ባለፉት ስድስት ወራት ከ400 ሺህ በላይ የግብርና ማሽነሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ ገብተዋል
***********
(ኢ ፕ ድ)
የግብርና ሚኒስቴር ባለፉት ስድስት ወራት 400 ሺህ 962 የተለያዩ የግብርና መካናይዜሽን ማሽነሪዎችን ከቀረጥ እና ታክስ ነጻ ወደ ሀገር ማስገባቱ ተገለጸ። ሚኒስቴሩ ሰባ ሺህ 718 መለዋወጫዎችም ወደ ሀገር ገብተው ስራ ላይ እንዲውሉ ድጋፍ ማድረጉም ተገልጿል።
በግብርና ሚኒስቴር የግብርና መካናይዜሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ በረከት ፎርሲዶ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ሚኒስቴሩ ለ 90 አስመጪዎች ከቀረጥ እና ታክስ ነጻ ማረጋገጫ በመስጠት አራት መቶ ሺህ 962 ለተለያዩ የግብርና መካናይዜሽን የሚውሉ ትራክተሮችን ፣ ኮምባይነር እና ሁለገብ መውቂያ ፣ ቢለር ፣ ኢንኩቤተር ፣ የእንስሳት መኖ ማቀናበሪያ ፣ የቡና መፈልፈያ ፣ የወተት ማለቢያ ፣ የሰብል ጸረ ተባይ መርጫ እና ሌሎች ለግብርና አገልግሎት የሚውሉ ማሽነሪዎች ወደ ሀገር እንዲገቡ ድጋፍ አድርጓል።
https://www.press.et/?p=93062

በኦሮሚያ ከሚያስፈልጉት 25 ሚሊዮን መጽሐፍት የታተመው ሰባት ሚሊዮን ብቻ ነው
👉 የ2ኛ፣4ኛ እና 6ኛ ክፍል መጽሐፍት ህትመት ለቀጣዩ ዓመት ተሸጋግሯል
***************
(ኢ ፕ ድ)
በኦሮሚያ ክልል በአዲሱ የትምህርት ካሪኩለም ከሚያስፈልገው 25 ሚሊዮን መጽሐፍት ውስጥ እስካሁን የታተመው ሰባት ሚሊዮኑ ብቻ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለጸ። የ2ኛ፣ 4ኛና 6ኛ ክፍል መጽሐፍት ህትመት ለቀጣዩ አመት መሸጋገሩም ተጠቁሟል።
https://www.press.et/?p=93064

የሀረሪ ክልል በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ያደረገውን 10 ሚሊየን ብር ድጋፍ ገቢ አደረገ
***************
(ኢ ፕ ድ)
የሀረሪ ክልል በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በተፈጠረው ድርቅ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች የሚውል 10 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለኦሮሚያ ቡሣ ጎንፋ ባንክ አካውንት ገቢ አድርጓል።
የክልሉ መንግስት ለዜጎቹ የሚያደርገውን ድጋፍ በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የተገለጸው።
የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በተፈጠረው ድርቅ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች 10 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑ ይታወሳል።

👉 “የነዋሪነት መታወቂያ እድሳት እንዲደረግልን ከጠየቅን አንድ ወር ቢሆነንም ማግኘት አልቻልንም”- ነዋሪዎች
👉 “ችግሩ ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኝ ኤጀንሲው ከከተማ አስተዳደሩ ጋር እየሠራ ነው” -የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት
*****************
(ኢ ፕ ድ )
የነዋሪ መታወቂያ እድሳት ለማድረግ ከጠየቅን አንድ ወር አልፎናል፤ የሚመለከተው አካል ችግሩን በፍጥነት ሊፈታልን ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች አሳሰቡ። የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ በበኩሉ፤ ችግሩ ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኝ ኤጀንሲው ከከተማ አስተዳደሩ ጋር እየሠራሁ ነው ብሏል።
https://www.press.et/?p=93155

በግማሽ ዓመቱ ከስደት የተመለሱ 97 ሺህ 303 ዜጎች ወደ ቀያቸው ተሸኝተዋል
*************
(ኢ ፕ ድ)
ባለፉት ስድስት ወራት ከስደት የተመለሱ 97 ሺህ 303 ዜጎች አስፈላጊው የገንዘብና የሥነ ልቦና ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ቀያቸው መሸኘታቸውን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ገለጸ።
ሦስት ሚሊዮን 836 ሺህ 113 ሴቶች መብትና ጥቅሞቻቸውን ለማስከበር መደራጀታቸው ተመልክቷል።
https://www.press.et/?p=93145

