ባለሀብቶች በአቪዬሽን ኢንቨስትመንት እንዲሰማሩ ጥሪ ቀረበ
**************
(ኢ ፕ ድ)
ለትራንስፖርት ተደራሽ ባልሆኑ የአገሪቱ የቱሪዝም መዳረሻዎች ላይ በትንንሽ አውሮፕላኖችና ሄሊኮፕተሮች ለመድረስ እንዲቻል ባለሃብቶች በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው እንዲሰማሩ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ጥሪ አቀረበ።
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው መንግስቴ በሰጡት መግለጫ የአየር ትራንስፖርት ለማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሁለንተናዊ እድገት ሚናው የጐላ ነው። በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ አራት አለም አቀፍ ኤርፖርት ደረጃ የተሰጣቸውን ጨምሮ 22 መደበኛ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
ኢትዮጵያ ካላት የቆዳ ስፋትና የህዝብ ቁጥር አንጻር በቂ አይደለም ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ተደራሽነቱን ለማሳደግ ባለሃብቶች ለትራንስፖርት ተደራሽ ባልሆኑ የአገሪቱ የቱሪዝም መዳረሻዎች ላይ በትንንሽ አውሮፕላኖችና ሄሊኮፕተሮች ለመድረስ የሚያስችሉ ግንባታዎች ላይ እንዲሰማሩ ጠይቀዋል። ለቱሪዝም እድገት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
የአቪዬሽን ሬጉሌሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ምስራቅ ጥላሁን በበኩላቸው፣ በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው የሚሰማሩ የከተማ አስተዳደሮች፣ ክልል መስተዳድሮችና የግል ባለሀብቶች ወደ ኢንቨስትመንት የሚሰማሩበት የአሰራር ማቀፍ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን በቅርቡ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋ የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙ የሚታወስ ነው።
በሞገስ ተስፋ

በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ውስጥ 397 ኪሎሜትር የአስፋልት መንገድ ግንባታ ተከናውኗል
********************
(ኢ ፕ ድ)
በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ውስጥ 397 ኪሎሜትር የአስፋልት መንገድ ግንባታ መከናወኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አሰታወቀ።
አሰተዳደሩ ባለፉት ስድስት ወራት የስራ አፈፃፀምና በቀጣይ ስራዎች ላይ ያተኮረ ውይይት አካሄደ።
በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ውስጥ 397 ኪሎሜትር የአስፋልት መንገድ ግንባታ ተካሂዷል። በመደበኛ፣ ወቅታዊና ከባድ ጥገና በአጠቃላይ 5,123 ኪ.ሜ የመንገድ ጥገና ስራ ተከናውኗል።
በበጀት አመቱ የመጀመሪያ 6 ወራት ለተከናወኑ ተግባራት 26.27 ቢሊየን ብር ወጪ ተደርጓል።

የፊታውራሪ ሃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ መኖሪያ ቤት የነበረው ታሪካዊ ቅርስ ዕድሳት ተጠናቆ ተመረቀ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የአሜሪካ ኤምባሲ ከዓለም ቅርሶች ፈንድ ጋር በመተባበር በአሜሪካ ግቢ የሚገኘውን በፊታውራሪ ሃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ የታነፀ ታሪካዊ ሕንፃ አድሶ አስመረቀ።
በኢትዮጵያ የአሜሪካን ጉዳይ ፈፃሚ አምባሳደር ትሬሲ ጃኮብሰን በምርቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንደተናገሩት፤ የአሜሪካ ኤምባሲ ከዓለም ቅርሶች ፈንድ ጋር በመተባበር ታሪካዊ ቅርሱን የማደስ ሥራ አጠናቆ አስመርቋል። https://www.press.et/?p=92930

የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ለሆቴል ዘርፉ መነቃቃት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደነበረው ተገለጸ
***************
(ኢ ፕ ድ)
36ተኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ የኢትዮጵያን የሆቴል ዘርፍ በማነቃቃት ረገድ ጉልህ ሚና ተጫውቷል ሲሉ ኢትዮጵያን ስካይላይትና የሒልተን አዲስ አበባ ሆቴሎች አስታወቁ።
https://www.press.et/?p=92907

