Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.1K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ባለፉት ስድስት ወራት ከብልሹ አሰራርና ሌብነት ጋር በተያያዘ ከ200 በላይ አመራርና ሰራተኞች ላይ ክስ ተመስርቷል
*******************
(ኢ ፕ ድ)
ባለፉት ስድስት ወራት ከብልሹ አሰራርና ሌብነት ጋር በተያያዘ ከ200 በላይ አመራርና ሰራተኞች ላይ ክስ ተመስርቷል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ብልሹ አሰራርና ሌብነትን የመከላከል ስራ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ገልጸው አገልግሎት አሰጣጥን ከወቅቱ ጋር እንዲሄድ ለማስቻል በርካታ ዘርፎችን የማዘመን እና የተገልጋዩን እርካታ ለማረጋገጥ የሚያስችል ስራ እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።
በኦሮሚያ ክልል የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋምና ለመከላከል የተለያዩ እቅዶች ታቅደው እየተሰሩ መሆኑን ተገለጸ
*********************
(ኢ ፕ ድ)

በኦሮሚያ ክልል የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋምና ለመከላከል የአጭርና የረጅም ጊዜ እቅዶች ታቅደው እየተሰሩ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ ገልጸዋል።

የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ በክልሉ የተከሰተውን ድርቅ አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፣ የክልሉ መንግስት ድርቅን ለመከላከል በርካታ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል።

በክልሉ በዚህ ዓመት ብቻ በተከሰተው ድርቅ 4 ነጥብ 3 ሚሊየን ዜጎች እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸውም የገለጹት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ ድርቅን ለመከላከል የአጭርና የረጅም ጊዜ እቅዶች ታቅደው እየተሰራ ነው ብለዋል።

በድርቅ ሳቢያ የሰው ህይወት እንዳያልፍ በአጭር ጊዜ እቅድ የተለያዩ ድጋፎች ተደርገዋል። የምግብ እርዳታና ውሃ በቦቴ እየቀረበ መሆኑን ጠቅሰው ጊዜ ችግሩን ለመፍታት በርካታ ፕሮግራሞች መነደፋቸውን ገልጸዋል።

የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም ተጠቃሽ ነው። በዚህም የደረቁ ምንጮች እየለመመለሙ ነው። ሌላው ህብረተሰቡ በተመጣጠነ ችግር ሊደርስበት የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ የልማት ትሩፋት ፕሮግራም ተጠቃሽ ነው ብለዋል።

በድርቅ ሳቢያ ከዚህ በፊት የሰው ህይወት አላለፈም፤ ወደፊትም በሰዎች ሕይውት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የተለያዩ ድጋፍ እየተደረጉ ነውም ብለዋል።

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ሶስት አመታት የዝናብ ችግር በመኖሩ ድርቅ ተከስቷል። ይሁን እንጅ እርብርብ እየተደረገ በመሆኑ የሰው ህይወት አልጠፋም፤ በቦረና አካባቢ ትምህርትና የጤና አገልግሎት አልተቋረጠም ብለዋል።
ሸገር ከተማን በቴክኖሎጂ ሽግግርና በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ አርአያ የምትሆን ለማድረግ በትኩረት ይሰራል
*****************
(ኢ ፕ ድ)

ሸገር ከተማ በቴክኖሎጂ ሽግግርና በኢኮኖሚ እንቅስቃሴዋ አርአያ የምትሆን ከተማ ለማድረግ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።

ሸገር ከተማ የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በዛሬው እለት በይፋ ስራ ጀምሯል፡፡

በ12 ክፍለ ከተሞችና በ36 ወረዳዎች በይፋ የተመሰረተችው ሸገር የሕዝቡን ባህል በማበልጸግ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግርና በኢኮኖሚ እንቅስቃሴዋ መልካም ምሳሌ የምትሆን ከተማ ለማድረግ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

ከተማዋ አዲስ አበባን በብዙ መልኩ እንደምትደግፍም አቶ ሽመልስ ገልጸዋል።

የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አባዱላ ገመዳ በበኩላቸው፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚኖሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ለዘመናት በብዙ መልኩ አስከፊ ድህነት ውስጥ እንደነበሩ አውስተው፤ ከተማዋ በዚህ መልኩ መመሰረቷ ከሕብረተሰቡም አልፎ ለአገርም ያለው ፋይዳ የጎላ ይሆናል ብለዋል።