ባለፉት ስድስት ወራት ከብልሹ አሰራርና ሌብነት ጋር በተያያዘ ከ200 በላይ አመራርና ሰራተኞች ላይ ክስ ተመስርቷል
*******************
(ኢ ፕ ድ)
ባለፉት ስድስት ወራት ከብልሹ አሰራርና ሌብነት ጋር በተያያዘ ከ200 በላይ አመራርና ሰራተኞች ላይ ክስ ተመስርቷል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ብልሹ አሰራርና ሌብነትን የመከላከል ስራ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ገልጸው አገልግሎት አሰጣጥን ከወቅቱ ጋር እንዲሄድ ለማስቻል በርካታ ዘርፎችን የማዘመን እና የተገልጋዩን እርካታ ለማረጋገጥ የሚያስችል ስራ እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።

በኦሮሚያ ክልል የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋምና ለመከላከል የተለያዩ እቅዶች ታቅደው እየተሰሩ መሆኑን ተገለጸ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
በኦሮሚያ ክልል የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋምና ለመከላከል የአጭርና የረጅም ጊዜ እቅዶች ታቅደው እየተሰሩ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ ገልጸዋል።
የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ በክልሉ የተከሰተውን ድርቅ አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፣ የክልሉ መንግስት ድርቅን ለመከላከል በርካታ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል።
በክልሉ በዚህ ዓመት ብቻ በተከሰተው ድርቅ 4 ነጥብ 3 ሚሊየን ዜጎች እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸውም የገለጹት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ ድርቅን ለመከላከል የአጭርና የረጅም ጊዜ እቅዶች ታቅደው እየተሰራ ነው ብለዋል።
በድርቅ ሳቢያ የሰው ህይወት እንዳያልፍ በአጭር ጊዜ እቅድ የተለያዩ ድጋፎች ተደርገዋል። የምግብ እርዳታና ውሃ በቦቴ እየቀረበ መሆኑን ጠቅሰው ጊዜ ችግሩን ለመፍታት በርካታ ፕሮግራሞች መነደፋቸውን ገልጸዋል።
የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም ተጠቃሽ ነው። በዚህም የደረቁ ምንጮች እየለመመለሙ ነው። ሌላው ህብረተሰቡ በተመጣጠነ ችግር ሊደርስበት የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ የልማት ትሩፋት ፕሮግራም ተጠቃሽ ነው ብለዋል።
በድርቅ ሳቢያ ከዚህ በፊት የሰው ህይወት አላለፈም፤ ወደፊትም በሰዎች ሕይውት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የተለያዩ ድጋፍ እየተደረጉ ነውም ብለዋል።
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ሶስት አመታት የዝናብ ችግር በመኖሩ ድርቅ ተከስቷል። ይሁን እንጅ እርብርብ እየተደረገ በመሆኑ የሰው ህይወት አልጠፋም፤ በቦረና አካባቢ ትምህርትና የጤና አገልግሎት አልተቋረጠም ብለዋል።

ሸገር ከተማን በቴክኖሎጂ ሽግግርና በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ አርአያ የምትሆን ለማድረግ በትኩረት ይሰራል
*****************
(ኢ ፕ ድ)
ሸገር ከተማ በቴክኖሎጂ ሽግግርና በኢኮኖሚ እንቅስቃሴዋ አርአያ የምትሆን ከተማ ለማድረግ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።
ሸገር ከተማ የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በዛሬው እለት በይፋ ስራ ጀምሯል፡፡
በ12 ክፍለ ከተሞችና በ36 ወረዳዎች በይፋ የተመሰረተችው ሸገር የሕዝቡን ባህል በማበልጸግ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግርና በኢኮኖሚ እንቅስቃሴዋ መልካም ምሳሌ የምትሆን ከተማ ለማድረግ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
ከተማዋ አዲስ አበባን በብዙ መልኩ እንደምትደግፍም አቶ ሽመልስ ገልጸዋል።
የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አባዱላ ገመዳ በበኩላቸው፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚኖሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ለዘመናት በብዙ መልኩ አስከፊ ድህነት ውስጥ እንደነበሩ አውስተው፤ ከተማዋ በዚህ መልኩ መመሰረቷ ከሕብረተሰቡም አልፎ ለአገርም ያለው ፋይዳ የጎላ ይሆናል ብለዋል።
ለቀድሞው የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንቶችና ለከተማዋ ምስረታ አስተዋፅኦ ላበረከቱት ግለሰቦች በአቶ ሽመልስ አብዲሳ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በአፋር ክልል ከ139 ሺህ በላይ የ7ኛና 8ኛ ክፍል መጽሐፍት ተሰራጨ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
በአፋር ክልል ከ139 ሺህ በላይ የ7ኛና 8ኛ ክፍል የአዲሱ ካሪኩለም መጽሐፍት ማሰራጨቱን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ የሥርዓተ-ትምህርት ዝግጅትና መማር ማስተማር ዳይሬክተር አቶ ዋልዶ ሀይሰማ እንደተናገሩት፣ ክልሉ ያሳተመውን 139 ሺህ የ7ኛና 8ኛ ክፍል የአዲሱ ካሪኩለም መጽሐፍትን አሰራጭቷል።
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=93230