የኢትዮጵያ መንግስት በጄኔቫ ከሚገኙ የባለብዙ ወገን ተቋማት ጋር ያለው ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ
******************
(ኢ ፕ ድ)
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጄኔቫ ቢሮ እና በስዊዘርላንድ የሚገኙ ዓለም አቀፍ ተቋማት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ፀጋአብ ክበበው በጄኔቫ የተመድ ቢሮ ዳይሬክተር ጄኔራል ለሆኑት ታቲያና ቫሎቫያ የሹመት ደብዳቤያቸውን አስገብተዋል።
አምባሳደር ፀጋአብ ከዳይሬክተር ጄኔራሏ ጋር በነበራቸው ውይይት መንግሥት በጄኔቫ ከሚገኙ ዓለም አቀፍ የባለብዙ ወገን ተቋማት ጋር ያለውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ውይይት ማድረጋቸውም ተገልጸዋል።
አምባሳደር ፀጋአብ ከበበው ጄኔቫ ዓለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ምክትል ቋሚ ተጠሪ አምባሳደር ያኒት አበራን ጨምሮ የሚሲዮኑ ባልደረቦች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
አምባሳደር ፀጋአብ በቅርቡ በተደረገው የአምባሳደሮች ሹመት ወደ ጄኔቫ ከመዛወራቸው በፊት በአውስትራሊያ የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉስልጣን አምባሳደር በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

በቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ከ800 ሺህ በላይ ሰዎች ተጎጂ ሆነዋል
👉 ሁለት ሚሊዮን 200 ሺህ የቤት እንስሳት ሞተዋል
👉 ከ604 ሺህ በላይ ሰዎች በመንግሥት እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል
*******************
(ኢ ፕ ድ)
በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ 807 ሺህ ሰዎች እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የዞኑ አስተዳደር ገለጸ።
በድርቁ ከሁለት ሚሊዮን በላይ እንስሳት መሞታቸው የተገለጸ ሲሆን ከ600 ሺህ በላይ ሰዎች በመንግስት ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሆነም ተጠቁሟል።
https://www.press.et/?p=92996

“የትግራይ ሕዝብ ዘላቂ ሰላም እንዲያገኝ ግልጽነት ያለው የሽግግር መንግስት ሊመሰረት ይገባል”
– አቶ ተሻለ ንጉስ የትዴፓ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
በትግራይ ክልል ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ግልፅነት ያለው አካሄድን የተከተለ የሽግግር መንግስት ሊመሰረት ይገባል ሲሉ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተሻለ ንጉስ ገለፁ፡፡
አቶ ተሻለ ንጉስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ ለትግራይ ህዝብ የተሟላ እና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት የሽግግር መንግስት ማቋቋም ወሳኝ ነው፡፡ ለዚህም ግልጽነት ያለው አካሄድ የተከተለ የሽግግር መንግስት ሊመሰረት ይገባል፡፡
https://www.press.et/?p=93004

ዝቅተኛ ውጤት ላመጡ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የአቅም ማሻሻያ ትምህርት ሊሰጥ ነው
***************
(ኢ ፕ ድ)
በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው ከ50 በመቶ በታች ውጤት ላመጡ ከ106 ሺህ በላይ ተፈታኞች ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጠው የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ትምህርት ፕሮግራም ለአራት ወራት ያህል በሀገሪቱ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
https://www.press.et/?p=93002