ለቀድሞው የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንቶችና ለከተማዋ ምስረታ አስተዋፅኦ ላበረከቱት ግለሰቦች በአቶ ሽመልስ አብዲሳ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በአፋር ክልል ከ139 ሺህ በላይ የ7ኛና 8ኛ ክፍል መጽሐፍት ተሰራጨ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
በአፋር ክልል ከ139 ሺህ በላይ የ7ኛና 8ኛ ክፍል የአዲሱ ካሪኩለም መጽሐፍት ማሰራጨቱን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ የሥርዓተ-ትምህርት ዝግጅትና መማር ማስተማር ዳይሬክተር አቶ ዋልዶ ሀይሰማ እንደተናገሩት፣ ክልሉ ያሳተመውን 139 ሺህ የ7ኛና 8ኛ ክፍል የአዲሱ ካሪኩለም መጽሐፍትን አሰራጭቷል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93230
በክልሉ ከበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከ100 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል
***********
(ኢ.ፕ.ድ)
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሁለት ሺህ 434 ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት መሸፈኑንና ከዚህም ከ100ሺህ ኩንታል በላይ የስንዴ ምርት እንደሚጠበቅ የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበከር ካሊፋ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ በክልሉ በአጠቃላይ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከተሸፈነው ሁለት ሺህ 434 ሄክታር መሬት ከ100 ሺህ ኩንታል በላይ የስንዴ ምርት ይጠበቃል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93232
ባለፉት ሰባት ወራት ከቡና ወጪ ንግድ 702 ሚሊዮን ዶላር ተገኘ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
ባለፉት ሰባት ወራት ከቡና ወጪ ንግድ ወደ ተለያዩ የዓለም መዳረሻ ሀገራት ከተላከ የቡና ምርት 702 ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ዶላር መገኘቱን የቡናና ሻይ ባለስልጣን ገለጸ።
በባለስልጣኑ የገበያ መረጃና ደህንነት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ቸሩ ኮሩ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ባለፉት ሰባት ወራት 126 ሺ 649 ነጥብ 02 ቶን በመላክ 702 ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ዶላር ተገኝቷል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93221
በግማሽ ዓመቱ ከማዕድን ዘርፉ የተገኘው ገቢ ዝቅተኛ ነው
************
(ኢ.ፕ.ድ)
👉324 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዶላር ታቅዶ 115 ሚሊዮን ዶላር ተገኝቷል
👉 ሕገወጥ ግብይትና የጸጥታ ችግር ዘርፉን ፈትነውታል
በ2015 በጀት ስድስት ወራት 115 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ። ሕገወጥ ግብይትና የፀጥታ ችግር የማዕድን ዘርፉ ዋነኛ ተግዳሮቶች መሆናቸው ተገልጿል።
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93217
የአድዋ ሙዚየም ፕሮጀክት አፈጻጸም 78 ነጥብ ሁለት በመቶ ደርሷል
******************
(ኢ.ፕ.ድ)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግዙፍ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽህፈት ቤት በአድዋ ሙዚየም ፕሮጀክት አፈጻጸም ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል።

የፕሮጀክቶች ግንባታ ጽህፈት ቤት ኮንትራት አስተዳደር ዳሬክተር ዳዊት ጥበቡ (ኢንጅነር) በመግላጫው እንዳሉት፣ ፕሮጅክቱ የአድዋን ድል ታሪካዊ ዳራ መነሻ አድርጐ እየተገነባ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክቱ ፊዚካል አፈጻጸም 78 ነጥብ ሁለት በመቶ ደርሷል።

አድዋን በሰፊው የሚገልጽና የተለያዩ የአገሪቱ ካባቢዎችን መነሻ (ዜሮ ዜሮ ) ኪሎ ሜትርን እንደ ምልክት የሚጠቀመው ፕሮጀክቱ ከታሪካዊ መነሻው ባሻገር እንደ ሲኒማ፣ የትራንስፖርት ተርሚናል፣ ካፍቴሪያና አዳራሶችን እንዲሁም የተለያዩ መዝናኛዎችን ያቀፈ መሆኑን ኢንጂነር ዳዊት ገልጸዋል።

የፕሮጀክቱ ግንባታ ለበርካታ ዜጐች የስራ እድል መፍጠሩንም ተናግረዋል።

ግንባታው በሚቀጥለው አመት ጥቅምት ወር ሙሉ ለሙሉ ተጠናቅቆ አገልግሎት እንደሚጀመር ተጠቅሷል።

በአዲሱ ገረመው
የግብርና ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ዛሆ ዚዩዋን ጋር ተወያዩ
********************
(ኢ.ፕ.ድ)

የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ከሆኑት ዛሆ ዚዩዋን ጋር ቻይና የኢትዮጵያን የግብርና ዘርፍ ለማዘመን በምታደርገው ሁለንተናዊ ድጋፍ ዙሪያ ውይይት አደረጉ፡፡

በኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን እና ምርታማነትን ለማሳደግ በዘርፉ ላይ ለሚሰሩ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት፣ ዘመናዊ የግብርና መሳሪያዎች እና ቴክኖሎጂዎች ድጋፍ ቻይና እንደምታደርግ በውይይታቸው አንስተዋል፡፡

በተጨማሪም በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የቻይና ባለሃብቶች በኢትዮጵያ የግብርናው ዘርፍ ላይ ተሰማርተው እንዲሰሩ የሚያችል ስራ እንደሚሰራም በውይይታቸው መገለጹን ከሚኒስቴሩ ያገኘነውመረጃ ያሳያል፡፡