Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.1K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በክልሉ ከበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከ100 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል
***********
(ኢ.ፕ.ድ)
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሁለት ሺህ 434 ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት መሸፈኑንና ከዚህም ከ100ሺህ ኩንታል በላይ የስንዴ ምርት እንደሚጠበቅ የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበከር ካሊፋ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ በክልሉ በአጠቃላይ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከተሸፈነው ሁለት ሺህ 434 ሄክታር መሬት ከ100 ሺህ ኩንታል በላይ የስንዴ ምርት ይጠበቃል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93232
ባለፉት ሰባት ወራት ከቡና ወጪ ንግድ 702 ሚሊዮን ዶላር ተገኘ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
ባለፉት ሰባት ወራት ከቡና ወጪ ንግድ ወደ ተለያዩ የዓለም መዳረሻ ሀገራት ከተላከ የቡና ምርት 702 ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ዶላር መገኘቱን የቡናና ሻይ ባለስልጣን ገለጸ።
በባለስልጣኑ የገበያ መረጃና ደህንነት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ቸሩ ኮሩ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ባለፉት ሰባት ወራት 126 ሺ 649 ነጥብ 02 ቶን በመላክ 702 ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ዶላር ተገኝቷል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93221
በግማሽ ዓመቱ ከማዕድን ዘርፉ የተገኘው ገቢ ዝቅተኛ ነው
************
(ኢ.ፕ.ድ)
👉324 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዶላር ታቅዶ 115 ሚሊዮን ዶላር ተገኝቷል
👉 ሕገወጥ ግብይትና የጸጥታ ችግር ዘርፉን ፈትነውታል
በ2015 በጀት ስድስት ወራት 115 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ። ሕገወጥ ግብይትና የፀጥታ ችግር የማዕድን ዘርፉ ዋነኛ ተግዳሮቶች መሆናቸው ተገልጿል።
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93217
የአድዋ ሙዚየም ፕሮጀክት አፈጻጸም 78 ነጥብ ሁለት በመቶ ደርሷል
******************
(ኢ.ፕ.ድ)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግዙፍ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽህፈት ቤት በአድዋ ሙዚየም ፕሮጀክት አፈጻጸም ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል።

የፕሮጀክቶች ግንባታ ጽህፈት ቤት ኮንትራት አስተዳደር ዳሬክተር ዳዊት ጥበቡ (ኢንጅነር) በመግላጫው እንዳሉት፣ ፕሮጅክቱ የአድዋን ድል ታሪካዊ ዳራ መነሻ አድርጐ እየተገነባ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክቱ ፊዚካል አፈጻጸም 78 ነጥብ ሁለት በመቶ ደርሷል።

አድዋን በሰፊው የሚገልጽና የተለያዩ የአገሪቱ ካባቢዎችን መነሻ (ዜሮ ዜሮ ) ኪሎ ሜትርን እንደ ምልክት የሚጠቀመው ፕሮጀክቱ ከታሪካዊ መነሻው ባሻገር እንደ ሲኒማ፣ የትራንስፖርት ተርሚናል፣ ካፍቴሪያና አዳራሶችን እንዲሁም የተለያዩ መዝናኛዎችን ያቀፈ መሆኑን ኢንጂነር ዳዊት ገልጸዋል።

የፕሮጀክቱ ግንባታ ለበርካታ ዜጐች የስራ እድል መፍጠሩንም ተናግረዋል።

ግንባታው በሚቀጥለው አመት ጥቅምት ወር ሙሉ ለሙሉ ተጠናቅቆ አገልግሎት እንደሚጀመር ተጠቅሷል።

በአዲሱ ገረመው
የግብርና ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ዛሆ ዚዩዋን ጋር ተወያዩ
********************
(ኢ.ፕ.ድ)

የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ከሆኑት ዛሆ ዚዩዋን ጋር ቻይና የኢትዮጵያን የግብርና ዘርፍ ለማዘመን በምታደርገው ሁለንተናዊ ድጋፍ ዙሪያ ውይይት አደረጉ፡፡

በኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን እና ምርታማነትን ለማሳደግ በዘርፉ ላይ ለሚሰሩ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት፣ ዘመናዊ የግብርና መሳሪያዎች እና ቴክኖሎጂዎች ድጋፍ ቻይና እንደምታደርግ በውይይታቸው አንስተዋል፡፡

በተጨማሪም በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የቻይና ባለሃብቶች በኢትዮጵያ የግብርናው ዘርፍ ላይ ተሰማርተው እንዲሰሩ የሚያችል ስራ እንደሚሰራም በውይይታቸው መገለጹን ከሚኒስቴሩ ያገኘነውመረጃ ያሳያል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለቦረና ዞን የድርቅ ተጎጂዎች ያዘጋጀውን ድጋፍ ወደ ስፍራው ላከ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለቦረና ዞን የድርቅ ተጎጂዎች ከተለያዩ ተቋማት እና የህብረተሰብ ክፍሎች ያሰባሰበውን ድጋፍ ዛሬ ማለዳ ወደ ስፍራው ላከ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል አደባባይ ተገኝተው ድጋፉን አስረክበዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንዳሉት ድጋፉ ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት እና የህብረተሰብ ክፍሎች መሰባሰቡን ተናግረዋል።

ድጋፉ 250 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት መሆኑን ጠቅሰው ድጋፉም በቀጣይ ሁተኛ ዙር እንደሚደረግም አመላክተዋል።

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝዳንት አወሉ አብዲ በዞኑ የተከሰተው ድርቅ በተከታታይ በክልሉ 10 ዞኖች ዝናብ አለመዝነቡን ተከትሎ መሆኑን ተናግረዋል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ላደረገው ድጋፍም ምክትል ፕሬዝዳንቱ ምስጋና አቅርበዋል።

በዛሬው እለት በተደረገው ድጋፍ የምግብ፣ የእንስሳት መኖ፣የውሃ ቦቴዎች ይገኙበታል።

በኦሮሚያ ክልል በተከሰተው ድርቅ 4 ነጥብ 3 ሚልዮን ዜጎች ድጋፍ እንደሚሹ ክልሉ ማስታወቁ የሚታወስ ነው።