(ኢ ፕ ድ)
በ2014 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ለቴክኒክና ሙያ ስልጠና የሚያስገባቸውን መቁረጫ ነጥብ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ይፋ አደረገ።
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈራያት ካሚል በሰጡት መግለጫ፤ በተፈጥሮ ሳይንስ ደረጃ 5 ወንድ 246ና ከዚያ በላይ፣ ለታዳጊ ክልልና አርብቶ አደር አከባቢ ወንድ 203ና ከዚያ በላይ፣ ሴቶች 218 ከዚያ በላይ፣ ለታዳጊ ክልልና አርብቶ አደር አከባቢዎች 202 ከዚያ በላይ እንዲሆን ተወስኗል ብለዋል።
ለሁሉም ክልሎች አካል ጉዳተኛ 149ና ከዚያ በላይ መሆኑን ገልጸዋል።
ለማህበራዊ ሳይንስ በደረጃ 5 ለወንዶች 203ና ከዚያ በላይ፣ ለታዳኪ ክልሎችና አርብቶ አደር አከባቢ ወንዶች 173ና ከዚያ በላይ፣ ለሴቶች 179ና ከዚያ በላይ፣ ለታዳጊ ክልልና አርብቶ አደር አከባቢ ሴቶች 171ና ከዚያ በላይና ለሁሉም ክልሎች አካል ጉዳተኞች 149ና ከዚያ በላይ መሆኑን ገልጸዋል።
በሄለን ወንድምነው
ዝርዝር መረጃውን ከሰንጠረዡ ይመልከቱ

#ዓድዋ_127‼️
127ኛው የዓደዋ ድል በዓል በምኒልክ አደባባይ መከበር ጀምሯል
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
127ኛውን የዓደዋ ድል በዓል በምኒልክ አደባባይ የመከላከያ ሠራዊት እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ማርች ባንድ ሀገራዊ ዝማሬዎችን በማሰማት መከበር ጀምሯል።
ዝግጅቱን ለመታደም የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ወደ ምኒልክ አደባባይ እያቀኑ መሆኑን በሥፍራው የሚገኙት የኢፕድ ዘጋቢዎች ተመልክተዋል።
በውብሸት ሰንደቁ

#ዓድዋ_127 ‼️
የዓድዋ ድል በዓልን ለማክበር የተለያዩ አገራት ወታደራዊ አታሼዎች በመስቀል አደባባይ ተገኝተዋል
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የጀግኖች ኢትዮጵያዊያንን ተጋድሎ ውጤት የሆነውን የዓድዋ ድል በዓል ለማክበር በመስቀል አደባባይ የተለያዩ አገራት ወታደራዊ አታሼዎች ተገኝተዋል።
የነጭ ወራሪን በማንበርከክ አኩሪ ገድል ስለፈጸሙ የአድዋ ድል ጀግኖች ከአውሮፖና ከተለያዩ አህጉራት ለመጡ ወታደራዊ አታሼዎች ገለጻ ተደርጓል።
ብርጋዴር ጄኔራል ካሳዬ ጨመዳና ሌሎች የቀድሞ ጦር ሠራዊት አመራሮችና አባላት በበዓሉ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።
ዓድዋ አፍሪካውያንን ያነቃቃ የነፃነት ደወል ነው፤ የአያት ቅድመ አያቶቻችን ተጋድሎ በትውልድ እየተዘከረ ይኖራል የሚሉ ሀሳቦች ከመድረኩ በጽሁፍ ተዘጋጅተዋል።
በበዓሉ ላይ ከተተያዩ አገራት ወታደራዊ አታሼዎች በተጨማሪ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በመስቀል አደባባይ ዓድዋን አስመልክቶ ወታደራዊ ትርዒት እንደሚደረግ ይጠበቃል።
በጌትነት ተስፋማርያም