በ23 ከተሞች ንፁህ የመጠጥ ውሃን ለማዳረስ የሚረዱ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ ነው
***************
(ኢ ፕ ድ)
በ23 ከተሞች የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን በተሻለ መንገድ ለማዳረስ የሚረዱ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃ አቅርቦት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ታምሩ ገደፋ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ ከአዲስ አበባና ድሬዳዋ በተጨማሪ በክልል ዋና ዋና ከተሞች የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች እየተተገበሩ ነው።
በጎንደር፣ ጅማ፣ አዳማ፣ ሐዋሳ፣ ባህር ዳር፣ ጅግጅጋ፣ ሰመራ፣ ጋምቤላ፣ አሶሳና በተለያዩ ከተሞች ላይ የውሃ ፕሮጀክቶቹ እየተከናወኑ ይገኛል። የየፕሮጀክቶቹ አፈጻጸም ደረጃ የተለያየ ቢሆንም በዘንድሮው ዓመትና በቀጣይ ዓመት የሚጠናቀቁ አሉ። ሁሉንም ፕሮጀክቶች ለማጠናቀቅ ደግሞ አራት ዓመታት ያስፈልጋሉ ብለዋል።
በከተሞች አካባቢ ለሚከናወኑት የውሃ ፕሮጀክቶች 70 ሚሊዮን ዶላር በጀት ተመድቦ ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል ሲሉም ገልጸዋል።
https://www.press.et/?p=93036

በድሬዳዋ ለዓባይ ግድብ ባለፉት ስድስት ወራት 3ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ተሰበሰበ
👉 በአስተዳደሩ እስካሁን የተሰበሰበው ድጋፍ 92 ሚሊዮን ብር ደርሷል
**************
(ኢ ፕ ድ)
በ2015 በጀት ስድስት ወራት ለዓባይ ግድብ ግንባታ 3 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ገቢ ከቦንድ ሽያጭ ማሰባሰቡን የግድቡ የድሬዳዋ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ 25 ሚሊዮን ብር ገቢ ለማሰባሰብ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።
https://www.press.et/?p=93092

ባለፉት ስድስት ወራት ከ400 ሺህ በላይ የግብርና ማሽነሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ ገብተዋል
***********
(ኢ ፕ ድ)
የግብርና ሚኒስቴር ባለፉት ስድስት ወራት 400 ሺህ 962 የተለያዩ የግብርና መካናይዜሽን ማሽነሪዎችን ከቀረጥ እና ታክስ ነጻ ወደ ሀገር ማስገባቱ ተገለጸ። ሚኒስቴሩ ሰባ ሺህ 718 መለዋወጫዎችም ወደ ሀገር ገብተው ስራ ላይ እንዲውሉ ድጋፍ ማድረጉም ተገልጿል።
በግብርና ሚኒስቴር የግብርና መካናይዜሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ በረከት ፎርሲዶ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ሚኒስቴሩ ለ 90 አስመጪዎች ከቀረጥ እና ታክስ ነጻ ማረጋገጫ በመስጠት አራት መቶ ሺህ 962 ለተለያዩ የግብርና መካናይዜሽን የሚውሉ ትራክተሮችን ፣ ኮምባይነር እና ሁለገብ መውቂያ ፣ ቢለር ፣ ኢንኩቤተር ፣ የእንስሳት መኖ ማቀናበሪያ ፣ የቡና መፈልፈያ ፣ የወተት ማለቢያ ፣ የሰብል ጸረ ተባይ መርጫ እና ሌሎች ለግብርና አገልግሎት የሚውሉ ማሽነሪዎች ወደ ሀገር እንዲገቡ ድጋፍ አድርጓል።
https://www.press.et/?p=93062

በኦሮሚያ ከሚያስፈልጉት 25 ሚሊዮን መጽሐፍት የታተመው ሰባት ሚሊዮን ብቻ ነው
👉 የ2ኛ፣4ኛ እና 6ኛ ክፍል መጽሐፍት ህትመት ለቀጣዩ ዓመት ተሸጋግሯል
***************
(ኢ ፕ ድ)
በኦሮሚያ ክልል በአዲሱ የትምህርት ካሪኩለም ከሚያስፈልገው 25 ሚሊዮን መጽሐፍት ውስጥ እስካሁን የታተመው ሰባት ሚሊዮኑ ብቻ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለጸ። የ2ኛ፣ 4ኛና 6ኛ ክፍል መጽሐፍት ህትመት ለቀጣዩ አመት መሸጋገሩም ተጠቁሟል።
https://www.press.et/?p=93064