Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
343 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው ለስራ ጉብኝት ሱዳን ካርቱም ገብተዋል
***************
(ኢ ፕ ድ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው ለአንድ ቀን የስራ ጉብኝት ሱዳን ካርቱም ገብተዋል::
የሱዳን ሪፐብሊክ የሽግግር ሉዓላዊነት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ጄኔራል አብደል ፈታሕ አል ቡርሃን አቀባበል አድርገውላቸዋል::
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በፖለቲካው ሂደት ላይ ከተሠማሩ ከሱዳን የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተወያዩ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በፖለቲካው ሂደት ላይ ከተሠማሩ የተለያዩ የሱዳን የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እና ከሦስትዮሽ መፍትሔ አፈላላጊ ቡድን አባላት ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ውይይት፣ የኢትዮጵያ ጣልቃ ገብ ያልሆነ መርሕ ለራሷ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ጭምር የሚሠራ መሆኑን በማረጋገጥ የሱዳን ሕዝብና ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ሀገር በቀል መፍትሔዎችን እንዲፈልጉ አበረታቷል ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ዘግቧል።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የትዊተር ገጽ ይከተሉ‼️
https://twitter.com/PressEthio
"የሕዝብን ሕይወት ለማሻሻልና የአገርን እድገት ለማረጋገጥ የሚተጉ ሁሉ እውቅና ይገባቸዋል"
- ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ
***************
(ኢ ፕ ድ)

የሕዝብን ሕይወት ለማሻሻልና የአገርን እድገት ለማረጋገጥ የሚተጉ ሁሉ እውቅና እንደሚገባ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ።

ፕሬዚዳንቷ የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የዳያስፖራ አደረጃጀቶች በተዘጋጀ የእውቅና መርሃ ግብር ላይ እንደገለጹት፤ እውቅና ጤናማ ፉክክር በመፍጠር የበለጠ ሥራ እንዲሠራ የሚያበረታታ ነው።

በመሆኑም የሕዝብን ሕይወት ለማሻሻልና የአገርን እድገት ለማረጋገጥ የሚተጉ ሁሉ እውቅና ይገባቸዋል ብለዋል።

ባለፉት ዓመታት በነበረው ችግር በጦር ሜዳ ከመሰለፍ ጀምሮ በየዘርፉ አገርን ለመደገፍ ብዙዎች መትጋታቸውን አስታውሰው፤ ዳያስፖራዎችም በዓለም ፊት ቆመው በመደገፍና በሌሎችም መስኮች ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።

እንደ አገር አሁንም በርካታ የቤት ሥራዎች መኖራቸውን ያስታወሱት ፕሬዚዳንቷ፤ አስከፊውን ምዕራፍ በዘላቂነት ዘግተን ኢትዮጵያን የሚመጥናት ቦታ ላይ ለማስቀመጥ በጋራ መቆም ይገባናል ብለዋል።

ዳያስፖራዎች በመልሶ ማቋቋም ጨምሮ በሌሎችም መስኮች የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

በፋንታነሽ ከንዴ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሱዳን ያደረጉትን የስራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ
****************
(ኢ ፕ ድ)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው በሱዳን ያደረጉትን የስራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል።

ቆይታቸው ከሱዳን የሽግግር ሉዓላዊነት ምክር ቤት እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

ከሱዳን የሽግግር ሉዓላዊነት ምክር ቤት እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ያደረጉትን ውጤታማ ውይይት ተከትሎ ከልዑካቸው ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሥራ ጉብኝት ዛሬ ወደ ሱዳን ካርቱም ማቅናታቸው ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የትዊተር ገጽ ይከተሉ‼️
https://twitter.com/PressEthio